The Association of Human Rights in Ethiopia (AHRE) has received reports of the atrocities in the Southern Region’s Konso Wereda of Ethiopia, with the use of excessive and lethal force against the Konso people. According to local sources dozens were killed, and thousands were evicted from their villages. More than 1500 houses were burned. AHRE expresses deep concern over the Ethiopian Government’s continued use of unnecessary force against protesters in various parts of the country. AHRE calls on … [Read more...] about AHRE urges Ethiopia to End the Atrocities and Human Rights Abuses Against The Konso People
Opinions
የኢትዮጵያ “የፌደራል ሥርዓት” ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች
እንደ መግቢያ ከዚህ በፊት “ኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓትን የምትከተል አገር አይደለችም” ብዬ ፅፌ ነበር። ዛሬም ትንሽ አዳብሬ በዚሁ ላይ ትንታኔ መስጠት አምሮኛል። ይህ ጽሁፍ ደግሞ እንዲነሳልኝ የፈለኩበት ምክንያት በቅርቡ የህወሃት አንጋፋ ታጋዮች የሆኑት አቶ ስዩም መስፍንና አቶ አባይ ፀሃየ በቅርቡ በኢትዮጵያ “ወቅታዊ” ጉዳይ ላይ የተሰኘ መግለጫ ሰጥተው ነበር። የነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት ንግግር ያዳመጠ ሁሉ የየራሱን ምልከታ ያስቀምጣል። እጅግ ብዙ ሰው ግን አዲስ ነገር የማይገኝበት ወቅታዊ የማይባል ያደርገዋል። አገሪቱን ህዝባዊ ተቃውሞ በሚንጥበት በዚህ ሰአት ቢያንስ ስለብሄራዊ መግባባት ስለ ብሄራዊ እርቅ ስለ ይቅርታ ማውራት ተገቢ ነበር። የፓለቲካ መሪ ምንም እንኳን የያዘው አቅጣጫ ለራሱ አዋጭ ቢመስለውም ነገር ግን ህዝብ ካልተቀበለው ራሱን ይመረምራል። ይህ ግን በኛ ሃገር … [Read more...] about የኢትዮጵያ “የፌደራል ሥርዓት” ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች
ተራራም ይሰረቃል? የራስ ዳሽኑ ፖለቲካ
ራስ ዳሸን ተራራ ከትግራይ "ክልል" ካርታ የመውጣቱ አሲዮ ቤሌማ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ሲነገር፤ "ደፍረውናል! ንቀውናል! ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል!" የሚለው የኮሎኔል መንግስቱ ንግግር በጆሮዬ ላይ አቃጨለ። ድፍረቱ እና ንቀቱ እንዳለ ሆኖ፣ በቁም የሞቱት ግን እኛ ሳንሆን እነሱ መሆናቸውን የሚያበስር የዜና እወጃ ነበር። ነገሩ እንጂ ሁሉም የተለመደ ነገር ነው። ውሃ ይጠፋል፣ መብራት ይጠፋል፣ ስልክ ይጠፋል፣ ገንዘብ ይጠፋል፣ ኮንዶሚንየም ህንጻም ይጠፋል። ይህ በህወሃት ፖለቲካ ጥርሳቸውን ላልነቀሉትም አዲስ ነገር አይደለም። ዘረፋም ለነሱ አዲስ አይደለም። መንግስት ሆነው ከተቀመጡ በኋላ እንኳን 10 ቶን ቡና ሰርቀዋል፣ የመብራት ጀነሬተሮች ሰርቀዋል፣ ከብሄራዊ ባንክ ወርቅ ሰርቀዋል ... የህዝብን ድምጽም በተደጋጋሚ ሰርቀዋል። ተራራ ተሰርቆ ሲመለስ ግን የመጀመሪያው … [Read more...] about ተራራም ይሰረቃል? የራስ ዳሽኑ ፖለቲካ
ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር
የአፍሪካ ነፃነት አብሪ ኮከብና በጀግና ህዝቧ አኩሪ ተጋድሎ ባለክብር የነበረቺው ኢትዮጵያ ዛሬ በከፋ ፈተና ውስጥ ገብታለች። በብርቱ ትግልና ጥንቃቄ መወገድ ያለባቸው ያገርና የህዝብ ደህንነት ስጋቶች ከፊቷ ተጋርጠዋል። የርስ በርስ ጦርነት ስጋት፣ የአስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እጦት፣ የማእከላዊ መንግስት አቅጣጫ ብዥታና የውጭ ጠላት ስጋት፣ ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህንና መሰል ያገርና ህዝብ ደህንነት ስጋቶች ለማስወገድና ጤናማ የፖለቲካ ድባብ ለመፍጠር ባስቸኳይ መንቀሳቀስና ሀገርና ህዝብን ካሳፋሪ ውድቀት ማዳን ያስፈልጋል። በኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ ያንዣበቡትን እነዚህን አደጋዎች ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው? በእርግጥስ ይቻላል? እነዚህን ያገርና የህዝብ ህልውና ፈተናዎች በማስወገድ የኢትዮጵያን ሁኔታ ሰላማዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ማድረግ የሚችለውስ ማነው? የሁሉም ጥያቄዎች መልስ … [Read more...] about ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፤ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ፤ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው
በትያትር ድርሰት ጽሁፎቹ ፤ በትርጉምና የግጥም ስራዎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ (ነፍሱን ይማርና) በ1987 ዓ.ም እዚህ በስደተኛነት ነዋሪ የሆንኩበት ሆላንድ ሀገር መጥቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርጎልን ነበር። እንደሚታወቀው ጋሽ ጸጋዬ የወያኔ መንግስት ስልጣን ላይ እንደወጣ የደረሰው ወይም የጻፈው አንድ “ሀሁ ፐፑ” የተሰኘ የትያትር ስራው ለህዝብ እንዳይታይ ታግዶበት ነበር። አዋሳን በመሰሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ደግሞ ተዋንያን መድረክ ላይ ሆነው ትያትሩን ሲተውኑ በወያኔ ወታደሮች በዱላ እየተደበደቡ ተውኔቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ሌላው ቀርቶ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ለታላቁ ጸረ-ፋሽስት፤ የኢትዮጵያ ሰማእትና አርበኛ ለአቡነ ጴጥሮስ ማስታወሻ የደረሰውን “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” የተባለውን ትያትር ለህዝብ … [Read more...] about ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፤ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ፤ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው
የሁለት እስረኞች ወግ!
አዋቂው፣ ዕውቁ እና ተወዳጁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ትሁቱ እና ሠላማዊው ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌን በአካል ያየኋቸው በ2003 መጨረሻ በአንድነት ፓርቲ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ነበር። ያኔ በጋራ የምንጦምርበትና ለእስር የዳረገን ዞን ዘጠኝ አልተመሠረተም ነበር። ነገር ግን ጓደኞቼ እና ባልደረቦቼ Soleyana እና Atnaf ሳንተዋወቅ በፊት እዚያ እንደነበሩ ኋላ ስናወራ ሰምቻለሁ። በርካታ ሰዎች በተገኙበት ያ ስብሰባ ላይ ዛሬ ዝዋይ ወኅኒ የተጣለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ተገኝቶ ነበር። ያቺ ስብሰባ እስክንድር ጥናታዊ ንግግር ያቀረበባት ስብሰባ ነበረች። ጥናታዊ ንግግሩ እና ውይይቱ በጥቅሉ በእነአንዱዓለም አራጌ መዝገብ የተከሰሱት 24 ሰዎች ላይ ማስረጃ ሆኖ መጥቷል። የእነአንዱዓለም አራጌ መዝገብ ብዙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች የተከሰሱበት መዝገብ ነው። የአዲስ … [Read more...] about የሁለት እስረኞች ወግ!
ምነዋ አቦይ ዓባይ!
ምነዋ አቦይ ዓባይ ጸሐዬ! በደም የሰከረውን ድፍርስ ዓይንዎን እያጉረጠረጡ ከስሙኒ ቀለሉሳ! ደኅናም ብቅል አልጠጡም? አቦይ በሚባሉበት ዕድሜዎ እንዲህ መዘላበድ?! ሽማግሌ አልነበሩም እንዴ?! ብቻ - አይ የኔ ነገር! ተሳስቼ! የናንተ ሽማግሌ የለውም ለካ! መዘላበድና መዛት ልማድዎ ነው። በዚያን ሰሞን፣ “ለጭቁን ብሔር ብሔርሰብ” ደረስንለት ባሉት አንደበትዎ፣ ኦሮሞ ወንድሞቻችንን “ልክ እናስገባዋለን” ብለው አልነበር። አቦይ ዓባይ! እግዚአብሔር፣ እንኳን ከዛተና ከወረወርም ያድናል። ኦሮሞው አንዲት ብረት ሳያነሳ በባዶ እጁ ልክ አስገባችሁ አይደል? ሲዋሹ መቼም ዕድሜዎን እንኳን ግምት ውስጥ አያስገቡም። ሲዝቱ በጆሮአችን እየሰማንዎት፣ በነጋታው፣ “አላልኩም! አልወጣኝም”፣ ተቆርጦ የተቀጠለ ድምጼ ነው እንጂ እኔ እንደዚያ አላልኩም እያሉ ሲዘላብዱ ያኔ ሰምተን፣ ታዝብንዎት። እንደገና … [Read more...] about ምነዋ አቦይ ዓባይ!
ልዑል በሉዓላዊ መንግስት ይሰለጥናል!
‶…ልዑሉ በሰዎች መንግስት ሁሉ ላይ ሙሉ ስልጣን እንዳለውና እነዚህንም መንግስታት ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ…″ ዳን.4፡32 ሉዓላዊ መንግስት (sovereign nation) በሌሎች ቅኝ ግዛት ወይም ባርነት ስር ያልወደቀ ራስ-ገዝና ነጻ መንግስት ሲሆን የሃገሪቱ የአመራር አካላት እንደመጨረሻው ውሳኔ ሰጪ አካላት ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ የህዝቡም ሰላምና የሁለንተና እድገት በሃገሪቱ አመራር አካላት ብቃትና ቅንነት ይወሰናል፡፡ ሉዓላዊነት ሌሎች አካላት በአንድ ሃገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ (meddle) ዋስትና እንደሚሰጥ በማሰብ አንዳንድ መንግስታት በማንአለብኝነት ከእግዚአብሔርም ከሰውም የሚያነካካ እርምጃ ሲወስዱ ይስተዋላሉ፡፡ ከነዚህም አንዱ ለትምህርታችን በቅዱሱ መጽሀፍ በስፋት የተተረከልን የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነጾር ነው፡፡ ይህ እግዚአብሔር ባርያዬ/አገልጋዬ … [Read more...] about ልዑል በሉዓላዊ መንግስት ይሰለጥናል!
የሰማዕታት ዝርዝር በከፊል
Partial list of Oromos that have been killed as a result of Excessive force by Ethiopian Government (TPLF's regime) armed forces during Peaceful demonstration on August 6,2016, Oromia, Ethiopia. (updated 4 September 2016) Nr Name Sex Age Zone Locality Killed by 1 Abbuu Muummee M 17 Arsii Ticho Agazi 2 Abdallaa Mohammed M - East Harageh Qobo Agazi 3 Abda Jiloo M 24 West Arsii Asasa Agazi 4 Abdaa Hasanoo M 31 West … [Read more...] about የሰማዕታት ዝርዝር በከፊል
ዲገላው የጎረቤታችን ድመት የገጠመው የሞት አደጋና የወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በንፅፅር ሲታዩ
በተወለድኩበት በሂርና ከተማ ጎረቤታችን የሆኑ እማማ የልፍተለው እናት የሚባሉ ደግ ሴትዮ ነበሩ። ታዲያ አንድ እሳቸው ያሳደጉት ድመታቸው ከቤት ሸሽቶ ወጥቶ በራሱ ተዳዳሪ ሆነ። በሀረርጌ ከአሳዳሪ ጌታው ቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ዱር ገብቶ በራሱ የሚተዳደር ድመት ዲገላ ድመት (ማለትም እንደ አውሬ ዱር የገባ ድመት ማለት ነው) የሚል ስም ይሰጠዋል። ዲገላ ቃሉ ከኦሮምኛ ቋንቋ የመጣ ሲሆን ዛሬ ግን በሀረርጌ ያሉ አማሮችም የአማርኛ ቃል አድርገውት ከላይ በገለጽኩት ትርጉሙ ይጠቀሙበታል። ይህ ድመት በራሱ ተዳዳሪ ከሆነም በኋላ በሰፈራችን ውስጥ ያሉ ጫጩቶችን እየበላ፤ ድስት እየከፈተ፤ የተሰቀለ ቋንጣ እያወረደ ወዘተ የሰፈሩን ነዋሪ በጣም አስቸገረ። ይህ ድመት የእኛንም የዶሮ ጫጩቶች በተደጋጋሚ በልቶብናል። ይህን ድመት እግዚሃብሄር ከገላገላቸውና ከገደለላቸው ለሂርና ስላሴዎች እጣን ይዘን … [Read more...] about ዲገላው የጎረቤታችን ድመት የገጠመው የሞት አደጋና የወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በንፅፅር ሲታዩ










