ለረጅም አመታተ የጣልኩትን ብዕር ድር ካደራበት ሰገባው እንድመዝ አስገደደኝ - በ ኢትዮ-ሚዲያ (Ethiomedia) እና በጎልጉል (Googlgule) ድህረ-ገፆች ላይ ከወራት በፊት በዶክተር ፍቃዱ በቀለ በተባሉ ግለሰብ በ"የተቆለፈበት ቁልፍ" መፅሐፉ ላይ የቀረበ አንድ ፅሑፍ። "ሃያሲው" በዘመናችን አቻ ያላገኙለት (ወደር የሌለው) መፅሐፉ መሆኑን ነው የገለፁልን። "...የስነ-ጽሁፍም ዋና ዓላማው በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን አስቀያሚም ሆነ ቆንጆ ነገሮች ስዕላዊ በሆነ መልክ መግለጽ ሲችሉና አንባቢውን በልዩ ሃሳብ ውስጥ ተመስጦ እንዲዋኝ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው።..." በማለት ካብራሩ በኃላ ከ`ዚህ አንፃር "የተቆለፈበት ቁልፍ" እንደተዋጣለት መሰክርነታችውን ይሰጣሉ። አንዲህ ሲሉ "....በታሪካችን ውስጥ በመጀመሪያ ጊዜ በልዩ አቀራረብ የተዘጋጀና የተጻፈ ትምህርታዊ መጽሀፍ ነው … [Read more...] about “የተቆለፈበት ቁልፍ” በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል!
Opinions
የኔ ሃሳብ
የኢትዮጵያ ወዳጅ ጆን ቤጀንት ዜና-ዕረፍት፣ የሃዘን መግለጫ
የኢትዮጵያ ወዳጅና የአፍሪካ ቀንድ አጋሮች [Partners in the Horn of Africa] የካናዳ ተራድኦ ድርጅት መስራች፤ በካናዳ የብሔራዊ መብቶችና ነፃነት ዋስትና ቻርተር በብሔራዊ ምክር ቤት እንዲፀድቅ አስተዋፅዖ ከተሳተፉት ጠበቃዎች አንዱ የነበረው ካናዳዊዩ ዮሐንስ ቤጄንት [John Baigent] ባደረባቸው ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ቤተሰባቸው፣ Partners in the Horn of Africaና በመላው ኢትዮጵያና ካናዳ የሚገኙ ወዳጆቻቸው ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቷቸዋል። ጠበቃ John Baigent ከአስራ ስድስት ዓመታት በፊት የመሰረቱት የግብረሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ በርካታ ሥራዎችን ሰርተዋል። የአፍሪካ ቀንድ አጋሮች ግብረሰናይ ድርጅትን ከሌሎች የዕርዳታ ድርጅቶች የተለየ የሚያደርገው ሁለት ዋና ዋና ቁም ነገሮች ይገኙበታል። እነርሱም:- 100% … [Read more...] about የኢትዮጵያ ወዳጅ ጆን ቤጀንት ዜና-ዕረፍት፣ የሃዘን መግለጫ
በነገራችን ላይ “ውይይቱ” የት ደረሰ?
የሙስናውን የመረጃ እጦት ኩምክና ሰምተን ስቀን ሳንጨርስ ሰሞኑን ደግሞ የውይይት ፉገራ አመጡ። ልክ እንደቀበሌ ስብሰባ ተቃዋሚዎችን በአዳራሽ ውስጥ አጉረው ሲያበቁ እነሱ ከመድረክ ሆነው ይቀልዱባቸዋል። የNBC ውን፤ የዴቭድ ሌተርማን ‘ሌት ናይት ሾው” (late night show) የሚመስል ነገር በቴሌቭዥን ለቀውብን ነበር። ሁለቱ ባለስልጣኖች፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ መድረክ ላይ ጉብ በለዋል። በአነስተኛና በጥቃቅን የተደራጁ 21 የፓርቲ መሪዎች ደግሞ እንደ ቲያትር ተመልካች አዳራሹ ውስጥ ተሰይመዋል። እነዚያ ከላይ፣ እነዚህ ከታች ተቀምጠዋል። እነዚያ ይናገራሉ፣ እነዚህ ደግሞ ይሰማሉ።… ሌላ ምን አማራጭ ሊኖራቸው? ውይይት ብለውታል። ሌላው አይደለም። አቀማመጣቸው ብቻ የውይይቱን አቅም እና ያይል ያሳብቃል። በሙስናው የመረጃ እጦትት ኩምክና ስቀን ሳናበቃ … [Read more...] about በነገራችን ላይ “ውይይቱ” የት ደረሰ?
EALING AMNESTY GROUP DEMANDS THE RELEASE OF ESKINDER NEGA
The Ealing Amnesty Group has recently declared that it has adopted Eskinder Nega as a focus for campaigning in 2017. This must be highly appreciated by the freedom and peace-loving citizens of the world. We hope other Groups also adopt other journalists, such as Journalist Temesgen Desalegn, whose health is currently seriously damaged in captivity in Zeway Prison. On 27 Friday 2017, Ealing Amnesty Group held a successful vigil in front of 17th Princess Gate, London, from where the diplomatic … [Read more...] about EALING AMNESTY GROUP DEMANDS THE RELEASE OF ESKINDER NEGA
80ኛ የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀን መታሰቢያ
የካቲት 12 ቀን 1929 አ/ም በአዲስአበባ 30,000 ኢትዮጵያውያን በግፍ ተገድለዋል በኢትዮጵያ የሚፈለገው ፍትህ ቫቲካን ፋሽስት ኢጣልያን ደግፋ ስለነበር የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ የተባበሩት መንግሥታትድርጅት በኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን ግፍ እንዲመዘግብ የኢጣልያ መንግስት ለኢትዮጵያ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል በቫቲካንና በኢጣልያ መንግሥት የተዘረፉ ንብረቶች ለኢትዮጵያ እንዲመለሱ በኢጣልያ በአፊሌ የተሠራው የጦር ወንጀለኛው የግራዚያኒ መታሰቢያ እንዲወገድ 80th Feb 19 Martyrs memorial Let us remember our Ethiopian martyrs massacred by Italian Fascists and demand justice Italian Fascists massacred over one million Ethiopians … [Read more...] about 80ኛ የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀን መታሰቢያ
ፎረም 65፦ ዕርቀ ሰላም በኢትዮጵያ
ዕርቅ ምንድን ነው? በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዕርቀ ሰላም ላይ የሚመክርና የመፍትሔ ሃሳብ የሚያመነጭ ውይይት አድርጓል። ፎረም 65 በጉባኤው ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ተወያይቷል። ያድምጡት! * ለመጪው ትውልድ መግባባትን እናውርስ። * Dhaloota Dhufuuf Wal-ta'insa, Haa Dhaalchifnuu. * ንመፃኢ ወለዶ ምርድዳእ ነውርስ። ፎረም 65 (info@65percent.org) … [Read more...] about ፎረም 65፦ ዕርቀ ሰላም በኢትዮጵያ
ከጥልቅ ተሃድሶው ማግስት ዘመቻ ዘ-ፀዓት
ለወትሮው ከገዢው ፓርቲ አካባቢ የተለመደው የተሃድሶ ትርጉምለየትያለ ነበር። “ኢህአዴግ” ስብሰባዎችን ያደርግና ሲጨርስ “የተሃድሶ ሰኣት!” ይባልና በዚያን ጊዜ የማእድ አገልግሎትና የተለያዩ መጠጦች የኪነት ትርኢት የሚቀርብበት ሰኣት ተሃድሶ ይባላል። ለአንድ የገዠው ፓርቲአባል ተሃድሶ ሲባል ቶሎ ወደ ህሊናው የሚመጣው ነገር ድግስ ይመስላል። ከስብሰባ በኋላ ዘና ማለት። ይሁን እንጂ በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጥልቀት በመታደስ ላይ ነን ሲሉ የገለፁ ሲሆን ይህ ተሃድሶ በአእምሮ መታደስን-መለወጥን የሚያሳይ እንደሆነ ተገልፃልናል። ይሁን ይሏል። መቼስ የተሃድሶ ትርጉም ከድግስ አልፎ እውነተኛ ትርጉሙን ከያዘና በአእምሮ መታደስን ከጨመረ አንዳንድ ለውጥ የናፈቀው ቢጓጓ አይፈረድም ይሆናል። በመሆኑም ተሃድሶከተለመደው ትርጉም አልፎ በአእምሮ መለወጥን መታደስን ሪፎርሜሽንን ካመጣ ግሩም ነበር። … [Read more...] about ከጥልቅ ተሃድሶው ማግስት ዘመቻ ዘ-ፀዓት
ካሰቡት ግብ ለመድረስ ፣ያመኑበትን ዓላማ አንግቦ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ!
የዛሬ አራት ዓመት ዐማራ ነኝ ብሎ ደፍሮ ለመናገር ብዙ ማሰብና ማውጠንጠን ይጠይቅ ነበር። ምክንያቱም ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት በዐማራው ነገድ ላይ የተነዛው ፕሮፓጋንዳ በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ዐማራ ነኝ እንዳይሉ ገደብ የጣሉ ነበሩ። የመጀመሪያው ምክንያት ዐማራው ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን በመሆኑ፣ ራሱን ወደ ነገድ ደረጃ ማውረድ ውርደት ወይም ከኢትዮጵያዊነት የሚያፋታው አድርጎ መቁጠሩ አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ነው። ሁለተኛው በኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ የሩቅና የቅርብ፣ የውጭና የውስጥ ጠላቶች የተራገበው ኢትዮጵያን የማጥፋት የተቀነባበረ ዘመቻ ዋነኛው ዒላማ ዐማራው በመሆኑ፣ የዐማራውን ማንነት ጥላሸት የቀባ፣ መልካም ስሙንና ዝናውን ያጎደፈ፣ «በጡት ቆራጭነት፣ በወራሪነት፣ በገዥ መደብነት፣ በጨቋኝ ብሔርነት፣ በነፍጠኝነትና በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጠሩ ለተባሉ ችግሮች ሁሉ ፈጣሪ» … [Read more...] about ካሰቡት ግብ ለመድረስ ፣ያመኑበትን ዓላማ አንግቦ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ!
የማናውቀው ታሪካችን
ታሪካችንን ባለማወቃችን ሁሌም ወደኋላ በመገስገስ ላይ እንገኛለን፤ ሰሞኑን አንዳንድ ዜና መዋዕሎችን ማንበብ ጀምሬ እስካሁን አራት ያህል አንብቤአለሁ፤ ከዚህ በፊት እየተንገዳገድሁ በግዕዝ አንብቤአቸዋለሁ፤ ዛሬ የሲራክ አሳታሚ ድርጅት በአማርኛ እያሳተማቸው በመሆኑ ምስጋና ይድረሰውና ሳልንገዳገድ በአማርኛ እያነበብሁ ነው፤ በዚህ ንባቤ ውስጥ አንዳንድ ያገኘኋቸው ሀሳቦች ስለራሳችን ያለን እውቀት ምን ያህል ጎደሎ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው፤ ለዛሬው ሁለት ሀሳቦችን ከላሊበላ ዜና መዋዕል፤ አንድ ደግሞ ከሱስንዮስ መርጫለሁ፤ እኔን እንዳስደነቁኝ ሌሎችንም ያስደንቃሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ አንደኛ፤ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በ1160 ዓ.ም. የነገሠው ገብረ መስቀል የሚባለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት "በነገሠ በአሥር ዓመቱ መራ ከተባለው አጠገብ የነበረውን ቤተ መንግሥት ወደሌላ ለማዛወር አስቦ … [Read more...] about የማናውቀው ታሪካችን
የአቦይ ስብሃት ነጋ የሙስና ወጎች
በአሜሪካ ሃገር፤ አንድ ባለስልጣን በሙስና ሲባልግ እስር ቤት ይገባል። በፊሊፒንስ አንድ ባልስልጣን የሙስና ወንጀል ቢፈጽም አሜሪካ ይገባል። የኛ ሃገር ባለግዜ ግን ሙስና ሲሰራ አሜሪካ እየተመላለሰ ይነግዳል። ለግዜው ልዩነቱ የዚህን ያህል ነው። ገለልተኛ የፍትህ አካል ባለበት ሃገር፤ ሙስና አፍ አውጥቶ አይናገርም፣ እግር አውጥቶም አይራመድም። አዲሱ ቀልድ፤ "ሙስና አለ፣ ማስረጃ የለም!" በያዝነው "ጥልቅ ተሃድሶ" ዘመን ሙስና ለሁለት ተከፍሎ እንዲታይ ተደርጓል። ማስረጃ ያለው ዘረፋ እና ማስረጃ የሌለው ዘረፋ። ልክ እንደ ግብር አከፋፈል። ግብር ከፋይ "ሀ" እና ግብር ከፋይ "ለ"። ምድቡ በዘረፋው መጠን እና በባለስልጣኑ ጉልበት ይወሰናል። የዘረፋው መጠን ከአስር ሺህ በር በታች ከሆነ እና ዘራፊው የድል አጥቢያ ታጋይ ከሆነ ማስረጃ ያለው፣ ሙስና ምድብ "ሀ" ይሆናል። መጠኑ … [Read more...] about የአቦይ ስብሃት ነጋ የሙስና ወጎች










