ስለ ሳሙኤል ግድያ ብዙ ነገር ተብሏል፡፡ ብዙዎች ቁጭታቸውን ገልፀዋል፡፡ ለእኔ ከሳሙኤል አወቀ ግድያ ምን እንማራለን? የሚለው ነው ትልቁ ቁም ነገር፡፡ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ንግግር ተናግረው የተገደሉ ሰዎች ጋር የሚመደብ ሰው ነው፡፡ የሳሙኤል ትውልድ አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፡፡ እንደገሚገሉት እያወቀ፣ ነገር ግን ያ ሞቱ ከንቱ እንዳይሆን አስፈላጊውን መረጃ አስቀምጦልናል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስተምረው ህዝቡ ለጣሊያን እንዳይገዛ ሰብከው ተገድለዋል፡፡ ለዚህም ሀውልት ቆሞላቸዋል፡፡ ይህ መታሰቢያ ለኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ልዕልና እና የአልበገሬነት ምልክት ሆኖ ለዘላለም ይኖራል፡፡ የአቡነ ጴጥሮስን ታሪክ ተማሪዎችም ይማሩበታል፡፡ የሳሙኤልን ንግግርም ወደፊት እድሜ ከሰጠን እኛ እናየዋለን፡፡ እኛ ባንደርስበት እንኳ መጪው ትውልድ … [Read more...] about “የሳሙኤል ግድያ ለታጋዮችም ለገዳዮችም ትልቅ ትምህርት ነው!”
በኤርትራ ላይ ምርመራው እንዲቀጥል ተወሰነ
በኤርትራ ላይ የሚካሄደው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ የሚጠረጠረውን በሰብዕና የሚፈፀም ወንጀል እንዲያካትት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ትናንት ወስኗል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እንዲመረምር የተቋቋመው ልዩ አጣሪ ኮሚሽን ሥራውን በአንድ ዓመት እንዲያራዝም የተስማማው አርባ ሰባት አባላት ያሉት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ክትትል አካል ነው፡፡ ምርመራው ሙሉ ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ እንዲካሄድ የምክር ቤቱ ውሣኔ አክሎ አሳስቧል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ይፈፀማል የተባለውን ጅምላ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ በአጀንዳነት እንዲያዝ ጥያቄ ያቀረቡት ጅቡቲና ሶማሊያ እንደሚያወግዙ አስታውቀዋል፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የምርመራውን ጊዜ መራዘም “ኤርትራ ውስጥ እየተፈፀሙ ያሉ” ያላቸው የሰብዓዊ … [Read more...] about በኤርትራ ላይ ምርመራው እንዲቀጥል ተወሰነ
“የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” !
ሰሞኑን ኦባማ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው በሚል፤ ከባህር ማዶ ጫጫታ፤ ከወደ አገር ቤት ደግሞ የጆሮ ብራና የሚጠልዝ ከበሮ ድለቃው ተጧጡፏል:: ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” !
ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት
አቶ አንዱአለም ተፈራ ከገዢው መደብ የምንለይበት በሚል ርእስ ባስነበቡን ጽሁፍ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚለውን አጠራር ለምን እንደመረጡ ያስረዳሉ፡፡ መጠሪያው ለወያኔ የማይገባው በመሆኑና አቶ አንዱዓለም መጠሪያውን ለመጠቀም ያአስቻለኝ ብለው ያቀረቡት ምክንያት በቂና ተገቢ ሆኖ ስላልተሰማኝ ይህችን አስተያየት ጻፍሁ፡፡ ትግሬ ስንል የኢትዮጵያ አንድ ክፍል በሆነው ትግራይ የተወለዱና ትግረኛ ቋንቋ የሚናገሩ ወይንም የወላጆቻቸው ስር ከዛ ሆኖ የትም ይሁን የት የተወለዱና ቋንቋውን ሊናገሩም ላይናገሩም የሚችሉትን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ስለሆነም የትግሬ ነጻ አውጪ ስንል ወያኔ ትናንትም የታገለው ዛሬም ሥልጣን ላይ ሆኖ የሚሰራው እነዚህን ነጻ ለማውጣት ነው፣ እነርሱም ነጻ አውጪነቱን አውቀውና አምነው የተቀበሉት ነው ወደሚል አንደምታ ይወስዳል፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ … [Read more...] about ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት
የጅዳ ቆንስላው ግቢ “ጅቦች”
* የጅዳ ቆንስል ለባላቴናው መሀመድ ፍትህ ይትጋ * የጅዳ ቆንስል የስደት ያሰናከለውን ወንድም ይሸኝ * "ጅቦቹ!" የአንባሳደሩን ተሀድሶ ያኮላሹት ይሆን? የማለዳ ወጌ መነሻ መድረሻ ከወራት በፊት ለኦማኗ ተገፊ ለአልማዝ እና ሰሞኑን እርዳታ ስናሰባሰብለት ለሰነበትነው ወንድም ወጣት አባወራ ለመሀመድ ስላደረጋችሁለት ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ ነው። በላዩ ላይ የአልማዝ እርዳታ ሀገር ቤት በእንክብካቤ ለያዛት ለሜቅዶንያ የማስረከባችን መረጃ አካፍየ በሳምንት እድሜ ለመሀመድ ሁሴን ከ10 ሽህ የሳውዲ ሪያል ወይም ወደ 60 ሽህ የኢትዮጵያ ብር የሚጠጋ ገንዘብ በላይ ማሰባሰቤን መረጃ ከማቅረቡ ጋር ምስጋናየን ለማስተላለፍ ነበር። ለዚህ መረጃ አቅርቦት ስሰነዳዳ በተዛማጅ ስለ ዜጎች መብት ጥሰትና ስለመብት ማስከበሩ ጭብጥ አስተምሮት እናገኝ ዘንድ አንድ መረጃ አገኘሁ። ምስጋናየን ወደ … [Read more...] about የጅዳ ቆንስላው ግቢ “ጅቦች”
የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው
በድርጅት ከዚያም ከፍ ብሎ በመንግስት ደረጃና በሃገር ደረጃ ግምገማ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ሁሉ ያምናል። የኣንድ ድርጅት ብቃትም በግምገማው ችሎታና ጥራት ሊለካ ይችላል።የኣንድ ሃገር የፖለቲካ መረጋጋት በፖለቲካ ለሂቆቹ የጠራ የሃገር የምናብ ስእልና ብስለት ሊለካም ይችላል። የፖለቲካ ቤቶች ሲኮለኮሉ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ ከፍ ያለ ግምገማን ይጠይቃል። ሃገሪቱ ያለፈችበትን የህይወት ጎዳና፣ የገጠማትን ችግር መንስዔና ውጤቶች በሰፊው መገምገም ለሚመሰረቱ የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረትና ለሚቀረጹ ፖሊሲዎች ጥራት ወሳኝ ነው። እንግዲህ በሃገራችን ኢትዮጵያ ግምገማ በሰፊው የተወራለት ጉዳይ የሆነው በዚህ መንግስት ጊዜ ነው። ህወሃት በጫካ ኑሮው ጊዜ የነበረው ማህበራዊ ህይወትና የትግሉም ባህርይ የየቀን ውሎውን እየገመገመ እንዲሄድ የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ስለከተተው በግለሰቦች ድክመትና … [Read more...] about የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው
… አልሞት አለኝ
በስራው ላይ ልፈላሰፍ ቅኔ ልቀኝ ግጥም ልጽፍ ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ የማደንቀው ሰው ነበረኝ ሳይሞትማ ሳይቀበር ስሙን ማንሳት እሱን ማክበር መስሎ ታይቶኝ ልምድን መስበር የማደንቀው ሰው እያለኝ ልጽፍለት ተቸገርኩኝ አቤት! ዕውቀት አይ! ቁመና ብልህ ደፋር ቆራጥ ጀግና ሀይማኖቱን አጠንካሪ ደግ ለጋስ ሰው አክባሪ ብዬ ልለው ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ ታሞ እያየሁ ዛሬ ቢያጣ ዛሬ ቢርበው በቁም ሆኖ ከምረዳው ከማከብረው ከማደንቀው እደርሳለሁ ሲሞትልኝ ከምድር በታች ሲውልልኝ ያንጊዜ ነው ስሙ ገኖ የሚነሳው እሱን ሆኖ የብዕር ጫፍ የሚመዘዝ እንባ የሚረጭ የሚተከዝ ሚጻፍለት ሚደነቀው ታሪክ ገኖ ሚነበበው ገንዘብ ከኪስ ሚመዘዘው ለሟች በድን አካሉ ነው ያን አይቼ ልምድ አብቶኝ የቆየ ወግ አንቆ ይዞኝ የማደንቀው ሰው … [Read more...] about … አልሞት አለኝ
የነፃነት መውጫው መንገድ፣ ታጋዩ፣ ሕዝቡን ጠንካራ ምሽጉ ማድረግ ሲችል ነው
የአንድ ለነፃነት የሚታገል ኃይል የመጀመሪያ ተግባሩ፣ ጠንካራ ምሽግ መገንባት ነው። ምሽግ ሲባልም መሬትን ጎርዶ ራስን መቅበር፣ ወይም ደግሞ በኮንክሪት መከታ እና ጠለላ ገንብቶ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወነጨፉ አውዳሚ የጦር መሣሪያ አረሮችን መከላከል አይደለም። ጠንካራ ምሽግ ሲባል፣ ታጋዩ ኃይል ነፃ አወጣዋለሁ የሚለውን ሕዝብ፣ ዓላማውን አሳውቆ፣ አሳምኖ እና አደራጅቶ የታጋዩ ኃይል የቀለብ፣ የመረጃ እና የሰው ኃይል ምንጭ ማድረግ መቻል ነው። በአጭሩ ሕዝቡን ባሕር፣ ታጋዩን ዓሣ ማድረግ መቻል «ለነፃነት እታገላለሁ» የሚል ኃይል የአደረጃጀት ስልት ሊሆን ይገባል። ይህን ያላደረገ ታጋይ ሌሎችን ነፃ ሊያወጣ ቀርቶ፣ ራሱም ነፃ አይሆንም። ራሱን ነፃ ያላወጣ ደግሞ፣ ብዙኃኑን ወደ ነፃነት ጎዳና ሊመራ አይቻለውም። ለነፃነት የሚታገሉ ኃይሎች ደረጃ በደረጃ ሊያሟሏቸው የሚገቧቸው ሁኔታዎች … [Read more...] about የነፃነት መውጫው መንገድ፣ ታጋዩ፣ ሕዝቡን ጠንካራ ምሽጉ ማድረግ ሲችል ነው
“ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ይጋቡ” ጠቅላይ ፍርድቤት
* “ፍቅር ፍቅር ነው” ኦባማ ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ጋር ጋብቻ መፈጸም ይችላሉ፤ ለእነርሱ የጋብቻ ሠርቲፊኬት መከልከል ሕገመንግሥቱን ይጥሳል በማለት የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መጋባት እንደሚችሉ ወሰነ፡፡ ለጋብቻ ቅድስናና ክቡርነት የሚከራከሩ “የእግዚአብሔርን ሕግ ምድራዊ ፍርድ ቤት ይህን መለወጥ አይችልም” በማለት ውሳኔውን አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡ በምንም መልኩ ይገለጽ ፍቅር ፍቅር ነው በማለት ፕሬዚዳንት ኦባማ ውሳኔውን ደግፈዋል፡፡ ዋናውን (ዓቃቤ ፍትህ) ጨምሮ ዘጠኝ የፍትህ ዳኞች የያዘው የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ የሰዶማውያን ጋብቻ ላይ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጉዳዩ ከቀረበለት ጊዜያት ተቆጥረዋል፡፡ በአሜሪካ የፍትሕ ሥርዓት ምዕራፍ ከፋች የተባለለት ውሳኔ አርብ ዕለት ሲተላለፍ የፍትሕ ዳኞቹ በአምስት ለአራት በመወሰን ነው ያጸደቁት፡፡ … [Read more...] about “ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ይጋቡ” ጠቅላይ ፍርድቤት
አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ
"የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል" አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም “ልማታዊ” በሚል ካባ የተከናነበውን የለየለት አንባገነናዊነት ሙሉ ድጋፋቸውን እየሰጡ ለመሆኑ የኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ጨምሮ በርካታ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡ ከምርጫው በፊትም ሆነ ከተጠናቀቀ በኋላ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካን መንግስት ያሳዩትም ድጋፍ የእዚሁ መገለጫ ነው፡፡ በአፋኝ አገዛዝ ውስጥ ላለ ሕዝብ ዲሞክራሲን፣ … [Read more...] about አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ










