የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም አገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድቅመት የሚከበር በዓል ነው፤ በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ ልማድና ወጋቻን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ለአዲስ ዓመት ወይም ለዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ዝግጅታችንም ሆነ አከባበራችን እጅግ በጣም ጠንካራና ደስ የሚል ነው፡፡ አዲስ ዓመት የሁሉ ነገር መጀመሪያ ነው ለዚህም ነው ብዙ እቅዶቻችን ከመስከረም ወር የሚጀምረው፤ ያቀድነው ነገር በዓመቱ መጨረሻ ሊሳካ ወይም ላይሳካ ይችል ይሆናል ቁም ነገሩ ግን በዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ለማሳካት የታሰበ እቅድ መኖሩ ነው፤ ለእቅዱ አለመሳካት ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ እነዚህን እንቃፋት የሆኑ ምክንያቶች ለይቶ ማወቅ በራሱ የእቀዱ አንድ አካል በማደረግ እንደገና ለመጪው አዲስ ዓመት ለተሻለ እቅድ ግባት ይሆናል፡፡ የዘንድሮ አዲስ ዓመት … [Read more...] about መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ …
Anuak Justice Council (AJC)
Reports Emerge of TPLF/ERPDF Efforts to Suppress Testimony in World Bank’s Investigation Regarding the Misuse of WB Funds in the Forced Displacement of Anuak and Related Land Grabs in Ethiopia’s Gambella Region Press Release (Vancouver, BC, Canada)— The Anuak Justice Council (AJC) has received disturbing reports from on-the-ground sources in refugee camps in the Republic of South Sudan and Kenya as well as from sources in Gambella, Ethiopia that the TPLF/EPRDF Government of Ethiopia is … [Read more...] about Anuak Justice Council (AJC)
“የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ
አምባገነነኖች ከሚታወቁበት አንዱና ዋንኛ መለያቸው መካከል ሁለተኛ ሰው አለማዘጋጀታቸው ነው። አቶ መለስ በድንገት ሲስፈነጠሩ በውል የታየው አስከሬን ደብቆ ድብብቆሽም የዚሁ ውጤት ነው። ኢሳያስ ከስልጣን ቢወገዱ ማን ይተካቸዋል? የሚለው ችግርም ጎልቶ የሚታየው ከዚሁ የአምባገነኖች በሽታ አንጻር ነው። ግጭትና ችግር ከመፈጠሩ በፊት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያንጫርረው ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) ፍርሃቻም ከዚሁ የመነጨ ይመስላል። በኤርትራ ህዝቡ በቃኝ ወደ ማለቱ ደረጃ መቃረቡን የሚጠቁመው የዘንድሮው ዓመት ሪፖርት ኤርትራ በቅርቡ መንግስት አልባ የመሆን እድሏ ሰፊ እንደሆነ ያወሳል። በቅርቡ "የሚከሽፉ መንግስታት" በሚል ስማቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ አገሮች መካከል ኢትዮጵያም ተመልክታለች። እኩል ወደ ስልጣን የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ … [Read more...] about “የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ
ሰንደቅዓላማችን (ትእምርተ-ኪዳናችን) ከየት መጣ ማንስ አጠፋው?
ስለ ሰንደቅ ዓላማ ትርጉም ስናወራ ሰንድቅ ዓላማ ማለት በዘንግ ወይም በመስቀያ ያለ ሰንደቅ ማለት ነው፡፡ መስቀያው ዓላማ ሲባል የሀገር ዓርማ የሆነው ባለቀለሙ መለያ ምልክት ደግሞ ሰንደቅ ይባላል፡፡ የሚለው አንዱ ሲሆን ሌላኛው ትርጉሙ ደግሞ ሰንደቅ ዓላማ የሚባለው ባለቀለሙ የመለያ ምልክት ብቻ እንጅ መስቀያውን አይጨምርም ሰንደቅ ዓላማ መባሉም ሰንደቁ የራሱ የሆነ ዓላማ እንዳለው ለማመልከት ነው የሚሉም አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የመንግሥት ሰንደቅ ከመሆኑ በፊት ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ንዋዬ ቅድሳት አንዱና እንዲያውም የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ሰንደቅ ነበር፡፡ በቤተክርስቲያን እነዚያ ሦስት ቀለማት አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ወይም ቀይ ቢጫ አረንጓዴው ቀለማት በንዋዬ ቅድሳቶቿ ሁሉ ላይ ከብራና መጻሕፍቶቹ እስከ መንበረ ታቦታተሕጉ ድረስ ይገኛል፡፡ ከጥንታዊ የብራና መጻሕፍት … [Read more...] about ሰንደቅዓላማችን (ትእምርተ-ኪዳናችን) ከየት መጣ ማንስ አጠፋው?
ስምና ገመድ!!
በተለያዩ ምክንያቶች ለረጅም ጊዜ አቋርጠነው የነበረውን የግጥም ጨዋታ እንደገና ጀምረናል፡፡ ከዚህ በፊት እናደርገው እንደነበረው አንባቢያን ይህንን ግጥም አንብባችሁ አስተያየታችሁን በግጥም እንድትሰጡና ጨዋታውን እንድታደምቁት እንጋብዛለን፡፡ ለዛሬ የመረጥነውን ግጥም ከነፎቶግራፉ ያገኘነው ከደመቀ ከበደ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው፡፡ገጣሚ ደመቀ ከበደን ለግጥሙና ለፎቶው ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ስምና ገመድ!! አዝማሪ እንዲህ አለ፤ "ሰው ሰበበኛ ነው - ምክንያት አያጣም እንኳን ዝናብ ዘንቦ - ሲዳምን አይወጣም፤" እኔ ግን እላለሁ፤ አተተ በተተ ወዘተ ወዘተ በሚል አርቲ ቡርቲ - ዕድሜ ከምንጨርስ ህይወት ከምናጣ ፋይዳ ላለው ነገር - ቁልቁለት እንውረድ አቀበት እንውጣ፤ ያኔ አላስወርድ ካለህ - ወይም አላስወጣ ማሰሪያ ከሆነህ - አሊያም ጋሬጣ ያኔ አይንህን … [Read more...] about ስምና ገመድ!!
በአዲስ አመትም ያላባራው ስቆቃ
በግልም ቢሆን አዲሱን አመት በሰላም እና በደስታ መቀበሌ እውነት ነው! መስከረም ጠብቶ ብዙ ቀናት ሳንቆጥር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርሰኝ የስደተኛ ወገን መከራ ግን ከአዲሱ አመት ዋዜማ ጀምሮ እስከ መባቻው አላባራም … አያንዳንዱን የወገን ስደት ሰቆቃ መከራ ጨክኘ ከመናገር ለመቆጥብ ያደረግኩት ትግል ላንዲት ቀን ቢሳካም ህሊናየ ግን እረፍት አላገኘም! በተለይ በአዲሱ አመት ዋዜማ "ብሪማን" ተብሎ በሚጠራው የጅዳው ትልቅ ማረሚያ ቤት የደረሰኝ መረጃ ያማል … ያሳለፍነው ሮመዳን ወር እንደገባ ጅዳ ውስጥ የትዳር ጓደኛውን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ በአሳር በመከራ ከተያዘ በኋላ ዘብጥያ የወረደው አዕምሮውን የሳተ ኢትዮጵያዊ ከጤነኛ ታሳሪ ሃበሾች ጋር ነብሰ ገዳይ ከተራ ወንጀለኛ ጋር ደባልቀው በማሰራቸው ደም እንዲፈስ ምክንያት ሆኗል በማለት ታሳሪዎች እያነቡ ገልጸውልኛል። ይህ ነፍሰ ገዳይ … [Read more...] about በአዲስ አመትም ያላባራው ስቆቃ
Ethiopians calling for Protest
The Unity for Democracy and Justice Party (UDJ), the most important opposition political party working under the narrowest political landscape in Ethiopia, in collaboration with other 33 opposition political parties is calling for massive anti government protest, urging people to take to the street of the capital Addis Ababa on 15 September 2013. The demonstration is the part of the campaign, “Millions of Voices for Freedom”, which has begun almost 3 months ago. Following the call, many are … [Read more...] about Ethiopians calling for Protest
የ፩ኛ ዓመት መልዕክት – የሚዲያ ተሃድሶ ግድ ነው!!
ዛሬ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተቋቋመ አንድ ዓመቱ ነው። ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ የደገፉን፣ ያበረታቱን፣ አስተያየት በመስጠት ያረቁንና በመድረካችን የተሳተፉ ያሉትን ያህል የምንሰራውን ስራ ለመቆጣጠር፣ የተመሰረትንበትን ግልጽ መስመር ለማስቀየር የሞከሩና ጨዋነት በጎደለው መልኩ የተዛለፉም አጋጥመውናል። ለሁላችም እንኳን ለአንደኛው ዓመት አደረሰን!! “ወፌ ቆመች በሉን" በማለት ከዓመት በፊት የሚዲያውን ሰፈር በአሃዱ ብለን ከተቀላቀልንበት ጊዜ አንስቶ የሰራነውን ስራ በጥሞና ለመመልከት ሞክረናል። ሌሎች ሚዲያዎችንና ብሎጎችንም ዳሰናል። የራሳችን ደካማ ጎን ስንፈትሽ እግረ መንገዳችንን ዙሪያችንን ስንቃኝ የሚዲያ ተሃድሶ (ሪፎርም) አስፈላጊ እንደሆነ ተረድተናል። አምነናል። "መቼ" ለሚለው ጥያቄ ምላሹ ዛሬ፣ አሁን፣ አሁኑኑ የሚል ነው። ድክመታችን ስንጀምር በዘረጋናቸው … [Read more...] about የ፩ኛ ዓመት መልዕክት – የሚዲያ ተሃድሶ ግድ ነው!!
ስጋቴን ልግለፅላችሁ
ሀገራችን በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ አደጋ ላይ ነች። ይኼን ሁላችንም እናውቀዋለን። የትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰውና በማድረስ ላይ ያለው ልክ የለሽ በደል፤ ተጽፎም ሆነ ተነግሮ አላበቃም። ገና ብዙ ይጻፋል። ገና ብዙ ይተረካል። ለነገሩ መቼ ይኼ ጉደኛ የወንበዴዎች ድርጅት በደሉን አበቃና! የመጨረሻው ለመቃረቡ ግን፤ የመውደቂያ ደወሉን ራሱ አስምቶናል። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መውደቁ አይቀሬ ነው፤ ቀን ከመቁጠር ባሻገር። ይኼ ሲከሰት ግን ምን ይከተላል የሚለው ጥያቄ እንደተንጠለጠለ ነው። ያልተመለሱ ብዙ ጥያቄዎች ዙሪያችንን አጥረውናል። ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ዘር፣ ጎሳ፣ ሀገር፣ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ኅብረተሰብ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ የነፃ አውጪ ድርጅት፣ ግንባሮች፣ ጥምረቶች፣ ትብብሮች፣ ደጋፊዎች፣ ተደጋፊዎች፣ . . . እነዚህ ሁሉ ፅንሰ ሃሳቦች … [Read more...] about ስጋቴን ልግለፅላችሁ
በ2005 እንዲህ ብለን ነበር!
በአዲሱ ዓመት የተመሰረትንበትን አንደኛ ዓመታችንን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ወቅቶች ለንባብ ካበቃናቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል መርጠን ለትውስታ አቅርበናል። ካቀረብናቸውም ሆነ በድረገጹ ላይ ያሉትን ጽሁፎች በመምረጥና በማሰራጨት ልደታችንን ታከብሩልን ዘንድ ግብዣችን ነው። በሌላ በኩል የዝግጅት ክፍላችን ኤዲሪቶሪያል ቦርድ አንባቢዎች በነጻነት አስተያየት እንዲሰጡ፣ አስተያየታቸውም ያለ አንዳች ገደብ እንዲታተም ወስኗል። በመሆኑም ጎልጉልን አስመልክቶም ሆነ በርዕሰ አንቀጽ ላይ ባስቀመጥነው ሃሳብ ላይ በመንተራስ አስተያየት ለምትልኩ "ከስድብና ከዘለፋ" ውጪ በደስታ የሚስተናገድ እንደሆነ አስቀድመን እንገልጻለን። የዓመቱ ምርጥ በማለት "መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ" እና "ጥቁሩ ሰው ይናገራል" የሚሉትን ቃለ ምልለስሶች በስጦታ አቅርበናል። መልካም አዲስ ዓመት፣ ለኛም መልካም አንደኛ … [Read more...] about በ2005 እንዲህ ብለን ነበር!










