መቼም እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን የኛ ብለን ክብር ሰጥተን ያመነው ሰው ደ’ሞ ከዳን። ይሄን ሰማሁ ይሄውልሽ አንቺም ሰሚው አይቅርብሽ እንደው ቢገርመኝ እንጂ ነገሩ፥ይሄማ ምኑ ይወራል የኛ ያሉት ሲከዳ፥ቃሉ ለአፍ ይመራል ብቻ ምን ይደረግ? ”ውሻ በቀደደው…” ይባል የል የሱስ መክደት ምን ይደንቃል? እንደው ግን ለነገሩ፤ እየገደሉ እያያቸው በደም ተጨማልቆ እጃቸው ከነሱ ጋር አብሮ እየደለቀ ከበሮ የተለጠፈው ውስጣቸው ምን አግኝቶ ምን አጥቶ ነው? በምኑስ ላይ ምን ሊጨምር? መች አነሰው? ንዋይ ክብር በይ ተይው ግድ የለም፤ መቼም-እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን። እንግዲህ ካልሰማሽም ስሚ፤ ከሰማሽም-ቻልአድርጊው እኛን ያልከዳን ማን አለ? የበደለን … [Read more...] about እኔና አንቺ…፪
Literature
ጽፈኪን
”ዛሬም ታለቅሳለች!”
''ዛሬም ታለቅሳለች!'' ትላ’ትናም - ዛሬም ቁማም - ተቀምጣም በውኗም - በህልሟም፤ እምባ እያዘነበች ደም እያፈሰሰች፤ ሁሉንም እያየች ዛሬም ታለቅሳለች።……. ‘’ረስታ - ተረስታ በራሷ ላይ ዘግታ፤ ከጥዋት እስከማታ እንቅልፏን ተኝታ’’። ተብሎ ተወርቶባት ለብዙ ዘመናት ታሪክ ተጽፎባት፤……. እሷ ግን፣ እሷ ናት ዓለም የሚያያት፤ እምባ እያዘነበች እህህ…… ትላለች ትንሰቀሰቃለች፤ ሁሉንም እያየች ዛሬም ታለቅሳለች።……… ተማፅኖ ተማሎ ተገዝቶ ምሎ ገ’ሎና አስገድሎ ፤ ‘’ለ’ርሀብ - ‘ርዛትሽ ለልመና - ፅናትሽ ለፍትህ - እጦትሽ ለሰላም - ለፍቅርሽ፤ መድሀኒት አውቃለሁ እኔ እሻልሻለሁ’’፤ ብሎ የሚገባው እምባዋን ሊጠርገው መፍሰሱን ሊያቆመው፤...... ጭራሽ አብሶባት ሀዘን ደራርቦባት፤ ማቁን አስለብሶ አመድ … [Read more...] about ”ዛሬም ታለቅሳለች!”
ምሁር (intellectual)
ከሰው ወይ ከአምላክ ፤ ተምሮ የረቀቀ ቀለም ብዙ የጠጣ ፤ ከባሕር እየጠለቀ ተለይቶ የወጣ ፤ በርቶለት የራቀ አንጥሮ አብጠርጥሮ ፤ መርምሮ የላቀ በአዎንታዊ እሴቶች ፤ ጌጦ ያሸበረቀ ደግነትን ከሸር ፤ ልማትን ከጥፋት ፤ ለይቶ የጠበቀ የሚያሰነካክለውን ፤ የት እንዴት እንደሆን ፤ ነቅቶ የጠነቀቀ ነበር ምሁር ማለት ፤ መሻል መብለጣቸውን ፤ አጣጥሞ ያወቀ አዬ ድንቄም አያ ii ፤ ምሁሩ ሊቅ ዐዋቂ የሀገር አደራ ጠባቂ በአረጋዊያን ተመራቂ በታናናሾቹ ተደናቂ ትውልድን አናጭ አምጣቂ አብእናን ቀራጭ አላቂ በዕውቀት በጥበብ አርቃቂ ለችግር መፍትሔን አፍላቂ የሥልጣኔን ብርሃን ፈንጣቂ ለሀገር ለወገን መከታ ለትውልድ ተስፋ አለኝታ መመኪያ ደጀን ስጦታ አይደለም ? ትርጉሙ ሲፈታ ? አዪ … እ !! ድንቄም ዐዋቂ የመጠቀ የእንስቷን ተስፋ የደመቀ በወላጅ … [Read more...] about ምሁር (intellectual)
ለቅሶ እንድረስ
ቀብር ውጡ ወዳጆቼ - ጌታ ብእር አረፈ ደራሲው ሰው ሆነ - ፈጣሪነቱን ተገፈፈ፤ በመጋኛ ተቦትልኮ - በዘር ሀረግ ተጠርንፎ ጌታ ብእር ተሻረ - ካባ ማእረጉን ተገፎ የት ይደርሳል ያልነው ጎበዝ - ተስፋ ያልነው ሽል ጨንግፎ፤ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለቅሶ እንድረስ
The Secret (ሚስጢሩ…)
ሚስጢሩ አሁን በሀይለኛ ሂደት ላይ ወቷል። እርስዎም የውለታ ምስጋናን፤የሚፈልጉትን ነገር በዓይነ ህሊና አስቀድሞ ማየትን፤የተግባር ሀይልን ሂደቶች የሚረዱበት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው።ለመሆኑ አስቀድመው ይሄን ሁኔታ የተሸጋገሩ ምን ይላሉ? ያሁኑ ማንነታችን ያለፈው አመለካከታችን ውጤት ነው። ቡድሃ የየቀኑ ምስጋናህ ፀጋ ወደ አንተ የሚመጣበት ማስተላለፊያ ቀዳዳ ነው ዋላስ ዋትልስ መተንበይ ሁሉንም ነገር ነው።የህይወት መጻኢ መስህቦች ቅድመ እይታ ነው። አልበርት አንስታይን ሀይለኛው ሂደት የምትፈልገውን አጥብቀህ መጠበቅ ሊረዳህ ይችላል ፍላጎት እንዳይርቅ ስትተኛም ሆነ ጠዋት ስትነሳ በያንዳንዱ ነገር ማመስገን አትርሳ በጅህ ባለ ነገር ማመስገን ስትጀምር መንገድ ትፈጥራለህ ሌላ ለመጨመር የምትፈልገውን በዓይነ ህሊና አስቀድመህ አይተህ አስተካክለውና ማግኘትህን … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
እኔና አንቺ … ፩
መቼም እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን ይሄው ደግሞ ተሰደንም ልንስማማ አልደፈርንም። ሳትሰሚኝ አጣጥመሽ እኔም ያንቺን ሳላውቅልሽ መግባባቱ እንዳቃተን በየአቅጣጫው ተበታትነን ስንፋተግ ዕድሜ ገፋን። እውነታውን ስንሸሸው፣ መወያየት ስንፈራ ቀለብ ሆነን ሀሜት ጉራ። በይ ተይው ግዴለም፣ ድሮውንም ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን። ለነገሩ ትተነውስ ወዴት ልንደርስ ግደለሽም እኛው ደፍረን እንዋቀስ የዕለት የዕለቱን ትተነው ዘላቂውን እንመርምረው። የጋራ ችግራችንን ተነጋግረን በጋራ እንፈታለን እያልን በአፍ ብቻ ስንወተውት ከልብ አጣን ስምምነት። ስለሀገሬ ስለሀገርሽ አንቺም ስሚኝ፣ እኔም ልስማሽ! የማተያት፤ የማልተዋት የጋራችን አንድ ሀገር ናት። ታዲያ … [Read more...] about እኔና አንቺ … ፩
ሀገር ማለት
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ አስቀድሞ ደራሲ በዓሉ ግርማ በኋላም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ግጥሞቻቸውን ጽፈው ነበር፡፡ ሌላም የጻፈ ይኖራል፡፡ ነገር ግን እነኝህ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎች ግጥሞቻቸውን ሲጽፉ የተቆነጸለ ወይም የተሳሳተ ትርጉም ሊያሰጥ በማያስችል ሁኔታ ግጥሞቻቸውን ባለመጻፋቸው እንደምገምተው እነሱም ሊሉ ባልፈለጉት መንገድ ተተርጉሞ የቅጥረኞች መጠቀሚያ እስከመሆን ድረስ በቃና ሕዝብን ለማደናገሪያ አገለገለ፡፡ ከሕዝቡ ጥቂት የማይባል ወገንም በመወናበድ ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ይዞ ማንጸባረቅ ያዘ፡፡ ይህም መሆኑ ሀገር በሕዝብ ልብ ውስጥ የነበራት ቦታና ትርጉም ከመዛባቱም ባሻገር በወደፊት የሀገር ህልውና ላይ ከባድ አደጋ የጋረጠ ሆኖ ቁጭ አለ፡፡ እናም እንደዜጋ አሳሰበኝና ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ለማረም የሀገርን ትርጉም ሳይቆነጸል ሳይጎነጠል ለማስፈር ተገደድኩና ይህችን ግጥም … [Read more...] about ሀገር ማለት
እንኳን ደስ አለን ለሁላችን!!
ይገርማቹሀል ይሄንንና እዚህ ላይ አሁን ለእናንተ ያላቀርብኩትን በግእዝ (አማርኛ) ፊደል ቁጥርና የቁጥር ስሞች መቸ፣ የት፣ እንዴት፣ ተፈጠሩ? የሚለውንና ባጠቃላይ በቋንቋችን ላሉ ሌሎች ምላሽ ያልነበራቸው ጉዳዮችን ምላሽ የሚሰጥ የጥናትና ምርምር ሥራ ከሐሳብ ወደ ተግባራዊ ሥራ ተሸጋግሬ መሥራት የጀመርኩት ዐሥራዎቹ መገባደጃ የዕድሜ ክልል እያለሁ ጀምሬ ነበር፡፡ ከብዙ ዓመታት ድካምና ጥረት በኋላም ሥራውን ጨረስኩ ባልኩ ጊዜ ምቹ ሁኔታና ጊዜ ይመጣል ብየ ብጠብቅ ብጠብቅ ቀጠሮ ያልያሳዘኝ ነገር መቅረቱ አሳሰበኝና ከሁለት ዓመታት ወዲህ ጀምሬ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃንና ዕውቅና ለሚሰጡ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ ተቋማት አቀረብኩት፡፡ ታዲያ እዚያ ያሉት ሰዎች ፊደላት ካልተነቀነሱ ሞተን እንገኛለን የሚሉና ከዚያም አልፈው ወደ 91 የሚደርሱ ሆሄያትን አስወግደው በተቋም ስም መጽሐፍ … [Read more...] about እንኳን ደስ አለን ለሁላችን!!
ስምና ገመድ!!
በተለያዩ ምክንያቶች ለረጅም ጊዜ አቋርጠነው የነበረውን የግጥም ጨዋታ እንደገና ጀምረናል፡፡ ከዚህ በፊት እናደርገው እንደነበረው አንባቢያን ይህንን ግጥም አንብባችሁ አስተያየታችሁን በግጥም እንድትሰጡና ጨዋታውን እንድታደምቁት እንጋብዛለን፡፡ ለዛሬ የመረጥነውን ግጥም ከነፎቶግራፉ ያገኘነው ከደመቀ ከበደ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው፡፡ገጣሚ ደመቀ ከበደን ለግጥሙና ለፎቶው ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ስምና ገመድ!! አዝማሪ እንዲህ አለ፤ "ሰው ሰበበኛ ነው - ምክንያት አያጣም እንኳን ዝናብ ዘንቦ - ሲዳምን አይወጣም፤" እኔ ግን እላለሁ፤ አተተ በተተ ወዘተ ወዘተ በሚል አርቲ ቡርቲ - ዕድሜ ከምንጨርስ ህይወት ከምናጣ ፋይዳ ላለው ነገር - ቁልቁለት እንውረድ አቀበት እንውጣ፤ ያኔ አላስወርድ ካለህ - ወይም አላስወጣ ማሰሪያ ከሆነህ - አሊያም ጋሬጣ ያኔ አይንህን … [Read more...] about ስምና ገመድ!!
The Secret (ሚስጢሩ…)
ስለተከሰተው ሚስጢርና የሚስጢሩን ቀላል መደረግ አሁን የሚጠይቁኝ አይመስለኝም።ይልቁንም አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ይሉኝ ይሆናል።ለዚህ በክፍል ሶስት ጽሁፌ መልስ ይዣለሁ።ከዛ በፊት ግን ታላቁ መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላል?የሚስጢሩ ተጠቃሚዎችስ ምን ይነግሩናል?ይሄን አንብበው ወደ ሚስጢሩ አጠቃቀም ይሻገሩ። "አምናችሁም፤ በፀሎት፤ የምትለምኑትን፤ ሁሉ ትቀበላላችሁ።" ማቴዎስ፤ ፳፩-፳፪ "የፀለያችሁትን፤ የለመናችሁትንም፤ እንዳገኛችሁት እመኑ። ይሆንላችሁማል።” ማርቆስ፤ ፲፩-፳፬ "ነገሮች ሁሉ፤ ይለወጡልህ ዘንድ ዓለም እንደገና ራሷን ታዘጋጃለች።” ዶ/ር ጆ ቫይታል "የመጀመሪያው መነሻህ ታማኒነት ይሁን።የደረጃውን መጨረሻ አጠቃለህ ማየት አያስፈልግህም።ዝም ብለህ ወደ መጀመሪያው ደረጃ ውጣ።" ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የሚስጢሩ አጠቃቀም የምትፈልገውን ለመፍጠር … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)









