ሰሞኑን የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ይመስላል ወያኔ/ኢሕአዴግ ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት ሰጥቷል። ዶላር እስካስገኘ ድረስ ሕፃናትንና ወጣት እህቶቻችንን በቁማቸው እየቸበቸበ ያለው ወያኔ ፀጉር መላጨት እንዳይጀምር ጠንቀቅ ነው። “አለና! ምንም አልሆንም! ምን ታመጣላችሁ! አሁንም ከማንም በላይ ነን” የሚለው የሰሞኑ የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ በሚገባ ለተረዳው ከሥልጣኑ አንፃር የወያኔን አቋምና የሀገሪቷን ቀጣይ ራዕይ መላሽ ነው። (ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about አይደለም እንዴ? ዋሸን እንዴ?
Opinions
የኔ ሃሳብ
Is TPLF prison empire in Ethiopia silently approach towards half a century!?
Since TPLF fights for 17 years as a guerrilla fighter against the military junta Derg Mengistu Hailmariam here are facts about the prison cell and situation are it’s major characteristics features of the group. Tigray people liberation front from the grass roots history they have got a famous prison cell which is highly secret full know as bado shidishte which is used to arrest those who are against them and prisoners who are sundered, wounded or hijacked by TPLF. It is used to torture, harsh … [Read more...] about Is TPLF prison empire in Ethiopia silently approach towards half a century!?
በማወቅና በማድረግ እውነትን መኖር?
የሕይወትን እውነትና ትክክለኛ ትርጉም ተረድተን በሰላምና በፍቅር ለመኖር የሚያስችል የአእምሮ መታደስ ለማድረግ የሚከተለውን ላካፍላችሁ፡ ከሁሉ አስቀድሜ ልረሳው የማልችለውን መልካም ባህላችንን ተጠቅሜ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን እላለሁ፤ እኔም ከሃገር፣ ከቤተሰብ፣ ከዘመድና ከጓደኛ ተለይቼ ባህሉንና ወጉን ጠንቅቄ ከማላውቀው ሕዝብ ጋር በእኛ አቆጣጠር ባለፈው ታሕሳስ 16 ቀን 2009 ዓ/ም የፈረንጆችን የገና በአል አክብሬ አሁን ደግሞ የእኛን ታሕሳስ 29 ቀን 2009 ላይ ከኢትዮጵያውያንና ከኤርትራውያን ወገኖቼ ጋር ለማክበር በዝግጅት ላይ ነኝ፤ እዚህ ላይ የቀን ልዩነት ቢኖርም የመከበሩ ዋና ዓላማና የቀኑ ባለቤት የሆነው ግን አንድ ነው፤ እሱም ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው በመሆን በሰው ልጆች መካከል በመመላለስ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ለማለት ድፍረት እንዲሆነን “አማኑኤል” … [Read more...] about በማወቅና በማድረግ እውነትን መኖር?
The TPLF Hired a Rubbish Writer to Defend it against Prof. Al Mariam
With an open mind, I read an article titled “TEACHING ALMARIAIM HOW TO WRITE” on the Aiga Forum website, the Tigrayan People’s Liberation Front’s (TPLF’s) mouthpiece. The article was written by Yenieta A, who claimed that Ethiopian political writers don’t know how to write. To make his point, he used Professor Al Mariam’s commentary titled “Ethiopia: Cry! Cry Freedom the Beloved Country!” as his example because he thinks Al Mariam is the worst kind of political writer. To help him to improve … [Read more...] about The TPLF Hired a Rubbish Writer to Defend it against Prof. Al Mariam
የምሥራች ነፃነት ላጣው
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን «እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ዜና ፍሥሓ…» « ትልቅ የምሥራች ዜናን እነግራችኋለሁ..»ሉቃ ፪፦፲-፲፬፤ ነገር ከሥሩ ውኃ ከጥሩ እንዲሉ የምሥራች ህገ ወንጌልን ለመታወጅ ያበቃውን ስንመረምር ፤ እግዚአብሔር አምላክ በጥንተ ፍጥረት የሰውን ልጅ ወደዚህ ምድር ፈጥሮ እንዲያስተዳድረው ከማድርጉ አስቀድሞ፤የሚተዳድርበትን የሥነ ፍጥረት ህግ አዘጋጀለት፤ ሥጋዊ አካሉ እንዳይዝል የሚያርፍበት ሌሊት ተሐድሶ የሚነሣበት መዓልትን ሰጠው፤ በጨረሯ ሙቀትን በነጸብራቋ ብርሃንን፤ በክበቧ ደስታን የምታጎናጽፈውን የሥሉስ ቅዱስ ተምሳሌት የሆነችውን ጨለማን የምታስወግደውን ፀሐይን አደለው። በልቶ የሚያረካውን ምግበ ሥጋን ሰጠው፤ በጥላው የሚጠለልብትን አበቦችን ዓይቶ በመንፈሱ የሚረካበትን ዕፀዋትን፤ አትክልትና አዝርዕትን የየብስ መደሰቻ መዝናኛውን … [Read more...] about የምሥራች ነፃነት ላጣው
“ኢትዮጵያን አፈራርሰን ኦሮሚያን እንገነጥላለን”
“ሀገር አጥፊው አረም በሀገሬ ሲስፋፋ፣ ሁሉም ተዳከመ የሚያርመው ጠፋ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እኔ አለቆርጥም ተስፋ፣ ሀገሬ ነው የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣ ጥቃቱ ይሰማው ሲቆረስ አካሉ።” ከሊቀ ማዕመራን አበባው ይግዛው “ወይ ሀገሬ” ከሚለው ግጥም የተወሰደ። የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ ለመቀራመት በተነሱበት ወቅት በተለያዩ ሀገሮች እገራቸውን ያስገቡት በሀይማኖት አስተማሪነት ሰም የቄስ ካባ አልብሰው የመረጃ (ሰላይ) ሰዎቻቸውን በመላክ ነው። ማርቲን ሉተር የተባለው የተባለው የጀርመን የሀይማኖት ሊቅ እ.ኢ.አ. በ1517 የካቶሊክ ሃይማኖት መሻሻል አለበት በሚል ያቀረበው ፅንሰ ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ዛሬ ሉተራን የሚባል የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ዋናው ቅርንጫፍ እንዲፈጠር አድርጓል። እዚህ ላይ የሉተራን ቤተ ክርስቲያን፣ የጀርመንና የኦሮሞ የሉተራን ቤተክርስቲያን … [Read more...] about “ኢትዮጵያን አፈራርሰን ኦሮሚያን እንገነጥላለን”
ለማንነታችን መከታ ያልሆነን፣ ለመጠቃታችን ምክንያት እየሆነ ነው!
ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በሕዝባችን ላይ፣ በተለይም በዐማራው ነገድ ላይ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በ«አርበኞች ግንቦት 7» እያመካኘ ነው። ለዚህም ምክንያት የሆነው አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በሚቆጣጠረው የብዙኃን መገናኛ ያላደረገውን አደረኩ፣ ያላዘመተውን ወታደር አዘመትኩ፣ «የክተት አዋጁ ፊሽካ ተነፋ»፣ በሁሉም ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴዎች እኔ አለሁበት፣ የምመራው እኔ ነኝ፣ የሚለው ወሬ ቀድሞ መነዛቱ ነው። ወሬው በትንሽ ተግባር ቢደገፍ ኖሮ ባልከፋ። ክፋቱ ምንም ዓይነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሳይጀምር፣ ኤርትራ በረሃ ከትሟል የሚባለው ፋኖ፣ የተከዜን ወንዝ ሳይሻገር፣ የወያኔ አገዛዝ አንገሽግሾት ባመቸውና በመሰለው መንገድ ጥይት የተኮሰውን ሁሉ የእኔ ነው ማለቱ፣ «ለወያኔ ሊበሏት ያሰቧትን … [Read more...] about ለማንነታችን መከታ ያልሆነን፣ ለመጠቃታችን ምክንያት እየሆነ ነው!
ሚዲያ አለኝ ተብሎ የሰው ስብዕና ላይ ክተት አይታወጅም
ሚዲያ እንደ ሰዎች አረዳድ የሚሰጠው ደረጃና አቅም የተለያየ ቢሆንም ያለ አንዳች ማመንታት “ኃይል” ወይም ኃይል ያላቸው መገልገያ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ሁሉም ሚዲያ “የሕዝብ” መሆናቸውን ቢገልጹም ፍጹም ነጻና ገለልተኛ ሆነው አይታዩም። ወደ አገራችን ሚዲያ ስንመጣ በውጭ ያሉትም ሆኑ በአገር ቤት፣ የግል የሚባሉትም ሆነ የመንግሥት የራሳቸው ወገንተኛነትና መንሸዋረር ይታይባቸዋል። ይህ እውነት ባደጉት አገሮችም ቢሆን ረቀቅ ባለ መልኩ የሚዘወተር ነው። ከሁሉም የሚቀፈው ግን ፍጹም ጭፍንነት ነው። ምክንያቱም በጭፍንነት ውስጥ አንድ ሰው ከተነገረውና ከተሞላው በቀር አሻግሮ ማየት አይችልምና ነው። “መቃብር ቆፋሪው እና የሬሳ ሳጥን ሻጩ የሚለው ተውኔት የተሰረቀ ነው” የማለት አዝማሚያ በሚስተዋልበት ስሜት የተጀመረ ቃለ ምልልስ። ሲጠናቀቅም የተለያዩ ጉዳዮች ውስጥ ትገባለህ “የባከንክ ነህ” … [Read more...] about ሚዲያ አለኝ ተብሎ የሰው ስብዕና ላይ ክተት አይታወጅም
“እውነተኛው የዘር ምንጭ?”
ዶ/ር ፍቅሬ በ “የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” መጽሐፉ አዲስ እሳት ለኵሶልናል። እሳቱ ባጭሩ፣ ሁሉም የሚስማማውን ታሪክ ይጻፍ የሚል ነው። ቍጥራቸውና ማንነታቸው ያልታወቀ አወዳሾቹ፣ “ሐቀኛ የኦሮሞ ልጅ የኢትዮጵያ ልጅ” “የመከራ ቀን ደራሽ” “የመከራ ቀን ልጅ” “የታሪክና የፍቅር አባት” “የኢትዮጵያ መድን” “የህዝብ እርቅ አባት” “አስታራቂ” “የኢትዮጵያ ቤዛ” “ነብይ” ብለውታል። ሙገሳው የለመደበት “ካብ ካብ፣ ጣል ጣል” ባህላችን ነው ብለን እንለፈው። አንዳንድ “ምሑራን” ጭሱ አፍኗቸው መስኮት ለመክፈት ይሯሯጣሉ። አንዳንዶች የጎሳ ክልል መደብዘዝ የሥልጣን ወንበር እንዳያሳጣቸው ሠግተው። ሌሎች በአገር ወዳድነት። አንዳንዶችም ያልተፈጠረ ንጹሕ ጎሳ በስውር የሚያውጁ ናቸው። ከኢትዮጵያ መንደር ውጭ ማሰብ የተሳናቸው፤ በምድር ዙሪያ የሕዝቦች አሠፋፈር፣ መፍለስና … [Read more...] about “እውነተኛው የዘር ምንጭ?”
የሕወሓትን “ሌጋሲ” በጨረፍታ
የወያኔው መንግሥት ያላወረሰን ነገር የለም፡፡ ሁለመናችንን እከክ በእከክ አድርጎናል - በቀላሉ በማይድን እከክ አውርሶን ወያኔም እኛም ጣር ላይ እንገኛለን - አሸናፊው ባልለየለት እልህ አስጨራሽ የአውራ ዶሮዎች ጦርነት ተጠምደን፡፡ የመለስና የድርጅቱ የሕወሓት ውርስ (ሌጋሲ) በአሥራዎች ቀርቶ በመቶዎች ዓመታትም ተዝቆ የማያልቅ ዕዳ አሸክሞናል፡፡ በኢኮኖሚውና በትምህርቱ ረገድ የደረሰብን ኪሣራ ምናልባት በጊዜ ሂደትና ደጋግ ዜጎች የአስተዳደሩን ልጓም ሲይዙ ሊስተካከል ይችላል፡፡ ይህም ሲባል ሚሊዮኖችን በእሳት አለንጋው እየገረፈ የሚገኘው ድህነት ጥርሱን አግጥጦና ዐይኑን አፍጥጦ ዜጎችን የበይ ተመልካች በማድረግ ከማንኛውም ጨዋታ ውጪ እያደረጋቸው እንደሆነና በትምህርቱም በኩል በዘልማድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ 85 በመቶው እንደሆነ ከሚነገርለት የሀገራችን ገበሬ በዕውቀት የማይሻሉ ምሩቅ ማይማን … [Read more...] about የሕወሓትን “ሌጋሲ” በጨረፍታ










