ግጥሙን በPDF ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ዓለም በቃኝ አለ!
Literature
የልጆቻችን ሀገር
አያቶቻችን የልጆቻችን መሬት ነች ብለው ደማቸውን አፍስሰው ሀገራችንን ከወራሪ ፋሽት ታደጉልን አባቶቻችን በውርስ እርስ በእርስ ሲጣሉ ሳይኖሩበት ሳያኖሩበት ይኸው አሉ ። ልጆች የሚሆነው ሳይገባቸው ውሉ የጠፋባቸውን አባቶቻቸው እያዩ ነው፤ ግራ መጋባታቸውን እየወረሱ ግራ እየተጋቡ ነው ፤ ወይ በሽሽት ላይ ናቸው፤ ነገር ግን እትብታቸው የተቀበረባትን ቀዬ ከማዶ ሆነው እያዪ የጨው አምድ ሆነው ቆመዋል፤ ብቻ ልቦቻቸው ያነባሉ። እንዲህ እያሉ:- የአያቶቻችን ቀዬ - የአባቶቻችን የጦር አውድማ፣ ለኛማ ህልም ብቻነች -ያልተጨበጠች ከተማ፤ ቆመንባት የምትፋጅ- ስንርቃት የምትናፍቅ፣ የሆነች -ነች የቅርብ ሩቅ፤ እንዳንተዋት ማረፊችን፣ እንዳይዛት ማን ፈቅዶልን?፣ አያስነካን - የማይጠግበው አባታችን፣ ብቻ እዛ ማዶ ተገትርን፣ እዚህም ከግለቱ ላይ ተጥደን ፣ ለልጆቻችን አስቀሩልን … [Read more...] about የልጆቻችን ሀገር
ጎተራው ወዴት ነው?¡
ሀገር በብረት ሲታጠር — ‘ግንቦት ሃያህ’ ሲከበር፤ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር — ዘመን በዘመን ሲቀየር፤ የስራ-ፈቶች ስብስብ መንጋ — ‘ፓርላማህ‘ሲከፈት ሲዘጋ..፤ ሱፍህን ገጥግጠህ — ከረባትህን ጠፍረህ፣ ወዝህን አሳምረህ — ካሜራ ፊት ቀርበህ፣ ጉሮሮህን..ጠርገህ — ፊትህ የከመርከውን ‘ሃያ ገጽ’ ገልብጠህ፣ ቁጥር እየቆጠርክ፣ አሃዝ እየጠራህ...፣ “ምናምን..ሺ.ቶን፣ ሚሊዮን ስልቻ፣ አምርተን አስገባን በዚህ ዓመት ብቻ...”፣ እያልክ ስትደሰኩር — ትንፋሽህ እስኪያጥር፣ ሰምቼህ ሳበቃ፣ የግርምት ጥያቄ እስኪማ ልሰንዝር፤ በልበ-ሙሉነት “ጠግብን በላን” ያልከው፣ ሕዝቡን ቆጥረህ ይሆን? ወይስ የቤትህን ያንተኑ ግሳት ነው?! ስርህ ተግተርትሮ፣ ላብ እያሰመጠህ፣ ያቀረብከው ‘ሪፖርት‘ እንዲያ ተውረግርገህ፣ የራስህን በጀት፣ የጓዳህን ወሬ፣ ወይስ የምስኪኗን … [Read more...] about ጎተራው ወዴት ነው?¡
ሰማሁ! እናቴ ሰማሁ!
ጠይም ፊትሽ መጥቆሩን፣ ትንፋሽሽ፣ ጥሎሽ መሸሹን፣ የፊትሽ ወዝ ማጠፈፉን አካል ቁመናሽ መርገፉን ሰማሁ እናቴ ሰማሁ፣ አይቻል የለ ችያለሁ። በዝምታ ተውበሽ በሰው ሸክም ተሞሽረሽ በኡኡታ … በዋይታ… መሸኘትሽን ሰማሁት አይቻል የለ ቻል አ’ረኩት የሆንሽውን ሳልጠይቅሽ ሳትነግሪኝ ጎንሽ ሆኜ ሳላዋይሽ ሳታዋይኝ ሞተሽ ቀብርሽ ሳልቆምልሽ ከቀረሁኝ እናቴ ሆይ! ፍረጂልኝ ፍረጂብኝ ምን ላድረገው? ምን ታረጊኝ? ስደት ዶጋ አመድ ያድርግህ! እንደ እናቴ ትንፋሽ ይንሳህ! ምንስ ብትነፍግ ብታሳጣ ካገር ወጪ ብታውጣ የናቴን! የናቴን እንኳን የመጨረሽ ሽኝቷን እንዴት! ከዓይኔ ታርቅ እንዴት! ከእግሬ ትነጥቅ አዎን! ግድየለም! ሞት መቼም ለኛ አዲስ አይደለም ግን! እናትን ያህል ነገር እንዴት ታሳጣኝ ቀብር? ምነው እናቴ አንችስ! ናፍቆትሽን … [Read more...] about ሰማሁ! እናቴ ሰማሁ!
እርሳስና ላጲስ
እርሳስ በጓደኛው፤ በብዕር እስክሪፕቶ ባለው ገደብ የለሽ፤ ነጻነቱ ቀንቶ እንዳሻው ቢናገር፤ የልቡን አውጥቶ እንዲህ አልክ ብሎ፤ ያለውን አጥፍቶ የሚያስወግድበት፤ በላጲስ አንሥቶ ስለማይከላ፤ ሲናገር አፍ ከፍቶ ፡፡ እሱ ግን ዘለዓለም፤ በላጲሱ ጠፍቶ መኖሩ አስመርሮት፤ በእጅጉ ተከፍቶ እኔስ ለምን እንዴት? ማለት ጀመረና ጠየቀ አፋጠጠ፤ ተሰማው ፍነና ነጻነቱን ሊያውጅ፤ ተነሣ ይሄ ጀግና ከእንግዲህ በኋላ፤ አለ ቆፍጠን ብሎ የነበረውን ፍርሐት፤ ከልቡላይ ነቅሎ ከእንግዲህ ወዲህ፤ አለ አንሥቶ ክንዱን ባናቴ ያለው ላጲስ፤ ገደብ የለሽ ሥልጣን አብቅቷል ብያለሁ፤ ይሰማ አዋጀ የሚጸና ይሆናል፤ በትውልድ ልጅ ልጀ ከዚህች ቀን በኋላ፤ ማንም ያላወቀ በእውቀት ያለበቃ፤ ከንቱ ያልጠነቀቀ ዐሥሬ እየጻፈ፤ እየለቀለቀ ዐሥሬ የሚያጠፋ፤ መሀይም የወደቀ ውሸት … [Read more...] about እርሳስና ላጲስ
የዝናብ ሀሳቦች
ዝናብ መች ይከፋል ቢዘንብ ምን አለ መብረቅ ባያስከትል እያጉረመረመ መዝነቡንስ ይዝነብ ማበስበሱን ቢተው ቀን የጣለ አይደል ሌት የሚያዳልጠው። ★★★ ሌቱን ሲዘንብ አድሮ ቀኑን ብራ ዋለ ለምን ይወቅሱታል ሰው መስራት ከቻለ ሲጥልም አይጣል ነው ዶፉ ከወረደ ማን አለብኝ ያለው ገደሉም ተናደ። ★★★ ዝናቡ ከመጣ "አህያ ማይችለው" በጊዜ 'ንጠለል ከወረደ አንዴ ነው እዲህ ከሚፎክር መጣሁ ቀረሁ እያለ ወርዶ ቢያሳርፈን እሱም እፎይ ባለ። ተጻፈ 8/5/2014 … [Read more...] about የዝናብ ሀሳቦች
“ትግሬ ትጠላለህ”
. . . ነፍሱን አይማርና! ያ! ቀጣፊ ከንቱ - የሂትለሩ ጉብልስ፣ አሳልፎ ሄደ፤ መሰሪ ትምህርቱን - ለበረከትና...ለነ አቶ ሽመልስ፤ እነሱም በተራ፣ ለታችኛው አሽከር ነጭ ውሸቱን ዘርተው፣ አጨዱት. . .፣ ከመሩት. . .፣ ማተብ-አልባ አድርገው፤ ከወያኔ ካድሬ፣ የውሸት ፋብሪካ፣ ተመርታ የወጣች፣ የዘረኞች ቋንቋ፣ “ትግሬ ትጠላለህ” የሚሏት ቃል አለች፤ ያገር ወዳዶችን ተቃውሞ ማስቆሚያ፣ በይሉኝታ ገመድ ሸብቦ ማሰሪያ. . .፣ ሆና ታገለግል ዘንዳ የተቃኘች፣ የጥላቻ ዜማ፣ ለጆሮ እምትቀፍ፣ ጩኸት የቁራዎች። . . . እዩትማ እንግዲህ፣ ወደ ውስጥ ሲሰምጥ፣ መብሰሉን ሲያቅተው፣ ሲላወስ እንደ ሊጥ፣ ራሱ በፈጠረው፣ ራሱን አስጨንቆ፣ ጭቃ ሲንከባለል፣ እኩዮቹን ክዶ፣ ራሱን አሳንሶ፣ ሚጢጢዋን ሲያክል፤ ስልጣኑ አስክሮት፣ የግፍ ሃብት ቆዝሮት፣ ንቀት አሳውሮት፣ … [Read more...] about “ትግሬ ትጠላለህ”
ወፍ፣ መብራትና እኛ!!
ይሄ የፓውዛ ግንድ - የመብራት ምሶሶ ያደምቀናል ስንል - ለጭለማው ደርሶ ለካ ጎጆ ሆኗል - የአዕዋፋት ማረፊያ የዕንቁላል መጣያ - የድካም መግፈፊያ፤ ወትሮም እንደዚህ ነው እያለ በሌለ- ላሰቡት ባልዋለ - በቆመ ህይወት ላይ ሲንደረደርበት - ብርቱ ዘሎት ሲሄድ - ሲያልፈው ነው የሚታይ!! (ፎቶ - አብርሃም አዳሙ) … [Read more...] about ወፍ፣ መብራትና እኛ!!
The Last Post-Cold War Socialist Federation
After the fall of the Berlin wall and the disintegration of the former USSR and Yugoslavia, it has widely been assumed that socialist federations have become a thing of the past. Ethiopia’s ethnic federal system however is essentially a socialist federal system based on the notion of the ‘right to self-determination of nationalities’ and a Marxist-Leninist organization of the state and party. This book assesses the Ethiopian ethnic federal system from the perspective of the principles of … [Read more...] about The Last Post-Cold War Socialist Federation
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፫
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ ሁለት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ የኚህ ሰው ማናቸው - አይነተኛ ተግባር አይደለም ሙሉውን - ታሪክ ለመዘርዘር ጥቆማውን አይቶ - አንባቢ እንዲፈልግ ይረዳል ብለን ነው - መንገዱን ለመጥረግ ተሰማ እሸቴንም - በዚህ አጭር ግጥም ማንነታቸውን - ማስቀመጥ ባንችልም በዜማ በቅኔ - አዋቂነታችው ምንጊዜም ይነሳል - ይጠራል ስማቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ - ከሹም እስከ ንጉስ ያገኙ ሰው ናቸው - እጅግ ታላቅ ሞገስ፡፡ ላሁኑ “እኚህ ሰው … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፫










