በቅርቡ የተመሰረተው የሰማያዊ ፓርቲ ‘‘የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ’’ በሚል መርህ ወደፊት የፖለቲካ ሥልጣን ሲይዝ የሚመራበትን አዲስ ህገመንግስት ማርቀቁን አስታወቀ። ረቂቅ ሰነዱ ላይ ምሁራንና ባለሙያዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ለሕዝብ እንደሚቀርብ ፓርቲው አስታውቋል። የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በአዲሱ ረቂቅ ሕገ-መንግስት ላይ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ውይይት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። በውይይቱ ላይ ከዚህ በፊት የነበሩ ሦስት ህገ-መንግስቶች ድክመትና ጥንካሬ ምንድን ነው? አዲስ በሚረቀቀው ህገ-መንግስት ምሰሶዎች ምን ይሆናሉ፣ ስልጣንና ሕዝብን እንዴት ማገናኘት ይቻላል በሚሉ ወሳኝ ንድፈ ኀሳቦች ላይ የጠለቀ ውይይት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። ‘‘የአሁኑ ሕገ-መንግስት የኢህአዴግ ፕሮግራም ቅጂ … [Read more...] about ሰማያዊ ፓርቲ ሕገ-መንግስት አረቀቀ
ሙስሊም ወንድማማች ዕገዳ ተጣለበት
የካይሮው አስቸኳይ ጉዳዮች ፍርድቤት የሙስሊም ወንድማማችን እና ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በሙሉ ከማንኛውም እንቅስቃሴ አገደ፡፡ የመካከለኛው ምስራቅ የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ አልጃዚራ እንደገለጸው ዕገዳው መሐመድ ሙርሲ ይመሩት የነበረውን እና ከሙስሊም ወንድማማች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለውን የእስላማዊው እንቅስቃሴ የፖለቲካ ክንፍ የነጻነትና ፍትሕ ፓርቲንም ሊጨምር ይችላል፡፡ በሕዝብ ድምጽ ሥልጣን የተረከቡትን መሐመድ ሙርሲ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የሙስሊም ወንድማማች ደጋፊዎችና ከፍተኛ አመራሮች አሁንም እየታሰሩና እየተገደሉ ይገኛል፡፡ ከፖሊስና፣ ከደኅንነትና ከመፈንቅለ መንግሥቱ ደጋፊዎች ጋር የሚደረገው ውዝግብ ደም አፋሳሽ ከመሆን አልፎ በወንድማማቾቹ እንቅስቃሴ ላይ “የአሸባሪነት” ታርጋ አስለጥፎበታል፡፡ ከዚሁ ጋር … [Read more...] about ሙስሊም ወንድማማች ዕገዳ ተጣለበት
ዲያስፖራ ላሜ ቦራ
ይኸ መጣጥፍ መጀመሪያ የተጻፈውና በኢትዮመዲያ፣ በኢካዲኤፍ፣ በአዲስ ቮይስ፣ በኢኤምኤፍ እና በጎልጕል ድረ-ገጾች የተበተነው በእንግሊዝኛ ተደርሶ ነበር። በጣም ብዙ አስተያየት ሰጪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዬም ኢ-ሜይል ሳይቀር የተሰማቸውን አካፍለውኛል። ሁሉም ወደ አማርኛ እንደመልሰውና ብዙ ኢትዮጵያውያን ለማንበብ ዕድል እንዲያገኙ አጥብቀው ስለአሳሰቡኝ ጥይቄአቸውን ተቀብዬ ወደ አማርኛ መለስኩት። ከኢትዮጵያ የሚደርሱን ቀልዶች ለዛቸው ጨምሯል። ሰሞኑን፣ አንድ ከአገር ቤት የመጣ እንግዳ፣ የወያኔ ባለሥልጣናት፣ ዲያስፖራን “ላሜ ቦራ” እያሉ እንደሚሾፉብን አጫውቶን አዝናንቶናል። እውን እኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ የተሰደድን ኢትዮጵያውያን ያለማቋረጥ የምንታለብ የካሽ ጥገቶች ነን? መቼም በኔ ዕድሜ ትምህርት ቤት የሄዳችሁ ሁሉ፣ስለላሜ ቦራ የተተረከ የልጆች ጣፋጭም አሳዛኝም ታሪክ ሳታነቡ … [Read more...] about ዲያስፖራ ላሜ ቦራ
በሳውዲ ወላጆችና የኤምባሲ ኃላፊዎች ተካርረዋል
ወላጆች ንብረቶቻቸውን ከዘራፊዎች ለማስጣል በሪያድ ከኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጋር እያደረጉ ያለው ትንቅንቅ ዛሬ ወደ ግጭት አመራ። በወላጆች እና በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ በዲፕሎማቶች መሃከል ሴፕቴምበር 22፣ 2013 ምሽት ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ለጊዜው ጋብ ቢልም መንግስት በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ የተማሪዎቹ ወላጆች በተደጋጋሚ ላቀረቡት ጥያቄ አስቸኳይ መላምት ካላፈላለገ ጉዳዩ የከፋ ሊሆን እንደሚችል የወላጆች ኮሚቴ አባላት ይገልጻሉ! በተለይ ዛሬ ሴፕቴምበር 22/2013 ምሽት በሪያድ ዓለምአቀፍ የኮሚኒቲ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች ኮሚቴ የሳውዲ መንግስት በውጭ ሃገር ዜጎች ላይ ያወጣውን ህግ ተከትሎ በኤምባሲው የተመረጠው የት/ቤቱ ህገወጥ፣ የቦርድ አስተዳደር «የመኖሪያ ፈቃድ አልተሞላም፣ ፓስፖርት አልታደሰም፣ ቦንድ አልገዛችሁም፣ ወላጆቻችሁ የድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች ናቸው፣ … ወዘተ» … [Read more...] about በሳውዲ ወላጆችና የኤምባሲ ኃላፊዎች ተካርረዋል
የፖለቲካ ኃይል ምንጮች
ክፍል አንድ የዝንጀሮዎቹ ጌታ አጭር ታሪክ የተወሰደው ቻይናዊው ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የሞራል ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው። ይኽ አጭር ታሪክ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ከየት እንደሚፈስላቸው (ምንጩ ምን እንደሆነ) እና እንዴት ምንጩን በመቆጣጠር የአምባገነኖችን አቅም መቆጣጠር አልፎም ምንጩን በማድረቅ አምባገነኖችን ማስራብ እንደሚቻል በምሳሌ አድርጎ ግልጽ ያደርጋል። ሰለዚኽ የሰላማዊ ትግል ተመራማሪው እና ዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስ ጠበብቱ ሲድኒ ታይ (Sidney Tai) ከቻይንኛ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ተረጎመው። የእንግሊዘኛ ትርጉሙን “በማጭበርበር መግዛት” (“Rule by Tricks”) የሚል ርዕስ ሰጠው እና ሰላማዊ ቅጣቶች (Nonviolent Sanctions) በሚል ርዕስ የአልበርት አነስታይን ሰላማዊ ትግል ምርምር ተቋም በሚያትማት ጋዜጣ ላይ … [Read more...] about የፖለቲካ ኃይል ምንጮች
እንኳን ደስ አለን ለሁላችን!!
ይገርማቹሀል ይሄንንና እዚህ ላይ አሁን ለእናንተ ያላቀርብኩትን በግእዝ (አማርኛ) ፊደል ቁጥርና የቁጥር ስሞች መቸ፣ የት፣ እንዴት፣ ተፈጠሩ? የሚለውንና ባጠቃላይ በቋንቋችን ላሉ ሌሎች ምላሽ ያልነበራቸው ጉዳዮችን ምላሽ የሚሰጥ የጥናትና ምርምር ሥራ ከሐሳብ ወደ ተግባራዊ ሥራ ተሸጋግሬ መሥራት የጀመርኩት ዐሥራዎቹ መገባደጃ የዕድሜ ክልል እያለሁ ጀምሬ ነበር፡፡ ከብዙ ዓመታት ድካምና ጥረት በኋላም ሥራውን ጨረስኩ ባልኩ ጊዜ ምቹ ሁኔታና ጊዜ ይመጣል ብየ ብጠብቅ ብጠብቅ ቀጠሮ ያልያሳዘኝ ነገር መቅረቱ አሳሰበኝና ከሁለት ዓመታት ወዲህ ጀምሬ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃንና ዕውቅና ለሚሰጡ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ ተቋማት አቀረብኩት፡፡ ታዲያ እዚያ ያሉት ሰዎች ፊደላት ካልተነቀነሱ ሞተን እንገኛለን የሚሉና ከዚያም አልፈው ወደ 91 የሚደርሱ ሆሄያትን አስወግደው በተቋም ስም መጽሐፍ … [Read more...] about እንኳን ደስ አለን ለሁላችን!!
አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት!
ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ። ቀን መስከረም 8: 2006 ለ5ኛ ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ኮኔትነር ውስጥ፡ የአንዲት ኢትዮጵያዊት አስዛኝ፡ ህልፈተ ህይወት የአካባቢውን ማህበረሰብ እምባ ሲያራጭ፡ ደረት ሲያዳቃ መዋሉን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ኮንትራት የመጣች የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗን የሚናገሩት እነዚህ የአይን እማኞች የወጣቷ ሬሳ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱን አረጋግጠዋል። የእህቶቻችን ሞት ከሚፈበረክበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የስደተኞች ጊዜ ያዊ መጠለያ ኮንቴነር፡ ያለምንም ህክምና እና በቂ መሰረታዊ ፍጆታ በለሌለበት ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ የኮንቴነር የብረት በር ተከርችሞባቸው ከሚገኙ እህቶቻችን መሃከል አንድ … [Read more...] about አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት!
ከፍተኛ መሬት መንቀጥቀጥ በኤርትራ ተከሰተ
ረቡዕ መስከረም 8፤2006ዓም ልክ በ6፡08 ሰዓት ላይ በኤርትራ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን CMI የተሰኘው የጣሊያን ዜና ወኪል አስታውቋል፡፡ በተለያዩ የዓለም ተቋማት የተገኘው መረጃ እንደሚያብራራው የመሬት መንቀጥቀጡ የተነሳው ከምጽዋ ጥቂት ኪሎሜትሮች ወጣ በማለት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ መጠኑ 5.0 ነው የተባለለት የመሬት መንቀጥቀጥ 18ሺህ ሕዝብ በሚኖርባት ምጽዋም ሆነ ባካባቢው ያደረሰውን ጉዳት ለማወቅ በቂ መረጃ እንደሌለ የዜና ወኪሉ ጠቁሟል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ በሱዳን መሰማቱንም የሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት አካባቢ መድረሱ የጠቆመው ዜና የሱዳን ከርሰ ምድር ጥናት ማዕከል 5.9 መጠን ያለው ስለመሆኑ የሰጠውን ማስረጃ በማከል አቅርቧል፡፡ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱንና ሰዓቱ ከመግለጽ በስተቀር ስለደረሰው ጉዳት የሰጠው መግለጫ … [Read more...] about ከፍተኛ መሬት መንቀጥቀጥ በኤርትራ ተከሰተ
አዳፍኔ ለመተኮስ የ “iPad” ዕገዛ
ከአንድ መቶ ሺ በላይ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውና እጅግ ደም አፋሳሽ በሆነው የሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት የአማጺያኑ ኃይል ከሚጠቀመው ቤት ሰራሽ መሣሪያዎች ሌላ የቴክኖሎጂ እሴቶችን በመቀላቀል የሚጠቀሙ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የሬውተር ዘጋቢ የሆነው መሐመድ አብደላ ባነሳው በዚህ ፎቶ ላይ እንደሚታየው የነጻ ሶሪያ ሠራዊት አማጺያን ከደማስቆ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ አዳፍኔ ለመተኮስ በ iPad ሲታገዙ ይታያል፡፡ የጦር መሣሪያ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ አማጺያኑ በፎቶግራፉ ላይ እንደሚታየው በቴክኖሎጂ ቢታገዙም የመተኮሻው ቱቦ አቅጣጫና አቀማመጥ በጣም በቅርብ በሚገኝ ዒላማ ለመምታት አስበው ካልሆነ በስተቀር አዳፍኔውን የሚተኩሱት ራሳቸውን ለማጥፋት ይመስላል፡፡ በምስሉ እንደሚታየው አማጺያኑ በጉዳዩ የረቀቁበት ቢመስልም አነጣጠራቸውና አተኳኮሳቸው “ቦምብ ጥሎ የመጸለይ” ዓይነት … [Read more...] about አዳፍኔ ለመተኮስ የ “iPad” ዕገዛ
የኤርትራ ጉዳይ በሶስት ትውልዶች ውስጥ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ እንደቀልድ እና እንደ እልህ የጀመሩት ''ኤርትራ ኢትዮጵያዊ አይደለችም'' ብሎም ''የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው'' አጀንዳን የሻብያ አጀንዳ እንዲሆን ካስደረጉ በኃላ ከእሳቸው በፊት የነበረው ትውልድ ባይቀበላቸውም የእሳቸውን ትውልድ ''የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው'' የሚለውን ገለፃ ለመንገር አላንገራገሩም። አቶ ኢሳያስ በአንድ ጎናቸው ተንቤን ትግራይ ቢወለዱም ያነሷት ጉዳይ ግን ኢትዮጵያን ለማዳከም ለዘመናት ከሚያልሙ አንዳንድ የአረብ ሀገራትም ሆነ ጎረቤት ሱዳንን የሚያማልል ብሎም ዳጎስ ያለ ድጎማ የሚያስገኝ የወቅቱ አዋጪ ''የገበያ ማስታወቅያ'' መሆኑን የተረዱት ይመስላሉ። ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ በነፃ ትምህርት ዕድል ይማሩ የነበሩት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ''የኤርትራ ነፃነት ግንባር'' (ELF) … [Read more...] about የኤርትራ ጉዳይ በሶስት ትውልዶች ውስጥ










