ያለፉት 23 አመታት በመንግስትና ተቃዋሚ መካከል ያለው ቅራኔ መፍትኤ አላመጣም። በጦርነት ስልጣን የያዘ መንግስት ዲሞክራሲ ይኸሁላችው ብሎ ይሰጥ ዘንድ አይቻለውም። በጦርነት መንግስት ለመቀየር የሚታገለውም ስልጣኑን ሲይዝ ከዚህ የተለየ አያደርግም። ኢትዮጵያ መውጫ ቀዳዳ ያጣች ትመስላለች። እሺ ብንል እርቅና መግባባት ዲሞክራሲን ለመውለድ ብቸኛ መንገድ ነው። እንዴት ማለት ጥሩ ነው። ሁላችንም የምንጠለልባት፦ በፍቅር ተሳስረን የምንኖርባትን ቤተ ኢትዮጵያን እንዴት እንገንባት? 1ኛ/ ሰላምን ብቻ መምረጥ ላይ መድረስ፦ የቤተ ኢትዮጵያ መሰረት። የስላሙን ትግል ከትግሎች ውስጥ እንደ አንዱ ሳይሆን እንደ ብቸኛ አማራጭ መውሰድ ይገባል። ኢትዮጵያ ለዚህ አይነት ሰላም ራሳቸውን የሰጡ ሰላማዊ ተቃዋሚ ልጆች አላት። ሰላምን ብቻ መምረጥ ወደ ዲሞክራሲ የሚያደርሰው የእርቅና መግባባት አስተሳሰብ … [Read more...] about የእርቅ ማኒፌስቶ፦ ወደ ዲሞክራሲ የሚያደርስ አማራጭ መንገድ
Opinions
የኔ ሃሳብ
ኢትዮጵያዊነት . . . ( ክፍል ፪ )
ባለፈው ጽሑፌ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፤ ከልቤ ያማምንበትን በጥቅሉ አስፍሬ ነበር። በዚያ፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ ማለት፤ ታሪካቸውን፣ ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ መላ የኑሮ ሁኔታቸውን ጨምሮ ማለት ነው። ሀገራችንን ኢትዮጵያን ማፍቀር ደግሞ፤ ዳር ደንበሯ፣ የተፈጥሮ ሀብቷ፣ ወንዞችና ተራሮቿ፣ ደጋ፣ ወይነደጋና ቆላ ምድሯ፣ አራዊቷ፣ የሚለዋወጡ አራቱ የሀገራችን አየር ጠባይ ወቅቶችን ማለት ነው። ሀገር ያለ መንግሥት ችግር ነው። መንግሥት ደግሞ በዚህ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን፤ በሕዝብ ፈቃድና ፍላጎት ኃላፊነቱ ተሠጥቶት የሚያስተዳደር ሀገራዊ ተቋም ነው። በዚህ ሂደት መንግሥት፤ ለመረጠው ሕዝብ ተንቆጥቁጦ ሥራውን ያከናውናል። በተገላቢጦሽ ሕዝብ መንግሥቱን ፈርቶ የሚኖርበት ሀገር፤ ለውጥ በሩን እያንኳኳ ነው። የዚህ አስፈላጊ ተቋምና የሕዝቡ ግንኙነት ይህ ነው። እናም … [Read more...] about ኢትዮጵያዊነት . . . ( ክፍል ፪ )
Why Free Trade Agreements with the EU will hurt African countries!
Impacts of Free Trade & Globalization Since 2002 the EU, African countries and including the Caribbean states have been conducting negotiations to reach Economic Partnership Agreements(EPAs) that might give opportunities for these states to get access for their products into the EU market. In turn the EU wants to get a free access to the African market. The negotiation has taken too long because of the nature and complexity of the issue and at the same time because of the intriguing … [Read more...] about Why Free Trade Agreements with the EU will hurt African countries!
የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን?
“የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን” የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን የሚለውን ቃል ለምን በትእምርተ ጥቅስ እንዳስቀመጥኩት የገባችሁ ይመስለኛል፡፡ ጣቢያው ስሙ እንደሚጠቁመው የሀገር የብዙኃን መገናኛ ሳይሆን እራሳቸውን በመንግሥት ስም ያደራጁ በአብዛኛው ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም ተፃራሪ የሆነ ጥቅም ፍልጎትና ዓላማ ያለው ቡድን ዓላማ ማራመጃ ከሆነ ዐሥርት ዓመታት አልፏልና ነው መትእምርተ ጥቅስ ማስቀመጤ፡፡ ይህ የብዙኃን መገናኛ ሕግና ሕዝብ እንዲሆን የሚጠብቀው ነገር ግን የመንግሥት (የሕዝብ) መሆን ያልቻለው ብሔራዊ የቴሌቪዥንና ሬዲዮ (የምርአየ ኩነትና የነጋሪተ ወግ) ጣቢያ ትናንትና በ19-12-2006 ዓ.ም. የግል የኅትመት የብዙኃን መገናኛዎችን በተመለከተ “ያልተገሩ ብዕሮች” በሚል ርእስ ዘጋቢ ፊልም ሲል በሠየመው ዝግጅት ዝግጅቱ ምንም እንኳን ዘጋቢ ፊልም (ምትርኢት) ለመሰኘት … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን?
የኢቲቪ “ያልተገሩ ብዕሮች” ዘጋቢ ፊልምና ያልተገራው አቀራረብ
ከሁለት ሰአቱ የኢቲቪ ዜና አወጃ ተከትሎ የቀረበውን "ያልተገሩ ብዕሮች" ዶክመንተሪ በደረቁ ሌሊት ድጋሜ ስርጭቱ ተከታትየ ጨረስኩት ... ላፍታ እንደተጠናቀቀ ዝም፣ ጭጭ አልኩና በሃሳቤ በህዝብ ገንዘብ ከፍተኛ ወጭ እየተደረገባቸው የሚሰራጩትን የመንግስት የህትመት ጽሁፍና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃንን አሰብኳቸው ... በምናብ ብዙ ርቄ ሔጀ በዶለደመ፣ ባልተገራ እና በተባውና በተገራው ብዕር ውስጥ ራሴን አትኩሮት ሰጥቸ የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶች በሃሳብ ተመላለስኩባች! ሰፊ ሽፋን ያለውን ኢቲቪና ራዲዮኑን፣ በየቀኑ እየታተሙ የሚወጡትን እነ አዲስ ዘመንን ጋዜጣንና የመሳሰሉት እሰብኳቸው ... አስቤ አሰላስየ ወደ ደረስኩበት ድምዳሜ ከማቅናቴ በፊት ግን በ"ያልተገሩ ብዕሮች" ዘጋቢ ፊልም ዙሪያ የታዘብኩትን ቀዳሚ አድርጌ የተሰማኝን ላካፍልዎ ወድጃለሁ... "ያልተገሩ ብዕሮች" … [Read more...] about የኢቲቪ “ያልተገሩ ብዕሮች” ዘጋቢ ፊልምና ያልተገራው አቀራረብ
ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል
ጉልበት አራዊት የሚተዳደሩበት ሕግ ነው፤ ሕገ አራዊት የሚባለው አራዊት የሚተዳደሩበት ጉልበት ነው፤ በአራዊት ዓለም ማናቸውም ነገር በጉልበት ያልቃል፤ በሰዎችም መሀከል ጉልበት አድራጊ-ፈጣሪ ሆኖ ጎልቶ ሲወጣ የአእምሮንና የኅሊናን መዳከም ወይም ጭራሹኑ አለመኖር ያመለክታል፤ ጉልበት አለን በማለት፣ ወይም ተመችቶናል በማለት፣ ወይም ጠያቂ የለብንም በማለት የማንኛውንም ሰው ሰብአዊ መብቱንና ሰብአዊ ክብሩን መግፈፍ ሦስት ነገሮችን ያመለክታል፤ አንደኛ ጉልበት እንጂ አእምሮና ኅሊና እንደሌለ፣ ሁለተኛ ጉልበት እንጂ ሕግ እንደማይከበር፣ ሦስተኛ በአንተ ላይ እንዲያደርጉብህ የማትፈልገውን አንተም በሰዎች ላይ አታድርግ የሚለውን ሕግ መጣስን ያሳያል፤ በመጨረሻም፣ ዘግይቶም ቢሆን በራስ ላይ ቅሌትን መጋበዝን ያስከትላል፤ የሌላውን ሰውነት ስናረክስ ሰውነትን በጠቅላላው ማርከሳችን ነው፤ ሰውነትን … [Read more...] about ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል
Ethiopian Special Forces can quell the unrest in Ferguson.
On 9, Aug, 2014 a white police man allegedly shot an unarmed African American teenager, Michael Brown, 18, in Ferguson Missouri, USA. Ever since Washington seemed unable to restore calm and tension in the city. However if the USA had invited Special Forces of the current Ethiopian government, the whole public chaos and mob would have been quelled in a matter of hours. For more than the past 23 years the Ethiopian government (EPDRF) has been diligently working in producing Special Forces who … [Read more...] about Ethiopian Special Forces can quell the unrest in Ferguson.
የብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ
ስለ ብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ አጠር ምጥን ተደርጎ የተዘጋጀውን ባለ አምስት ነጥብ የዳሰሳ ጥናት (survey) ለዚሁ ጉዳይ ሲባል ብቻ ወደ ተዘጋጀው ድህረገፅ እዚህ ላይ በመጫን በመሄድ ድምፅዎን ያሰሙ። የዝምተኛው ብዙሃን ድምፅ ጭምር ሳይቀር እስቲ ይሰማ! ፖለቲካውንና ፍልስፍናውን አርባ አመት አውጠንጥነን አረጀንበት። እንዲሁ ስንባዝን እድሜያችን አልቆ አንድ ባንድ ወደ ሞት ልንሄድ ነው። እርቅና መግባባትን ማን ጠላ? መላው ጠፍቶብን እንጂ። አይ መላውም አልጠፋን እንደ እውነቱ ከሆነ። ኢትዮጵያ መፍትሔ ሊያመጡ የማይሳናቸውን ልጆች ወልዳ ሳለ እንደ መካን ቁጭ ብላ መቆዘም አይገባትም። እስቲ የልበ ሰፊው፦ የአስተዋዩና የጨዋው ሕዝብ ድምፅ እንስማው። ባለስልጣኑ በራሱ ጡንቻ ተማምኖ ተቃዋሚውን ከመንጫጫት በላይ ምን ያመጣል ብሎ ሲንቅ፦ ተቃዋሚው ምንም ይሁን ምን ባለስልጣኑ … [Read more...] about የብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ
The perils of outsourcing the fight for freedom
I could have titled this piece ‘Obama and his Africa peace keepers’ but that would not be fair. Anybody with half a brain can see that I am trying to make my issue to be his problem. Excuse me just because fighting for my right is beneath my dignity there is no reason to impose on him that I am unable to do for whatever reason. Dear Mr. President we Africans are not amused! This is what appeared on The Guardian ‘According to President Obama, who announced a series of American support and … [Read more...] about The perils of outsourcing the fight for freedom
ኢትዮጵያዊነት ማለት ክፍል ፩
“ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። ” አብዛኛዎቻችን በየጊዜው የምናነሳው ጉዳይ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ሀቅና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አይደለሁም የሚለውን ጥያቄ አይደለም። በየቦታው፣ በተገኘው አጋጣሚ፣ በየዕለቱ በሕዝቡ ላይ የሚደረገውን በደል እናውጠነጥናለን። ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይንም አይደሉም የሚለው ከጥያቄያችን መካከል አይደለም። መቼም አርባ ዓመት ሙሉ፤ በአረመኔው መንግሥቱ … [Read more...] about ኢትዮጵያዊነት ማለት ክፍል ፩









