ህወሓት/ኢህአዴግ በራሱ ጉባዔ (ፓርላማ)፣ በራሱ ባለሥልጣናት፣ በራሱ ፈቃድ፣ በራሱ በሚተዳደረው ሚዲያ፣ ፈቅዶም ሆነ ሳይፈቅድ በሚገዛለት ሕዝብ ፊት ይፋ ያደረገው የስኳር ፕሮጀክት ዝርፊያ በራሱ አስፈላጊ ርምጃ ለመውሰድ በቂ ሆኖ ሳለ ሙስናን በመታገል ስም እስካሁን መቆየቱ በራሱ አነጋጋሪ ነው፡፡ ምክንቱም አፈቀላጤ ነገሪ ሌንጮ እንዳለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ደሙን የሚጠጡት የበላይ ኃላፊዎች እነማን እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነውና፡፡ ችግሩ ያለው ዋናዎቹን መዥገሮች ማን ይንቀላቸው የሚለው ላይ ነው፡፡ በኢህአዴግ ውስጥ የሚፈጠሩ አደገኛ የፖለቲካ ልዩነቶች ለማስተንፈስና የአመራሩንና አባላቱን አፍ ለማስዘጋት መለስ ዜናዊ ያደርገው እንደነበረው “የሙስና ዘመቻ” ሲጀመር ይህ ያሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በቅርቡ “ጥልቅ ተሃድሶ” በሚል “ዘመቻ” ሲጀመር … [Read more...] about ዋናዎቹ “መዥገሮች” ትንንሾቹን ነቀሉ!
የህወሃት/ኢህአዴግ ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ከሒዝቦላና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ጋር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አገኘ
የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት አልፏል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን ኮሪያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ጋር በእኩል ቀርቦ መታየቱ “የአሜሪካና ኢህአዴግ ወዳጅነት ወዴት?” አስብሏል፡፡ በዕለቱ ዘጠን አጀንዳዎች ለውሳኔ የቀረቡ ሲሆን የኢትዮጵያን ጉዳይ ጨምሮ የአውሮጳ ህብረት ሒዝቦላን አሸባሪ ድርጅት በማለት እንዲጠራው፤ የሰሜን ኮሪያን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ ከዚህ በፊት የወጣው እንደገና እንዲተገበር፤ ኬኒያ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዳታካሂድ፣ በቬኒዙዌላ ያለውን የሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውስ … [Read more...] about የህወሃት/ኢህአዴግ ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ከሒዝቦላና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ጋር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አገኘ
ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን!
የነጋዴዎች አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ገዥው ፓርቲ ከየአቅጣጫው በመወጠሩ - የችግሩን ትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር አለበት። የተለመደ የፉገራ ካርዳቸውን መዘዝ አድርገው ለዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ሰጡዋቸው። ኦቦ ነገሪ ሌንጮ 34 የመንግስት ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ትናንት ምሽት አብስረዋል። እነማን እንደታሰሩ ግን አልገለጹም። ታሳሪዎቹን ሊያውቁዋቸው ስለማይችሉ ሊገልጹ እንደማይችሉ ግልጽ ነው። እንደወትሮው ተጽፎ የተሰጣቸውን ከማንበብ ውጭ አማራጭ የላቸውም። የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን መታሰር እንደማንኛውም ተራ ሰው በዜና የሰሙት ነገሪ ሌንጮ ምን አፍ ኖሯቸው ስለ ባለስልጣናት መታሰር ይነግሩናል? ስራዎቼን ሁሉ በግምት ነው የምሰራው - መረጃ እንኳን አይሰጡኝም የሚሉ ጠቅላይ ሚኒስትርስ ምን አቅም ኖሯቸው ጉዳዩን ያስፈጽሙታል? የሙስና ጉዳይ … [Read more...] about ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን!
በጉጂ ዞን ከፍተኛ ውጊያ ተነስቷል
የአማሮ ህዝብ (ኮሬ ጎሳ) እና በጉጂዎች መካከል ከእሁድ (23 ጁላይ) ምሽት ጀምሮ ከባድ በሆነ የድንበር ግጭት መቀስቀሱን ወደ ስፍራው የተጓዙ እማኞች አረጋግጠዋል። ከእሁድ ምሽት ጀምሮ በተነሳው የጎሳዎች ግጭት እስከአሁን ያልበረደ ሲሆን በግጭቱ ሳቢያ በርካታ ቤቶች በመቃጠል ላይ መሆናቸውን ስፍራው ድረስ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ችለናል። በፎቶው ላይ እንደሚታየው በተነሳው ቃጠሎ አካባቢው በጭስ እየተሸፈነ ይገኛል። የአማሮ መንገድ በግጭቱ ሳቢያ ስለተዘጋ ወደ ዲላ ከተማ መውጣትም ሆነ ወደ ወረዳዋ መግባት እንዳልተቻለ የአይን ምስክሮቹ ገልጸዋል። የጸቡ መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን በውል ባይታወቅም የሚመመለከተው አካል ጉዳዩን ችላ እንዳለውም ለማወቅ ተችሏል። አንዳንድ ታዛቢዎች ወያኔ አሁን ከገባበት ማጥ ለመውጣት ሲል እንዲህ አይነት ግጭቶችን ሆን ብሎ እንደሚያስነሳ ይናገራሉ። … [Read more...] about በጉጂ ዞን ከፍተኛ ውጊያ ተነስቷል
መንግስት እንደ ሞስኮ ጣና እንደ ፑቲን!
የበርሊን ግንብ ከፈረሰ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በዲሴምበር 5, 1989 ዓ.ም. በምስራቅ ጀርመኗ የድሬዝደን ከተማ ነዋሪው በነቂስ ወደ ጎዳና ወጥቶ ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያሰማ ነበር። የተቃውሞው ኃይል እየበረታ ሲመጣ ህዝቡ ወደ አንድ ህንፃ መትመም ጀመረ። ላለፉት 40 ዓመታት የራሱን ህዝብ መተንፈሻ በማሳጣት ከፍተኛ አፈና ያደርግ ወደነበረው የደህንነቱ መስሪያ ቤት፥ወደ ''ሽታዚ'' ተብሎ ወደሚጠራው መስሪያ ቤት። ጥቂት ወጣቶች ግን የሽታዚን ቢሮ ሰብሮ ከገባው ህዝብ በመነጠል በጥቂት ሜትሮች ርቀት ወደሚገኝ አንድ ህንጻ አመሩ።የወጣቶቹ ወደ ህንፃው እየተጠጉ መምጣት ያሳሰበው የጥበቃ ሰራተኛ በፍጥነት ወደ ውስጥ ዘልቆ በመግባት አንድ ቀጭን እና አጭር የሆነን የ37 ዓመት ሰው አስከትሎ ወደተሰበሰቡት ሰዎች አመራ። ያም ቀጭኑ ሰው ጥርት ባለ ጀርመንኛ ''ይህ ህንፃ የሶቭየት ህብረት … [Read more...] about መንግስት እንደ ሞስኮ ጣና እንደ ፑቲን!
የጥላቻ መንስዔ፣ መዘዝና መፍትሄ
የጥላቻ መንስዔው ፣ መዘዙና መፍትሄው ምን ነው? በዚህ ላይ ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው። ፕሮፌሰር ብርሃኑ በኦልድ ዶሚኒየን ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው። … [Read more...] about የጥላቻ መንስዔ፣ መዘዝና መፍትሄ
የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት
የአስቸኳይ (የአፈና) ግዜ አዋጁ ገና አልተነሳም። በአዲሱ የግብር ትመና ሳብያ ከዳር እስከዳር የተነሳው ሕዝባዊ አድማ እና አመጽ ግን አዋጁን ውድቅ ያደረገው ይመስላል። አንድ ስርዓት ራሱ ያወጣው ህግ በህዝብ ሲሻርበት - ያኔ ነው ያበቃለት! ከቶውን "የአለምን ኢኮኖሚ እየመራች ያለች ሃገር" የበጀት ሸክሟን ለምን በህዝብ ላይ መጣል እንዳለባት ግልጽ አልሆነም። እውነታው ከነዚህ ሁለት እይታዎች ውጭ አይሆንም። ይነፋ የነበረው የእድገት ቀረርቶ እና ይነገር የነበር ሁለት ዲጅት እድገት ቁጥር ሁሉ ውሸት ነበር፣ ወይንም ደግሞ የሃገሪቱ ሃብት በጥቂቶች እየተዘረፈ ነው። ጆሮን ያሰለቸው የ"እድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ" ዘፈን ቀዝቀዝ ማለት ሲጀምር የ "ደብል ድጅቱ" የፈጠራ ተረት እንደ በረዶ እየነጻ መሄዱ አልቀረም። እድገቱ የህዝቡን ህይወት አልለወጠም። ተጀምሮ ከሚቋረጥ ህንጻ … [Read more...] about የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት
ትዝታ – ሀዲስ አለማየሁ
ቅኝት - መስፍን ማሞ ተሰማ የቃኚው ማስታወሻ፤ ጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣ ጁላይ 2 / 2017 “ራስ እምሩን በተመለከተ” በሚል ርዕስ አንድ ፅህፍ ለንባብ አብቅቷል። ይህ የጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣን አቋም ያንፀባረቀው ፅሁፍ ሙያዊ ሥነምግባርን (ፕሮፌሽናል ኤቲክስ) ከብቃትና ከሃላፊነት ጋር ያዋደደ ስህተቱንም በግልፅና ያለማወላወል የተቀበለና ለእርማቱም መፍትሄን ያመላከተ መሆኑ የድረገፁን ዝግጅት ክፍል የሚያስወድሰውና በአርአያነትም ከመጀመሪያው ረድፍ የሚያቆመው ይሆናል። የሚዲያ ተልዕኮ መሰረቱ እንዲህ ሲሆን ተዓማኒነቱንና ሚዛናዊነቱን ያረጋግጣልና። በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በተፃፈው ‘አዳፍኔ’ መፅሀፍ ላይ ክቡራ ልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴ በአርበኝነታቸው ሳይሆን ‘ከጣሊያን ደሞዝ ተቆራጭ የሆነላቸው ባንዳ’ ተደርገው ከባንዶች የስም ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ለዚህ ቃኚ … [Read more...] about ትዝታ – ሀዲስ አለማየሁ
ስምህን ሳላነሳ፣ የተወጋ አይረሳ!
ስምህን ሳላነሳ፣ ምኑን ሆንከው ፀጋ ለአብሮነት መኖር፣ እየሆንክ አደጋ፣ አድርገህ ከያዝከው፣ የሙሉቀን ሥራ ለማቃባት ደም፣ ኦሮሞን ካማራ። ‘ጀሃዳዊ ሃረካት’፣ እና ‘አኬል ዳማ’ በለምለሟ አርሲ፣ በአኖሊ ከተማ ወያኔ ያቆመው፣ የጥላቻ ሃውልት የተሸከመው እጅ፣ የተቆረጠ ጡት ሆነ ውጤት አልባ፣ አነሰ አሉህ እንዴ አሽከርካሪዎችህ፣ ፍጠር ሌላ ዘዴ? ጦርና ጎራዴ ሕዝቡን ለማማዘዝ ድንገት ቱግ ብለህ፣ የምትረጨው መርዝ። ዕውቀት ነበርኮ፣ ወገንን ለመጥቀም ተከባብሮ እንዲኖር፣ ተዋዶ በሰላም አየ ያንተስ መማር፣ “በረከተ መርገም”!! ተስፋ ለቆረጠ፣ ቀን ለጨለመበት ለጭቁን ወገኑ፣ መላ ለጠፋበት ታጭዶ ለሚወቃው፣ በአግዓዚ ጥይት በአላሚ እሩምታ፣ በቅሊንጦ ታጥሮ ዶጋመድ ለሆነው፣ በሳት ተንጨርጭሮ ፍዳውን ለሚያየው፣ እሥር ቤት ታጉሮ እርቃኑን ለቀረው፣ … [Read more...] about ስምህን ሳላነሳ፣ የተወጋ አይረሳ!
The story of Nigist Yirga: one brave girl among thousands in TPLF terror House
Nigist Yirga Tefera is a twenty-four-year-old girl and a resident of kebele18 in Gonder City. As most of the youth in Ethiopia she is craving for fair governance, equality, democratic rights and an end to extremely corrupt and ethnocentric rule.Standing up for her basic rights took her to Kaliti prison cell since June 2008. Nigist is accused by the TPLF court with terrorism, helping terrorist organizations and participating in and organizing demonstrations against the regime.Her case was heard … [Read more...] about The story of Nigist Yirga: one brave girl among thousands in TPLF terror House










