ያስገረሙኝና ፈገግ ያሰኙኝ የማህበራዊ ሚዲያ ‹‹ጥቅሶች›› 1. ‹‹የድሃ ልጅ ስሙ ሀብታሙ ነው›› 2. ‹‹ሰውና ድፎ በትዕዛዝ እንደፋለን›› 3. ‹‹ቁንጅና ይኑርሽ እንጂ ፀባይ በዱላ ይመጣል›› 4. ‹‹የሴት ልጅ ግርዛትና ሚስድኮል ይቁም›› 5. ‹‹ኡፍ በማለት ትንፋሽ እንጂ ብሶት አይወጣም›› 6. ‹‹ለህይወትህ ዋጋ፣ ለልጆችህ ዳቦ ስጥ!›› ሰፈር ውስጥ የሰማኋቸው አዲሶቹ የሸገር ልጆች ቃላት • ‹‹በጤ›› - በጣም ለማለት • ‹‹በኔ›› - በእናትህ ለማለት • ‹‹እሱ እኮ እምባ ነው›› - የቅርብ ተቆርቋሪ ነው ለማለት • ‹‹ጠበዘዝነው›› - በላነው ለማለት • ‹‹ዘጭ ብያለሁ›› - ጠግቤያለሁ ለማለት • ‹‹ኤም ጢ ›› - መስሚያዬ ጥጥ ነው/ አልሰማህም ለማለት ታክሲ ላይ ያነበብኳቸው፡ 1. ‹‹ሰው ብቻ ነው የምንጭነው፤ በስህተት የገባ ካለ … [Read more...] about የአፍታ እፍታዎች
Literature
ጽፈኪን
ቅኝ ግዛት!
ምነው በቀደም ለት እንቢልታ ሲነፋ ከበሮ ሲደለቅ፣ ከዘመናት ግዞት ነፃ የወጣንበት፣ ብለህኝ አልነበር አፍሪካ ነፃ ናት? "'አፍሪካ . . . ሀገራችን አፍሪካ የኛ ናት አፍሪካ አፍሪካ. . ." ተብሎ ሲዘመር የጥቁሮች ነፃነት? ታዲያ ዛሬ ለሊት፣. . . የሰማሁት ዋይታ ያዳመጥኩት ጩህት፣ ሲያከብሩ እዳትለኝ የበአሉን ማግስት? ዋሽተህኛል እንዴ . . . ? ትርጉሙን አዛብተህ? . . . ሆኖ እንዳይሆን ብቻ፣ ነፃ መሆን ማለት ካልሆኑ አቻ ላቻ ፣ ለወሬ ማድመቂያ ዳንኪራ መርገጫ፣ ነፃነት ነፃነት እያሉ ማፋጫ፣ ድቤ መደለቂያ በባዶ መንጫጫ ? እኔን ነፃ ያርገኝ. . . በዚች መሬታችን በምንኖርባት፣ የጥቁር ደም አጥንት በግፍ ባለቀባት፣ ነፃነት አግኝቶ ደምቆ `ሚኖርባት ? የሰላምን አየር ተንፍሶ `ሚድርባት ነጭ ነው ወይ ጥቁር . . . … [Read more...] about ቅኝ ግዛት!
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፭” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አምስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ለሀገር ለወገን - ውለታ የሰራ ስሙ ለዘለዓለም - ይኖራል ሲጠራ ነገር ግን ታሪኩን - ያረገውን በጎ አንባቢው አለበት - መረዳት ፈልጎ እኛ ለማስታወስ - ይሄንን አድርገን ለማቅረብ ችለናል - መላኩ በያንን እኚህ ስመ ጥሩ - ኢትዮጵያዊ ዶክቶር ሙሉ እድሜአቸውን - ደክመዋል ለሀገር። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮
የሎሬት ህመሙ ቢያመኝ
ይሞላ ብዪ ስኳትን፣ ህልሜ እልም እያለ ቢፈትነኝ ለህሊናየ አድር ብዪ ስማስን፣ ድካሙ ቢሸበርክኝ ተስፋ አልቆርጥም ባልኩ በተጋሁ፣ ህመሙ ቢደቁሰኝ ብላቴን ጌታ ታወሰኝ፣ ጸጋየ ህመሙ ዘልቆ ወጋኝ የጸጋየ ህመሙን ታመምኩ መላ ቅጡን አስጠፋኝ። ውስጤ ቢደማ ቢታወክ፣ የጸጋየ ሮሮ በአይነ ህሊናየ መጣብኝ የመጨረሻው እስትንፋስ ቃሉ፣ ሎሬት ህመሙ አመመኝ "እኔ ለእኔ ኑሬ አላውቅም " ብሎ ያለን የስንብት ጸጸት ቃሉን አዘከረኝ፣ ....... ........ ....... ......... ........ ...... የጸጋየ ጸጸት ... "የማይሰማ ወጨት ጥጄ - እፍ ስል የከሰመ ፍም፣ ውርዴም ይፈወሳል ብዬ - የሰው እከክ ስዘመዝም፣ በሰው ቁስል መቁሰል በቀር - እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም፡፡ የማይነጋ ህልም ሳልም - የዘመን ደዌ ሳስታምም፣ የማያድግ ችግኝ … [Read more...] about የሎሬት ህመሙ ቢያመኝ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፭
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አራት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ኃይለማርያም ማሞ - የጦሩ ገበሬ ፈረሱን እንደሰው - አስታጠቀው ሱሬ መተኮሱንማ - ማንም ይተኩሳል ኃይለማርያም - ማሞ አንጀት ይበጥሳል በማለት በዜማ - የዘመርንላቸው ኃይለማርያም - ማሞ ማለት እኚህ ናቸው። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? –፭” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፭
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫" በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሶስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በፊት የታወቁ - ገነው በስራቸው ዛሬ ሚታወሱ - በቴዲ ልጃቸው ስምህ ይጠራልህ - ብትሞትም ያላቸው ካሳሁን ገርማሞ - ማለት እኚህ ናቸው ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ እኚህ ሰው ማናቸው – ፬? ቃልም አልተነፍስ - ፍንጭም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሁለት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ "የእንዳልካቸው አባት የእንዳልካቸው ልጅ መውለድ አስተካክሎ እንደዚህ ነው እንጂ" በማለት አዝማሪ የገጠመላቸው ቢትወደድ መኮንን ማለት እኚህ ናቸው እኚሁ ትልቅ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ መጽሐፍትን የጻፉም ነበሩ። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፩” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አንድ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ሲጠሩ የኖሩ - በዶክቶር ማዕረግ የውጪ ጉዳይን - የመሩልን በወግ በጥሩ ስራቸው - የሚነሱ ሁሌ ስማቸው ምናሴ - አባታቸው ኃይሌ ተብለው ሚጠሩ ባለስልጣን ናቸው ምስላቸው ተለቆ - ሳምንት ያየናቸው ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ እኚህ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፩
ከአዘጋጆቹ፤ የዘወትር የጋዜጣችን ተሳታፊና የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ርዕስ በየሳምንቱ የታዋቂ ሰዎችን ፎቶ ከግጥም ጋር በመላክ ጥያቄ ለማቅረብና አንባቢያንን ለማሳተፍ ውሳኔ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ከግጥምና ፎቶ ጋር ለሚቀርብ ዝግጅት አንባቢያን ጥያቄውን በግጥም በመመለስ እንዲሳተፉ እንፈልጋን፡፡ በሳምንቱ ቀጣዩን “እኚህ ሰው ማናቸው?” ስናትም መልሱን አብረን እናወጣለን፡፡ በዚህ መልክ ውይይቱ እንዲቀጥል ለማድረግ ያቀድን ሲሆን አንባቢያንም የእውቅ ሰዎች ፎቶዎችና ማንነታቸውን ብትልኩልን ለማስተናገድ የምንችል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ በተለይ የታዋቂ ሰዎች የልጅነት ፎቶዎች ቢሆን የበለጠ አስተማሪ ይሆናል ብለን እናስባለን፡፡ ለዛሬው የእኚህን ታዋቂ ሰው ፎቶ ከግጥም ጋር አቅርበናል፡፡ ምላሹን ከእናንተ እንጠብቃለን፡፡ ይህንን የዝግጅት ሃሳብ ላቀረቡትና … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፩
ሽፈራው ወይም ሞሪንጋ
ይህ መጽሐፍ ያከተተው የሚከተሉትን ዝርዝር ጉዳዮች ነው፡፡ ማውጫው ላይ እንዲህ ተቀምጧል.... ምእራፍአንድ ሽፈራው ወይም ሞሪንጋ ምንድነው? 1. የሽፈራው ወይም ሞሪንጋ ዓይነቶች 1.1. የሽፈራው ዓይነት ብዛትባንዳንድ አገሮች 1.2. በሰሜን አፍሪካ ዛፎች፥ ቁጥቋጦዎችና እጾች ጎራ ውስጥ የሚካተቱ የሽፈራው ዘሮች 2. ሽፈራው ባለም ላይ የሚበቅልባቸው አገሮች 2.1. ባፍሪካና በእስያየሚበቅሉባቸውአንዳንድ አገሮች ናሙና 2.2 በየአገሩ ለሽፈራው የተሰጡ የመጠሪያ ስሞች ምእራፍ ሁለት የሽፈራው ጥቅሞች 1. ቅጠል፣ አበባ፣ ፍሬ፣ እንቁሪባ፣ ስርና ግንድ ምንነት 2. ከቅጠሎች የሚገኙ ቪታሚኖችና ሚኔራሎች ጥቅሞች 2.1 የሽፈራው ትኩስ-እርጥብ ቅጠል ጠቀሜታ 2.2 የሽፈራውቅጠልዱቄት ጠቀሜታ 2.3 የሽፈራው ቅጠል ሻይ አሠራር 2.4 በሻይ መልክ መውሰድ … [Read more...] about ሽፈራው ወይም ሞሪንጋ










