በአርዕስቱ ለመጥቀስ እንደሞከርኩኝ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከትውልድ ለትውልድ ሲተላለፍ የመጣው ከገዥዎችና ከረዳቶቻቸው የውጪ ኃይላት ጋር ነው። ይህ ህዝብ በነፍጥ አንጋቾች ቅኝ (አቅኝዎች) ሥር ከቀደቀበት ጊዜ አንስቶ አስከ ዛሬ ድረስ ትግሉን ያቁዋረጣበት ጊዜ የለም። ይህም የሆነበት ወቅት ብናስብ ሴሜቲኮች (ሓበሾች) ወደ ምስራቅ አፍሪካ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ነው። እነዚህ ህዝብ ወደ ምስራቅ አፍሪካ የመጡት በተለያየ ጊዜ ሲሆን፣ ሰበባቸውም የተላያየ ነው። ከመጡም በኃላ በኩሾች ንጉሥ (አባ ገዳ) “ኩሳ” በተባለ የሥልጣን ወይም የንግሥና ስም ስር በመተዳደር ነው። ቀስበቀ እየበረከቱ ሲሄዱ በተንኮልና በኃይል የነበረውን የኩሽ ህዝቦችን መስተዳድር ደምስሳው ሥልጣኑን ተቆጣጠሩ። የዛጉዌዎች ሥርወመንግስት መሃል ገብ እንጂ እስካሁን በሥልጣኑ ሲፈራረቁበት ቆዩ። እስኪ አቶ አምሳሉ ገ/ኪዳን … [Read more...] about የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከጭቁን የአማራ ህዝብ ጋር ሳይሆን ከገዢው መደብና ከቀድሞው ሥርዓት ነፋቂዎች ጋራ ነው።
ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን “የመርዝ ብልቃጥ”
ኢትዮጵያን እየመራ የሚገኘው ኢህአዲግ/ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን እርስ በርሱ እንዳይተማመን፣ እንዲነቃቀፍ፣ እንዲጠራጠር ከእዚህ ባለፈ ደግሞ ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ 22 ዓመታትን ዘለቀ። ህዝቡ እለት ከእለት በገዢው መንግስት የሚወጠኑለትን የእርስ በርስ ማጋጫ ተንኮሎች እየተመለከተ ልቦናው በእጅጉ እየደማ ነው። አንድ ወራሪ የውጭ ጠላት ሊሰራ የሚችለውን ያህል ህዝብን ከሕዝብ ጋር የማጋጨት ሥራ ኢህአዲግ/ወያኔ በትክክል ሰርቶበታል። የሃገሪቱን ፌድራል አስተዳደር በየትኛውም ዓለም ያልታየ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ደገሰላት። ፌድራላዊ አስተዳደር በዘመናዊው ዓለም አንዱ እና አማራጭ የአስተዳደር ዘይቤ ይሁን እንጂ በየትኛውም ሀገር መሰረት የሚያደርገው የመልክዓ ምድርን አቀማመጥ እና ታሪካዊ አሰፋፈርን ነው። እርግጥ ነው ጣልያን ሀገራችንን በወረረ … [Read more...] about ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን “የመርዝ ብልቃጥ”
ወፈ ግዝት!
መግቢያ ወያኔ የማትሞክረው የለም። አንዳንዴ አቅሟን አታውቅም ልበል? በዚያን ሰሞን፣ ቺፍ ሳጂን ዘመድኩን የተባለ የወያኔ ጉደኛ የፖሊስ ባለጊዜ፣ የቮኤውን ጋዘጠኛ፣ ሰሎሞን ክፍሌን በስልክ ሲያስፈራራ፣ “ዋሺንግተን አይደለም፣ ሰማይ ቤት ብትሆን መጥቼ እወስድሀለሁ” ነበር ያለው[1]። የወያኔ ካድሬ ጉዶች፣ በለስ አንዴ ከቀናቸው፣ ሁሌ የሚቀናቸው ይመስላቸዋል። ከኢትዮጵያው ውጪም፣ የኢትጵያውያንን ሕልውና ለመቆጣጠር ያምራቸዋል። ሲያምራቸው ይቅር። ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽሙት ግፍ አንሶአቸው፣ ባህር ማዶም የቁጥጥራቸውን መረብ አሻግረው ለመዘርጋት የኢትዮጵያን ገንዘብ እንደ ጉድ ይረጩታል። ኬኒያና ጂቡቲ ቀንቶአቸው ይሆናል። እንግሊዝ ግን፣ ኬኒያም፣ ጂቡቲም አይደለችም። ሆድ-አደሮችን ወያኔ ትቆጣጠራቸው እንደሆን እንጂ ሌሎቻችን ዕምነታችንንም ሆነ መብታችንን አናስነካም። … [Read more...] about ወፈ ግዝት!
ኢህአዴግ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት?
ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን ተጠቆመ። አልሸባብንና አልቃይዳን ከምንጩ እናጠፋለን በሚል ስትራቴጂ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው አሜሪካ ከጉድጓዱ ለመውጣት ወስናለች። ኢትዮጵያዊያን የሚያምኑትና የሚቀበሉትን መሪ በድፍረት አደባባይ የማውጣት ሃላፊነቱ "አገር ወዳድ" በሚሉ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጫንቃ ላይ ነው። ህወሃት ያቋቋማቸው ጥቃቅን መንግስታት ከህዝብ ይልቅ ለህወሃት የወደፊት እቅድ ታማኝ በመሆን መጓዛቸው ከቀን ወደቅን የፈጠረው ስሜት ኢህአዴግን እየበላው እንደሆነ የጠቆሙ የዜናው ምንጮች፣ ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም አባት ሊሆን ቀርቶ የራሱንም ችግር መፍታት ወደማይችልበት የቁርሾ ማሳ ውስጥ እንደሚገኝ አመልክተዋል። ህወሃት “በነጻ አውጪነት” ያሰላውና፣ ይህንኑ … [Read more...] about ኢህአዴግ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት?
የለም
እንትን የለም እንትን የለም በእንትን እጥረት ህይወት ማዝገም እንትና እንትን መጠቋቆም መደማደም ተስፋ ያጣ ተስፋችንን ግዜ ሰጠን እንደማከም እሱ እነሱ እንደዛ እያልን ለራስ ሚሆን ግዜ አጠረን ----- Zeynu Seid ----- ከAfendi Muteki ፌስቡክ የተገኘ … [Read more...] about የለም
አምባገነናዊውን ስርዓት አቅፈውና ደግፈው የያዙት ምዕራባዊ አገራት
በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጭቆና፣ ስቃይ እና መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካደረጉት ምክንያቶች መካክል አንዱ፣ የወያኔ መንግስት ከምዕራባዊያን የሚያገኘው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ሙገሳ ትልቅ ቦታ ይይዛል። ከነዚህ መንግስታት የሚያገኘው ድጋፍ እና ሙገሳ ምክንያት የማን አለብኝነት ስሜት ስርዓቱ እንዲሰማውና የኢዴሞክራሲያዊ ስርዓት በህዝቡ ላይ እንዲንያሰራፉ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ስርዓቱም ከነችግሩ ለረዥም ጊዜ በስልጣን እንዲቆይ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የምዕራባዊያን ድጋፍ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። እነዚህ ሀገራት የራሳቸውን ብሄራዊ ጥቅም ብቻ ትኩረት በመስጠታቸው ላለፉት 25 ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ በጭቆና ውስጥ እንዲያሳልፍ አድረገውታል። የሀገሪቱ መልካምድር\ጅኦግራፍያዊ አቀማመጥ፣ የመንግስት ለምዕራባዊያን ፍላጎት አጎብዳጅነት እና … [Read more...] about አምባገነናዊውን ስርዓት አቅፈውና ደግፈው የያዙት ምዕራባዊ አገራት
የሰላማዊ ሰልፍ መንፈስ መመለስ
በበርካታ ኢትዮጲያዊያን ትውስታ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ሲባል ወደ አእምሮአቸው የሚመጣው በምርጫ 97 ሰሞን የነበሩት ህዝባዊ የመብት ጥያቄዎች ናቸው። በወቅቱም ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው ከአሁን በውሃላ ማንም ሰው አደለም ተሰልፎ ሰብሰብ ብሎም መቆም አይችልም ብለው ማስጠንቀቂያ በመስጠት ህዝቡን በየእስር ቤቶ ካጎሩት በውሃላ መብትን በሰልፍ የመጠየቅ ነገር በዛ በይስሙላ ህገ መንግስት ላይ ብቻ ተወስኖ በሰልፍ መብትን የማስከበር መንፈስም በእጅጉ ተቀዛቅዞ ነበር። እንደውም በአንድ ወቅት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳን ከእስር መፈታት አስመልክቶ ለተጠራው ሰልፍ መንግስት ከሁለት መቶ ሃምሳ ሰው በላይ መሰለፍ አይፈቀድም የሚል ብዙዎችን በግርምት ያስደመመ ተሰምቶ የማያውቅ የሰላማዊ ሰልፍ ፍቃድ አሰጣጥ ሂደትንም አስተውለን ነበር። ምንም እንኳን በራሱ በወያኔ … [Read more...] about የሰላማዊ ሰልፍ መንፈስ መመለስ
ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት ይቻላልን?
ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት በቅድሚያ ሀገር ማለት ራሱ ምን ማለት ነው? እንዴትስ ትፈጠራለች? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይኖርብናል፡፡ ሀገር ማለት በአንድ ጥላ ስር የሚኖርባት ትልቅ ቤት ማለት ናት፣ ሀገር ማለት ጋርዮሽ ማለት ናት፣ ሀገር ማለት ከመንደር ከቀየ የገዘፈች የጋራ ጥቅም የፈጠሩ ሕዝቦች የራሳችን የግላችን የሚሉት የተከለለ ምድርና በውስጡ ያሉ ሁሉ ነገሮች ማለት ናት፡፡ ሀገር እንዴት ትፈጠራለች? ሀገር በሦስት መንገድ ትፈጠራለች የተለያየ ቋንቋ ባሕል ሃይማኖት ወዘተ ያላቸው ሕዝቦች በመልክአ ምድር አቀማመጥ በአየር ንብረት መመሳሰልና ተጽዕኖ ሊጋሩት በሚፈልጉት ወይም በሚገደዱት የተፈጥሮ ሀብት አጣማሪነት በስምምነት ትፈጠራለች፡፡ የጋራ ጥቅም ባላቸው ወይም በፈጠሩ አንድ ዓይነት ቋንቋ ባሕል ሃይማኖት ወዘተ ባለው ሕዝብ ያንን የጋራ ጥቅም ለራሳቸው ብቻ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት ይቻላልን?
Open Letter to Italian Minister of Foreign Affairs
Ufficio Relazioni con il Pubblico The Honorable Minister of Foreign Affairs, Federica Mogherini Ministero Affari Esteri Piazzale della Farnesina, 00135 Roma ITALY Your Excellency: The Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause presents its compliments to the Honorable Foreign Minister of Italy, Federica Mogherini. Our Alliance recalls, with deep appreciation, the long and historic relations between our two nations, Ethiopia and Italy, and wishes to draw Your Excellency’s kind … [Read more...] about Open Letter to Italian Minister of Foreign Affairs
ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው
ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው። ጎልጉል ከዲፕሎማት ምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል። የዜናው ምንጮች ዝርዝር ህጉን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የሚደነገገውን አዲስ ህግ ጥሰዋል በሚል የሚከሰሱ ምዕመኖች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የሚያዝ አንቀጽ አለበት። አዲሱ ህግ ከሽብርተኞች ህግ ጋር የሚጣቀስ … [Read more...] about ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው










