እስካሁን ለምን በተደጋጋሚ ከሸፍን? እንደምን አላችሁ፣ አሰላሙ አሌይኩም፣ አካም ጂርቱ፣ እንደምን አረፈዳችሁ (good afternoon everyone)። የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ በዚህ ስብሰባ ላይ እንድናገር ስለ ጋበዘኝ ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ። ከእናንተ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጋር በመሆን ስለምትወዷት አገራችን የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት መብቃት ታላቅ ዕድል ነው። በአሁኑ ወቅት አገራችን በከባድ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፤ ይህም ቀውስ በአንድ ጊዜ የተከሰተ ሳይሆን ለዓመታት ሲጠራቀምና ሲከማች የቆየ ነው። የአገራችን የወደፊት ሁኔታ ሁላችንንም የሚያሳስበን በመሆኑ እናንተም ይህንኑ ሃሳብ እንዳቀርብ በጠየቃችሁኝ መሠረት እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት በመሥራት ለአገራችን የተሻለ የወደፊት ተስፋ ማምጣት እንዴት እንደምንችል ሃሳቤን … [Read more...] about የጋራ የሆነች ኢትዮጵያ እንዴት እንመሠርታለን?
A Call To Boycott Ginbot 20 Celebration in New York
Subject: Occasion at the Church of Holy Family at 315 East 47 St on June 3, 2017 Dear Sir/Madame We respectfully ask you NOT to celebrate Ginbot 20. Unless you are protesting, your presence at the Church of Holy Family on June 3, will mean you are celebrating ethnocentrism, the torture and killings of innocent Ethiopians.Instead we ask you to spend your precious time praying for thousands of Ethiopians who have been killed and tortured, millions that are starving and millions that are denied … [Read more...] about A Call To Boycott Ginbot 20 Celebration in New York
መቼ ነው እውነተኛው የትግል ማዕከል የሚፈጠረው?
መክሸፍ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፤ መገለባበጥ እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ዛሬም እንዳምናና ታቻምናው፤ ታጋዩን ክፍል ወደ አንድ ለማስባሰብ የሚሯሯጡ ሞልተዋል። ዛሬም የሃሳብ እና የተግባር አንድነት ብቻ ሕዝቡን ለድል እንደሚያበቃ መሰበኩ አላቋረጠም። የነበረው ተመክሮ ሳይፈተሽ፤ በፍላጎትና በምኞት ላይ ብቻ በመመርኮዝ፤ አዲስ ተዋንያን አዲስ ቅኝት ይዘው ወደ መድረኩ ብቅ ይላሉ። አሁንም ከመልሱ ይልቅ ብዙ ጥያቄዎችን ያነገበ ሂደት ቦታውን ወርሷል። ነበርኩበት። አልፌበታለሁ። እስካሁን ቦታውን ይዞ የነበረው፡ “ምንም ይሁን ምንም፤ ኢትዮጵያን እናድን!” በሚልና፤ “ሁላችሁም የያዛችሁትን እርግፍ አድርጋችሁ በመተው፤ እኛ በምንላችሁ ተሰባሰቡ!” የሚል ነበር ጥሪው። የዛሬው ግን ለየት ያለ ነው። የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል ሆነና፤ በሥልጣን ላይ ባለው የትግሬዎች ገዥ ቡድን … [Read more...] about መቼ ነው እውነተኛው የትግል ማዕከል የሚፈጠረው?
የትግሬ-ቤጃዎች ማንነት
ይህ ጽሁፍ እንዲታተምላቸው የላኩት (Bill Teferedegn: bill.teferedegn@yahoo.co.uk) ናቸው። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡ … [Read more...] about የትግሬ-ቤጃዎች ማንነት
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመንግሥት ውሸት፣ የሃይማኖት ተቋማት ውድቀት፣ … (ክፍል ሦስት)
የትግራይ ሕዝብ “ነጻ አውጡኝ” ብሎ ሳይሰይማቸው፣ ሳይመርጣቸው፣ ሳይጠይቃቸው፣ ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብለው የሰየሙ ወንበዴዎችና ሽፍቶች የምኒልክ ቤተመንግሥት ከገቡ 26 ዓመታት ተቆጥረዋል። በቂም፣ በበቀል፣ በክፋትና በኢሞራላዊ ተግባራት የተሞሉ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ፈጽሞ የሚያጠራጥር፤ ማንነታቸው ይህ ነው ተብሎ የማይታወቅ፤ በሐሰት ስም ከበረሃ እስከ ቤተመንግሥትና ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የታዩ፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ የትግራይን ሕዝብ ያስጨፈጨፉ (ሐውዜንን ይጠቅሷል)፤ ሲነሱ አንዳች ገንዘብ ያልነበራቸው መናጢዎች በበረሃ የድሃ ረሃብተኛ እህል ዘርፈው በመሸጥ፤ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያን ሐብት ሙልጭ አድርገው ዘርፈው ሲያበቁ “የራሳችን ንብረት ነው” በማለት ኤፈርት የሚባል የወንበዴዎች ሃብት ማከማቻ ቋት የፈጠሩ፤ ከበረሃ እስከ መንግሥታዊ ሥልጣን … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመንግሥት ውሸት፣ የሃይማኖት ተቋማት ውድቀት፣ … (ክፍል ሦስት)
“ዕድሜ ለግንቦት ሃያ…”
በግንቦት 20 ዋዜማ ዋልታ ቴሌቪዥንን እያየሁ ነው። ጋዜጠኛው ዝግጅቱን ከአመት አመት በማይቀየሩት መፈክሮች (ለምሳሌ "ግንቦት 20 የህዝቦች ሁሉ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ቀን ነው) ጀመረና፣ ዛሬም በጭንቅላቴ ውስጥ የሚፈነጩትን ጥያቄዎች ዘርዝሬ ለማሰብ እንኳን እድል ሳይሰጠኝ፣ "ከግንቦት 20 ወዲህ የተወለዱ ልጆች ስለዚህ ቀን ምን ያውቃሉ?" ብሎ ለመጠየቅ በየትምህርት ቤቱ መዞር ጀመረ። የ17 አመቷ ቆንጅዬ ልጅ በፍፁም የራስ መተማመን፣ " እኛ ባንደርስበትም በአባቶቻችንና በእናቶቻችን ላይ ላይ የነበረው ጭቆና የቀረበት ቀን ነው" አለች። ከልጅቱ በኋላ አንድም ሳያነቅፋቸው ቀኑን በኢቲቪኛ፣ በፋናኛ እና በዋልታኛ የሚተነትኑ ወጣቶችን ሳይ ቆይቼ፤ ሌላ የ18 አመት ልጅ ብቅ ብሎ " ግንቦት ሃያ ባይኖር እኔም እዚህ አልገኝም ነበር" ሲል ውሃዬን ተጎንጭቼ ዋልታን … [Read more...] about “ዕድሜ ለግንቦት ሃያ…”
“ሲሾም ያልበላ… ድሮ ቀረ” — [የግንቦት 20 ወግ]
አንጀት አርስና አንገት አስደፊ አስተያየት አንጀታቸው ካረረ ሽማግሌ። በመስሪያ ቤታችን የግንቦት 20 በዓልን እያከበርን ነው። ክቡር ሰብሳቢው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ብዙ የበዙና የተባዙ የለውጥ ማሳያዎችን ሲናገሩ ቆይተው በመጨረሻ እንዲህ አሉ፡- "...ባጭሩ ከግንቦት 20 ድል በኋላ ተቆጥሮ የማያልቅ ብዙ ለውጥ አምጥተናል። በተለይም ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል ረገድ ሙስና በማኅበረሰቡ ዘንድ ነውር ሆኖ እንዲታይ አድርገናል። ሁላችሁም እንደምታውቁት ድሮ ድሮ... "ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል"... እየተባለ በድፍረት ይነገር ነበር። ይህ ማለት ሲሾሙ መብላት ሲሻሩ ላላመቆጨት ወሳኝ መሆኑን ኅብረተሰቡ አምኖበት ነበር። አሁን ግን ይህ አባባል እየቀረና እየተረሳ ነው። ይህም የትግል ውጤት ነው።" ሰብሳቢው ይህንን በክብር እየተናገሩ እያለ ጋሽ ደፋሩ እጃቸው ላጥ! አድርገው አወጡ። … [Read more...] about “ሲሾም ያልበላ… ድሮ ቀረ” — [የግንቦት 20 ወግ]
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመሬት ነጠቃና ስደት (ክፍል ሁለት)
የዛሬ 26 ዓመት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ብሎ የሰየመ የወንበዴዎችና የሽፍታዎች ስብስብ በምዕራባውያን አንጋሾቹ ታግዞ የምኒልክን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቃላት እንደ እሣት እየተፉ ታሪክ ፈጽሞ ሊረሳው የማይችለውን ንግግር ያደረጉት ድንቅ ኢትዮጵያዊ ነበሩ – ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!! ስለ ኤርትራ መገንጠል እና ስለ ህወሃት የአስፈጻሚነት ተግባር የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው ይህንን ነበር የተናገሩት፤ “… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮትዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመሬት ነጠቃና ስደት (ክፍል ሁለት)
በግንቦት 20 ያተረፍኩትና የጎደለብኝ
ግንቦት 20 ከመደዴ ቀንነት ተመንጥቆ፣ ቅድስና ተቀብቶ መዘከር ከጀመረ ይኽው ሀያ ስድስት አመት ሆነ፡፡ በየካቲት 1983 አ.ም. ጎንደር በኢህአዴግ ሲያዝ፣ እኔና ጓደኞቼ እናስተምርበት ከነበረው ከጎርጎራ መንደር፣ በውጫሌ በኩል በኢህአዴግ ተሸኝተን፣ ደሴ ላይ አንድ ኩንታል ስንዴ ተመጽውተን አዲስ አበባ ገባን፡፡ ውጫሌ ላይ የሸኙን የኢህአዴግ ታጋዮች ቀድመውን አዲስ አበባ እንደሚገቡ ነግረውን ነበር፤ እንዳሉት ቀድመውን ባይገቡም፣ ብዙ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ ከኢህአዴግ የመጨረሻ ግዛት ከውጫሌ የደርግ ግዛት እስከነበረው የሀይቅ ከተማ የነበረውን የፈሪ ምድር ያቋረጥነው በእግር ነበር፡፡ ያንን ረባዳ ለምለም ስፍራ በእግር ስጓዝ አስበው የነበረው (አሁን ምኞት ብለው ይሻላል) ልብን የሚያሞቅ፣ ብርታት የሚሰጥ ነገር እስካሁን ከህሊናዬ አልጠፋም፡፡ " . . . . ከሁሉም በላይ የደርግ … [Read more...] about በግንቦት 20 ያተረፍኩትና የጎደለብኝ
የሚንተከተከው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢና አንድምታዎቹ!
ጋምቤላ እና ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ኦጋዴን አደጋ ላይ ናቸው! ኦጋዴን ተገንጥሎ ወደ ሞቃዲሾ እንዲጠቃለል መለስ ዜናዊ ፈርሟል። የሰነዱ ግልባጭ እንግሊዞች እጅ አለ። ወያኔ በሶስት አቅጣጫ እንደ ቆዳ የተወጠረ ቡድን ነው ሲባል ፩ ለዘመናት ሲተዳደርበት የኖረው ኢህአዴግ በሚለው ማእቀፍ ውስጥ የነበረው የአሽከርና የሎሌ ግንኙነት ማብቃቱና በራሱ በህወሃት መካከል ያለው የሃይል ክፍፍል ያመጣው አጠቃላይ የስርአቱ አደጋ መሆኑ፣ ፪ ለረጅም ግዜ ሞቅ ቀዝቀዝ ሲል የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ መልኩን ቀሮ ወደ ማይመለስ ህዝባዊ ተጋድሎ ማደጉና ከህዝባዊ ተጋድሎው ጀርባ ያሉት ነፍጥ ያነሱትን ድርጅቶች የመገዳደር ወይንም ችግሩን በፖለቲካዊ ውይይት ለመፍታት አቅም የማጣቱ ምክንያት ሲሆን ፫ኛው ክንፍ ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ ላይ የተፈጠረው አለም አቀፍ የሃይል አሰላለፍ ላይ "በዚህ ሰፈር … [Read more...] about የሚንተከተከው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢና አንድምታዎቹ!






![“ሲሾም ያልበላ… ድሮ ቀረ” — [የግንቦት 20 ወግ]](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2015/01/eprdfs-economic-policy-233x300.jpg)


