ከደቡብ ኦሞ እስከ መተማ፤ ከጅጅጋ እስከ ጋምቤላ፤ ከመቀሌ እስከ ባሌ፤ ከወልቃይት እስከ ኮንሶ! በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ቅድመ-አያቶች፣ አያቶች፣ ወላጆችና ልጆች፤ ሦስትና ከዛም በላይ የሆነ ትውልድ ተመሳሳይ በሆኑ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሃል ተተብትቦ የሚማቅቅ ከሆነ የዛ ማህበረሰብ ጉዞ ጤናማነትና አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡ በእንዲህ አይነት ማህበረሰብ ውስጥ መሰረታዊ የሆኑና የጎሉ ለውጦች ብዙም አይስተዋሉም፡፡ አንዳንዶቹም ለውጦች የቁልቁለት ጉዞ ውጤቶች ይሆኑና በራሱ ብቻ ሳይሆን በአያቶቹም ቁስል የሚማቅቅ፣ መቃብር ቆፋሪና ሸክሙ የከበደው ትውልድ ይፈጠራል፡፡ ይህ አይነቱ ትውልድ የተጫነውን ሸክሙን አራግፎ በነገ ህይወቱና ጥቅሞቹ ዙሪያ ላይ በማተኮር ለፈጠራና ለምርምር ሊያውለው የሚችለውን አቅሙንና ጊዜውን ያልኖረበትን ትላንትን እያመነዠከና የወረሰውን … [Read more...] about ግፍ በገፍ የሞላበት አገር!
Opinions
በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው የህወሃት ድብቅ ሤራ
ከዚህ በታች የምታነቡት በትግረኛ ተጽፎ የህወሓት ባለስልጣናት የተወያዩበትና የተስማሙበት ድብቅ መረጃ ነው። ይህ ረቂቅ ዶኩመንት በወያኔም ባለስልጣናት ተቀባይነት አግኝቶና ጸድቆ በተግባር በአስቸኳይ በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ በተግባር ላይ እንዲውል ስምምነት ተደርሶበታል። ይህ በትግረኛ የተዘጋጀውና ወደ አማርኛ የተተረጎመው ሰንድ የተዘጋጀውና በህወሃት ባለስልጣናት እንዲተገበር ያቀረበው በብዕር ስሙ ዘጽኣት አናንያ በሚል ስም የሚታወቅ እውነትኛ ስሙ ግን ጎይቶኦም የማነ ገብረኣናንያ የተባለ ቀንደኛ የህወሃት ስውር ፊታውራሪ ነው። ከትግረኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመውን ከዚህ ቀጥሎ ያንብቡ። በትግረኛ የተጻፈው በመጨረሻዎቹ ገጾች ላይ ማንበብ ይቻላል። ባለፉት 15 ኣመታት በትንሽ ግለሰቦች ሲነሳ የቆየ ባሳለፍናቸው ትንሽ ኣመታት ደግሞ የተቃውሞ ቅርፅ እየያዘ … [Read more...] about በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው የህወሃት ድብቅ ሤራ
ከተማርኩት ቁጥር 1
ያሜሪካ ቆይታዬ በጣም አጭር ነው። ሁለት አመት እንኳን አይሞላም። ላገሩ አሁንም ላገሩ ባዳ ለወንዙ እንግዳ ነኝ። ገና ብዙ ያልገባኝ ነገር አለ። ግን በዚህች አጭር ጊዜም ቢሆን ብዙ ጠቃሚ ነገር ተምሬያለሁ ብል “አይ ገና ምኑ ተይዞ” እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ለምን ቢባል ልማር ላለ ሳር ቅጠሉ እውቀት መሆኑን ታውቁታላችሁ ብዬ ነው። ይልቅስ ለመሆኑ ምን ተማርክ ብትሉኝ ወጌን እጀምራለሁ። አዎ! ብዙ ነገር። ከእንግዲህ ምናልባት ሰሚ ካገኘሁ ከተማርኩት እያልኩ በተከታታይ አንዳንድ ነገር ለማካፈል አቅጃለሁ። ታዲያ እኔ ትምህርት አገኘሁበት ያልኩት ነገር ከታወቀ የቆየ ወይም የፊደል ቆጣሪ ግንዛቤ ሆኖ ካገኛችሁት የሞተውን አባባ ይለዋል ወይም የልጅ ነገር ሳትሉ ሃሳብ ስጡበት። እኔ አላማዬ መማር ስለሆነ ከስህተቴ እማራለሁ። ከተማርኩት ቁጥር 1 ወደፍሬ ነገሩ ከመግባቴ በፊት … [Read more...] about ከተማርኩት ቁጥር 1
የሃገራችን መድብለ ፓርቲ ሥርዓት ተግዳሮቶች
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ውይይት ለማንሳት ስነሳ በ1994 ዓ.ም የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በቤተ መንግስት ውስጥ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ሲወያዩ አንድ ምሁር የተናገረው ነገር ትውስ አለኝ። ትዝ ይላችሁ እንደሆነ የዚህ ምሁር ንግግር ብዙዎችን ኣስደምሞ ነበር። ለማስታወስ ያህል ይህ ምሁር ለራሳቸው ጠቅላይ ሚንስትር ለነበሩት ለአቶ መለስ እንዲህ ነበር ያለው። “እዚህ አገር ሌላ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ተመስርቶ፣ ገበሬው ውስጥ ገብቶ ፋይዳ ያለው ለውጥ አይኖርም እርስዎ እያሉ። አይኖርም። ምክንያቱም እርስዎ እንዳይኖር ያደርጉታልና ነው። እስካሁን በዚህ ተሳክቶልዎታል በሚቀጥሉት ሃያ ኣመታትም ይህንኑ ያደርጋሉ።” የሚገርመው ይህ ምሁር ምንም ውስብስብ ነገር አልተናገረም። ብዙ ምጡቅ አሳቦች በዚህ ስብሰባ ላይ ተነስተው ነበር። ይሁን እንጂ በተለይ የዚህ … [Read more...] about የሃገራችን መድብለ ፓርቲ ሥርዓት ተግዳሮቶች
$200 million deal to bring slavery period in the 21st century
The Bank Hapoalim has made a deal to loan 200 million dollar for the purpose of assisting the rapid growth of land grabbing in Ethiopia. In the Omo valley in Ethiopia farmers are being forcibly displaced from their land in the pretext of sugar plantation which is financed and sponsored by the largest Israel’s bank (Bank Hapoalim) with more than $200 million. The Ethiopian government amazingly brought the 18th and 19th century slavery and colonial period back and applied the slavery methods on … [Read more...] about $200 million deal to bring slavery period in the 21st century
ይድረስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጉልበት ላላችሁ ሁሉ
ልጆች ሆነን ታላላቆቻችን ጉልበት አለን ብለው በደል ሲፈጽሙ "እግዚአብሔር በቀዳዳ ይየው!" እንል ነበር፤ ለመርገምም እየፈራን አንዲያው ድርጊቱ እንዲመዘገብልን ማሳሰባችን ይመስለኛል፤ አሁንም እንደዚያ ለማለት ይቃጣኛል፤ ግን አግዚአብሔር በሰማይ ላይ መኖሩን፣ በእያንዳንዳችን ውስጥ መኖሩን የቤተ ሃይማኖት ሰዎች እንኳን ማመናቸው በሚያጠራጥርበት ዘመን ለዓለማዊ ባለሥልጣኖች የእግዚአብሔርን ስም ማንሣት ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፤ ሆኖም እኔ ስለማምንበት የራሴን አሳውቃለሁ፤ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር ነች፤ ኢትዮጵያን ጎድቶ የተጎዳ እንጂ የተጠቀመ የለም፤ ኢትዮጵያን አዳክሞ የደከመ እንጂ የበረታ የለም፤ ኢትዮጵያን አደህይቶ የደኸየ እንጂ የበለጸገ የለም፤ ኢትዮጵያን አዋርዶ የተዋረደ እንጂ የተከበረ የለም፤ ይህ የታሪክ ሐቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዓላማችሁ ምንድን ነው? … [Read more...] about ይድረስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጉልበት ላላችሁ ሁሉ
ኢትዮጵያን የሚወክሉ የተለያዩ ወገኖች፤
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ መጋቢት 1፤ 2008ዓም፤ ዋሽንግቶን ዲሲ፤ የአፈጻጸም ማጠቃለያ፤ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የካቲት 6፤ 2008ዓም (February 14, 2016) በአሜሪካ የሜሪላንድ ጠቅላይ ግዛት ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ ባደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ “የኢትዮጵያ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ ምክርቤት” መመሥረቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ምክርቤቱ የተመሠረተው ሕዝባዊ ጉባዔው ከመካሄዱ በፊት በነበሩት ሦስት ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ወገኖች ባካሄዱት ስትራቴጂካዊ ውይይት ነበር፡፡ ምክርቤቱ “የእኛ ለኛ” ወይም የሕዝብ ለሕዝብ ንቅናቄ ሲሆን ዕርቅ፣ የጉዳት ፈውስና ርትዓዊ ፍትሕ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን መካከል ለማምጣት የሚተጋ ይሆናል፡፡ አጀማመር፤ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ገና … [Read more...] about ኢትዮጵያን የሚወክሉ የተለያዩ ወገኖች፤
በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል ጥናት ውጤት ማጠቃለያ ዘገባ!
ኢትዮጵያ አገራችን እያከተመ ባለው ምዕተ-ዓመት ሁለት የተለያዩ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ለውጦችን አስተናግዳለች። የመጀመሪያው በ1966 የፈነዳው አብዮትና ሶሻሊስታዊ እንቅስቃሴ ሲሆን፣ ሁለተኛው በክስተቱም ሆነ በውጤቱ እጅግ የተለየው ደግሞ ከ1983 ጀምሮ የተንሰራፋው የዘመነ መሳፍንት ተምሳሌት ወያኔ መራሹ ፓለቲካ ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል ጥናት ውጤት ማጠቃለያ ዘገባ!
ኢህአዴግ እንዲህ ነው
ዛሬ በስልጣን ላይ ያለው ጉደኛ ቡድን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በየጊዜው ቅርጹንም ሆነ ይዘቱን ሲቀያይር መኖሩን መስራቾቹ ነግረውናል። አንዳንዱን እያየንም ታዝበናል። ከመገለጫዎቹ ጥቂቶቹ አንባገነንነት፣ ገዳይነት፣ አፋኝነትና ጠባብነት ወይም ዘረኝነት እንዲሁም ጥላቻ ናቸው። ከዚህ ጥቅል ተፈጥሮው ሌላ ስልጣን ከያዘም ጊዜ ጀምሮ የሚታዩበት ግልፅ ባህርያት አሉ። አንደኛው እውነታን መካድ ወይም አለመቀበል ነው። አይኑ ስር ያለውን ግልፅ እውነታ አይቀበለም። በተለይ ተቃውሞ ወይም ውድቀት ወይም የሃሳብ ልዩነት ከሆነ በጭራሽ አይደራደርም። አዘውትሮ የሚጠቀምበት አሰልች ስልት ለእውነታው ወይም ለችግሩ ሃሰተኛ ባለቤት መፈለግ ነው። ይህም ተቃዋሚ ፓርቲ፣ አክራሪ ቡድን፣ ፀረሰላም ሃይል፣ ፀረልማት፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል። እንዴት ያለ በሽታ ነው ጃል! ትክክለኛውን ህመም ለይቶ ትክክለኛ … [Read more...] about ኢህአዴግ እንዲህ ነው
የመለስ ዜናዊ ራእይ
መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ የጠላት ጠላት ደመኛ ጠላት ነው። ከአባቱ፣ ከእናቱና ከአያቶቹ የወረሰው በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ የፈጸመው ግፍ፤ የሃገር ማፍረስ ድርጊት በታሪክ የማይረሳ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የህወሓት አመራርንም ይጨምራል። የስም ዝርዝራቸውን በተለያዩት ጽሁፎቼና ከዚህ በላይም ስላካተትኳቸው እንሱን መመልከትና ማመሳከር ይቻላል። የመለስ ዜናዊ ራእይ በኢትዮጵያ ልማት፣ እድገት፣ ዲሞክራሲ ማለትስ ምን ማለት ነው? በእርሱ አመራር ለ21 ዓመታት ኢትዮጵያ በልማትና በዲሞክራሲ አብባለች የሚሉት የህወሓት ደጋፊዎችና አጋር ድርጅት ተብለው የሚጠሩት ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ኢትዮጵያ ስብስብ ብቻ ናቸው። ብዙ ለሆዳቸው ያደሩም አሉባቸው። ነገሩ የተጋላቢጦሽ ነው። መለስ ዜናዊ የሚመራው ህወሓትና አመራሩ በተፈጥሮው ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ዲሞክራሲ ነው። ህወሓት አፈጣጠሩ አምባገነን እና ፋሽስት፣ … [Read more...] about የመለስ ዜናዊ ራእይ










