ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት በዘረኛው የትግሬ ነፃ አውጪ የአገዛዝ መዳፍ ሥር የታፈነውን ሕዝባችንን ወደ ነፃነትና የዴሞክራሲ ምዕራፍ ለማሸጋገር የጋራ ትግል ለማድረግ ሲሞከር ቆይቷል። ሆኖም በእነዚህ ዘመናት ውስጥ የተፈጠሩት የፖለቲካ ኃይሎች ትብብር፣ ቅንጅት፣ ኅብረት እና ውህደት አንዱም ከዳር ሳይደርስ እንዲሁ ሲሰበሰብና ሲበተን ከርሟል። እንደ አባባልም እንደ መታወሻም “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” የሚለው የዶ/ር መረራ ጉዲና መፈክር አንዱም ገቢራዊ ሳይሆን አብዛኞቹ የፖለቲካ ተቋማት በአገዛዙ ጫናና በራሳቸው ደካማ አደረጃጀት ህልውናቸው እየጠፋ ለሐገር የሚተርፍና ትውልድ የሚረከበው አንድም አግባቢ የጋራ ማዕከል ሳይመሰረት በኪሳራ የታጀቡ ዓመታትን አሳልፈናል። ትብብር የጉልበት ምንጭ ነው።ትብብር ድልን ማቅረቢያ ዘለቄታዊና ሠላማዊ ሽግግርን ማሳለጫ መሳርያ ነው።ትብብር ከሚከሰረው … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ተስፋና ሥጋት!
Opinions
ከኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ-ምልልስ በስተጀርባ
ጠንቋይና ፖለቲከኛ የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ። ሁለቱም ተገልጋያቸውን ለማምታታት የትኩረት አቅጣጫ ማስቀየርን ተክነውበታል። ኢሳያስ አፈወርቂ በዚህኛው - የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ - ገለጻቸው ራሳቸውን ሳይቀይሩ ሌላውን ለመቀየር የተነሱ ግብዝ ነው የሆኑት። ይህ "ቃለ-ምልልስም" አንድ አላማ አለው። አላማውን ለማወቅ ቃላቶችን መሰንጠቅም አያስፈልግም። ግልጽ ነው። 'ብዙ ስላልተሰራበት' መልዕክቱ የተጠበቀውን አላማ የመታ አይመስልም። ቃለ-ምልልሱ የተደረገበት ወቅት፣ የተመረጠበት ሰዓት የሚሰጠን ግልጽ የሆነ ግን የተለየ ትርጉም አለ። ጠያቂዎቹ በሻዕቢያ ላይ የነበራቸው የፖለቲካ አቋም ከመቅጽበት መቀየሩ በራሱ የሂደቱን ግራጫ ምስል ያሳየናል። "ሁሉን ቢናገሩ ሆድ ባዶ ይቀራል" ይላሉ አበው። እነዚህ ጉዳዮች ውስጥ ገብቶ መላ-ምቶችን መዘርዘሩ አስፈላጊ ባይሆንም (አንዱ መላ ምት … [Read more...] about ከኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ-ምልልስ በስተጀርባ
«ችግሩን ለማስወገድ፣ ግለሰብ ወይም ቡድን መወገድ አለበት» ዐባይ ፀሐዬ
የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) አጠቃላይ ግብ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። የዚህ ግብ መዳረሻ ደግሞ በኢትዮጵያዊነታቸው በጽኑ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን እና ከሁሉም በላይ፣ የዐማራውን ነገድ ማጥፋት ሲቻል እንደሆነ በማመኑ፣ ላለፉት 43 ዓመታት የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን፣ ነባር ሃይማኖቶችን፣ የአገራዊነት መገለጫ የሆነችውን ሰንደቅ ዓላማችንን፣ በሕዝቡ መሀል የአንድነት መገለጫ የሆኑ ተቋሞችንና አሠራሮችን፣ ግንኙነቶችን በአዋጅ አጥፍቷል። በዐማራው ነገድ ላይ የተቀነባበረ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጽሟል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ ተደርጓል። የትግሬ-ወያኔ ለዚህ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና የዐማራውን ነገድ ለማጥፋት ላለመው ዓላማው ወደ ግቡ መዳረስ … [Read more...] about «ችግሩን ለማስወገድ፣ ግለሰብ ወይም ቡድን መወገድ አለበት» ዐባይ ፀሐዬ
ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ የፖለቲካ ትግል፤ ወይንስ የተበታተነ ተቃውሞ?
የያዝነውን እናጢን! ምን እያደረግን ነው? የትግሬዎቹ ገዢ ቡድን በሚያደርገው የዕለት ተዕለት አውዳሚ ተግባሩ በመቆጣት፤ ለተቃውሞ መነሳትና፤ ይህን አካል በተግባሩ ወንጅሎ፤ በደሎቹን መዘርዘሩ አንድ ነገር ነው። ይህ ተቃውሞ ነው። በመቃወምና ይህ መደረግ የለበትም ብሎ በመጮህ፤ የተወሰነ ግብን ማስገኘት ይቻላል። ተግባሩ ግን ይቀጥላል። ቢበዛ ቢበዛ፤ በተግባሩ ሂደት ላይ ትንሽ ማስተካከያ ማስከተል ይቻላል። ከዚያ በተረፈ ግን፤ ይህ በመፈጸም ያለ በደል፤ በድጋሚ እንዳይከሰት የሚያቆመው ነገር የለም። ይሄን በማድረግ የሚረካ ሊኖር ይችላል። እንደገና፤ ይህ ተቃውሞ ነው። በታቃራኒው ደግሞ፤ የተፈጸሙትና በመፈጸም ላይ ያሉት በደሎች፤“መደረግ የለባቸውም!” ብሎ መነሳት ብቻ ሳይሆን፤ “የዚህ ሁሉ ምንጩ፤ አንድ አካል ነው። ይህ አካል መንግሥታዊ ሥልጣኑን ባንድ መንገድ ወይንም በሌላ፤ በጁ … [Read more...] about ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ የፖለቲካ ትግል፤ ወይንስ የተበታተነ ተቃውሞ?
በሁዳዴ ጾም የአህያ ልኳንዳ!
አህያን ጅብ ብቻ ሲበላው ነው የምናውቀው! "ደሳለኝ" ተብሎ ስለሚጠራው አህያ፤ በወያኔ ሚዲያ የተተረከልን ታሪክ መሳጭ ነው። እነሱ ጫካ ውስጥ በነበሩበት ወቅት፣ አስገደ ገብረስላሴ በ45 ብር ገዝቶ ለወያኔ ማጓጓዣ ይሆን ዘንድ አበረከተ። ይህ "ደሳለኝ" የሚባለው አህያ ከባድ ጭነት እየተሸከመ ያገለግላቸው ነበር። በአንድ ወቅት በጦርነት ተሸነፉና ይዘውት የነበረውን ስፍራ ለቅቀው ተበታተኑ። ከቀናት በኋላ አንዳንዶቹ ወደቀድሞ ምሽጋቸው ተመልሰው ለመምጣት እንኳን ሲቸገሩ ደሳለኝ ግን መንገዱን ሳይስት እዚያው ስፍራ ይጠብቃቸው ነበር። በመጨረሻም የአህዮች አለቃ ተባለና "ብፃይ" (ጓድ) የሚል የማዕርግ ሹመትን አገኘ። አሁን ደሳለኝ በህይወት የለም። ወያኔዎች ግን በበኩር ልጁ እየተጽናኑ እንደሆነ ይናገራሉ። አባቱ አብሮን ብዙ ተጉዟል ሲሉ፣ "ለልጁ" የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ሹመት … [Read more...] about በሁዳዴ ጾም የአህያ ልኳንዳ!
Horrifying Testimony of Torture in TPLF Prison: Ethiopia
Note: Ethiopia is a current non-permanent member of UN security council and a member of UN human rights council VOA Interview: Part-1 (23 March 2017) + Part-2 (25 March 2017): Habtamu Ayalew: Former spokesman of Andenet Party (Ethiopia) VOA Introducer, Alula Kebede: Today’s guest for democracy in action program is Mr. Habtamu Ayalew, former spokesperson of the opposition, Andenet Party (unity party) in Ethiopia. Mr. Habtamu was subjected to two years of imprisonment, waiting for trial after … [Read more...] about Horrifying Testimony of Torture in TPLF Prison: Ethiopia
ከቆሻሻ ኑሮና ሞት ለመላቀቅ ቆሻሻውን ስርዐት ማስወገድ
ነገሩ ሁሉ ከድጡ ወደማጡ በሆነባት ሀገራችን በየጊዜው የሚፈራረቁት ሰቆቃዎች ልብን በሀዘን ካራ ማድማታቸውን እንደቀጠሉ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከደረሱብን መዓቶች ጥቂቱን ብናነሳ፤ በረኃብ አለንጋ እየተገረፉ ደጃፋቸው ላይ ድፍት ብለው የቀሩትን፣ መብታቸውን ለመጠየቅ ሲጮሁ የጥይት ራት የሆኑትን፣ የኢሬቻን በዓል ለማክበር አምረው ደምቀው እንደወጡ ገደል ሰብስቦ ያስቀራቸውን፣ እንዲሁም በቅርቡ በቆሻሻ ናዳ ታፍነው እስከወዲያኛው ያንቀላፉትን ወገኖቻችንን በቁጭትና በመሪር ሀዘን እናስባለን። እነዚህን አደጋዎች ይበልጥ አሳዛኝና አስከፊ የሚያደርጋቸው ደግሞ በሀገሪቱ የተንሰራፉት አምባገነንነት፣ ዘረኝነት፣ ምዝበራ፣ ራስወዳድነትና ግድየለሽነት ውጤት መሆናቸው ነው። በአስራዎች በመቶ እድገት ሽምጥ ስለሚጋልበው ኢኮኖሚዋ ነጋ ጠባ የሚዘመርላት የወያኔዋ ኢትዮጵያ ዘራፊዎቿ ከቪላ ቪላ … [Read more...] about ከቆሻሻ ኑሮና ሞት ለመላቀቅ ቆሻሻውን ስርዐት ማስወገድ
አደራዳሪ የሌለው ድርድር፥ ሐኪም የሌለው ሆስፒታል ነው
አገራችን ባለፈው ዓመት ካለፈችበት ህዝባዊ ተቃውሞዎች አንፃር ኢሕአዴግ ከህጋዊ አገራዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ማድረግ እንደሚፈልግ መግለፁ ለብዙዎቻችን ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ነበር። ሆኖም በቅድመ ድርድር ሂደቱ ወቅት ኢሕአዴግ ያሳየው አካሄድ ሚጠቁመው ከድርጅቱ አመራር ውስጥ አንዳንዶቹ አገራችን ያለችበትን አደገኛ ሁኔታና ሂደት በአግባቡ ያላጤኑ ፥ አደጋውን አለባብሰው ማለፍ የመረጡ ፥ ብቃትና አቅም የሌላቸው ፅንፈኛ ጥቂቶች የድርድር ተስፋውን እያጨለሙት መሆኑን ነው። ኢሕአዴግ ከደርግና ከአፄው ስርዓት ያልተማረው ዋና ቁምነገር ሁሉን ተቆጣጥሮ ሁልጊዜ እያለባበሱ ማለፍ እንደማይቻል ነው። እስከ መጨረሻው ሰጥቶ መቀበልን ያልፈለገው ደርግ ዛሬ የታሪክ አመድ ሆኗል። በፍጥነት ተሃድሶ ማድረግ ያልፈለገው የአፄው ስርዓት ዛሬ የሚገኘው በጥቂት አረጋውያን ትዝታ ውስጥ ብቻ … [Read more...] about አደራዳሪ የሌለው ድርድር፥ ሐኪም የሌለው ሆስፒታል ነው
ከሩስያ በአሜሪካ የፖለቲካ ሂደት ጣልቃ ገብነት ምን እናነባለን?
አሜሪካ ለሩስያ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ናት። የአሜሪካ ርዕዮተ ዓለም ከሩስያ ርዕዮተ ዓለም የተለየ ነው። በአሜሪካ፤ ከሀገሪቱ የግለሰብ የሃሳብ የነፃነት የተነሳ፤ ከሀገራቸው ይልቅ ራሳቸውን የሚያስቀድሙ ሰዎችም በመንግሥት መዋቅርም ይሁን በንድግ ተግባሩ ውስጥ በኃላፊነት የሚገኙ አሉ። ይህ የግል አመለካከታቸው፣ የራሳቸው ከመሆኑም በላይ፤ በማንም ግለሰብ፤ የበላይ አለቃቸውም ሆነ ለነሱ ተጠያቂ በሆኑ ግለሰቦች ዘንድ፤ አያስገምታቸውም። በአንጻሩ፤ እንደሩስይ ባሉ የአምባገነኖችን የበላይነት በሚያመቻቹና በሚያሞግሱ ሀገራት፤ (ይህ አብዛኛውን በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ያጠቃልላል። የኢትዮጵያውን የትግሬዎች ወገንተኛ ወራሪ ቡድንንም ይጨምራል።) ነዋሪዎቹ፤ ግለስብ ግለሰብነቱን አጥቶ፤ በገዥዎቹ ፍላጎት የሚተረጎም ማንነትን እንዲቀበሉ ስለሚገደዱ፤ የገዥዎቻቸው አገልጋዮች ናቸው ማለት ይቻላል። … [Read more...] about ከሩስያ በአሜሪካ የፖለቲካ ሂደት ጣልቃ ገብነት ምን እናነባለን?
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
መጋቢት 2009 ዓ.ም ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ ዕትም የወያኔ አገዛዝና የካድሬዎቹ አስከፊ ተግባሮች ተገሎ የማያልቀው የአማራ ሕዝብ ስቃይና መከራ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊነት የጎሳ ፖለቲካና መዘዙ በኢትዮጵያ ትርፍ የሌለው ልፋት ዴሞክራሲ የውሃ ሽታ የሆነባት አገር አመፅ በተግባር ሲተረጎም ሕገ-መንግሥቱ የተፃፈው ለማን ነው? ወዘተ ርዕሰጉዳዮችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ በማካተት ታትሟል፤ መጽሔቱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት










