ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about ነገረ-ኢትዮጵያ
Right Column - Primary Sidebar
በአዲስ አበባ ውሃ እስከ 20ቀናት ይጠፋል
* "የውኃ ምርት ችግር የለብንም የኤሌክትሪክና የማሰራጨት እንጂ" የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የፌዴራል መንግሥት መቀመጫና የአፍሪካ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፣ ለሁለትና ሦስት ቀናት ይጠፋ የነበረው የውኃ ችግር እስከ 20 ቀናት እየጠፋ መሆኑንና ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ በተለይ ከሳሪስ እስከ ቃሊቲ፣ አየር ጤና፣ ወይራ ሠፈር፣ ለቡ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ፒያሳ፣ ሽሮ ሜዳ፣ መርካቶ፣ የካ በተለያዩ ወረዳዎች አራት ኪሎ (አልፎ አልፎ) በአጠቃላይ በከተማው ከአምስት እስከ 20 ቀናት ውኃ ጠፍቶ እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ ስንታየሁ አበበ የተባሉ የሳሪስ አቦ ማዞሪያ አካባቢ ነዋሪ እንደገለጹት፣ የውኃ ችግር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱ ያስገርማቸዋል፡፡ ቀን ቀን ይጠፋና እኩለ ሌሊት ይመጣላቸው በነበረው ውኃ ሲማረሩ፣ ይባስ ብሎ የመጥፋቱ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ውሃ እስከ 20ቀናት ይጠፋል
መርገምተ ወያኔ
“በረከተ መርገም” የሚያስፈልግ ቃሉ፣ ዛሬ ነው ተራገም ባለቅኔው ኃይሉ። ቅኔህን አፍሰው እንደድሮ እንደጥንት፣ ላሁን ዘመን ገዢ ያስፈልጋል መርገምት። አንተ በርግማንህ የጠበጠብካቸው እነዛ ሊቃውንት በፍልስፍናቸው ተወቃሽ በመሆን ቢያተርፉም ክፉ ስም ለውጥ አስገኝተዋል ላለንባት ዓለም ነገር ግን ያሁኑ ለስልጣን ለሀብቱ፣ ለስጋ ቁመናው ለሰፊው ቀፈቱ፣ አስሮ ሲያንገላታ ቆይቷል ሲገድል፣ አፍስበት በሱም ከርግማንህ ጠበል፣ ድሮ በሊቆቹ እርግማን ከጨረስክ፣ ምን ይሰራል ብለህ ወይም መርገም ከተውክ፣ እንዳሻህ በልና ፍቀድልኝ፣ ለኔ የርግማን በረከት አለኝ በወያኔ ካስፈለገም አምጣ ድርሻህን መዋጮ፣ የእኔን ግን ልጀምር ከወያኔው ቁንጮ ከኢትዮጵያ ምድር ከአብራኳ ወጥተህ፣ አንባሻዋን ገምጠህ ወተቷን ጠጥተህ፣ ፊደል ቆጥረህባት በሜዳዋ ሮጠህ፣ በፍቅር በደስታ … [Read more...] about መርገምተ ወያኔ
ልማታዊ መንግሥትና አዲሱ የአባ ወራ አስተዳደር ለአፍሪቃ
ኢህአዲግ ለሚቀጥሉት አርባ ዓመታት ለመግዛት በማለም፣ ላለፉት ዓመታት የሚከተለውን የአስተዳደርና የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ „በባለ ራዕዩ“ መሪያቸው የ ተነደፈውን ባደባባይ ለውይይት ለማቅረብ እየሸነጠው ነው። በመሰረቱ ወጣም ወረደ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ይህ ፖሊሲ በተግባር ይውል እንደነበረ ባለሙያዎች ሆኑ የውጭ ሀይሎች ደጋፊዎቻቸው የሚያውቁትና የአደባባይ ምስጢርም ነው። አሁን ግን ይበልጡን ጡሩንባ ተለቆለት፣ ባደባባይ እንዲወጣና አዲስ የሚነዳ የርዕዮተ ዓለም ፈረስ ሆኖ ብቅ ያለው፣ የቀድሞው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቲዎሪ ነዳጅ ስለ አለቀና የሚያሳምን ስም ስላላተረፈ፣ ለአገዛዝ ማሰንበቻ፣ በልማት ስም፣ ልማታዊ መንግሥት /developmental state/ የሚባለው የተወሰነና ከዛኛው የበለጠ ሌጂትሜሲ/ ተቀባይነት ያስገኛል በሚል ምኞት ነው። በተለይም በልማት ሰበብ ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች … [Read more...] about ልማታዊ መንግሥትና አዲሱ የአባ ወራ አስተዳደር ለአፍሪቃ
ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጪ!? ኡክሬይን
ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጪ አለበለዚያ ድንጋይ ብለው ይጥሉሻል ይባላል! ለራስህ እውቅበት፣ ትርጉም እንዳታጣ ለማለት ነው፣ መቼም ይህን ታውቁታላችሁ! ነገሩን ወደ ዘመናችን ዓለም አቀፍ ፖለቲካ ስናዞረውና ልንማርበት፣ ተመክሮ ልናገኝበት ከፈለግን እንደሚከተለው ነው። ሰው ህዝብ ሀገር ለራሱ ሲል፣ ወዳጅ ረዳትና ነገረፈጅ በዓለም መድረክ ላይ አለኝ በሎ፣ በራሱ ሳይሆን በነርሱ ተማምኖ ነገር ዓለሙን ከተወው፣ ለራሱ ሲል ካላወቀበት የኋላ ኋላ ጉድ ጉድ ተብሎ፣ መቼም ምን ይደረግ ተብሎ ይተዋል፤ ይወድቃል፤ ለወሬውም ይረሳል ማለት ነው። ጉድ አንድ ሰሞን ነውና ሊቢያ ጉድ ጉድ ሲባል ከርሞ ዛሬ ተረስቷል! ኢራክማ የት የሌለ፤ ስለ አፍጋኒስታንም ለማለገጫ ከልሆነ በስተቀር ብዙም ልብ አይባል! ግብጽም ከሰሞኑ ትንሽ ሰንበት ብሎ ይረሳል፤ የመን ተረስቷል፣ ሲሪያም ጨዎቹ(ፖለቲከኞቹ) … [Read more...] about ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጪ!? ኡክሬይን
ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ
የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ። በርግጥም ሁላችን ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣ እንደገና መልሰን የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው። በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢተ ዳንዔል ላይ ኣንድ ናቡከደነጾር የተባለ ንጉስ ኣንድ ጊዜ ጠቢባንን ጠርቶ የህልም ፍቺ … [Read more...] about ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ
ኔልሰን ማንዴላና ህፀፆቹ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንትና የገዢው የኤኤንሲ /የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ/ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩትን ኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ ከሦስት ትውልድ ያላነሰ አፍሪካዊና የሌላው አህጉር ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። እኝህ ሰው ይበልጥ ከሚታወቁባቸው ጉዳያቸው ውስጥ በአገሪቱ በነበረው አፓርታይድና ዘረኛ ስርዓት ለ27 ዓመታት መታሰራቸው ብሎም ከእስር በኋላ ለአሳሪዎቻቸውና በብዙ ሚሊዮን ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያንን አንገብግበው ለገዙ የዘር መድሎ ለፈፀሙ እንዲሁም የግርፋት የግድያና የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን ለሰሩ ነጭ በዝባዦቻቸው ይቅር ማለታቸው ዋነኛው ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ኔልሰን ማንዴላና ህፀፆቹ
አያስቅም! አጭር ወግ
በብሄራዊ ትያትር አካባቢ አንዲት አነስተኛ ምግብ ቤት ነበረች። «ገሊላ ምግብ ቤት» ትባል ነበር። በአዲስ አበባ «ቁምራ» ከመግባቱ በፊት በአካባቢው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በምሳ ሰዓት ይህችን ምግብ ቤት ያጨናንቋት ነበር። ቁምራን የማታውቁ ካላችሁ፤ ለጽድቅ የሚደረግ መንፈሳዊ ጾም እንዳይመስላችሁ። እድገትና ትራንስፎርሜሽኑ ያመጣው አዲስ ክስተት ነው - ቁርስ ምሳና ራት በአንድ ጊዜ የመመገብ ዘዴ። «ኑሮ በዘዴ፣ ጾም በኩዳዴ» ይባል ነበር። ይህ አባባል አሁን መኖ በዘዴ በሚል ተቀይሯል። መቼም ሁሉም ነገር በነበር እየቀረ ነው። ጋዜጠኛ አቤል አለማየሁ በቅርቡ ባሳተመው "የአዲስ አበባ ጉዶች" የሚል መጽሃፉ ላይ ስለዚህች ታሪካዊ ምግብ ቤትም ትንሽ ብሏል። የምግብ ቤትዋ ባለቤት "ገሊላ ምግብ ቤት" የሚለው ጽሁፍ በከፊል አጥፍተውታል። አሁን ምግብ ቤት የሚለው ተነስቶ "ገሊላ" … [Read more...] about አያስቅም! አጭር ወግ
በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው?
"በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው “Who is in Charge?” የሚለው ጥያቄ ያሳሰባቸው ቧልተኞች የፈጠሩትን ቀልድ ላልሰማችሁ ላሰማችሁ፡፡ (ኮፒራይቱ የሰፊው ህዝብ እንደሆነ ይታወቅልኝ!) አንዱ ኤፍኤም ሬዲዮ ይደውላል - ዘፈን ለመምረጥ። ደዋይ - ዘፈን ለመምረጥ ነበረ፤ የእገሌን … ኤፍ ኤም- ማን እንበል? ከየት ነው? ደዋይ- የገዢው መደብ አባል ነኝ---- ከደቡብ! ኤፍ ኤም- (ደንገጥ ብሎ) ከደቡብ … እሺ ዘፈኑ ይቀጥላል … (የኤፍኤሙ ጋዜጠኛ ከድብልቅልቅ ስሜት ሳይወጣ ሌላ ዘፈን መራጭ ይደውላል) ኤፍ ኤም- ሄሎ … ማን እንበል? ከየት ነው? ደዋይ - ዘፈን ለመምረጥ ነበር ኤፍኤም- ራስህን አስተዋውቀን? ደዋይ - የገዢው መደብ አባል ነኝ - ከትግራይ! ኤፍኤም - እንዴትነው ነገሩ? አሁን ከደቡብ ደውሎ የገዢው መደብ አባል ነኝ … [Read more...] about በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው?
ሰላማዊ ወይስ የትጥቅ ትግል ወይስ ማንፈራጠጥ
የተማረ ወይም የእውቀት ባለቤት እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል ሰላማዊ ይሁን ወይስ በትጥቅ ትግል የሚለውን የጦፈ ክርክር ሲያደርግ ሃያ ሁለት ዓመታት ሆነው፤ ዳኛ የሌለበት ክርክር ስለሆነ የመደማመጥ ግዴታ ታይቶበት አይታወቅም፤ ስለዚህም በሁለቱ መሀከል ያለው ልዩነት ግልጽ ሆኖ አያውቅም፤ አንድ፣ ከሁሉ በፊት ሰላማዊ ትግል በሀሳብ ደረጃ መሆኑንና የትጥቅ ትግል ደግሞ በተግባር መሆኑን ለይቶ ለመረዳት ችግር ሆኖ ቆይቶኣል፤ በሌላ አነጋገር ሰላማዊ ትግል በሀሳብ፣ በንግግር፣ በተለያዩ ሀሳብን ለማስለወጥ መቀስቀሻ በሚሆኑ መንገዶች ተቃውሞን መግለጽ ነው፤ በአንጻሩ የትጥቅ ትግል በጠመንጃ ወይም በጉልበት ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ነው፤ ሁለት፣ እንዲህ ከሆነ በሰላማዊ ትግል ለሚያምኑ ሰዎች ያለምንም ጥርጥር በተለያዩ … [Read more...] about ሰላማዊ ወይስ የትጥቅ ትግል ወይስ ማንፈራጠጥ










