• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በክብር ሲጠበቁ የነበሩት በረከት ለዳግም ህክምና ሳውዲ አረቢያ ሾልከው ገቡ

October 31, 2014 11:54 pm by Editor Leave a Comment

በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ስሞኑን ህመሙ ጠንቶባቸው ከሁለት ወር በፊት በሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕልና ተጭነው በድብቅ ለህክምና ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የሚገኝ አንድ «ቡግሻን» እየተባለ የሚጠራ ሪፈራል ሆስፒታል የልብ ቧንቧ ማስፋት  ህክምና ቢደረግላቸውም የባለስልጣኑ የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ ባለማሳየቱ ለዳግም ህክምና ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ከሳምታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በዚህ እንዳለ  ዛሬም የአቶ በረከት ጤንነት መልካም ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ምንጮች የሆስፒታሉን የምርመራ ውጤት አብነት ጠቅሰው ይናገራሉ። አቶ  በረከት በጤንነታቸው መታወክ ፍጹም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚገልጹት እነዚህ ውስጥ አዋቂዎች  ቀደም ሲል ባለስልጣኑ ህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት ወደ ሳውዲ አረቢያ በሚስጥር ለህክምና መግባታቸውን ተከትሎ በተለያዩ ድህረገጾች ዜናው በስፋት መናፈሱ  በውስጣቸው በተፈጠረው አለመረጋጋት በልባቸው ምት አለመስተካከል በወቅቱ በቂ  ህክምና መውሰድ እናዳልቻሉ ታውቋል። የአቶ በረከት የጤነንት ሁኔታ ዛሬም አስተማማኝ እንዳልሆነ የሚያውሱ እነዚህ የአይን እማኞች  ከእለት ተዕለት የባለስልጣኑ የአካል መጠን  በማይጠበቅ ሁኔታ መቀነስ እና የፊታቸው ገጽታ መለዋወጥ  በውስጣቸው መልካም ነገር እንደማይታይ ያሳብቃል ብለዋል።

የአቶ በረከት ስሞኦን  ህይወት ለመታደግ የአቅማቸውን ያህል ጥረት እያደረጉ የሚገኙ «ቡግሻን» የሳውዲ አረቢያ ሆስፒታል ዶክተሮች ስለበሽታው አደገኝነት ግንዘቤ በማስጨበጥ አቶ በረከት ከተለያዩ መጠጦች እና አእምሮ አደንዛዥ እጾች መራቅ እንዳለባቸው እና የጤነንታቸው ሁኔታ አስተማማኝ ሁኔታ እስኪደርስ እረፍት መውሰድ እንደሚገባቸው ሙያዊ ምክሮቻቸውን ለገሰዋቸዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ አቶ በረከት ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲያቀኑ የህክምና ውጪያቸውን እየሸፈኑ ከሚገኙት  ሼክ አላሙዲን ባሻገር ለኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት ሚስጥር መሆኑ አያሌ ወገኖችን በስፋት እያነጋገር ነው። ከሁለት ወር በፊት አቶ በረከት እኩለ ለሊት  ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ ሳውዲ አረቢያ በሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕላን በድብቅ ለህክምና መግባታቸው ለኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወሬው የደረሰው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ  በዘ-ሃበሻ  እና ጎልጉል ድህረገጾች  በተለቅቁ መረጃዎች መሆኑን የሚናገሩ ምንጩች ለሁለተኛ ጊዜ ዳግም ህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲመለሱ በሼክ አልሙዲን በኩል በክብር «በፕሮቶኮል» ሊገቡ እንደሚችል በወቅቱ ከጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት  የወጡ መረጃዎች ቢያረጋግጡም የአቶ በረከት ስሞኦን እንደተለመደው በድብቅ  ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባት  ባለስለስልጣኑ በውስጥም በውጨም ጥሩ ወዳጅ እንደሌላቸው የሚነገረውን ሃቅ ያጠናክረዋል ብለዋል።

አቶ በረከት ትላንት በተደረገላቸው ምርመራ የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው የሚገልጹ የሆስፒታል መረጃዎች  ባለስልጣኑ የተሰጣቸውን ምክር እና የተለያዩ መድሃኒቶቻቸውን ይዘው ከሆስፒታሉ ውጭ ወደሚገኘው ምስጢራዊ ማረፊያቸው ማቅናታቸው ተገልጾዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና መስረት አቶ በረከት ስሞኦን ዛሬ ማምሻውን ለአስቸኳይ ጉዳይ ህክምናቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመልሱ ምስጢራዊ መረጃዎቻችን አክለው አረጋግጠዋል። Ethiopian Hagere Jed Bewadi

(Ethiopian Hagere ዜናውን የላኩልን በOct 31፣ 2014 ነበር በሥራ መጣበብ ሳናቀርበው በመዘግየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ይህንን ዜና ከዚህ አንጻር አንባቢያን እንዲያነቡት ለማሳሰብ እንወዳለን)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule