• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢህአዴግ እንዲህ ነው

March 10, 2016 12:42 am by Editor Leave a Comment

ዛሬ በስልጣን ላይ ያለው ጉደኛ ቡድን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በየጊዜው ቅርጹንም ሆነ ይዘቱን ሲቀያይር መኖሩን መስራቾቹ ነግረውናል። አንዳንዱን እያየንም ታዝበናል። ከመገለጫዎቹ ጥቂቶቹ አንባገነንነት፣ ገዳይነት፣ አፋኝነትና ጠባብነት ወይም ዘረኝነት እንዲሁም ጥላቻ ናቸው።

ከዚህ ጥቅል ተፈጥሮው ሌላ ስልጣን ከያዘም ጊዜ ጀምሮ የሚታዩበት ግልፅ ባህርያት አሉ። አንደኛው እውነታን መካድ ወይም አለመቀበል ነው። አይኑ ስር ያለውን ግልፅ እውነታ አይቀበለም። በተለይ ተቃውሞ ወይም ውድቀት ወይም የሃሳብ ልዩነት ከሆነ በጭራሽ አይደራደርም። አዘውትሮ የሚጠቀምበት አሰልች ስልት ለእውነታው ወይም ለችግሩ ሃሰተኛ ባለቤት መፈለግ ነው። ይህም ተቃዋሚ ፓርቲ፣ አክራሪ ቡድን፣ ፀረሰላም ሃይል፣ ፀረልማት፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል። እንዴት ያለ በሽታ ነው ጃል! ትክክለኛውን ህመም ለይቶ ትክክለኛ መድሃኒት ከመፈለግ ይልቅ ያለምክንያቱ ምክንያት መፈለግ።

ሁለተኛ መለያ ባህሪው ደግሞ እንቢተኝነት ነው። ኢህአዴግ ግትር ነው። እየተሸነፈ አሸናፊነቱን አያምንም። እየወደቀ አለሁ ይላል። እየጠፋ መልማቱን ይሰብካል።

ውድቀቱን እየጣለ ስኬቱን ብቻ ያወራል። የሚያሳዝነው ታዲያ የሚወድቀው ብቻውን ሳይሆን ከሃገር ጋር መሆኑ ነው። ብቻውን ቢወድቅ ኖሮ የእጁን አገኘ ማለት ብቻ ይበቃ ነበር።

ሌላው ጠባዩ ጥላቻና ቅራኔ ነው። ልዩነት የህልውናው መሰረት ነው። የሚፈልገው ልዩነት ብቻ ሳይሆን ጥላቻን የሚወልድ ልዩነት። የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነቱ ሳይሆን በልዩነቱ እንዲታወቅ ይፈልጋል። ብሄር ብሄረሰቦች የሚላቸው ቡድኖች እንዲስማሙ አይፈልግም። ፍቅራቸውን የሞት ያህል ይፈራዋል። እነርሱ ሲጣሉ ሽማግሌ ሆኖ በበላይነት መኖር ይፈልጋልና እነርሱ መስማማት የለባቸውም። ያሁኑ የአማራና ዖሮሞ በበለጠ መቀራረብ እንቅልፍ የነሳውም በዚህ ባህሪው ምክንያት ነው።

የመጨረሻውና እጅግ አደገኛው ባህሪው ሃገሪቱን በራሱ ያገዛዝ ዘይቤ ራሱ ነግሶ ለመኖር የሚያሳየው ቅዠት ነው። ለኢህአዴግ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊነት ውጭ ሃይማኖት  የለም። ከልማታዊ መንግስት ውጪ አማራጭ ከንቱ ነው። ለኢትዮጵያ ከጎሳ ፌደራሊዝም በላይ ላሳር ነው። በጥቅሉ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ችግር መፍትሄው የኢህአዴግ አስተሳሰብና የኢህአዴግ ዘለአለማዊ አገዛዝ ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ጨርቅን ጥሎ ማበድ የት አለ ጎበዝ?

በመጨረሻም ለኢህአዴግና የሃገሬ ሰዎች ምክር ብጤ አለኝ።

በመጀመሪያ ለኢህአዴግ፣

ኢህአዴግ፣ እባክህ አስተሳሰብህም ሆነ አገዛዝህ ፎርሿልና ንቃ። የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር ለዘለቄታዊ የሚፈታው በማን አለብኝነት፣ በትእቢት፣ በእብሪትና ፉከራ ሳይሆን ባስተዋይነት፣ በሆደሰፊነት፣ በምክክርና በፍቅር ነው። ይህን ሳትገነዘብ ቀርተህ በያዝከው  የጥፋት ጎዳና ዘመቻህን እቀጥላለሁ የምትል ከሆነ ግን መጨረሻህ እንጦረጦስ ባይሆን ከምላሴ ጸጉር!

ያገሬ ሰዎች፣ ተቃዋሚ ሃይላትና ዳያስፖራ፣

ይህን የታሪክ አጋጣሚ የኢትዮጵያን ህዝብ ያንድነት ጎጆ እንደገና አሳምረን ለመስራት እንጠቀምበት። የህዝብን አንድነት የሚያውክና ለቡድናዊ ጥቅም ካልሆነ በቀር ለህዝብ የማይጠቅም ጥላቻን በመዝራት ለኢህአዴግ ላገርና ህዝብ መምቻ ዱላ አናቀብለው። አሁን የሚታየውን የመቀራረብ መንፈስ አበልፅጋችሁ ቀጥሉ። የችግራችን መፍትሄው ፍቅር ነው። ከተቀራረብንና በሰለጠነ መንገድ ከተወያየን የተበላሸውን ጠግነን የጎደለውን ሞልተን ህዝብ የሚኮራባት ሃገረ ኢትዮጵያን መፍጠር የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም። እናም ተባበሩ! ልዩነትን ጤንነት እንጂ በሽታ አታድርጉት። ይህ ወቅት የፍትህና ዴሞክራሲ አንባ የሆነች ታላቋን ኢትዮጵያ የምንፈጥርበት አጋጣሚ ነውና ሁላችንም እናስተውል።

ቸር ይግጠመን

ህሩይ ደምሴ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule