ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሬድዮ ጋዜጠኛ በነበረበት ጊዜ ወደ ጋሞ ጎፋ ለስራ ሲሄድ፣ በድንገት ካጋጠመችው የሐመር ቆንጆ ጋር የተነሳው ፎቶ ነው። ምልልሱን ያንብቡ። በደመቀ ፀሐይ ከወለላዬ በቀን አጋማሽ ላይ - በደመቀ ፀሐይ አካሏ ተጋልጦ - በግማሽ የሚታይ፣ የተዋበች ሐመር - መንገድ ላይ ብትወጣ አዬ ጋዜጠኛው - የመጣበት ጣጣ፣ እሷ ግን እቀፊው - ሳሚው ሳሚው ብሏት ጎኑ ብትጠጋው - አሹላ ያንን ጡት፣ የሱም አጉል ፍራት - የሷም አጉል ድፍረት በደመቀ ፀሐይ ---------- ሰውም ይፈራል ወይ? ከአበራ ለማ ጌታ ወለላዬ - ምነዋ አልፈራ መትረየስ ደግና - ፊቴ ተገትራ፤ ደ’ሞኮ አወጣጧ - ከጫካው ከዱሩ መፍራት ይነሰኝ ወይ - እንግዳው ላገሩ፤ አያድርስ እንጂ ነው - touch down ብትለኝ በዚህ በጠራራ - መጋኛስ … [Read more...] about የሐመሯ ቆንጆ
Literature
ጽፈኪን
“የኔ” የምለውን፤
ባለፈው "ምን ይባላል?" በሚል ርዕስ ላቀረብነው የብሌን ከበደ ግጥም በመሳተፍ ጨዋታውን በግጥም ላደመቃችሁት Yaredo Enkubi እና በለው ምስጋናችን የላቀ ነው:: ሌሎችም በፌስቡክ ገጻችን በኩል አስተያየት የሰጣችሁንን ከልብ እናመሰግናለን:: ለዛሬ ደግሞ የዘወትር ተሳታፊያችን የካናዳው ከበደ ይህንን ግጥም ለከውንናል - "የኔ" የምለው በማለት ለላኩልን ግጥም እናንተስ ምን ትላላችሁ? "የኔ" የምትሉትን በማለት ጨዋታውን እናድምቀው - ሃሳባችንን እንንወጣው - የልባችንን እንግለጽ:: “የኔ” የምለውን፤ ታሪኬን ኩራቴን መብቴን ነፃነቴን ...ኢትዮጵያዊነቴን ከውስጤ አውጥታችሁ መሬቴን ወስዳችሁ፤ ቤቴን አፍርሳችሁ መንገድ ብትሠሩ ፎቅ ብትደረድሩ ቢትረፈረፍ እንኳን መብራቱ ባቡሩ እኔ “የኔ” ብየ እስካልተቀበልኩት፤ እስካልያዝኩት ድረስ ምንም አይመስለኝም ቢነድ፤ … [Read more...] about “የኔ” የምለውን፤
ምን ይባላል!
ከዚህ በፊት ስናደርግ የነበረውን የግጥም ጫወታ በበርካታ ምክንያቶችና ለመቀጠል ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለn:: በተቻለን ሁሉ እንደገና ለመጀር እየሞከርን በመሆኑ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በአጫጭር ግጥሞች ታላላቅ መልክቶችን የምታስተላልፈውን የብሌን ከበደን ግጥም ለዛሬው አቅርበናል - ግጥሙን ያገኘነው ከብሌን ፌስቡክ ገጽ ላይ ነው:: እስቲ እናንተም የፌስቡክ ውሎዋችሁን ስንኝ ቁዋጥሩበት:: ምን ይባላል! ውሎና አዳሬን እዚህ ተወዝቼ ሰፈሬን መንደሬን ቀዬዬን ዘንግቼ ከጠለቀው ባህር `ከፌስ ቡክ `ገብቼ ጥቂት ሞጫጭሬ ብዙ እውቀት አጊኝቼ ሀሳብን ደግፌ ካልመሰለኝ ትቼ አሁንም እዛው ነኝ መስኮቴን ከፍቼ ። አንድ ጊዜ በላኘ ቶኘ አንድ ጊዜ በስልኬ አይኖቼን ተክዬ እዛው ተላክኬ ቀንና ሌት ሳልመርጥ ስገባ ስወጣ ያ ደሞ ምን አለ ይሄ ምን አመጣ ያቺ ምን … [Read more...] about ምን ይባላል!
ነጋ ደግሞ !
ላስታምም የሆዴን ጩርር ..... ርታ፤ ላዳምጥ የወስፋቶቼን ጩኸት ጫጫታ፤ የማያቋርጥ የረሃብ ሳል ልስል፤ እሹሩሩ እያልኩ ረሃብን ላባብል፤ ልደማ ልቆስሌ ልገዘገዝ በችጋር፤ በቁም ሞቼ - ላልኖር ስኖር፤ በብርሃኗ ላላጌጥ - ጮራዋ ለኔ ላይፈነጥቅ፤ ነጋ ደሞ ! ...... ሌላ ቀን - ፀሐይ ወ'ታ ልትጠልቅ :: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ነጋ ደግሞ !
ሆሳዕና
ከቤተ ፋጌ እስከ እየሩሳሌም ማቴዎስ ም.፪፩፣ ፩-፩፯ ወደ እየሩሳሌም ወደ ቤተ ፋጌ ደርሰው ነበርና ደብረዘይት ግርጌ በዛን ጊዜ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሎ አዘዘ ጠራና ሁለቱን ከዛ ከፊታችሁ ከምትገኝ መንደር አህያ ታስራለች ከውርጫዋ ጋር ሂዱ ቅደሙና አምጡልኝ ፈታችሁ ማንምደግሞበዚህ አንዳችም ቢላችሁ በሉና ንገሩት ጌታ አስፈልጎታል ይሄንን ሲሰማ ወዲያው ይሰዳታል። ፅዮን ሆይ ንጉስሽ ባህያ ጀርባ ላይ ይመጣለንዳለው አስቀድሞ ነብይ ደቀ መዛሙርቱም ሄደው አመጡለት እንዳዘዘው ሆነ እንዲፈጸም ትንቢት። ባህያ ተቀምጦ እየሱስም ሲደርስ ከህዝቡ ብዙዎቸያነጠፉ ልብስ ሌሎችም እንዲሁ ከዛፉ ጫፍ ጫፉን ቆርጠው በመጎዝጎዝ ሸፈኑት መንገዱን ቀድመው የደረሱ የተከተሉትም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በአርያም የተባረከ ነው መጪ በጌታ ስም እያሉ በመጮህ … [Read more...] about ሆሳዕና
ደስ ይበለን በዚህ ብስራት
አድዋ! በድልሽ የተገኘ ምስራች ጊዜው ረዘመ ብሎ ሳይሰለች ዕድሜው በዕድሜ ላይ እየጨመረ ጀግኖችን እንደገና እያነሳ እየደመረ ዛሬም በልጅ ልጅ ልጅ ልጅ ልጅ….ታሪክሽ ታውቀ የድል ብስራትሽ በዓለም ዓለም ዓለም ዓለም….አንጸባረቀ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ሻማ መሆንሽ ተወራ ሀገር ለሀገር ተሰማ ይሄው ተከበረ መቶ አስራ ስምንተኛ ዓመት ሁላችንም ደስ ይበለን በዚህ ብስራት የአበው ተጋድሎ የጀግንነት ደም ታሪኩ ተወሳ በከንቱ ፈሶ አልቀረም የአባ ዳኘው መድፍ አሁንም አገሳ መልሶ የጣይቱ ስም ተጠራ ተወደሰ አባ ነፍሶ እንደገና አስተጋባ የአድዋ ድል ገኖ ታየ ተደነቀ አባ መቻል ሀብተ ጊዮርጊስ አባ መላ ስራው በድጋሚ ጎላ። አድዋ! በድልሽ የተገኘ ምስራች ጊዜው ረዘመ ብሎ ሳይሰለች ዕድሜው በዕድሜ ላይ እየጨመረ ጀግኖችን … [Read more...] about ደስ ይበለን በዚህ ብስራት
የለም
እንትን የለም እንትን የለም በእንትን እጥረት ህይወት ማዝገም እንትና እንትን መጠቋቆም መደማደም ተስፋ ያጣ ተስፋችንን ግዜ ሰጠን እንደማከም እሱ እነሱ እንደዛ እያልን ለራስ ሚሆን ግዜ አጠረን ----- Zeynu Seid ----- ከAfendi Muteki ፌስቡክ የተገኘ … [Read more...] about የለም
“ሰዋስው ተማር”
አንድ የሰዋስው ተማሪ ውሃ ለመቅዳት ወደ ጉድጓድ ሄደ፡፡ ሆኖም በጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ተንሸራተተና ከጉድጓዱ ውስጥ ተደፋ፡፡ እዚያም ሆኖ ዋይታውን ሲለቀው አንድ መንገደኛ ሰማውና ሊረዳው መጣ፡፡ “ምን ሆንክ?” “እንደምታየው ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ልሰጥም ነው፤ ቶሎ ገመድ አምጥተህ ካላወጣኸኝ መሞቴ ነው” “እሺ ገመድ ልፈልግና ልምጣ፤ እስከዚያው ግን የጉድጓዱን ዳር ይዘህ ለመንሳፈፍ ብትሞክር ይሻላል” መንገደኛው ይህንን ተናግሮ ሊሄድ ሲል ተማሪው አላስችል አለው፡፡ እናም “አንድ ጊዜ ቆየኝ እስቲ” በማለት መንገደኛውን ከመንገድ ጠራውና እንዲህ አለው፡፡ “ቅድም የተናገርከው ዐረፍተ ነገር የሰዋስው ደንብን የጠበቀ አይደለም፤ ስለዚህ ላስተካክልልህ ብዬ ነው የጠራሁህ”፡፡ መንገደኛው ይህንን ሲሰማ በጣም ተናደደ፡፡ ከጉድጓድ ውስጥ ለሚንቦጫረቀው ተማሪም እንዲህ አለው፡፡ “እንደዚያ … [Read more...] about “ሰዋስው ተማር”
እናቴ የእኔ እናት…
እኔ ልሙት አንቺ፣ አንቺ ትሞች እኔ፣ ሳያውቅብን ቀኑ፣ ሳናውቅበት ቀኑን፣ በቁም ያለን መስሎን፣ እናቴ እኔና አንቺ፣ ተለያይተን ቀረን። ሞትን መቀበር ነው፣ በጉድጓድ መከተት፣ ከምድር በታች መዋል፣ ብለህ አትናገር፣ ሌላ ሞትም አለ፣ አታውራ ዝም በል። በእኔና በእናቴ፣ በልጅና በእናት፣ ደርሷል ቆሞ መሞት፣ ቀኑ ወር ተክቷል፣ ወራት ብዙ ዓመታት፣ ሳታየኝ ሳላያት። አዎን! አለች አለሁ፣ አለን እንላለን፣ በስጋ ቆመናል፣ ነገር ግን ውሸት ነው፣ የለሁም የለችም፣ መለየት ገድሎናል። እንዴት ነው፣ ያለችው?፣ እንዴት ነው፣ ያለሁት? እሷ ልጄ እንዳለች፣ እኔ እናቴ እንዳልኳት፣ ተስፋችን ሞቶብን፣ ላታየኝ ላላያት፣ ቆመናል አልልም፣ የለሁም የለችም፣ እናቴ የእኔ እናት... … [Read more...] about እናቴ የእኔ እናት…
መርገምተ ወያኔ
“በረከተ መርገም” የሚያስፈልግ ቃሉ፣ ዛሬ ነው ተራገም ባለቅኔው ኃይሉ። ቅኔህን አፍሰው እንደድሮ እንደጥንት፣ ላሁን ዘመን ገዢ ያስፈልጋል መርገምት። አንተ በርግማንህ የጠበጠብካቸው እነዛ ሊቃውንት በፍልስፍናቸው ተወቃሽ በመሆን ቢያተርፉም ክፉ ስም ለውጥ አስገኝተዋል ላለንባት ዓለም ነገር ግን ያሁኑ ለስልጣን ለሀብቱ፣ ለስጋ ቁመናው ለሰፊው ቀፈቱ፣ አስሮ ሲያንገላታ ቆይቷል ሲገድል፣ አፍስበት በሱም ከርግማንህ ጠበል፣ ድሮ በሊቆቹ እርግማን ከጨረስክ፣ ምን ይሰራል ብለህ ወይም መርገም ከተውክ፣ እንዳሻህ በልና ፍቀድልኝ፣ ለኔ የርግማን በረከት አለኝ በወያኔ ካስፈለገም አምጣ ድርሻህን መዋጮ፣ የእኔን ግን ልጀምር ከወያኔው ቁንጮ ከኢትዮጵያ ምድር ከአብራኳ ወጥተህ፣ አንባሻዋን ገምጠህ ወተቷን ጠጥተህ፣ ፊደል ቆጥረህባት በሜዳዋ ሮጠህ፣ በፍቅር በደስታ … [Read more...] about መርገምተ ወያኔ










