ቴዲ በክርስቶስ ተቦርነም በጲላጦስ እንዲት ይመሰላሉ? ምሳሌያዊ አነጋገሮች ተረቶቻች፣ የታላላቅ ሰዎች አባባሎች መጽሐፍትና ገጠመኞች እየተጠቀሱ ንግግር መክፈቻም ሆነ የጽሁፍ መነሻ መሆን በፊትም የነበረ አሁንም የቀጠለ የተለመደ ነገር ነው። እንደዚሁም የክርስቶስ ቃል የሀዋርያት ትንቢት ምሳሌና ተግሳፅም እንደቦታው አስፈላጊነት የሚጠቀስበት ጊዜ አለ። ይህም የሚሆነው ትምህርት ለመስጠት የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ እንደአስፈላጊነቱም ጊዜውና የተፈጸመውን ድርጊት ለማስተማር ነው። በሰርግ ጊዜ ጌታ በሰርግ ቦታ ተገኝቶ ባዶዎቹን እንስራዎች በጣፋጭ ወይን ሞላቸው ተብሎ ትምህርት እንደሚሰጠው። አንተም ለጽሁፍህ መነሻ ያደረከው ቃል በማትዮስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፯ ቁጥር ፲፩. ሰፍሮ ይገኛል። ቃሉም እንደሚያስረዳው እየሱስ በዛን ጊዜ ይሁዳ አሳልፎ ስጥቶት ሽማግለዎችና የካህናት … [Read more...] about ክንፉ ምን ነካህ?
US Lobbying Firm (SGR) Cozy with a Ruthless Dictatorial Regime in Ethiopia For 1.8 Million Dollars
Lobbying Firms in the US are known to represent big corporations like oil, construction, food manufacturing and pharmaceutical industries, trying to persuade lawmakers to support business friendly legislations. As this is a controversial practice, politicians running for office do not want to be associated with Lobbying firms. In fact, it was a major discussion topic during the 2016 presidential election season for both candidates. The main reason for politicians to discredit lobbying firms … [Read more...] about US Lobbying Firm (SGR) Cozy with a Ruthless Dictatorial Regime in Ethiopia For 1.8 Million Dollars
የትግራይ ብሄርተኞች ዕብሪትና የጣናው ሞገድ ፈተና በመቀሌ!
“የትምክህት ፈረስ፣ ነፍጠኛ፣ የምኒልክ ርዝራዥ፣ አማራ አህያ፣ ገና መቶ ዓመት እንገዛሃለን፣ …” የመቀሌ ከነማ ደጋፊዎች ጭፈራ “የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች የመልስ ጭፈራ የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆን? ያስፈራል! በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድድር ከፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ቀጥሎ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች የተለየ ትኩረት ይስባሉ። የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ወደ ፕሪሚየርሊግ ለማደግ የሚደረጉ ፍልሚያዎች በመሆናቸው የተመልካቾችን ቀልብ ይስባሉ። የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ምድብ “ሀ” ላይ የተደለደሉት ክለቦች በወጣላቸው መርሐ-ግብር መሰረት ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጨዋታቸውን አድርገዋል። የዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆኑት መቀሌ ከነማ እና ባህርዳር ከነማ (የጣናው ሞገድ) በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ግቢ (FB campus) … [Read more...] about የትግራይ ብሄርተኞች ዕብሪትና የጣናው ሞገድ ፈተና በመቀሌ!
የጃንሆይ እናት!
ነገሩ ትንሽ ቆየ። እኔ ግን በሆነ አጋጣሚ በቅርቡ ነው ቃለ ምልልሱን የሰማሁት። ተስፋዬ ገብረአብ አዲስ ስላሳተመው - “የጀሚላ እናት” መጽሃፍ፤ ከጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበር። በትክክል እንዳዳመጥነው ከሆነ፤ “የቀዳማዊ ኃይለስላሴ እናት ስም ጀሚላ ነው፤ አንድ ወገናቸው ስልጤ ጉራጌ ነው - በሌላ ወገን ኦሮሞ ናቸው።” ይለናል። በመቀጠልም፤ “የጀሚላ እናት በአቶ በዛብህ ተጠልፈው ነበር። አቶ በዛብህ ከምኒልክ ጋር በጦርነት ሞቱ። የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ወይም የጀሚላ እናት እልፍኝ ውስጥ፤ በአጼ ምኒልክ ተገደሉ።” የሚሉና ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ የልብወለድ ነገሮች በመጽሃፉ ውስጥ ማካተቱን በቃለ ምልልሱ ላይ ሰማን። ወደ ኋላ በመመለስ ‘በወቅቱ ምላሽ የሰጠ ሰው ይኖር ይሆን?’ በማለት አንዳንድ ድረ ገጾችን ብመለከት፤ በዚህ የተዛባ ታሪክ ምክንያት… … [Read more...] about የጃንሆይ እናት!
የኮሌራው ምሥጢር! የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ”?
በህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማና ድጋፍ ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተርነት የሚወዳደረው ቴድሮስ አድሃኖም የመመረጡ ጉዳይ አደጋ ገጥሞታል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበረበት ወቅት ሦስት የኮሌራ ወረርሽኞች በምሥጢር እንዲያዙ ማድረጉ ለዳይሬክተርነት እንዳይበቃ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ እንደ አሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይህ ጉዳይ የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ” ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ሜይ 13፤2017 ዓም “የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅትን ለመምራት የሚወዳደረው እጩ ወረርሽኝ በመደበቅ ተከሰሰ” በሚል ርዕስ ባስነበበው ዜና የቴድሮስን የመመረጥ ተስፋ ስለሚያጨልመው የኮሌራ ወረርሽኝ ምሥጢር በዝርዝር አትቷል፡፡ በያዝነው የግንቦት ወር (ከሜይ 22፣ 2017) ጀምሮ በጄኔቫ በሚካሄደው የአንድ ሳምንት ስብሰባ ድርጅቱን ለመምራት ከሚወዳደሩት ሦስት … [Read more...] about የኮሌራው ምሥጢር! የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ”?
ፍትህን ሰቀለው በፍትህ ስም የፕሮፓጋንዳ ዳንኪራ – የጨለማው ሳምንት!!
የ“ፍትህ” ወይስ የጨለማ ሳምንት? (ርዕሰ አንቀጽ) “ገንዘብ ሲናገር ፍትህ ጸጥ ይላል!” ይህ የተጻፈው በአንድ የጎንደር እስር ቤት ውስጥ ነው። የተጻፈው በግድግዳ ላይ ሲሆን በብዕር ወይም በቀለም አይደለም። ፍትህ ከተጓደለባቸው አንዱ የእጁን ጣት በመብጣጥ በደሙ ነው። ፍትህ የተዛባባቸው ይህንኑ አባባል ልክ እስር ቤት እንደገቡ ይሳለሙታል። በብዙ የአገሪቱ ማጎሪያዎች ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት ገላጭ ሃረጎች ይጻፋሉ። ፍትህን አደባባይ ሰቅለው በምስኪኖች ህይወት ለሚጫወቱ ይህ ሁሉ ስላቅ ነው። ፍትህን አደባባይ ሰቅለዋት፣ በፍትህ ስም እየማሉ በድግስ ሊያሽካኩ ይወዳሉ። ፍትህ የዜጎች ሁለንተናዊ ህይወታቸው ትርጉም የሚያገኝበት ውድ ጉዳይ ነው። ይህንን ሃቅ የበረሃው አባዜው አልለቅ ያለው ህወሃት ጥንቅቆ ያውቀዋል። ሊክደውም አይችልም። ለዚህም ነው “ህገ መንግስት፣ ህግ፣ አዋጅ፣ የሰብዓዊ … [Read more...] about ፍትህን ሰቀለው በፍትህ ስም የፕሮፓጋንዳ ዳንኪራ – የጨለማው ሳምንት!!
ገድለህ ማረው
የሰራህን በዓይንህ አይተህ ሲወሻክት ወይም ሰምተህ ልታቆመው ብትነሳ በዝምታ ፊት ብትነሳ አፍሮ ይተው እንዳይመስልህ ስምህን ነው ሚከትፍልህ ከዛ - ይልቅ ነገርህን አ’ርገህ ድብቅ ትንሽ ጊዜ ብትጠብቅ እንደወትሮው ሱሱን ሊያደርስ ካ’ንዱሊቀምስ ካ’ንዱ ሊልስ ከሰው ጋራ ሲቀላቀል ባልታሰበ የፊት ተንኮል ተይዞልህ ፊትህ ሲቀል መፋረጃህ ያን ጊዜ ነው ተቀላቅለህ አብረህ በለው ወይንም በዓይንህ ገድለህ ማረው (ወለላዬ ከስዊድን) … [Read more...] about ገድለህ ማረው
ተቦርነ በየነ “አንተ አልክ?” – ቴዲ አፍሮን
እንዲህም ሆነ። የይሁዳ ገዥ የነበረው ጲላጦስ ክርስቶስን አስጠርቶ "አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህን?" ሲል ጠየቀው። ክርስቶስም መልሶ "አንተ አልክ?" አለው። ሰማይን ያለ ምሰሶ ያቆመው ክርስቶስ "ጥፋ" የምትል ቃል ብቻ ከአንደበቱ ቢያወጣ ኖሮ ጲላጦስ አይደለም መላው ቂሳር ክምድረ-ገጽ በጠፉ ነበር። ታዋቂዎች በአዋቂዎች ላይ የሚቀልዱበት ይህ የገሃዱ አለም እውነታ ግብረ-ገብ ወደ ግብግብ በተቀየረበት በዚህ ዘመን ባሰበት እንጂ አልጠፋም። ጥንት አንቺ-ትብሽ፣ አንተ-ትብስ ይባል የነበረው ብሂል አሁን በ“አንቺ ብስብስ አንተ ብስብስ” ተቀይሯል ሲል አንዱ አጫወተኝ። ከቶውንም ስድብን እንደ ስንቅ በከረጢት ቋጥረው በሚጓዙበት የፌስቡክ ዘመን መስመር የመልቀቁ ነገር አዲስ ሊሆን አይችልም። "አንተ አልክ?" ብሎ ማለፍ ምን ይጎዳል? ብላቴናው ላይ አንዳች እንከን ሲያጡ፣ የጠወለገን የጥላቻ … [Read more...] about ተቦርነ በየነ “አንተ አልክ?” – ቴዲ አፍሮን
እንባ ካለ አሁን እናልቅስ!! ሊታመን ባይችልም አማኑኤል ሆስፒታል እንዲህ እየሆነ ነው!
“ቅባትና ደረቅ” በአማኑኤል የአዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ታካሚዎች እንደ ደረጃ መዳቢ የተሰጠ ስም ነው። ታሪኩ ዘግናኝ፣ ኅሊናን የሚፈትን፣ ወዴት እያመራን እንደሆነ ግራ የሚያጋባ፣ መፈጠርን የሚያስጠላ፣ ሲሰሙት ግራ የሆነ፣ ቃላት ሊገልጹት የማይችል የክሽፈታችን ሁሉ ከሽፈት ነው። አማኑኤል ሆስፒታል ተኝቶ ለመታከም አርባ ሺህ ብር እንደሚከፈል ከመስማት በላይ ዘግናኝ ጉዳይ የለም። ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ ሌሎችም ጉዳዮች አሉ። በአማኑኤል ሆስፒታል ሴት የአዕምሮ ህመምተኞች መደፈራቸውን፣ ሲያረግዙ ጽንስ የሚቋረጥበት ክሊኒክ በውስጥ በተደረገ ስምምነት ይሰጥ እንደነበር ይፋ በተሰማ ጊዜ ጫጫታ ተሰምቶ ነበር። ጉዳዩን በወቅቱ ይፋ ያደረጉት አንድ የሆስፒታሉ ነርስ ነበሩ። ዛሬ ያ ግፍ ተመርምሮ መልስ ሳያገኝ ተጨማሪ ጉድ እየሰማን ነው። የሟቹ መለስ ዜናዊ ባለቤት የበላይ ጠባቂ ሆና ስትመራው … [Read more...] about እንባ ካለ አሁን እናልቅስ!! ሊታመን ባይችልም አማኑኤል ሆስፒታል እንዲህ እየሆነ ነው!
“ደሸት” የብርሃን እውነት!
“ደሸት” የብርሃን እውነት! የማጂ፣ የጂማ፣ የመንዲ፣ የመደባይ አባት የማራ፣ የዥማ፣ የገንቲ፣ የአሬቲ ... አያት የአማራው፣ የኦሮሞው፣ ... የዘር ግንድ አውራ የመተሳሰሪያ እውነተኛ ምንጭ አሻራ! “ደሸት” ኢፋ ዹጋ ፍጥረተ ማለዳ የዘር ሀረግ ገመድ ምስጢራዊ ጓዳ አባ ቃሉ አባ ውሉ አያ ፍቅሩ ትስስሩ ዘረ ሸጋ ኢፋ ዹጋ መሆንህን አምኖ አማራ ኦሮሞ ስምህን በስሙ አትሞ “ደ”ን ደግ ብሎ አንብቦ “ሸ”ን ሸበበ ብሎት አንግቦ “ት”ን ትስስር ይለዋል ውልደቱን ከትቦ “ደሸት” የዘር ምንጩ አባ እቅጩ ስመ ክብሩ ውስጠ ምስጢሩ “ደሸት” የብርሃን እውነት! (ኢፋ ዹጋ!) ዘሩን ሲያበዛ ሲዘረጋ ማጂ፣ ጂማ፣ መንዲ፣ መደባይ ብሎ ሰይሞ የዘር ሲሳይ መደባይ ስሙን ከስሙ … [Read more...] about “ደሸት” የብርሃን እውነት!









