ማሳሰቢያ፣ የዚህ ጽሁፍ መልዕክት ያለንበትን የተወሳሰበ የዓለም ሁኔታ ለማሳየት ብቻ ነው። የዚህ ጽሁፍ ሌላውና መሰረታዊው ዓላማ የተወሳሰበውን ዓለም ሁኔታ እስካልተረዳን ድረስ ወይም ለመረዳት የማንፈልግ እስከሆነ ድረስ ለነፃነት የሚደረገው ትግል የተሟላ ሊሆን አይችልም። ጽሁፉ ማንንም ለማወናበድ የቀረበ ወይም ደግሞ አንድን ርዕዮተ-ዓለም ለማስፋፋት የታቀደና ወይም በጥላቻ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ሆኖ መወሰድ የለበትም። በማስረጃ የተደገፈ ነው። ሁለተኛ፣ ይህ ዐይነቱ ጽሁፍ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮችና የኢንቬስቲጋቲቭ ጋዜጠኞች ስራ ነው። ስለሆነም ወደ ፊት የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮች እንደዚህ ዐይነቱንም ሁኔታ እያተቱ ቢያቀርቡ ብዙ ሃሳቦችን ማንሸራሸር ይቻላል። ሶስተኛ፣ ይህ ዐይነቱ አቀራረብ በጣም አድካሚ ስለሆነ ተግባሩን ለፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮች አስተላልፋለሁ። ብዙ ነገሮችን … [Read more...] about ከአምባገነንነት ባሻገር
የተመላሾች ጉዳይ …
በርካታ ከሳውዲ ወደ ሃገር ቤት የተመለሱ ዜጎችን በሚመለከት የጀርመንና የአሜሪካ ራዲዮን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን አንድ አይነት የሚመስል መረጃ ግፉአን ተመላሾችን እማኝ እያደረጉ መረጃ አቀብለውናል ። "ራፕለር " በታዝነው ሳምንት ባቀበለን መረጃ ሻንጣቸው ጠፍቷቸው በአንድ የሻንጣ ማጠራቀሚያ ግቢ ሻንጣቸውን ሲፈትሹ የሚያሳየውን ፎቶ አስደግፎ የተመላሾችን አስተያየት አካቶበታል። ዜጎች ወደ ሳውዲ ሲሰደዱ ከቤተሰብ ፣ ከዘመድ አዘመድ አዝማድና ከተለያዩ ቦታወች የወሰዱትን የብድር ገንዘብ ስላልመለሱ ኑሯቸው የሰመረ እንዳልሆነ እየተናገሩ ነው ። ሃገር ቤት ገብተው የስራ ማጣት እና እሳት የሆነው የኑሮ ውድነት ግራ ያጋባቸው በርካቶችም አሁንም መልሰው ለስደት እንደቋመጡ እኛ የምንቀርበው መረጃ ባይስማማ የፈረንጆቹ መገናኛ ብዙሃን የሚያቀርቡት የገሃዱን እውነት አንድምታ … [Read more...] about የተመላሾች ጉዳይ …
የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ግልፅ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል
በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከተካተቱት ንዑስ አርዕስቶች ውስጥ - የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ እርምጃ ምን መምሰል ይገባዋል? የኢትዮጵያ የቅርብ ወቅታዊ ተግዳሮት ምንድን ነው? የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ህዝብን የሚንጥ እና ሚልዮኖችን ከጎናቸው የሚያሰልፍ የፖለቲካ ራዕይ ለሕዝቡ ማሳየት ለምን አልቻሉም? እና ሌሎችም... መግቢያ ኢትዮጵያን ውክፕድያ በድህረ ገፁ ላይ እንዲህ ይገልፃታል:- ''ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ርዕሰ ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ ዓመት የሚያንስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ … [Read more...] about የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ግልፅ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል
ጥምቀት ወይስ ካርኒቫል? ለምን?
ሀገራችን ካሏትና ሐበሻን እንደ ሐበሻ ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያ ከሌሎች ተልይታ እንድትታወቅ ካደረጓት ታሪካዊና ባሕላዊ መለያዎቿ ምንጫቸው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በጉልህ ከሚታወቁት ባሕላዊ ኩነቶቻችን ውስጥ ሃይማኖታዊ አሻራ ያላረፈበት አንድም ባሕላዊና ታሪካዊ ክንውን እሴትና ቅርስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡ ይህ ሁኔታ በሌላ በኩል ሕዝቡን ሃይማኖቱን ከባሕሉ ጋር ማዋሐድና ማሰላሰል እስከመቻል የደረሰ ቅሩበ እግዚአብሔር ሕዝብ በማሰኘት አድናቆትን ሲያስቸረው ቆይቷል፡፡ ከነዚህ ሀገራችንንና ሕዝባችንን እንደ ሀገርና ሕዝብ መለያው ወታወቂያው እንዲሆን ካደረጉት ድንቅና ብርቅ እሴቶች ውስጥ አሁን ህልውናቸው አደጋ ላይ ከወደቁት አንዱን አንስተን እናወራለን፡፡ የጥምቀት በዓል አከባበርን ፡፡ ሌሎቹን በሌላ ጊዜ እናያለን ፡፡ የጥምቀት በዓል ከሀገራችን ሌላ … [Read more...] about ጥምቀት ወይስ ካርኒቫል? ለምን?
አሳዛኙ የትውልድ ህይወት በሳውዲ አረቢያ «ጂዛን» ከተማ!
ጂዛን እየተባለ በሚጠራ የሳውዲ አረቢያ ግዛት ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌለውን ጨምሮ ከ50 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይነገራል። የጂዛን ከተማ ሳውዲ አረቢያን ከየመን የሚያዋስን ከተማ እንደመሆኗ በባህር የሚመጡ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ሪያድ እና ጅዳ ከተማ ለማቅናት በመሸጋገሪያነት እንደሚጠቀሙባት ይነገራል። በዚች የድንበር ከተማ አያሌ ኢትዮጵያውያን ጉዳዩ በወል በማይታወቅ ምክንያት ያለ ፍርድ ለ 4 እና 5 አመታት ታስረው የሚሰቃዩባት ከተማ መሆኗን የሚነገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ወደ ሃገር ለመመለስ ጥያቄ ያቀርቡ አያሌ ወገኖቻችንም በሪያድ የኢትዮጵያን ኤንባሲ እና ለጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እስካሁንም ምላሽ ባለማግኘቱ ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መሆኑን ይናገራሉ ። ይህ በዚህ እንዳለ ከሁሉም በላይ እስከፊ አስከፊ በለው የሚገልጹት ምንጮች … [Read more...] about አሳዛኙ የትውልድ ህይወት በሳውዲ አረቢያ «ጂዛን» ከተማ!
የመረጃ ነፃነት?
‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡ መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡ በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም … [Read more...] about የመረጃ ነፃነት?
ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል
በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ … [Read more...] about ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል
ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?
ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የአገር ተወላጅ እና የውጭ አገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሃቅ ነው። ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በስልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሰራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከአገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ስራ የመሳሰሉ ዘመናዊ (Secular) ትምህርት ቀስመው አገራቸውን ለመርዳት ወደ አገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን የእነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?
The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW)
In appreciation of Ethiopian Sports Federation in North America (ESFNA) for the Support Given to The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) in 2013 The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) sends its well wishes for a happy and peaceful new year to all members of our community. We are grateful to individuals and organizations that have supported us in 2013. We would like to extend our special thanks to the Ethiopian Sports Federation in North America (ESFNA ) for the support … [Read more...] about The Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW)
የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃትማጥፊያ መዳኒት
ካለመታደል ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ … [Read more...] about የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃትማጥፊያ መዳኒት










