ገነት አበበ ሞላ ትባላለች፤ የልጅነት ጊዜዋን ሩጣ ያልጠገበች በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ኮረዳ ነች። ከዛሬ 3 አመት በፊት ነበር በኑሮ ውድነት የተጎሳቆሉ ቤትሰቦችዋን ከድህነት ለመታደግ በወቅቱ እስከ ገጠር በዘለቀው የአሰሪና ሰራተኛ የደላሎች ዘመቻ ከአርሲ ኮሌ ወረዳ ኩዬ ከተማ ተመልምላ የማይጨበጠውን የአረቡን ዓለም መከራ ለመጋፈጥ ተስፋ ሰንቃ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናቸው። በወቅቱ በሰው ልጆች ህይወት ዶላር ለማግበስበስ በየአካባቢው በተከፈቱ የአሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲ ደላሎች ከእናቶቻቸው ጉያ ተነጥቀው ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰውን እድሜዎቻቸውን ቆልለው ፓስፖርት የወሰዱ ህጻናት ሳይቀሩ በቀን 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች ያለህይወት ዋስትና ወደ ሳውዲ አረቢያ በጅምላ ይላኩ የነበረበት ወቅት በመሆኑ ወጣት ገነትም ሰው እንደሆነው እሆናለሁ ብላ … [Read more...] about በኢህአዴግ ለባርነት የተሸጠችው ወገን ሰቆቃ
Ethiopia shall overcome
In May of 2005 the noble idea of bringing change by peaceful means died a violent death in Ethiopia. The Tigrai People Front declared in no uncertain terms power sharing is not part of the equation. They have proved it three times since then. What part of that do we have a problem accepting? The TPLF party does not just whisper. They shout so loud that the whole body shakes from the vibration caused by the violent, vile and wild savage scream. That did not stop well-meaning and brave … [Read more...] about Ethiopia shall overcome
ሳይገባቸው ቻይና በነገራቸው የሚያውቁትን የሚረሱ ማን ያስተምራቸው!
የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ በየመንገዱ ጠመንጃ የያዘ ሊያስፈራራን የሚሞክር ሆድአደር እያየን፣ እንደዚሁም በየጫካው ያሉትን እያሰብን ሰላማችንን ከምናጣ አበባውን ትተን፣ ሩዙን … [Read more...] about ሳይገባቸው ቻይና በነገራቸው የሚያውቁትን የሚረሱ ማን ያስተምራቸው!
“መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ”
በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለ16 ተከታታይ ቀናት በጨለማ ክፍል መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ፡፡ የካቲት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ (የፓርቲው የጎንደር አደራጅ አቶ አግባው ሰጠኝ)፣ የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች "መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ" እያሉ እንደሚደበድቧቸውና በጨለማ ክፍል እንዳሰሯቸው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ አሁንም መረጃየን ሰብስቤ አልጨረስኩም በሚል ተጨማሪ 8 ቀናት ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ተጠርጣዎቹ በማዕከላዊ እየደረሰባቸው የሚገኘውን ሰቆቃ አስመልክተው ለፍርድ ቤት አቤት ማለታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የቀረበበትን አቤቱታ እንዲያስተካክል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በጎንደርና … [Read more...] about “መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ”
“አሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን (አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን)”
በተለያየ ጊዜ በተለያየ የክህደት አስተምህሮ በመሰናከል በመውደቅ ከዚህች ሐዋርያዊት አንዲት ቤተክርስቲያ እየተለዩ በኑፋቄያዊ አስተምህሮ ጸንተው በመቀጠል ለዚህች አንዲት ሃይማኖት አንዲት ቤተክርስቲያን ጠላቶች የሆኑ ዲያብሎስን የሚያገለግሉ ከ40 ሽህ በላይ ይቆጠራሉ፡፡ ሃይማኖት ነንም ይላሉ፡፡ ክርስቶስ በወንጌሉ ሐዋርያትም በመልእክቶቻቸው እንደተናገሩት ግን ከአንዲቷ በስተቀር ይሄ ሁሉ ሃይማኖት ነኝ ባይ ዝግንትል ሐሰተኛና ዲያብሎሳዊ የክህደትና የጥፋት መንገዶች ናቸው፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ ሲቃረብ ብዙዎች ሐሰተኞች መምህራን በየ እልፍኙ የሚሰብኩላቸው ሐሰተኞች ኢየሱሶች ሐሰተኞች ክርስቶሶች ይመጡ ዘንድ እንዳላቸውና ከእነሱም እንድንጠበቅ አስጠንቅቆናል፡፡ ማቴ. 24፤1-28 “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ. 4፤5 “መንፈስ ግን በግልጥ በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ … [Read more...] about “አሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን (አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን)”
ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?
በሐዋሳ ለጊዜው የጉዳቱ መጠን ያልታወቀ የእሣት ቃጠሎ መድረሱን በአደጋው ያዘኑ ገለጹ፡፡ ከስፍራው እንደተሰማው ለሰኞ አጥቢያ የተነሳው ቃጠሎ ምናልባትም በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛው ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አደጋው ሲደርስ የእሣት አደጋ “አገልግሎት” በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ አስነስቷል፡፡ ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት ላይ ነፍሳት ባረፉበት ወቅት የደረሰው የእሣት አደጋ መነሻው በትክክል ባይታወቅም ማምለጥ የሚቻልበት ባለመሆኑ አሟሟቱ የከፋ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተለያዩ ወገኖች በምስል ይፋ ያደረጉት ቃጠሎ እንደሚመለክተው የእሣቱ መጠን በቀላሉ የሚቆጣጠሩትና አደጋውን የሚቀንሱበት እንዳልነበረ ያስረዳል፡፡ በሐዋሳ ታሪክ ከፍተኛ ነው የተባለው ይህ ቃጠሎ በህይወት ላይ ያደረሰው አደጋ በትክክለኛው ቁጥሩ ባይገለጽም ከሥፍራው የደረሰን አጭር መልዕክት እንደሚያስረዳው ከሰባት የማያንሱ … [Read more...] about ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?
የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት
* ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ ይዘረፋል!! የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል። የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል። የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና … [Read more...] about የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት
በአርሲ ጅብ በሰውና የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት አደረሰ
በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በሌሙና- ቢልቢሎ ወረዳ ሌሊት ላይ መኖሪያ ቤት የገባ አንድ ጅብ በሰውና በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ጎሳ አማን እንደገለጹት፥ ጅቡ በሰውና እንስሳት ላይ ጥቃት ያደረሰው በሌሙዲማና ሁላሃሳ የገጠር ቀበሌ ነው። የካቲት 10 ቀን 2007 ከሌሊቱ 10 እስከ 11 ሰዓት በሁለት አርሶ አደሮች የእንስሳት በረትና መኖሪያ ግቢ በመግባት በሁለት አባወራና ስምንት የቤት እንስሳት ላይ ንክሻ መፈጸሙን ገልጸዋል። አርሶ አደሮቹ የቤት እንስሳቱን ከጅቡ ለማስጣል በገጠሙት ግብ ግብ የተደናገጠው ጅብ ወደ ጭላሎ ተራራ ሊያመልጥ መቻሉን አስታውቀዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል አንደኛው ብልታቸው ላይ ሌላው አርሶ አደር ደግሞ በሆዳቸውና ሌላ አካላቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት አሰላ … [Read more...] about በአርሲ ጅብ በሰውና የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት አደረሰ
“ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ”
ወቅታዊው የቴሌቭዥናችን አዝማች፤ ... ሰማንያ አንድ ዜሮ ዜሮ- ኤ ብለሽ መላዕክት ከላልሽ፣ አባይን ገድበሽ ሽልማት በሽበሽ። .... 8100 .... 8100 .... 8100-A A A የምትለው ዜማ በብዛት ትለቀቃለች። ኮሜዲያን ተሰብሰበው የሰሩዋት ዜማ ናት። ቀልደኞቹን ማኖ ለማስነካት ተብላ የተቀነባባረች ነገር ናት የሚሉም አሉ። የቴሌቭዥኑን ጣብያ ከፍቶ የሚመለከተው ሰው እጅግ ጥቂት ቢሆንም መልእክቱ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መደመጡ አልቀረም። የዚህ ማስታወቅያ አላማ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የእጣው ዝርዝር ግን ለብዙዎች እንግዳ ሳይሆን አልቀረም። አንዲት አዛውንት የልጃቸውን ተንቀሳቃሽ ስልክ እያነሱ ይቀጠቅጣሉ። በሳምንት ሶስቴ 8100 እየደወሉ 'A' ፊደልን ይጫናሉ። ከብዙ ግዜ በኋላ ታዲያ ልጃቸው አወቀባቸው። በመገረምም ለምን ይህንን ሁሉ ግዜ መደወል እንደፈለጉ ጠየቃቸው። … [Read more...] about “ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ”
የኢትዮጵያ ጉዳይ
ግልፅ ደብዳቤ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ሀገር ማለት ባሕርዳር ዛሬም ስለልጆቿ አነባች የአምባገነኖች አከርካሪ በተባበረ የሕዝብ ክንድ ይሰበራል በሴቶች ላይ የሚፈጸም በደልና ጾታዊ ጥቃት ይቁም ኢትዮጵያዊነት በዘር ማንነት አይደበዝዝም ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገው ትግል በቀላሉ አይቀለበስም ፖሊስና ሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ መጽሔቷ በእነዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ታተማለች፡፡ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ










