ከአዘጋጆቹ፤ ወዳጃችን ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ዓምድ ሥር ለአገራቸው የለፉና የደከሙ ኢትዮጵያውያንን እንዲነሱ፣ እንዲወደሱ፣ እንዲከበሩ፣ ... በማድረግ ግሩም ሥራ ሲሰሩ ቆይተው ባለፈው ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት እናንተ አንባቢያን ታሪካቸው መነሳት አለበት የምትሉትን ከፎቶ ጋር እንድታቀርቡ ጥሪ አድርገው ነበር፡፡ የአገራችን ታሪክ በሚያስደነገጥ ፍጥነት እየወደመ ባለበት በአሁኑ ወቅት በህይወት ያሉትንም ሆነ የሌሉትን አንስተን ማወደስ ተገቢ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ልንሳተፍበት የሚገባ አገራዊ ጥሪ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ትኩረታችን እና ኃይላችንን የሚወስደው ነገር አንድ ብቻ መሆን የለበትም ምክንያቱም እየደረሰብን ያለው ጥቃት ከበርካታ አአቅጣጫ ነውና፡፡ ስለዚህ አሁንም ይህንን ዓምድ በከፈትንበት መልኩ ሥራቸውና ታሪካቸው እንዲነሳ የምትፈልጉት ሰው ካለ ፎቶውንና … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፰
Literature
የኢሕአዴግ ቁልቁለት
“ፋክት” መፅሔት ላይ ቋሚ አምደኛ በመሆን በየሳምንቱ በወቅታዊ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የሚያተኩሩ ፅሁፎችን ወደ አንባቢ ሲያደርስ የነበረው ሙሉዓለም ገ/መድኅን አዲስ መጽሐፍ ለኅትመት አብቅቷል፡፡ የመፅሃፉ ርዕስ፡- የኢሕአዴግ ቁልቁለት ደራሲ ፡- ሙሉዓለም ገ/መድህን የገፅ ብዛት፡- 235 ዋጋ ለአገር ውስጥ፡- 52 ብር ለውጪ አገር፡- 20 ዶላር አጠቃላይ ይዘት መፅሃፉ በአራት ክፍሎች እና በአስራ አራት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፣ ክፍል አንድ ላይ “ቁልቁለቱን በኢሕአዴግ ጎዳና” በሚል አምስት ምዕራፎች ተካተዋል፡፡ በዚህ ክፍል ብሶት ወለደኝ የሚለው ህወሓት ተነሳሁለት የሚለውን የትግል ዓላማ እንዴት እየቀለበሰው እንደመጣ በዝርዝር ያስቃኛል፣ በመስመር መሀል ከጫካ ጀምሮ የህወሓት የፖለቲካ አሽከር ስለሆነው ኢህዴን/ብአዴን ፖለቲካዊ ክሽፈት ያነሳል፣ ለቁጥር ብቻ … [Read more...] about የኢሕአዴግ ቁልቁለት
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፯
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፮” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ ስድስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ መልስና አዲስ በታሪክ መዛግብት መጀመሪያ ምዕራፍ ስራ ታሪካቸው ምንም ሳይዛነፍ የተጻፈላቸው የሚነሱ ሁሌ እኚህ ስው ነበሩ ሸዋረገድ ገድሌ ሸዋረገድ ገድሌ ቆፍጣናዋ አርበኛ የተባሉ ናቸው የጦር ጥበበኛ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፯” ደግሞ ወለላዬ ሃሳባቸውን ቀይረው አንባቢያንን ለማሳተፍ እንዲረዳ ከቀደምት ታሪካችን እስካሁን ያልተጠቀሱ ነገር ግን እናንተ አንባቢያን መታወቅ ይገባቸዋል የምትሉትን … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፯
“እማይቻለው – ለተቻለው”
... እንዴት ነበር ከቶ ውጣ-ውረዱ...? ...ተረተር፣ ሸለቆ...፣ አቀበት፣ ቁልቁለቱ...፣ ...ጉድባው፣ ጉብታው...፣ አባጣ-ጎርባጣው...፣ ...እሾኽ፣ እንቅፋቱ...፣ መሰናክል፣ ምቱ...፣ ...ጠመዝማዛው ጉዞ...፣ እንዴት ነው መንገዱ? የያሬድ ልጅ ጠቢብ - መንፈስ የማኅሌታይ፣ የሰልስቱ ዜማ - ግዕዝ፣ እዝል፣ አራራይ፣ ነፍስን መሳጭ ቅኝት፣ ገነተ-ሕይወት አምሳል፣ አንቺሆዬ፣ ባቲ፣ ትዝታ፣ አምባሰል፣ ዓለም ኖታ ሳይነድፍ - የነበርንን እኛን፣ ሕዳሴ-ወጥበብ - ዳግም አስተዋውቀን፤ የ”ክፉ ቀን” ጓድህን፣ የደስታ ምንጭህን፣ የውጥን አጋርህን... ፒያኖህን ይዘህ ምጠቅ ክበርበት፣ ውጣ ተራራውን እስክትደርስ ከጫፉ... ከምኩራቡ ስፍራ ያምላክ ቃል ካለበት፤ ፍጹም ልቀህ ቆመህ ከዚያ ክቡር ማማ፣ የገደል ማሚቶው ዘልቆ እስከሚሰማ፣ በአምባሰል መንፈስ፣ … [Read more...] about “እማይቻለው – ለተቻለው”
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፮
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አምስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ብዙ ስለሰሩ መኮንን ሀብተወልድ መገለጽ አለበት ታሪካቸው የግድ ብዙዎችም አውቀው ይህን ተናግረዋል እየዘረዘሩ ታሪክ አስፍረዋል ቆፍጣናው መኮንን እኚህ ስመ ጥሩ የአክሊሉ ሀብተወልድ ወንድምም ነበሩ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፮” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፮
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አራት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ የወልደጊዮርጊስ ቢታይ ምስላቸው ሁሉም ሰው አወቀ እስከታሪካቸው እንደዚህ በሥራው ያገኘ ሰው ሞገስ ምንግዜም ይኖራል በጥሩ ሲታወስ ወልደዮሀንስም በልጃቸው ሥራ አብረው ይጠራሉ ይዘው ትልቅ ስፍራ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭
የመጨረሻው ደወል !
ኳ! ኳ! ኳ! ይላል፤ በማርያም ደጃፍ - በገብርኤል፤ በጎርጊስ ደጅ - በሩፋኤል፤ በጨርቆስ ደጃፍ - በአማኑኤል፤ በተክልዬ - በሚካኤል፤ ኳ! ኳ! ኳ! እያለ፤ የመጨረሻው ደወል ተደወለ፤ አትንበርከክ በቃ ! ቆመህ የጴጥሮስን ሞት ሙት አለ:: (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የመጨረሻው ደወል !
“አልመች አለው ጎኔ!”
ጥበብ የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ስሜት የሚገለጽባቸው ቀዳሚው እያዝናና የሚያስተምር ዘርፍ ቢሆንም አሁን አሁን ግን ያ እየሆነ አይታይም። የማፍር፣ የምኮራባቸው ጥበበኞች ጉዳይ አሁን አሁን ያሳስበኝ ይዟል ... እናም የጎልማሳው አቀንቃኝ የጃኪ "አልመች አለው ጎኔ!" ጣዕመ ዜማ ውስጥ ስሜቴን ቢነካካው፣ የማፍር የምኮራባቸው፣ ጥበበኞች ... ብየ ጀመርኩት! የጥበብ ሰዎች በግል እንደ ተራ ዜጋ የፈቀዱትን ፖለቲካ አቋም የመያዝ መብታቸውን የማከብር ቢሆንም ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ከእውነተኛ የህዝብ መብት ጥያቄና ስሜት ሳይሆን ለሆዳቸው ሲያድሩ ማስተዋል ስሜትን ይጎዳል። በተለይም ደግሞ የጥበብ ሰዎች ለሆዳቸው አድረው ከገዥ አንባገነኖች ጋር ወግነው የህዝብ ድምጽ ሳይሆን የፖለቲካ ፖርቲዎች ቱልቱላ ሲሆኑ ማየት ያማል። ያለመታደል ሆኖ በእኛ ኢትዮጵያ ከጥቂት የጥበብ ሰዎች በስተቀር … [Read more...] about “አልመች አለው ጎኔ!”
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬
የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ "እኚህ ሰው ማናቸው?" በሚል ርዕስ ግሩም ዝግጅት ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። ይህንን ዝግጅት በጥያቄና በግጥም መልክ የሚያቀርቡት እንደመሆኑ ምላሹም በግጥም እንዲሆን አንባቢያንን እርሳቸውም እኛም እናደፋፍራለን። ወለላዬ ከተለያዩ የግልና መሰል የህይወት ውጣውረዶች በኋላ አሁን ዝግጅታቸውን እንደገና ጀምረዋል። ጎልጉልም በደስታ እንኳን ደህና መጡ ይላቸዋል። የመጨረሻው "እኚህ ሰው ማናቸው?" ፲፫ኛው ነበር የዚያን መልስ ከአዲሱ ጥያቄ ጋር አቅርበናል። ወዳጃችን ወለላዬ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ ምስጋናችን ይድረስዎ። ከዚህ በፊት ኮሎኔል ታምራት ይገዙን አቅርቤ መልስ ሳልሰጥ አቋርጨ ነበር። አሁን ከመልሱ ጋር አዲስ ልኪያለሁ መልስ ይዘን የቀረብነው ምስላቸውን በፊት ይባሉ ነበረ ኮሎኔል ታምራት ኮሎኔል ታምራት ታምራት … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬
ሆሳዕና
ማቴዎስ .21፥1-17 ወደ እየሩሳሌም ወደ ቤተፋጌ ደርሰው ነበርና ደብረዘይት ግርጌ በዛን ጊዜ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሎ አዘዘ ጠራና ሁለቱን ከዛ ከፊታችሁ ከምትገኝ መንደር አህያ ታስራለች ከውርጫዋ ጋር ሂዱ ቅደሙና አምጡልኝ ፈታችሁ ማንም ደግሞ በዚህ አንዳችም ቢላችሁ በሉና ንገሩት ጌታ አስፈልጎታል ይሄንን ሲሰማ ወዲያው ይሰዳታል። ፅዮን ሆይ! ንጉሥሽ ባህያ ጀርባ ላይ ይመጣል እንዳለው አስቀድሞ ነብይ ደቀ መዛሙርቱም ሄደው አመጡለት እንዳዘዘው ሆነ እንዲፈጸም ትንቢት። ባህያ ተቀምጦ ኢየሱስም ሲደርስ ከህዝቡ ብዙዎች እያነጠፉ ልብስ ሌሎችም እንዲሁ ከዛፉ ጫፍ ጫፉን ቆርጠው በመጎዝጎዝ ሸፈኑት መንገዱን ቀድመው የደረሱ የተከተሉትም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በአርያም የተባረከ ነው መጪ በጌታ ስም እያሉ በመጮኽ ይናገሩ ነበር አንድ ላይ … [Read more...] about ሆሳዕና










