ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተቃውሞና ዓመጽ የተወጠረው ህወሃት/ኢህአዴግ በአስሩም ክፍለከተሞች የሚገኙ እስከ 600 የሚደርሱ የመሬት ባለሙያዎችን ካገደ በኋላ የአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ሞሳኞች ያላቸውን 85 አመራሮችና ሠራተኞችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ “የመሬት ከበርቴውን” አባይ ጸሃዬንስ ማን ይደፍራቸው ይሆን የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡ በአባይ ጸሃዬ “ልክ እናስገባለን” ተግባራዊ እንዲሆን የታሰበው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ከተስተጓጎለ በኋላ ህወሃት/ኢህአዴግ ማስተር ፕላኑን “ትቼዋለሁ” ቢልም የኦሮሞ ሕዝብ ያስነሳው ተቃውሞ ግን እስካሁን አልበረደም፡፡ “መልካም አስተዳደርን አሰፍናለሁ” በሚል ኢህአዴግ የሕዝቡን ቀልብ ለመሳብ ከላይ ታች እየተራወጠ ነው የሚሉ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንደሚሉት ኪራይ ሰብሳቢነት ለመዋጋት በሚል … [Read more...] about “የመሬት ባላባቱን” አባይ ማን ይድፈራቸው?
ህወሃት ራሱን “ሳያጸዳ” በሌላው ዘምቷል
“የኢህአዴግን መርህ እስከተከተለ ድረስ መሃይምም ቢሆን ሚኒስትር እናደርጋለን” ያሉት መለስ ዙሪያቸውን “የበታች” በሆኑ ሹሞች አስከብበው የቆዩት ያለምክንያት አልነበረም፡፡ “አዋቂ፣ ጠቢብ፣ ባለራዕይ፣ ምንተስኖት፣ …” የሚሉ “ማዕረጎችን” አስገኝተውላቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር የፈለጉትን ሥልጣን ላይ ያስቀምጣሉ፤ ከዚያ በሙስና ያበሰብሳሉ፤ ከዚያም ወደ “ቆሻሻ ቅርጫት” ይጥላሉ፡፡ በሕይወት ለቆዩት “ቅርጫቱ” ትልቅ መድህን ሲሆን ለዚያ ያልታደሉት ግን ትርጉሙ ሌላ ነው፡፡ ይህ የመለስ አሠራር የህወሃት መመሪያ ሆኖ ቆይቷል፤ አሁንም እየተሰራበት ነው፡፡ በኦሮሞ ከተሞች በተነሳው ሕዝባዊ ንቅናቄ የተደናገጠው ህወሃት ከረፈደ “ጽዳት” ጀምሯል፡፡ የችግሩ መንስዔ ራሱ ሆኖ “ልክ መግባት” ሲገባው ለህዝብ “ሥራ ላይ ነን” ለማለት “የኦህዴድን አመራሮች” ማንሳቱ አስታውቋል፡፡ የጎልጉል እማኝ … [Read more...] about ህወሃት ራሱን “ሳያጸዳ” በሌላው ዘምቷል
የጃዋር መሃመድ ቅኝቶች
መገናኛ ብዙሃንን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ግን እንደ በረሃ ተኩላ እያደፈጠ ይናከሳል። ሲናከስ ደግሞ ማንንም አይምርም። ውለታ የሚባል ነገር አያውቅም። ይሉኝታ አይነካካውም። እፍረትም በእርሱ ዘንድ የለችም። ከቶውን መቀበል እንጂ መስጠትን አያውቅም። አስር ተቀብሎ በዜሮ የሚሸኝ ጀግና ነው። በዚህ ተግባሩ አድናቂው ነኝ። “እኔ-ነኝ” ያለ የዲሲ ፖለቲከኛን ሳይቀር ከአንዴም ሁለቴ እንደማስቲካ እያኘከ መትፋቱን እንመሰክራለን። የጡት አባቱ የሆነው ኦነግንም ቢሆን "A Critical Assessment of the Oromo Liberation Front” በሚለው መጣጥፉ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርጎ የጠረበ ፍጡር ነው። ይህ ሰው እንደገና ተመልሶ የ”ነፍጠኛውን ሚድያ” ለመጠቀም የማይሞክርበት ምክንያትም የለም። ጃዋር … [Read more...] about የጃዋር መሃመድ ቅኝቶች
ያገር ያለህ!!! የዳኛ ያለህ!!!
1/ መግቢያ በድሮ ጊዜ ሰው በሰው ሲበደልና ፍትሕ ሲጓደል ‘ያገር ያለህ’ ወይም ‘የዳኛ ያለህ’ በማለት ይጮህ ነበር፤ ይህ ዓይነቱ የተበዳይ ጮኸትም ለትውልድ መርገም እንዳይሆን ተብሎ በአካባቢው በሚኖሩ እድሜና ልምድ ጠገብ ሺማግሌዎች ገላጋይነት/ዳኝነት የበደለ እንዲክስ የተበደለ ደግሞ እንዲካስ በማድረግ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ይደረግ ነበር፤ እኔም ዛሬ በዲሞክራሲ ስም በምድራችን ውስጥ እየሆነ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ /በተለይ ባለውለታ በሆነችው በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ውስጥ/ ቀረብ ብየ ስመለከት ይህ እውነተኛ የፍትህ ፈላጊዎች ያገር ያለህ ጩኸት ትዝ ብሎኝ ለኢትዮጵያውን በሙሉ ለውይይትና ለመፍትሄው ፍለጋ ጭምር የሽማግሌ ዳኞች ያለህ በማለት ጮኸቴን ላቀርብ ተገደድኩ። መቸም ለተወሰኑ ዓመታት ከአገሩ ራቅ ብሎ ለኖረ ኢትዮጵያዊ የአዲስ አባባ ገጽታ ቀየር እንደምትልበት ይታመናል፤ … [Read more...] about ያገር ያለህ!!! የዳኛ ያለህ!!!
ከድጡ ወደ ማጡ፣ አሰብ በአረቦች እጅ ገባች
የአገራችን አንድነትና ብሎም ሕልውና በቋፍ ባለችበት በዚህ ቀውጢ ወቅት ውይይቱ ሁሉ ማተኮር ያለበት ለሥጋቶቹ ምንጭና ምክንያት ስለሆኑት ስለ ዴሞክራሲ ደብዛ መጥፋት፣ ስለፍትህ መቅጨጭ. በብሔረሰቦች መካከል ስለሚታዩት ጥላቻና ግጭቶች እነዚህን የወለደው ሥርዓት ስለመለወጥ ብቻ መሆን አለበት ሌላው ሁሉ ገብስ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውጭ በሆኑ ጉዳዮች መነጋገር ሥርዓቱን ለውጦ ዴሞክራሲና ፍትህ ለማስፈን በሚደረገው ትግል ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደመቸለስ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሆኖም ዘላቂ የአገር ጥቅሞችን መዘንጋት የኋላ ኋላ ሕልውናን ወደ መፈታተን ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ አገር ከሌለ ዴሞክራሲ ምን ሊፈይድ ፍትህስ ምን ሊረባ? ምናልባት የአገር ሕልውናን እስከመፈታተን ሊደርሱ ከሚችሉ ከዋነኛ የአገር እሴቶች አንዱ የባህር በር አለመኖር ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሁኔታ በማይጨው … [Read more...] about ከድጡ ወደ ማጡ፣ አሰብ በአረቦች እጅ ገባች
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
መጽሔቱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
አድዋ! 120 ዓመት!
“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ በታዩ ጊዜ የኢጣሊያን ክፍል አሸበሩት” የበርክለይ ምስክርነት፤ አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ፤ ገጽ 195 … [Read more...] about አድዋ! 120 ዓመት!
ጊዜ በማያደበዘዝው የአድዋ ድል ማግስት…
የዓለም ህዝብ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ድል ያደረገውን የጥቁር ጦር መሪ አጤ ምኒልክን ለማወቅ እጅግ ጓጓ፡፡ ምስላቸውን ለማየት ተቁነጠነጠ፡፡ ሙሉ ታሪካቸውን ለመስማት ተንሰፈሰፈ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም፤ "እንኳንም ደስ አለዎት" ለማለት ከቁጥር የበዙ ደብዳቤዎች ይጎርፉላቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በፖስታ ቤት በኩል የኢትዮጵያ ቴምብር የተለጠፈበት መልስ እንዲላክላቸው ይጠይቁ ነበር፡፡ ለምን… ? ቴምብሩ ላይ ያለውን የምኒልክን መልክ ለማየት፡፡ ባለ ብዙ ዝናና ክብር ባለቤት የሆኑትን የምኒልክን ጥቁር ፊት ለማየት፡፡ የሰው ሀገር ሰው ሁሉ፤ "ዝናውን እንደሰማሁ መቼ ሄጄ ባየሁት"፣ "በጀግንነቱ እንደ ተማረኩ መች ተጉዤ ባገኘሁት"፣ "ካሁን ካሁን ፈቅዶልኝ ወታደር ሆኜ ባገለገልኩት" ያለላቸው አጤ ምኒልክ የኛ ናቸው፡፡ በዓለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ያንበረከከ … [Read more...] about ጊዜ በማያደበዘዝው የአድዋ ድል ማግስት…
“ሀገራችን ላይ እየኖርን አይመስለኝም” ታክሲ አሽከርካሪ
“ሁላችንም የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን።ሕጉ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክሥራ ውጪ እንሆናለን።’’ በዛሬው ዕለት የታክሲ ማቆም አድማ ካደረጉት የታክሲ አሽከርካሪዎች በከፊል፡፡ በአዲስ አበባ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ደንብን ለማስከበር ከአምስት ዓመት በፊት የወጣውና በከፊል ሲተገበር የነበረው ሕግ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ በመጀመሩ የአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች በሙሉ በዛሬው ዕለት ሥራ የማቆም አድማ መተው ውለዋል፡፡ ፌደራሉ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ትናንት ባወጣው መግለጫ ትግበራው ለሦስት ወር መራዘሙን አስታውቋል፡፡አሽከርካሪዎቹ ደግሞ “ለሦስት ወር ማራዘም መፍትኄ አይደለም ዘላቂ መፍትሄ እንፈልጋለን” ይላሉ፡፡ አሽከርካሪዎችን የአዲስ አበባን ፖሊስ ኮሚሽንን ያነጋገረችው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘገባ … [Read more...] about “ሀገራችን ላይ እየኖርን አይመስለኝም” ታክሲ አሽከርካሪ
ብሶት የወለደው የኦሮሚያ አመጽ ተቆንጥሮ አስመራ ላይ ተላከከ!
በኦሮሚያ የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኛነትና ዓመጽ ተከትሎ ስለጠፋው የሰው ህይወት እርግጠኛ አሃዝ የሚጠቅስ አልተገኘም። ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና የአገር ውስጥ ቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚሉት የህወሃት አንጋቾች ከ200 በላይ ንጹሃንን ገድለዋል። በነጻ አውጪ ስም አገሪቱን እየመራ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር - ህወሃት፣ አመጹን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ ቆይቶ በስተመጨረሻ ችግሩን ቆንጥሮ አስመራ ልኮታል። ወታደርና ከባድ መሣሪያም ወደ ድንበር አስጠግቷል። መፍትሔው ጭፍን ብሔረተኝነት ሳይሆን ሁሉንም በሰብዓዊ ፍጡርነት ማየት ነው የሚሉ አካላት “ጆሮ ያለው ይስማ፣ ልቡና ያለው ያስተውል” እያሉ ነው፤ ርምጃቸውንም ከጊዜ ጋር አዋዝተዋል። ህወሃት የትጥቅ ትግልን የራሱ “ንግድ ምልክት” አድርጎ መውሰዱ የማይዋጥላቸው “ለህወሃት ብቻ የትጥቅ … [Read more...] about ብሶት የወለደው የኦሮሚያ አመጽ ተቆንጥሮ አስመራ ላይ ተላከከ!










