ጭቃ እያቦካ ጭቃ እየለወሰ ጭቃ እየጋገረ ጭቃ እየጎረሰ ያረፈደው አያ ከጭቃው ገበያ ያውና ብቅ አለ ከጭድ መሃል ወጣ በጨመለቅ እጁ ሊጨብጠኝ መጣ። 'መቼም ከጭቃ ነው ተፈጥሮ ስሪቴ' ብዬ እንዳልጨብጠው 'እምቢኝ!' አለኝ ቤቴ "ጭቃማ አይደለሁም! _ ነኝ እንጂ ውብ ሸክላ ታሽቶና ተቦክቶ በውቅ የተኮላ ይታጠብ በቅድሚያ አቅርብለት ውሃ ለጨቀየው ነፍሱ በነገር ቤት ዝሃ" ብሎ ይሞግተኛል ተላላው መንፈሴ ውሃውን ረስቼ ጭቃን በማንገሴ እነሆኝ በል እንካ አንተ ጭቃ ለዋሽ ኮዳዬን ዘቀዘቅኩ ለእድፍህ አባሽ። የመንፃት ቀንህን አታርቀው ጓዴ ውሃዬን ተጠቀም ላፍስልህ ላንዴ ከዚያም ልጨብጥህ ደርሳለሁ ዘመዴ ጭቃ እያቦካ ጭቃ እየለወሰ ጭቃ እየጋገረ ጭቃ እየጎረሰ ስንቱ ሰው መሰለህ ደግሞ የታደሰ ከመቡካት በኋላ ውበት የለበሰ። … [Read more...] about ጭቃና ውኃ
Literature
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሴት ማናቸው? – ፱” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ዘጠኝ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ (እንደተለመደው በየሳምንቱ መልሱን ተከታትለን ባለማቅረባችን ለአንባቢያንና መልሱን አዘጋጅተው ልከው ላቆየንባቸው ወለላዬ ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን::) መልስ ትንሽም ቢሆኑ - ቁጥራቸው ባይበዛ የድሮ ዘፋኞች - ነበራቸው ለዛ ከነዛ መካከል - በድፍን ከተማ ታዋቂ ነበሩ - እሳቱ ተሰማ ምስጋና አቀርባለሁ - መልስ ለሰጣችሁ እሳቱን እወቁ - ደግሞ ሌሎቻችሁ ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲” ወለላዬ የሚከተለውን … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲
ትኩረት – ከውጪ ቋንቋዎች ለተወረሱ ቃላት
የሀገራችን ቋንቋዎች ከውጪ ቋንቋዎች በርካታ ቃላትን ወርሰዋል፡፡ ይህም ከብሉይ ዘመን ጀምሮ ይታይ የነበረ ክስተት ነው፡፡ የመወራረሱ አድማስ ስፋቱን የጨመረው ግን በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቀጣዮቹ አንድ መቶ ሀያ ዓመታት ውስጥ የታዩት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ክስተቶች የሀገራችን ቋንቋዎችን ለውጪ ቋንቋዎች ተጽእኖ የበለጠ ክፍት እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል፡፡ ታዲያ ከሶስት ሺህ ከሚልቁት የውጪ ቋንቋዎች መካከል ለሀገራችን ቋንቋዎች ብዙ ቃላትን ለማውረስ የበቁት አራቱ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱም ዐረብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣሊያንኛና እንግሊዝኛ ናቸው፡፡ የቱርክ እና የጀርመን ቋንቋዎችም ጥቂት ቃላትን ለሀገራችን ቋንቋዎች አበርክተዋል፡፡ ***** ዐረብኛ በሀገራችን ቋንቋዎች ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር የቻለው በዋናነት የእስልምና ሀይማኖት የአምልኮና … [Read more...] about ትኩረት – ከውጪ ቋንቋዎች ለተወረሱ ቃላት
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ስምንት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በብዙ ትያትር - የመድረክ ዝግጅት ዝናን ያተረፉ - ቀርበው በመታየት «የአዛውንቶች ክበብ» - በተለይ ሲነሳ እስከዛሬ ድረስ - ያላጡ ሙገሳ አስካለ አመንሸዋ - ማለት እኚህ ናቸው ከእድሜው በረከት - አሁንም ይስጣቸው። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱
የኔኛው
አንዱ አንበሳ ነው. . . ወገኑ ሲነካ ዘራፍ ነው የሚለው። ሌላው ደግሞ ጅብ ነው. . . የሚበላ አግኝቶ ግዳይ የጣለ ዕለት፥ ወገኑን ሳይጠራ ጭራሹን አይነካት። የኔኛው ውሻ ነው ለያውም ተናካሽ፥ የራበው ወንድሙን ወገኑን አስለቃሽ። የሞተ አግኝቶ በልቶ ይጠግብና፥ ወገኖቹ ውሾች እንዳይበሉ ይልና፥ እዛው ጋር ይተኛል እያባረራቸው፥ ትንሽ እንዳይቀምሱ ሊከለክላቸው። ግን ቁራና ጭልፊት ከሰማይ የሆኑት፥ ምንም አይላቸው ስስቱን ሲበሉት። ----- (By Gemechu Merera) 23/11/2009 … [Read more...] about የኔኛው
የማይጮኹት . . . በዓሉ ግርማን የበሉት ጅቦች
“ይህችን ውድ የሆነች ትንሽ ቁራሽ ሕይወት እንደ አብርሃም ቤት የለኝ፣ እንደ ሙሴ መቃብሬ ላይታወቅ፡፡ መኖር - መጻፍ - ሕይወትን በተስፋ ወደፊት እየኖርኩና ወደኋላም እያስተዋልኳት፡፡” በዓሉ ግርማ - ደራሲው እውቁን ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማን በአጸደ ሕይወት ካጣነው፤ በዘንድሮው የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ሠላሳ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ውድ ባለቤቱ ወይዘሮ አልማዝ አበራ በዘመነ ኢሕአዴግ ስለ ባለቤቷ ከቤት እንደወጣ መቅረት ጉዳይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርባ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ምስክርነቷን እንድትሰጥ ተደርጋ ነበር፡፡ ያንን የእሷን የፍርድ ቤት የምስክርነት ቃል የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቅርቦ ካስደመጠንም ሁለት አሠርታት ዓመታት እንደዋዛ ሊቆጠሩ ነው፡፡ ውድ ባለቤቱ ወ/ሮ አልማዝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበችውና እልክና ቁጭት የተመላበት የምስክርነት ቃሏ አንድምታ እንዲህ … [Read more...] about የማይጮኹት . . . በዓሉ ግርማን የበሉት ጅቦች
መርፌ
አንድ ቀን ተነስቶ፣ መርፌ ተቆጥቶ፣ መርፌ ተበሳጭቶ፣ አልሰጥም ያለ ቀን - ያንን ቀዳዳውን፣ ክር አንጀቴን በላኝ - እንጃለት መግቢያውን። … [Read more...] about መርፌ
እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሰባት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ማራቶን ማራቶን ማራቶን ልዕልቷ አበበና ማሞ ሆኑ ባለቤቷ ማራቶን ደንግጠሽ አቤን ብትቆጪ ዕድሉ የኛው ነው የትም አታመልጪ ብለው ያወደሱ - ሜክሲኮን ኦሎምፒክ የኳስ ስም ሲነሳ - የሚታውሱ ሰርክ ግጥም ያቀበሉ - ለብዙ ዘፋኞች ዝናን ያተረፉ - በስፖርት ዓለም ሰዎች አገር የሚሸበር - ድምጻቸው ሲሰማ እኚህ ሰው ነበሩ - ስለሞን ተሰማ፡፡ ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፰” ወለላዬ የሚከተለውን … [Read more...] about እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰
ዛፎች
ከዛፎች መካከል ዛፎች ሲቆረጡ ዎዮው ላሽሟጠጡ፡ ዎዮው ላላገጡ፡ የተጨፈጨፉት የተቆረጡቱ፡ ለምሣር እጄታ ተገጥመው ሲመጡ። … [Read more...] about ዛፎች
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በተለይ በዚህኛው በርካታዎች በመሳተፋችሁና በግጥም ምላሽ በመስጠት ዝግጅቱን ላሳመራችሁ ሁሉ በድጋሚ ምስጋናችን ይድረሳችሁ - ቀጥሉበት:: የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ስድስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በአፄ ሚኒሊክ - የአገዛዝ ዘመን ኤርትራ በሚገኝ - የስዊድን ሚሽን በኋላም ውጪ ሀገር - ብዙ የተማሩ በዕውቀታቸውም - ለሀገር የሰሩ በሹመት የቆዩ - ሆነው ነጋድራስ ታሪክ ያረሳቸው - እስከዛሬ ድረስ ገብረህይወት ባይከዳኝ - በሚል የጻፋችሁ ስህተት የለውም - ልክ ነው … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯










