አድዋ የኢትዮጵያ፣ አድዋ የአፍሪካ፣ አድዋ የጥቁር ህዝብ ታሪክ ነው። በዕለተ ጊዮርጊስ የካቲት ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ ስምንት ሀገር ወራሪ ጦር በምሥራቅ አፍሪካ አከርካሪው የተመታበት ዕለት። የዓለም ድሀ ሀገሮችን የናቀና ጦር መሣሪያውን የተማመነ ኃይል በጋሻ ጎራዴ የተንበረከከበት፣ የነፃነት ጮራ ከወደ ምሥራቅ አፍሪካ የፈነጠቀበት፣ ታሪካዊ የድል ቀን አድዋ። ትናገር አድዋ። ትመስክር አድዋ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ … [Read more...] about ትናገር አድዋ
Opinions
የኔ ሃሳብ
ዜግነትና የስደተኞች መብትና ግዴታ
ስደተኞች ወደኢትዮጵያ የሚልኩት ጠገራ ብር ብዙ እንደሆነ አውቃለሁ፤ አንዳንድ ስደተኞች ለእንደኔ ያለ ወገኖቻቸው በብዙ መንገድ እርዳታ እንደሚያበረክቱ አውቃለሁ፤ በአንጻሩም አንዳንድ ስደተኞች ትንሽ ጠገራ ብር ይዘው መጥተው የሀኪም ቤትና ሌላም ዓይነት የንግድ ድርጅት (ሀኪም ቤቱን ከንግድ ጋር ያገናኘሁት አውቄ ነው) እያቋቋሙ ደሀውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እየገፈፉ የሚከብሩም እንዳሉ አውቃለሁ፤ ስደተኞች በአጠቃላይ ለአገራቸውና ለወገናቸው መብት በፖሊቲካው መስክ የሚያደርጉትን ትልቅ አስተዋጽኦ አውቃለሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የሚከነክነኝ ነገር አለ፡፡ ለእኔ ዜግነት ማለት የአገር ባለቤትነት ነው፤ የአገር ባለቤትነት መብቶችንና ግዴታዎችን ያጎናጽፋል፤ አንድ ሰው ስደተኛ ሲሆን የተወለደበትን አገር ባለቤትነት ከነመብቶቹና ግዴታዎቹ በፈቃዱ ትቶ ለሌላ አገር የሚያስረክብ ይመስለኛል፤ እዚህ ላይ … [Read more...] about ዜግነትና የስደተኞች መብትና ግዴታ
የዐድዋ ድል “የታሪክ አጋጣሚ” ወይስ በዕቅድ የተከወነ?
ሰሞኑን የዐድዋ ድል መታሰቢያ 121ኛ ዐመት የሚዘከርበት ወቅት ነው። በፍቃዱ ዘ. ኀይሉ የተሰኘ ከታቢ (blogger) "Bilisummaa adda-ዋ!" በተሰኘ እና በድረ ገጽ እና በፌስ ቡክ በተሰራጨ አነጋጋሪ ጽሑፉ ስለ ዐድዋ ድል እና ስለ ምኒልክ አመራር ብዙ ቢልም በተለይ ኹለቱ ትርክቶች የሚጐረባብጡ፤ ፈራቸውን የሳቱ ኾነው ስላገኘኹዋቸው እነሱ ላይ ሀሳቤን ማካፈል ወደድኩ። ኹለቱ የበፍቃዱ ዘኀይሉ “Bilisummaa adda-ዋ!” ትርክቶች፤ 1) የዐድዋ ድል በታሪክ አጋጣሚ የተከሰተ ነው እና 2) ዐድዋ የጨቋኝ ምርጫ የተሰኙት ናቸው። ኹለተኛው ትርክት ቃል በቃል ባይኾንም የዐድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከነጭ ጨቋኝ የጥቁር ጨቋኝ መርጦ የተዋጋበት እንጂ የዐድዋ ጦርነት ሕዝቡ ለነጻነት የተዋጋበት ጦርነት አይደለም ነው። በትክክል ተረድቼው ከኾነ በፍቃዱ መነሻ ሀሳቡን ያገኘው … [Read more...] about የዐድዋ ድል “የታሪክ አጋጣሚ” ወይስ በዕቅድ የተከወነ?
ለማሳጠር መስራት፤ ስለመርዘምም ማሰብ
በፌብርዋሪ 11 እና 12, 2017 በሁለቱ ቀናት ውስጥ በአምስቱም ክፍለ ዓለማት በሚገኙ ከአርባ በላይ በሚሆኑ ከተሞች ለአርበኞች ግንቦት 7 የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ የተደረጉ በዓላዊ ዘመቻዎች መካሄዳቸውን የበረታ በየአካባቢ በተደረጉት ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ለዓይን ምስክርነት ሲበቃ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ደግሞ በሚዲያዎች የታደመው ይመስለኛል። በዝግጅቱ ላይ ከድጋፍ ማሰባሰቡ በተጓዳኝ ለአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በስካይፔ ከየአካባቢው ጥያቄዎች እየቀረቡ መልስ ሲሰጥም ስለነበር፤ በዚህ አጋጣሚ ከቀረቡት ልዩ ልዩ ጥያቀዌዎች ውስጥ አንድ ሃሳቤን የሰረቀው ጥያቄ "የትጥቅ ትግሉ በተጠበቀው ፍጥነት አልሄደም" የሚለው ነበር። ጥያቄው ማንም የባርነት ቀንበር የከበደው ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ሊያነሳው ጥያቄ እንደሆነ የሚያጠያይቅ አይመስለኝም። የመከራና የጭነቀት … [Read more...] about ለማሳጠር መስራት፤ ስለመርዘምም ማሰብ
“ዉሃ በሌለበትና ቱሃን በበዛበት ጣቢያ እያንገላቱኝ ነው”
ዳንኤል ሺበሺ ከወህኒ ያስተላለፈው መልእክት ከቤተሰቡ በተገኘው መረጃ መሰረት ዳንኤል የተወለደው በደቡብ ኢትዮጵያ ነው፡፡ ያደገው እንደአብዛኛው ኢትዮጵያዊ በለምለሟ ቁጫ ወረዳ አረንጓዴ መስክ ሮጦና ተራራና አቀበት ወጥቶ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ንቁ ነበርና ቤተሰቡ ወደ ትምህርት ቤት ሰደደው፡፡ ተማረ፡፡ እስከ ዩኒቨርስቲ በመዝለቅም ቀጠለ፡፡ ከዚያም ሳይማር ወዳስተማረው ህብረተሰብ በመመለስ ማገልገሉን ተያያዘው፡፡ ግና ትምህርት የአለማችንን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲለይ አስችሎት ነበርና በሚሰራው ስራ ብቻ ሊረካ አልቻለም፡፡ ህዝቡ ላይ የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ ፍትህ እጦት እንደሚያሰቃየው ተመለከተ፡፡ ወጣቱ ዳኒ በተደጋጋሚ እንደሚናገረው ‹‹ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና ግፍ ከንፈር በመምጠጥ ብቻ ማቆም እንደማይቻል አውቅ ነበር፡፡ እንደ አንድ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ … [Read more...] about “ዉሃ በሌለበትና ቱሃን በበዛበት ጣቢያ እያንገላቱኝ ነው”
ፕሮፌሠር ፍቅሬን ለቀቅ ቧልትህን ጠበቅ
ሰሞኑን በፕሮፌሠር ፍቅሬ ስራዎች ለማሾፍ እና የእርሳቸውን ክብር ለማውረድ በጅምላ እየተካሄደ የሚገኝ የስም ማጥፋት ስራ እየተመለከትኩኝ ነው አንዳንዶቹ ባለማወቅ እና ከብስለት ማነስ የሚያደርጉት መሆኑን ባውቅም የተወሰኑት ግን ሆን ብለው የሚፈፅሙት ተግባር መሆኑን ለማወቅ ችያለው፡፡ በፕሮፌሰሩ ላይ እየተካሄደ የሚገኘው የማንቋሸሽ ተግባር ከየት እንደመነጨ ለምን እንደሚካሄድና እነማን እንደሚፈፅሙት መመልከቱ መልካም ይመስለኛል፡፡ ፕሮፌሠር ፍቅሬ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2008 ዓ.ም ለንባብ ያበቁት የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ትክክለኛ የዘር ምንጭ የተሰኘው መፅሐፍ ለገበያ ከዋለ በኋላ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ ተፈላጊ መፅሐፍ በመሆን መነበብ የቻለ ትልቅ መፅሐፍ ነው በዚህም በኢትዮጵያ የመፅሀፍ ታሪክ ውስጥ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ በተደጋጋሚ በመታተም ታሪክ የሰራ መፅሀፍ ነው፡፡ ይህ … [Read more...] about ፕሮፌሠር ፍቅሬን ለቀቅ ቧልትህን ጠበቅ
የካቲት 66 መሪ ኮከቡን ያጣ አብዮት
(የካቲት 66 ሕዝባዊ አብዮት 43ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ) ኢትዮጵያ ሀገራችን ታዳጊ ሀገሮችን በተለይ አፍሪካን እንደ ቅርጫ የተቀራመቱት ቅኝ ገዥዎችና ወራሪዎችን ጥቃት መክታ የግዛት አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለማንም ባዕዳን ወራሪ ኃይል ሳትደፈርና ሳትገዛ የኖረች የማንነታችንና የክብራችን መግለጫ ናት። ዮሐንስ በመተማ፣ ቴዎድሮስ በመቅደላ፣ ምኒልክ በአድዋ እየተባለ የሚነገርላቸው፣ የሚጻፍላቸው፡ የሚዘፈንላቸው ነገስታቶች በሀገር አንድነትና በኢትዮጵያዊነት ማንነት ወራሪን ያሳፈሩና ዓለምን ያስደነቁ ኢትዮጵያዊነት የክብርና የአንድነት ተምሳሌትነቷን ያስፃፉና ያስተረኩ እስከዛሬም ሆነ ወደፊት ይህ ማንነታቸውን ታሪክ የሚያወሳላቸው ነገስታት ናቸው። በነዚህ ነገስታቶች የአገዛዝ ዘመን የሀገር አንድነትንና የግዛት ነፃነትን በማስከበር ደረጃ በየጊዜው ስማቸው የሚጠራ … [Read more...] about የካቲት 66 መሪ ኮከቡን ያጣ አብዮት
ወያኔ እንዲህ እያሰበ መሆኑ ጭምጭምታ ተሰማ፤ ዕውነት ከሆነ ጥቅምና ጉዳቱ ምን ይሆን?
ዛሬ ላለንበት ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ከመኖር ወደ አለመኖር ያደረሳቸውን ምክንያት መገንዘብ፣ ለምንፈልገው መፍትሔ ጥርጊያ መንገድ ይከፍትልናል። ከትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (የትግሬ-ወያኔ) የትግል ጉዞ እንደምንረዳው፣ ችግር በገጠመው ቁጥር፣ ዓላማውንና ቆሜለታለሁ የሚለውን ሥርዓት እንደ እባብ ገላ በሌላ በመተካት ጊዜ ይገዛል። ከማኦ ዜ ዱንግ እስከ ኤንቨር ሆጃ፣ ከካርል ማርክስ እስከ ሌኒን፣ ከሂትለር እስከ ደቡብ አፍሪቃ የአፓርታይድ አገዛዝ ያሉትን ርዕዮተ-ዓለሞች ካንዱ ወደ ሌላው ከብርሃን ፍጥነት በፈጠነ ሁኔታ በመቀያየር ኅልውናውን ለማራዘም ይሞክራል። የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት ያራመደው በዘር ጥላቻ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካና አገሪቱንና ሕዝቡን በነገድ ሸንሽኖ ያደረሰው ጥፋት፣ በተለይ ከ2007 እስከ 2009 ዓም ያሉት ዓመታት ሕዝቡ ሊሸከመው … [Read more...] about ወያኔ እንዲህ እያሰበ መሆኑ ጭምጭምታ ተሰማ፤ ዕውነት ከሆነ ጥቅምና ጉዳቱ ምን ይሆን?
የአርዮስ ፍሬዎች
“ለሌላ አደገኛ የጦርነት አዋጅ በወገናችን ላይ ታወጀ” በሚል ለተጻፈው መልስ ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በጎልጉል ድረገጽ ላይ እራሳቸውን ተሃድሶ ብለው በሚጠሩ ነገር ግን እውነተኛ ማንነታቸው ለሰወሩት ወይንም በማንነታቸው ለሚያፍሩት፣ የምንፍቅና አቀንቃኞች መልስ ይሆን ዘንድ ነው። በመምህር ምህረተአብ ላይ ላቀረቡት ትችት ከሞላ ጎደል መልስ ይሆናቸዋል ብዬ አምናለሁ። ጸሃፊው፤ አቤቱታውን ሲያሰማ እንዲህ ይላል፤ ተወልደን ባደግንበት ኦርቶዶክስ በቴ ክርስትያን “የፍቅር ምሳሌ ሊሆኑ በሚችሉ አገልጋዮች ላይ የጦርነት አዋጅ ታወጀብን” ተወልደን ያደግንበት ከማለት፤ ተዘርተን የበቀልንበት ቢል ማንነቱን ይበልጥ ይገልጸዋል ብዬ አምናለሁ። የመወለድና የመዘራት ትርጉሙ ካልገባቸው ለማለት ነው። ሲጀመር ይህች ቤተ ክርስቲያን ባጎረሰች የተነከሰች ለመሆኗ ጸሃፊው እራሱ ይክደዋል ብዬ … [Read more...] about የአርዮስ ፍሬዎች
አድማሱ “ዛፍ” በቆረጠበት ጊዜ – (የዩኒቨርሲቲው ሥነ ውበታዊ ክስመት)
“እና - እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዐይኑ የታወረ፣ እግረ ኅሊናው የከረረ፤ ባሕረ ሐሳቡን ያልታደለ፣ የውበት ዐይኑ የሰለለ፣ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ አበባ እኮ አይደለም አለ፡፡ ያልታደለ፤…” (“እሳት ወይ አበባ”) “እና - እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዐይኑ የታወረ፣ እግረ ኅሊናው የከረረ፤ ባሕረ ሐሳቡን ያልታደለ፣ የውበት ዐይኑ የሰለለ፣ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ አበባ እኮ አይደለም አለ፡፡ ያልታደለ፤…” (“እሳት ወይ አበባ”) መግቢያ ታኅሣሥ 29 ቀን፣ 2009 ዓ.ም. በዓለ ገና፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ዕድገትና ደረጃን በሚመለከት በጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት በሚያስተምር ግለሰብ ዋና የመረጃ ሰጪነት፣ ዘጋቢ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ተላልፎ ነበር፤ የፕሮግራሙ አቀራረብም፣ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት አድማሱ ጸጋዬን … [Read more...] about አድማሱ “ዛፍ” በቆረጠበት ጊዜ – (የዩኒቨርሲቲው ሥነ ውበታዊ ክስመት)










