ቴዲ በክርስቶስ ተቦርነም በጲላጦስ እንዲት ይመሰላሉ? ምሳሌያዊ አነጋገሮች ተረቶቻች፣ የታላላቅ ሰዎች አባባሎች መጽሐፍትና ገጠመኞች እየተጠቀሱ ንግግር መክፈቻም ሆነ የጽሁፍ መነሻ መሆን በፊትም የነበረ አሁንም የቀጠለ የተለመደ ነገር ነው። እንደዚሁም የክርስቶስ ቃል የሀዋርያት ትንቢት ምሳሌና ተግሳፅም እንደቦታው አስፈላጊነት የሚጠቀስበት ጊዜ አለ። ይህም የሚሆነው ትምህርት ለመስጠት የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ እንደአስፈላጊነቱም ጊዜውና የተፈጸመውን ድርጊት ለማስተማር ነው። በሰርግ ጊዜ ጌታ በሰርግ ቦታ ተገኝቶ ባዶዎቹን እንስራዎች በጣፋጭ ወይን ሞላቸው ተብሎ ትምህርት እንደሚሰጠው። አንተም ለጽሁፍህ መነሻ ያደረከው ቃል በማትዮስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፯ ቁጥር ፲፩. ሰፍሮ ይገኛል። ቃሉም እንደሚያስረዳው እየሱስ በዛን ጊዜ ይሁዳ አሳልፎ ስጥቶት ሽማግለዎችና የካህናት … [Read more...] about ክንፉ ምን ነካህ?
Opinions
US Lobbying Firm (SGR) Cozy with a Ruthless Dictatorial Regime in Ethiopia For 1.8 Million Dollars
Lobbying Firms in the US are known to represent big corporations like oil, construction, food manufacturing and pharmaceutical industries, trying to persuade lawmakers to support business friendly legislations. As this is a controversial practice, politicians running for office do not want to be associated with Lobbying firms. In fact, it was a major discussion topic during the 2016 presidential election season for both candidates. The main reason for politicians to discredit lobbying firms … [Read more...] about US Lobbying Firm (SGR) Cozy with a Ruthless Dictatorial Regime in Ethiopia For 1.8 Million Dollars
የጃንሆይ እናት!
ነገሩ ትንሽ ቆየ። እኔ ግን በሆነ አጋጣሚ በቅርቡ ነው ቃለ ምልልሱን የሰማሁት። ተስፋዬ ገብረአብ አዲስ ስላሳተመው - “የጀሚላ እናት” መጽሃፍ፤ ከጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበር። በትክክል እንዳዳመጥነው ከሆነ፤ “የቀዳማዊ ኃይለስላሴ እናት ስም ጀሚላ ነው፤ አንድ ወገናቸው ስልጤ ጉራጌ ነው - በሌላ ወገን ኦሮሞ ናቸው።” ይለናል። በመቀጠልም፤ “የጀሚላ እናት በአቶ በዛብህ ተጠልፈው ነበር። አቶ በዛብህ ከምኒልክ ጋር በጦርነት ሞቱ። የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ወይም የጀሚላ እናት እልፍኝ ውስጥ፤ በአጼ ምኒልክ ተገደሉ።” የሚሉና ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ የልብወለድ ነገሮች በመጽሃፉ ውስጥ ማካተቱን በቃለ ምልልሱ ላይ ሰማን። ወደ ኋላ በመመለስ ‘በወቅቱ ምላሽ የሰጠ ሰው ይኖር ይሆን?’ በማለት አንዳንድ ድረ ገጾችን ብመለከት፤ በዚህ የተዛባ ታሪክ ምክንያት… … [Read more...] about የጃንሆይ እናት!
ተቦርነ በየነ “አንተ አልክ?” – ቴዲ አፍሮን
እንዲህም ሆነ። የይሁዳ ገዥ የነበረው ጲላጦስ ክርስቶስን አስጠርቶ "አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህን?" ሲል ጠየቀው። ክርስቶስም መልሶ "አንተ አልክ?" አለው። ሰማይን ያለ ምሰሶ ያቆመው ክርስቶስ "ጥፋ" የምትል ቃል ብቻ ከአንደበቱ ቢያወጣ ኖሮ ጲላጦስ አይደለም መላው ቂሳር ክምድረ-ገጽ በጠፉ ነበር። ታዋቂዎች በአዋቂዎች ላይ የሚቀልዱበት ይህ የገሃዱ አለም እውነታ ግብረ-ገብ ወደ ግብግብ በተቀየረበት በዚህ ዘመን ባሰበት እንጂ አልጠፋም። ጥንት አንቺ-ትብሽ፣ አንተ-ትብስ ይባል የነበረው ብሂል አሁን በ“አንቺ ብስብስ አንተ ብስብስ” ተቀይሯል ሲል አንዱ አጫወተኝ። ከቶውንም ስድብን እንደ ስንቅ በከረጢት ቋጥረው በሚጓዙበት የፌስቡክ ዘመን መስመር የመልቀቁ ነገር አዲስ ሊሆን አይችልም። "አንተ አልክ?" ብሎ ማለፍ ምን ይጎዳል? ብላቴናው ላይ አንዳች እንከን ሲያጡ፣ የጠወለገን የጥላቻ … [Read more...] about ተቦርነ በየነ “አንተ አልክ?” – ቴዲ አፍሮን
ተደናቂ ለሆነ የፍትሕ አገልግሎት ስለ ተሰጠ ሽልማት
ጋዜጣዊ መግለጫ ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ ተደናቂ የሆነ የፍትሕ አገልግሎት በመፈጸማቸው ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው ለተዘረዘሩት ሽልማት ያበረከተ መሆኑን ይገልጻል፤ ቀሲስ/ዶር. ምክረ-ሥላሴ ገብረ አማኑኤል፤በፋሺሽት ኢጣልያ የኢትዮጵያ ወረራ ዘመን ስለነበረው የቫቲካን ሚና ግንዛቤ እንዲገኝ በደረሱት መጽሐፋቸው አማካኝነት ስላበረከቱት አስተዋጽኦ፤ ሚር. ኢያን ካምፕቤል፤ ፋሺሽቶች በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙዋቸው የጦር ወንጀሎች በደረሱዋቸው መጽሐፎች ስላበረከቱት አስተዋጽኦ፤ ሚር. ቫሌሪዮ ቺሪያቺ፤ ፋሺሽት ኢጣልያኖች፤ በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙት የጦር ወንጀልና ባሁኑ ወቅት በመኪያሔድ ላይ ስላለው የፍትሕ ጥረት ግንዛቤ እንዲገኝ ፊልም በማዘጋጀት ስላበረከተቱት አስተዋጽኦ፤ አቶ ከባዱ በላቸው፤ ፋሺሽት ኢጣልያኖች፤ በቫቲካን የትብብር ድጋፍ፤ … [Read more...] about ተደናቂ ለሆነ የፍትሕ አገልግሎት ስለ ተሰጠ ሽልማት
የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!! 87ኛ ዓመት
መግባቢያ! የሀገረ-ኢትዮጵያ የእውቀት አደባባይ በአስፈሪ ዝምታ ተውጧል። ምሁራኖቻችን ከህዝባዊ ተዋፅኦ አፈግፍገዋል። የአደባባይ ምሁራን ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በመናመን ላይ ባሉ ብርቅዬ የዱር እንሰሳት መመሰል ከጀመረ ዓመታት አልፈዋል። ቁጥራቸው የበዛ ምሁራን አገዛዙ በፈጠረው የጥቅመኝነት ፖለቲካ ጥላ ስር መጠለል ምርጫቸው ሆኗል። ጥቂት የማይባሉት ደግሞ የባዕድ አገር ስደትን መርጠዋል። ሕዝባዊ መድረኮቻችንን ፋይዳ ቢስ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮችና በተዛቡ የታሪክ ትርክቶች፤ በዘውጋዊ አጥርና አገራዊ ከፍታን መፍጠር በማይችሉ ሙግቶች ተውጠዋል። ዕድሮችና የመረዳጃ ማህበራት ሳይቀር ዘውጋዊ ቅርጽ (አጥር) ሰርተዋል። አገሪቱ ለገባችበት የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ቅርቃርና ለማህበራዊ ችግሮቻችን መፍትሔ ይሰጣሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው የፖለቲካ ልሂቃን አገሪቱን ለአራት አስር ዓመታት ክፉኛ … [Read more...] about የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!! 87ኛ ዓመት
የእግዚአብሔር መልእክት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል
"ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደአለላ ብትሆን እንደአመዳይ ትጸዳለች እንደደምም ብትቀላ እንደባዘቶ ትጠራለች፤ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምጹም ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናገሮአልና፡፡" ኢሳ. 1/18. በእግዚአብሔር ለሚያምን ሰው፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜም፣ ለዘለዓለም ሙሉና የማይወዳደሩት ኃይል እንዳለው ለሚያምን ሰው፣ ለእግዚአብሔር ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም አሁን መሆኑን ለሚያምን ሰው "ኑና እንዋቀስ" (በእንግሊዝኛው "come now let us reason together") ማለት ለእግዚአብሔር ምን ያህል መውረድ እንደሆነ መገንዘብ የሚዳግት አይመስለኝም፤ የእንግሊዝኛው ትንሽ ሻል ያለ መስሎ "ኑና እንከራከር" የሚል ቢሆንም ከመጨረሻው የላይኛው ዳኛ ጋር መከራከር የሚችለው ማን ነው? እግዚአብሔር … [Read more...] about የእግዚአብሔር መልእክት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም
የዋልድባ ገዳም በህዋሓት መሪዎች በዓይነ ቁራኛ የወደቀው ገና ትግሉ እንደተጀመረ ነው። የዋልድባ ገዳም የህወሓት መሪዎች እንዲወድም ሃሳብ ያቀረቡት በ1973 መጨረሻ አካባቢ ሲሆን፣ አቅማራ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በወቅቱ የህወሓት መናኸሪያ ነበር። በተመቤን ውስጥ የሚገኘው ቦታ በፕሮፓጋንዳ ጽ/ቤት ተሰብስበው ወሰኑ፤ በስብሰባ የነበሩት አመራር ፖሊት ቢሮው በሙሉ ነበር። እነሱም፣ ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ገደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ ነበር። በወቅቱ ማ/ኮሚቴ የነበሩ ናቸው። በዚህ ስብሰባቸው የዋልድባን ገዳም እጣ ፈንታ ወሰኑ። ዋልድባ እንዲወደም! የዋልድባ ገዳም ለብዙ መቶ ዘመናት የቅዱሳን፣ ብፁአን፣ ባህታውያን፣ ቀሳውስት፣ አባቶች፣ ደናግል፣ ዲያቆናት ወዘተ ሰፈር በመሆን በኢትዮጵያ ቅዱስና በታሪክ ትልቅ ምእራፍ የያዘ ገዳም ነው። ይህ ቅዱስ ገዳም … [Read more...] about ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም
ለዴሞክራሲ አርበኞች ተባብሮ ለመታገል የሚያስችል ቀላልና ጠቃሚ ሃሳብ
አስቀድሞ የከበረ ሰላምታ ይድረሳችሁ፤ በዚህ ማስታወሻ የቀረበውን ሃሳብ ጠቃሚ ነው የምትሉ ስለጠቀሚነቱ፤ ጎጂ ነው የምትሉም ስለጎጅነቱ የሚታያችሁን ምክንያቶች ጨምራችሁ መልስ እንድትሰጡ ትጠየቃላችሁ፤ ሌሎች ይህ ሃሳብ ከተላለፈበት ዕለት ቀደም ብሎ ተደራጅታችሁ እንቅስቃሴ የጀመራችሁና በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያልገባችሁ ካላችሁ ተቀላቅላችሁ ድምጻችሁን ማሰማት ትችላላችሁ። በጉዳዩ ላይ ድምጽ ለማሰማት ግለሰቦችም መብታችሁ የተጠበቀ ነው። መልስ ስትሰጡ ግን አድራሻችሁን ማኖር አትርሱ። የመልሱ ውጤት ከታየ በዃላ ቀጣይ ሂደት ይኖራ ተብሎ ተስፋ ይደረጋል። ለዚህ ጽሁፍ መነሻ፤- ከወራት በፊት አቶ ዘውዴ ጉደታ የተባሉ ወንድም "የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ እና የአገር አንድነትን "ያገቱት" ሦስት ተጻራሪ ሃይሎች" በሚል ርዕስ አንድ ሰፋ ያለ ጽሁፍ አስነብበው ነበር። ከዚያም በላይ የጸሃፍያን … [Read more...] about ለዴሞክራሲ አርበኞች ተባብሮ ለመታገል የሚያስችል ቀላልና ጠቃሚ ሃሳብ
የበጋው መብረቅ (ሌፍተንት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ)
. . . ጃጋማ በውጊያ ብቻ አልነበረም ብስለቱ በአስተዳደርም የተደነቀ ነበር።ለምሳሌ፤ከአምቦ መንገድ በላይ ያሉት ነዋሪዎች ጥራጥሬ እያዋጡ ቆሎ እየቆሉ ለአርበኛው ይረዳሉ፤ከአምቦ መንገድ በታች ያሉት ግን የጃገማ አርበኞች ሙጀሌ የወረሳቸው ሰለሆኑ ይህን የተሰነጣጠቀ እግራቸው ችሎ መራመድ አይችሉም፤ስለዚህ እንኳን እኛን ከኢጣሊያ ስራዊት ሊጠብቁን እና ሊከላከልሉን ቀርቶ ለራሳቸውም ሰለማይሆኑ በምንም ነገር አንረዳቸውም ማለታቸውን ጃጋማ ሰማ። ለሰራዊቱም ትእዛዝ ሰጥቶ ወደ ሃያ ሺህ ከብቶቻቸውን አስነዳባቸው፤ ህዝቡም በጣም ተደናግጦ ምነው ምላሳችንን በቆረጠው በሚል በጣም ተደናገጡ።ቀንበራቸውን ተሸክመው የጃጋማ ጦር የሰፈረበት ቦታ ድረስ በመሄድ እግዚኦ አሉ። ወጣቱ መሪ ጃጋማ እንዲህ አላቸው (እኛ ከእናንተ የወጣን የእናንተ ልጆች ነን፤ጠላት የሚንቀን አንሶ ለሐገራችንና ለእናንተ በባዶ … [Read more...] about የበጋው መብረቅ (ሌፍተንት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ)









