ምዕራባዊያኑ በኛ ላይ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው? በእርግጥም ጽሑፉን ካነበባቹህ በኋላ እንደኔ ሁሉ እናንተም “ምዕራባዊያኑ በእኛ ላይ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው?” እንደምትሉ አልጠራጠርም፡፡ ይሄንን እንድል ያስገደደኝ ጉዳይ አንድ ህክምና ላይ አተኩሮ ጽሑፎችን የሚያትም መካነድር ላይ አንድ ይዝ (ሊንክ) ተጠቁሞ አገኘሁና ከፈትኩት ከዚያ እላቹህ ፈጽሞ ያላሰብኩትና ያልጠበኩት እጅግ ደግሞ የገረመኝን ነገር አገኘሁ፡፡ ምዕራባዊያኑን ስናውቃቸው ብዙ ነገሮችን እያወሩ የሴት ልጅ ግርዛትን ከእኛና እኛን ከመሰሉ ሀገራት ሁሉ “ጎጂ ባሕል” በማሰኘት ለማስቀረት ምንያህል እንደደከሙና እያስቀሩትም እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ይሄንን አየሁት ያልኳቹህን ይዝ (ሊንክ) ካየሁት በኋላ ግን እነዚህ ሰዎች ወይ ስለኛ ግርዛት ምንም በማያውቁት ነገር ላይ ነው የሚዘባርቁት ወይ ደግሞ ከሚሉን ነገር … [Read more...] about የምዕራባዊያን የሕክምና ማዕከላት የሴት ልጅ ግርዛትን ተቀበሉ በስፋትም እየፈጸሙ ነው!
Opinions
የኔ ሃሳብ
በክብር ሲጠበቁ የነበሩት በረከት ለዳግም ህክምና ሳውዲ አረቢያ ሾልከው ገቡ
በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ስሞኑን ህመሙ ጠንቶባቸው ከሁለት ወር በፊት በሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕልና ተጭነው በድብቅ ለህክምና ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የሚገኝ አንድ «ቡግሻን» እየተባለ የሚጠራ ሪፈራል ሆስፒታል የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና ቢደረግላቸውም የባለስልጣኑ የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ ባለማሳየቱ ለዳግም ህክምና ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ከሳምታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬም የአቶ በረከት ጤንነት መልካም ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ምንጮች የሆስፒታሉን የምርመራ ውጤት አብነት ጠቅሰው ይናገራሉ። አቶ በረከት በጤንነታቸው መታወክ ፍጹም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚገልጹት እነዚህ ውስጥ አዋቂዎች ቀደም ሲል ባለስልጣኑ ህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት ወደ ሳውዲ … [Read more...] about በክብር ሲጠበቁ የነበሩት በረከት ለዳግም ህክምና ሳውዲ አረቢያ ሾልከው ገቡ
Is Ethiopia’s Sovereign Debt Sustainable?
Determining the sustainability of a developing country’s public debt is a challenge. This is because most developing countries in general and Sub Saharan Africa (SSA) countries in particular face an undiversified export base, a large share of agriculture in GDP (which itself is characterized by low yields) with large share of labor force in the primary sector, and complex governance and instability problems. Debt management becomes even more complex if the countries in question have persistent … [Read more...] about Is Ethiopia’s Sovereign Debt Sustainable?
The Ethiopians and their recent history
We all repeat by rot that our country is three thousand years old. It has always been like that ever since I remember. Not a single year more or one day less. I doubt anyone knows the details but we all seem to be happy repeating that mantra. I am not going to argue nor go on a fishing expedition to prove it right or wrong. To tell you the truth I am very comfortable with that aspect of our history. We are poor, when it comes to technology we are very backward, we still experience real famine … [Read more...] about The Ethiopians and their recent history
ምጽዓት
"በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በበእኔ ታምነሃልና ይላል እግዚአብሔር፡፡" ትንቢተ ኤርምያስ 39/15-18 ኑዛዜ ኤርምያስን አነበብሁ፤ጉድ ነው! አንድ የማውቀውን ነገር አረጋግጥሁ፤ ብዙ የማላውቃቸው ነገሮችን አወቅሁ፤ የማውቀው ነገር ሂሳብ የተማረ ሰው ምን ጊዜም ጭፍን ሎሌ መሆን የማይችል መሆኑን ነው፤ ሂሳብ የተማረውን ሰው ለጭፍን ሎሌነት የሚቀጥረው … [Read more...] about ምጽዓት
ከምርጫ ’97 “የተማረው” ኢህአዴግና የሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ከሰሞኑ ለመነሻ ያህል የቀረበ ነው በሚል ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ለፓርቲዎቹ ለማስተዋወቅ ሞክሮ ነበር፡፡ ይህን የጊዜ ሰሌዳና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ከፓርቲዎቹ ጋር ለመምከር በሶስት ዋና ዋና ከተሞች (አዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሀዋሳ) ፓርቲዎቹን ከፋፍሎ ለውይይት ጠርቶ የነበረ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ ፓርቲዎች መድረኩን ጥለው መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ፓርቲዎቹ የምርጫ ጊዜውን በተመለከተ ከመነጋገራችን በፊት በርካታ ልንነጋገርባቸውና ሊስተካከሉ የሚገቡና በደብዳቤ ለምርጫ ቦርድ የገለጽናቸው ጉዳዮች ስላለሉ ለእነዚያ ጉዳዮች ቅድሚያ መሰጠት ይገባዋል ከሚል መነሻ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ቦርዱ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ እንዳለ የቀጠለ ቢሆንም፡፡ ያም ሆነ ይህ ምርጫ ቦርድ ለውይይት ያቀረበው ረቂቅ የምርጫ ጊዜ … [Read more...] about ከምርጫ ’97 “የተማረው” ኢህአዴግና የሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ
“አርማጌዶን” የፍጻሜያችን ፍጻሜ!
በዚያው ሰሞን ነው የወያኔ ባለሥልጣናት ሲያሾፉብን “ይሄንን ሁሉ ሰይጣናዊ ድርጊት የሚፈጽሙት በዓላማ እነሱ መሆናቸው ተረስቶ” ከመሀከላቸው አንዱ ምን አለ “የሕወሀት መሪዎች በዚህ ወቅት በብሔሮች መካከል ያለው የጥላቻ መንፈስና የወደፊት የሀገሪቱ ሁኔታ እጅግ አሳስቧቸዋል በጣምም እየተጨነቁበት ያሉበት ጉዳይ ነው የብሔራዊ እርቅ ጉዳይ አስፈላጊነቱ የግድ እንደሆነ ያስባሉ እንዴትና ከማን ጋራ እንደሚጨርሱት ተቸግረው ነው እንጅ….” ብሎ ቀለደብን፡፡ ከእኛም ወገን ደግሞ ጅሎቹ የዋሀኑ ተላሎቹ እውነት መስሏቸው በየፊናቸው አንዳንድ ነገሮችን እስከማለት ደረሱ፡፡ ወያኔ ግን ወያኔ ነውና ንጹሕ መስለው አሳሰበን ካሉ በኋላም እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም በዓላማ ይሄንን ሰይጣናዊ የዘርና የሃይማኖት ግጭት ፍጅት ለመፍጠር ሴራውንና ድርጉቱን እየፈጸመ ይገኛል ተፈጥሯዊ ባሕርይው ነውና እስካለ ጊዜ … [Read more...] about “አርማጌዶን” የፍጻሜያችን ፍጻሜ!
የጅዳው ት/ቤታችን እንደ አረቡ አብዮት ከድጡ ወደ ማጡ!
የጅዳ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት በተወሳሰበ የአሰራር፣ አመራር ሂደት ውስጥ በማለፍም ቢሆን የመማር ማስተማር ሒደቱን ከጀመረ ሁለት ወር ደፍኗል። በሁለት ወራት ልጆቻችን ተምረው ተመለሱ ብሎ ለጠየቀ ምላሹ ቆሽት ያሳርራል። በእስካሁኑ የትምህርት ቅበላ ባለው ከስድስት ያላነሰ ክፍለ ጊዜ የሚማሩት ከሁለትና ሶስት ክፍለ ጊዜ ሲሆን አልፎ አልፎ አራት ክፍለ ጊዜ ብቻ ተምረው ይመለሳሉ። ይህን እውነታ ልጆቹን እንደማዋያ ጥሎ ዘወር የሚለው ባይተዋር ወላጅ ከልጆቹ ይሰማዋል። የልጆቹን ደብተር አገላብጦ የሚመለከት የእኔ ቢጤ ብስጩ አባት ደግሞ ከልጆቹ ከመስማት አልፎ በማስረጃ ደብተሩን ሲያገላብጥ የሚታዘበው እውነታ ነው። በአንዳንድ ክፍሎች ዘመናዊውን ትምህርት ትምህርት የሚያሰኙት የእንግሊዝኛና የሒሳብን ጨምሮ ከፍ ሲል የኬሚስትሪ፣ የፊዚክስ፣ የባዮሎጂና የኮምፒውተር ትምህርቶች … [Read more...] about የጅዳው ት/ቤታችን እንደ አረቡ አብዮት ከድጡ ወደ ማጡ!
The honorable Ato Gebru Asrat and his politics
The honorable Ato Gebru Asrat has written a very fat book that is five hundred pages long. I am assuming that the purpose of the book was to present himself as a person of vision and to show us his leadership ability and a map of the road to the future. Unfortunately, he has a handicap that cannot be glossed over since for many years he has operated as member of that infamous organization TPLF (ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) that is still creating havoc in the life of our people and our country. It is a … [Read more...] about The honorable Ato Gebru Asrat and his politics
ሥነ-ኪን ወይስ ኪነ-ጥበብ?
ብዙውን ጊዜ ሥነ-ኪን ወይም የጥበብ ሥራ፣ ነገረ-ጥበብ ማለት እንፈልግና ኪነ-ጥበብ የሚለውን ቃልና ሥነ-ጥበብ የሚለውን ቃል እያጣረስን ስንጠቀም እንስተዋላለን፡፡ ኪነ-ጥበብ ወይም ኪነ-ጥበባት የሚለው ቃል ራሱ ግራ የተጋባ ቃል ነው፡፡ ልንጠቀምበት ፈልገን በምንጠቀምበት ቦታ ሁሉ ሰዋስዉ የተሳሳተ (Grammatically wrong) በሆነ መንገድ ነው፡፡ ቃሉ የግዕዝ ቃል ቢሆንም እነኝህን ሁለት ቃላት ማጣመር ግን የሰዋስው ስሕተትን ይፈጥራል፡፡ ምክንያቱም ኪን የሚለው ቃል ትርጉም ራሱ ጥበብ ማለት ነውና፡፡ ስለዚህም ኪነ-ጥበባት ስንል ጥበበ ጥበባት ማለታችን ነው ማለት ነው፡፡ ይሄም ማለት የጥበቦች ጥበብ ወይም ከጥበቦች ሁሉ የበላይ ጥበብ የሚል ትርጉምን ይሰጣል እንጅ አጠቃላይ የጥበብ ሥራ ዘርፍ ማለት አይደለም፡፡ ንጉሠ ነገሥታት ማለት የነገሥታት ንጉሥ ማለት እንደ ሆነ ሁሉ ማለት … [Read more...] about ሥነ-ኪን ወይስ ኪነ-ጥበብ?










