የሚከተለው ውጤት ድህረ ገፆች ላይ ከወጡት ፅሁፎቼ ሊንክ በማድረግ በዚህ ድህረ ገፅ ላይ የተሰበሰበ የዳሰሳ ጥናት ነው። ጥናቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ቢሆንም ለመንደርደሪያ ጥናትና አሳብ ሊረዳ ይችል ይሆናል ብዬ አስባለው። ይህ ማለት ስለ እርቅና መግባባት ውስብስብ ጥያቄ እልባት ለማግኘት አይደለም። ያ በእኔ አይሞከርም ከአቅሜ በላይ ነውና። ዓላማዬ ስለ እርቅ ቅድመ ሁኔታዎች መንደርደሪያ አሳብ ለመሰብሰብ በማሰብ ነው። እነሆ ድምፅ የሰጡትን ሰዎች አሳቦች አጠርና ጠቅለል አድርጌ ከዚህ በታች በጥሬው አቅርቤያለው። የራሴን ትንታኔ ትቸዋለሁ። ያንን ለአንባቢው እተዋለሁ። በዚህ ዳሰሳ ጥናት ላይ የተሳተፉትን ከልብ አመሰግናለው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ። ፍቅርም ይስጠን። Q1: Which generation are you? የትኛው ትውልድ ነዎት? 77.5% I am 30 years old or … [Read more...] about የእርቅና መግባባት ዳሰሳ ጥናት ውጤት
Opinions
የኔ ሃሳብ
ለወገን ችግር ደራሹ ወገን ነው!
ባለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል የቱን ያህል የከበደ እንደሆነ የሚያውቀው የግፉ እና የመከራው ተሸካሚ የሆነው ዐማራው መሆኑኑን ማንም አይስተውም። ያም ሆኖ ግን፣ ሰብአዊነት የሚሰማው ማናቸውም ሰው፣ በሰዎች ላይ የሚፈጸምን ግፍ እና በደል በራሱ ላይ እንደተፈጸመ በመቁጠር፣ ድርጊቱን ለማስቆም የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል። ለተራቡት የርሃብ ማስታገሻ ያጎርሳል፤ ለታረዙት የእርቃን መሸፈኛ ከፈን ይለግሣል፤ ለተጠሙት የውኃ ጠብታ ያስጎነጫል፤ አልፎ ተርፎም ግፍ ፈጻሚዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል። በዓለም ዙሪያ በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በወገኖቹ ላይ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የሚፈጽመውን ግፍ ለዓለም ኅብረተሰብ ከማጋለጥ በተጨማሪ ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ ላጡ ወገኖቹ የሚችለውን ያህል እጁን ከመዘርጋት … [Read more...] about ለወገን ችግር ደራሹ ወገን ነው!
በግልጽ እንነጋገር
በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ የፖለቲካ ሁኔታ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ የለም። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም አንድ ስምምነት ላይ ነን። በአንድነት ያልተገኘንበት፤ ምን ይደረግ? በሚለው መፍትሔ መሥጠቱ ላይ ነው። መፍትሔ ደግሞ ከመቅረቡ በፊት፤ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አልፎ፤ በግንዛቤያችን ደረጃ ያለንበትን መመርመሩ ግዴታ ይሆናል። እንግዲህ የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛ ይኼው የግንዛቤያችን ጉዳይ ነው። በትግሉ ዙሪያ፤ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ ግለሰቦች ሞልተናል። እያንዳንዳችን የምንፈልገውን እናውቃለን። የሚያስማማን ደግሞ እያንዳንዳችን ከምንፈልገው መካከል ያለው የጋራ ፍላጎታችን ነው። ይህ የየግል ፍላጎታችን በሀገር ደረጃ ሲቀመጥና የጋራ የሆኑት ከመካከሉ ተጎልጉለው ሲወጡ፤ ሀገራዊ መታገያ ዕሴቶቻችን ነጥረው ብቅ ይላሉ። በዚህ ጽሑፍ፤ የሀገራችን፣ የትግላችን፣ የምሁራን ሚናና … [Read more...] about በግልጽ እንነጋገር
Obang addresses Civil Society Policy Forum at the IMF and World Bank meeting
Address by Obang Metho, Executive Director of the SMNE, to the Civil Society Policy Forum at 2014 Annual Meetings of the International Monetary Fund (IMF) and the World Bank Group (WBG), Washington, DC Thank you for inviting me to share in this panel discussion on “The Role of World Bank Indicators in Agricultural Development.” Today’s discussion is very relevant in that the World Bank is investing billions of dollars into agribusiness. Various new tools have been designed to measure and … [Read more...] about Obang addresses Civil Society Policy Forum at the IMF and World Bank meeting
“መጪው ምርጫ ይቅርብን”
ጥላ መጽሔት 11ኛ ዕትም “መጪው ምርጫ ይቅርብን” በሚል ርዕስ እና ከዚህ በታች ያሉትን ጦማሮችና ሌሎችን አካትታ ወጥታለች፡፡ ከቢን ላደን ግድያ በስተጀርባ ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች በስደትም አንደኛ? የወያኔ ፍትሃዊ ምርጫ! መሬት ቆርሶ ... የአገር ስሜት ሳይኖረው ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ የመጽሔቷን የሽፋን ገጽ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about “መጪው ምርጫ ይቅርብን”
ዘዳግም!
የደመራ ዋና ዓላማ፤ “ሲቃወምና ሲጻረር የነበረውን የዕዳ ጽህፈት ክርስቶስ ከነ ሕግጋቱ በመደምሰስ በመሰቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው” (ቆላ ፪፡፲፬)። ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው፤ የተደበቀውን እውነት ለመግለጥ፤ በሰው ላይ ተጭኖ የነበረውን ዕዳ ለመደምሰስ፤ ለሰባዊ ክብርና ልዕልና ተጻራሪ የሆነቱን ነገሮች ለማስወገድ ነው። [በሰፊው መረዳት ከፈለጉ ይህን ሰንሰለት ይጫኑ። ደመራ] ሙሴ አራቱን የኦሪት መጻሕፍት ከጻፈ በኋላ፤ በአራቱም መጻሕት የገለጻቸውን ጠቅለል አድርጎ በድጋሚ ያቀረበበት አምስተኛው መጽሐፍ ዘዳግም ይባላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሰባዊ ክብርና ልዕልና ተጻራሪ የሆነውን ለማስወገድ የገለጸባቸውን ኃይለ ቃላት ለማስጨበት “አማን አማን እብለክሙ” እያለ በመደጋጋም ተናግሯል። በጸሎተ ቅዳሴያችንም “ተንስኡ ለጸሎት” የሚለውን እንደጋግማለን። ቃጭልም … [Read more...] about ዘዳግም!
የኢትዮጵያ (የክርስቶስ) ቤተክርስቲያን የጣር ድምፅ!
ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳቹህ እጽፍላቹህ ዘንድ ግድ ሆነብኝ ይሁ. 1፤3 በዚህ ጽሑፍ ላይ ጥንታዊቷና ሀገር በቀሏ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ ከምእመናኗ ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ ማሽቆልቆል መንስኤውንና ተጓዳኝ ነገሮችን እናያለን፡፡ ይሄንን እንድናይ ግድ የሚልበትም ምክንያት ይህ አደጋ ኢትዮጵያዊ የሆነውን ማንነትና እሴት ለማጥፋት በተለያየ መንገድ ሲጥሩ የኖሩ ባዕዳን ጥረታቸው ሠምሮላቸው አሁን ላይ ኢትዮጵያዊነት በዜጎች ዘንድ ዋጋ እያጣና እየጠፋ ከመሄዱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላለውና የሚነቃ ካለ ለማንቃት በማሰብ ነው፡፡ ስለ እውነት ለመናገር ከማንነት አንጻር ካየነው ለመረዳት ያለን አናሳ የታሪክ እውቀታችን ካልገታን በስተቀር ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ላይ በየትኛውም የእምነት ድርጅት ውስጥ ያለ ዜጋ ሁሉ ትናንትና የኢትዮጵያ … [Read more...] about የኢትዮጵያ (የክርስቶስ) ቤተክርስቲያን የጣር ድምፅ!
መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ከአዘጋጆቹ፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው “ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?” በሚል ርዕስ ለጻፉት ሥርዓት ጠብቆ ምላሽ የሚሰጡ ተቀብለን እናትማለን ባልነው መሠረት ኢብኑ ሙነወር “መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው” በሚል ርዕስ ጨዋነት በተሞላበት አጻጻፍ የላኩልንን ምላሽ ከዚህ በታች አትመናል፤ ምስጋናችንንም እናቀርብላቸዋለን፡፡ ሌላ አዲስ አጀንዳ እስካልመጣ ድረስ በዚሁ ይህንን ውይይት የቋጨን በመሆኑ ምላሽ ጽሁፎችን የማንቀበል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ ጉዳዩን መቀጠል የሚፈልጉ ከጸሐፊዎቹ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋውና ኢብኑ ሙነወር ጋር በኢሜይል ወይም በፌስቡክ ወይም በሌላ በሚያመቻቸው መንገድ በመገናኘት ሃሳባቸውን መላክ ይችላሉ፡፡ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መንግስት ለአመራሮቹ በሰጠው ስልጠና ላይ … [Read more...] about መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
“አሸባሪ ብዕሮች”
የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር "ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።" ነበር ያለው። አንባገነኖች ፕሬስን ይፈራሉ። ይጠላሉም። የህዝብ መሰረት የሌላቸው፤ በራሳቸው የማይተማመኑ ሁሉ ነጻ ሃሳብን ይጠላሉ። ነፍጥን ብቻ ተማምነው በሕዝብ ጫንቃ ላይ የሚቀመጡ፤ እንደምን ነጻ አመለካከትን ሊቀበሉ ይችላሉ? ፍጹም አንባገነናዊነት በሰፈነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች፤ ህግ አውጭው ህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ የለም። ይህንን ቁጥጥር በጥቂቱም ቢሆን ተክቶ ይሰራ የነበረው ነጻው ፕሬስ ነው። ከዚህም አልፎ ሕዝቡ መብቱን እንዲያውቅና መብቱንም እንዲያስከብር ብዙ ሰርቷል-ፕሬሱ። ሙስናን አጋልጧል፣ እንደ እንባ … [Read more...] about “አሸባሪ ብዕሮች”
ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?
ከአዘጋጆቹ ማሳሰቢያ፤ በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈረው ሃሳብ በከፊል ወይም በሙሉ የጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣን አቋም የሚገልጽ አይደለም፡፡ እንደ ሚዲያ የማንንም ሃይማኖት በመንቀፍም ሆነ በመደገፍ አቋም አንይዝም፡፡ በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈረው ሃሳብ በሙሉ የጸሃፊው ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ነው፡፡ ጽሁፉን አስመልክቶ በጨዋነት ማስረጃዎችን በመጥቀስ ለመመለስ ለሚፈልጉ ሁሉ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል፡፡ አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኘው አገዛዝ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ከነሐሴ 18 እስከ መስከረም 16 ድረስ 800 ለሚሆኑ የመካከለኛ አመራሮቹ የፖሊሲና ስትራቴጂ ሥልጠና በሚሰጥበት ወቅት የእስላም ሴቶች በትምህርት ተቋማትና መንግሥታዊ በሥሪያ ቤቶች ሂጃብና ኒቃባቸውን እንዲያወልቁ ሲጠየቁ “እኛ እንድናወልቅ የምንገደድ ከሆነ ክርስቲያኑም ማተቡን … [Read more...] about ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?










