• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አምስተኛ ቀኑን ያሳለፈው የሕንጣሎ ወረዳ ተቃውሞ ቀጥሏል

January 20, 2020 08:45 am by Editor 1 Comment

የክልሉ መንግስት ምላሽ ቢጠየቅም ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ትላንት አምስተኛ ቀኑ አልፏል

በትግራይ ክልል የሕንጣሎ ወረዳ ነዋሪዎች በአዲሱ የአስተዳደር መዋቅር ሒዋነ ከምትባለው ወረዳ ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን ተቃውመዋል። “በአቅራቢያችን መተዳደር እንፈልጋለን” በማለትም ከመቀሌ ከተማ ወደሳምረ በሚወስደው ደንጎላት በሚባል አካባቢ መንገድ ዘግተው የክልሉ መንግስትን ምላሽ በመጠባበቅ አራተኛ ቀናቸውን ደፍነዋል።

ለመንገዱ መዘጋት ምክንያቱ የ“ወረዳችን ይመለስልን” ጥያቄ በማቅረብ ከህብረተሰቡ በተወከሉ ነዋሪዎች አማካኝነት ላለፉት ስድስት ወራት ያክል ወደክልል አስተዳደር ተመላልሰው ቢጠይቁም ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት የተነሳ መሆኑን ተናግረዋል።

አዲስ ዘመን ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪ አቶ መሀሪ ገብረ፤ “ህብረተሰቡ ሌላ ሃሳብ የለውም፣ ዓላማው ወደክልሉ ቢሮ በመመላለስ ላነሳው ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ነው” ብለዋል።

አራተኛ ቀኑን የደፈነው ከሕንጣሎ ከተማ ወደ ሳምረ የሚወስደው መንገድ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደሌለውም ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል።  

የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች በአካል ተገኝተው ህብረተሰቡን ማነጋገራቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ ህብረተሰቡ የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች እንደማይፈልግና ከክልል አስተዳደር አካላት በአካል ተገኝተው እንዲያናግሯቸው እንደሚፈልጉም ተናግረዋል። 

ከሕንጣሎ እስከ ሒዋነ እስከ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ስላለው የሚፈልጉትን አገልግሎት ለማግኘት ስለሚቸገሩና ሕንጣሎ ወደሒዋነ መቀላቀሉ ተገቢ ባለመሆኑ እንዲስተካከል ጠይቀዋል። ሕንጣሎ ወረዳ ተመልሷል በሚል ስያሜውን ይዞ በህንጣሎ ያሉትን እንደ ደንጎላት ሳምረ ያሉ ቀበሌዎችን ይዘው ወደሒዋነ ከተማ መቀላቀሉ ትክክል አይደለም ብለዋል። ወረዳው ሕንጣሎና በእዛ አካባቢ ያሉ ቀበሌዎች እንዲይዝም ጠይቀዋል።  

በአደረጃጀቱ ላይ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ህዝቡን እንዳላነጋገሩ የጠቆሙት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ፤ ከዚህ ይልቅ ከአንዳንድ የቀበሌው አመራሮች ጋር ብቻ ተነጋግረው መወሰናቸው ለቅሬታው መፈጠር ምክንያት መሆኑን ነግረውናል። 

የክልሉ መንግስት ሕዝቡ በአቅራቢያው እንዲተዳደር በሚል ባወጣው የከተማ አወቃቀር የስምንቱ ቀበሌ ወኪሎች ተውጣጥተው ከወረዳ እስከክልል ድረስ ጥያቄውን ቢያቀርቡም ምላሽ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

በጉዳዮ ምላሽ ለማግኘት ወደ ትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ጋር ደጋግመን ብንደውልም ምላሽ አላገኘንም።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ሐዱሽ ካሱን በስልክ አግኝተናቸው በነዋሪዎቹ ቅሬታና ተቃውሞ ምላሽ እነዲሰጡ ጠይቀናቸው ጉዳዩን እንደማያውቁት አሳውቀውናል።

ጉዳዮን አጣርተው ሊነግሩን መልሰን እንድንደውል የገለጹልን ቢሆንም፤ ለህትመት እስስገባንበት ጊዜ ድረስ ደጋግመን ብንደውልም ስልካቸውን ሊያነሱልን አልቻሉም።

ምንጭ፤ ኢፕድ

አምዶም ገብረሥላሴ በፌስቡክ ገጹ “ሕንጣሎ 70 እንደርታ_እምቢተኝነት!” እንደገለጸው የሕንጣሎ ወረዳ ህዝብ ተቃውሞ መንገዱ እንደተዘጋ 5ተኛ ቀን_ኣልፈዋል። ሕንጣሎ ህዝብ 105 ሺህ ብዛት ኑዋሪ ያላት ወረዳ ናት።

የህወሓት መንግስት ለህዝባዊ ጥያቄው ቀና መልስ በመመለስ ፈንታ ለሰሓርቲና ሳምረ ወረዳ ህዝቦች “ዓረና” እንናንተን ለመጉዳት ብሎ ያዘጋጀው ተቀውሞ ነው” እያለ ቅስቀሳ እያካሄደበት ይገኛል።

ይሁን እንጂ ህዝቡ ሊሰማቸው ኣልታለም። በተለይ የሰሓርቲ ህዝብ “እኛም በዓረናነት ፈርጃቹ ስታንገላቱን ነበርና ኣናምናቹም” በማለት ራሱ እየመከታቸው ይገኛል።

ወዳጄ ሕንጣሎ ማለት ተራ ህዝብ እንዳይ መስልህ። በቀዳማይ ወያነ ትግል ውስጥ የኣምበሳ ድርሻ ያለውና ታጋዮቹ ባንዴራችን የኢትዮጵያ ባንዴራ! ራሳችን በራሳችን እናስተዳድራለን! ሁሉም ዜጋ እኩል ነው! ገረብ ዓረና ወያነ ትግራይ ብለው ያወጁበትና ቃልኪዳን የገቡበት ማይደርሁ የሚገኝበት ታሪካዊ ቦታ ናት።

ፍትሕ_ለሕንጣሎ_ህዝብ!

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተምቤን ወጣት ወደ መቐለ የሚወስድ መንገድ ሊዘጋ ነው! ምክንያቱ በደርግ ግዜ የነበረ የተምቤን አውራጃ አስተዳደር መመለሰ አለበት የሚል ነው።

ተጨማሪ የጣንቋ አበርገለ ወረዳ ወጣቶችም በደርግ ግዜ የነበረ ወረዳችን ይመለስልን ተቃውሞ ወደ ሳምረ የሚወስድ መንግድ ሊዘጋ ነው።

ተመሳሳይ የውቅሮ ክልተ አውላዕሎ ወጣትም ከአድግራት ከተማ ወደ መቀለ የሚወስድ መንገድ ሊዘጋ ነው። ምክንያቱም  በደርግ ግዜ የነበረ የዞን አስተዳደራችን ይመለስልን ነው።

በመቀጠል የትግራይ ህዝብ ከስሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ  ምዕራብ ታላቅ ተቃውሞ ሊያሰማ ነው።
የትእምት ባለቤት ሊታወቅ ይገባል ነው!

የህወሃት ቀንደኛ ደጋፊና ተሟጋች የሆነው ዳንኤል ብርሃኔ የህንጣሎን ጉዳይ በማራከስ ይህንን በማለት በፌስቡክ ገጹ ጽፏል፤

“ሽረ አካባቢ ሁለት ቦታ መንገድ ተዘግቶ እንደነበር ሰምቻለሁ። አንዱ – ከሽረ በስተሰሜን ዓዲ ነብርኢድ ላይ ሲሆን፤ የወረዳ መሆን ጥያቄ ያላቸው ሲሆኑ፤ ለበኣል ወደሽረ ከተማ የሄደው ደብረጺዮን ሳያነጋግረን መሄድ የለበትም ብለው ነው።
ሁለተኛው – ከሽረ በስተደቡብ (ወደ አክሱም መስመር) ዓዲ ኢታይ አካባቢ ሲሆን መሳሪያ ጭነው ሊንቀሳቀሱ የነበሩ የመከላከያ መኪኖች እንዲቆሙና ወደካምፕ እንዲመለሱ ለማድረግ ነው።”

ይህንን በትግራይ የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ ለዳንኤልና ለሌሎች የህወሓት/ትህነግ አገልጋይ ሎሌዎች ለሆኑት የተሰጠው አስተያየት እንዲህ ይነበባል፤

“የዳንኤል ብርሃነ ምርጥ ውሸት! አንተ ቀዳዳ ያኔ ኦሮምያ ወይም አማራ ክልል ቢሆን በምስል አስደግፈህ የተደረገና ያልተደረገ አቀናብረህ ትፅፍ ነበር።ለምን ታድያ አሁን ልሳንህ ተዘጋ? ጌታህ ህወሓት ሲነካ የትግራይ ህዝብ ድምፅ ለማፈን ትሞክራለህ። አንተ ማትረባ በትእምት ገንዘብ የሰከርክ የህሊና እስረኛ። መቼ ነው አንተ የህዝብ ድምፅ የምትሆነው በእርግጠኛነት አንተና መሰሎችህ ዋጋቹን የምታገኙበት ሩቅ አይደለም። Habtom Berhe, Senait Mebrahtu, Alula Solom, G/ medhin G/her, Medhin G/sellase እናንተ ሁላቹ የማትረቡ የህወሓት አገልጋዮች ናችሁ። እስኪ እውነት አክቲቪስቶች ከሆናቹ የትግራይ ህዝብ ድምፅ አሰሙን። እስኪ የዓዲ ነብሪኢድ፣ ሕንጣሎ ተቃውሞዎችና መንገድ የመዝጋት እንቅስቃሴዎች ከነመፍትሔዎቻቸው አስቀምጡ እውነት የትግራይ ህዝብን ድምፅ ከሆናችሁ። ይህ በቅማንት ቢሆን ግን ትተለተሉ ነበር ምድረ ቱልቱላ ካድሬዎች። አሁንም ደግሜ ልንገራቹ እናንተና የናንተ ዓይነቶቹ የህዝብ ድምፅ የሚያፍኑ ዋጋቸውን ያገኛሉ። ልክ እንደ ህወሓት ተጠያቂዎች ናቸው።”

ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ ረገብ ያለ ቢሆንም በቀጣይ ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መረጃዎች ይጠቁማሉ። ትህነግ/ህወሓትም ይህንን እምቢተኝነት መስበር እየሞከረች ሲሆን የምትወስደው እርምጃ የበለጥ እምቢተኝነቱን ወደሌላ ክፍል እንዳያዘዋውረው ፍርሃት እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, hintalo, Middle Column, tigray, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tadesse Gebregzi says

    January 21, 2020 06:38 pm at 6:38 pm

    Peace based on the fear of God,remember Raesi Weldeslassie ruled from around these places.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule