ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስለገለምሶው መምሬ ሙላቱ የምትተርክ አንዲት ጽሑፍ ለጥፌ ነበር፡፡ አሁን ሳስበው ግን ያቺ ጽሁፍ መሀል መንገድ ላይ ተቆርጣ የቀረች ሆና እየታየችኝ ነው፡፡ ስለዚህ ለናንተም፤ ለወገንም፣ ለታሪክ ጸሓፊያንም እንዲጠቅም ይህችኛዋን ሐተታ እጨምርበት ዘንድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በ1981 የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ይመስለኛል፡፡ ከትምህርት ቤት መልስ የጨዋታ ጓዶቼን ፍለጋ “ኒብራ” ከተሰኘው የገለምሶ ከተማ ዋነኛ ጎዳና ወረድኩ፡፡ ጓዶቼን ብዙም ርቀት ሳልሄድ ከትልቁ የጋሽ መሐመድ በከር መደብር በረንዳ ላይ አገኘኋቸው፡፡ እዚያም የኳስ ጨዋታ ሰዓታችን እስኪደርስ ድረስ በትረባና በፉገራ መናቆር ጀመርንና አንዱ ሌላውን ለማብሸቅ ይሞካክር ገባ (በጊዜው ትረባ፣ ፉገራና ለከፋ ጊዜያችንን የሚገፋልን ትልቅ መዝናኛችን ነበር)፡፡ እኛ የነበርንበትን በረንዳ በስተግራ … [Read more...] about የክርስቲያንና የሙስሊም ፍቅር በገለምሶ
Right Column - Primary Sidebar
ከቦታቸው መፈናቀልን የተቃወሙ ኢትዮጵያዊያን እስራትና ግድያ እናወግዛለን!
ሰሞኑን ከአዲስ አበባ አቅራቢያ ያሉ ብዙ ከተሞችን በዋና ከተማው ስር ለመጠቅለል የወያኔ አጋዛዝ “ የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን” በሚል ያወጣውን አቅድ፣ የማፈናቀል እርምጃ ነው ብለው በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ለማሰማት ሰልፍ የወጡ ዜጎችን በጅምላ ገድሏል፣ ብዙዎቸን አቁስሏል፣ በገፍ አስሯል። በአምቦ ከተማ ብቻ አስካሁን በተገኑት መረጃዎች በትንሹ 47 የሚሆኑ የተገደሉና ብዙ የቆሰሉ ሲገኙበት፣ በጅማ ካምፓሶች፣ ወለጋ፣ መቱ፣ ቦሉ ሆራ፣ አዳማ ሃረሚያና በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ የጭካኔ አርምጃ ወስዷል። ኢሕአፓ-ወክንድ ይህን የወያኔ ኢሰብአዊ ድረጊት አጅግ በመረረ ቃል ያወግዛል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ከቦታቸው መፈናቀልን የተቃወሙ ኢትዮጵያዊያን እስራትና ግድያ እናወግዛለን!
መምህር ግርማ አስማተኛ/አጥማቂ?
ከዝግጅት ክፍሉ - ይህንን ጽሁፍ የላኩልን ጋዜጠኛ መስፍን አብርሃ በግልጽ እንደጠቆሙት ይህንን ጉዳይ በተመለከተ መምህር ግርማም ሆኑ የርሳቸው ደጋፊም ይሁን ተቃዋሚ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ በመስጠት በጨዋነት የሚልኩልን አስተያየት የምናስተናግድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን:: በኢትዮጵያ አገራችንና ኢትዮጵያዊ ወይም የአበሻ ዘር ባለበት በዓለማችን ክፍል በአሁኑ ወቅት ስለ መምህር ግርማ ወንድሙ የማያውቅ ቢያንስ ያልሰማ የለም። መምህር ግርማ በመጀመሪያ መስቀል አደባባይ በሚገኘው በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ቀጥሎም በኤረር ሥላሴ ቤተክርስቲያን የማጥመቅና የፈውስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመምህር ግርማ አገልግሎት ላይ በተለይም የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሃይማኖት ተከታዮች በሆንን ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ የሃሳብ ልዩነት እየተፈጠረ አንዳንድ አካባቢም … [Read more...] about መምህር ግርማ አስማተኛ/አጥማቂ?
የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚጠቀሙበት የፖለቲካ ፎርሙላ
ፎርሙላ (ቀመር) አንድ የጎሳ ፖለቲካ ማለት በመጀመርያ ቤተሰብህን የተለዩ ፍጥረት እንደሆኑ መስበክ መጀመር ማለት ነው። እነርሱ የተለዩ መሆናቸውን በደንብ ማሰብ ሲጀምሩልህ ደግሞ በመቀጠል የሰፈርህን እና የወንዝህን ሰዎች ልዩ መሆናቸውን በሚገባ መስበክ ነው። የሰፈርህን ሰዎች ልዩ እና የተለዩ መሆናቸውን ስትነግር ግን የአንተ ቤተሰብ ጋር እንደማይደርሱ ግን ደግሞ ከቤተሰብህ ዝቅ ባለ መልክ የተለዩ መሆናቸውን ወትውታቸው። በመጨረሻ አንተ የቤተሰብህም ሆነ የሰፈርህ ብቸኛ አለቃ መሆንህን ትነግራቸውና ከሰፈርህ ማዶ ያሉ ሰዎች ደግሞ እርኩስ፣ የተለዩ፣ ጥንትም አባቶችን ሲበድሉ እንደነበሩ የሆነ ያልሆነ ተረታ ተረት እየነገርክ ተራራ የሚያህል ጥላቻ እንዲያድርባቸው አድርግ። ፎርሙላ (ቀመር) ሁለት ከእዚህ በኃላ በሰፈርህ ሰዎች እና ማዶ ባሉ ሰፈር ሰዎች መካከል በአንተ የጦር … [Read more...] about የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚጠቀሙበት የፖለቲካ ፎርሙላ
የሕግ አምላክ የሞተባት አገር፤ በሕገ መንግሥት ሳይሆን በወያኔ የጫካ ሕግ ለሃያ ዓመታት
ለከት ያጣው የወያኔ ጭካኔ እና የማይነጥፈው የሕዝብ ትእግስት ኢትዮጵያን ወዴት እየወሰዷት እንደሆነ አገሪቱ ዛሬ ያለችበት ውጥንቅጥ ሁኔታ በግላጭ ያሳያል። በመግደል አባዜ የተለከፉት የወያኔ ተጋዳላዮች ዛሬም መግደላቸውን ቀጥለዋል። ለይስሙላ በወረቀት ላይ የሰፈረው ሕገ-መንግስት እና በውስጥ የያዛቸው መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች ለወያኔ ተጋዳላዮች ምናቸውም እንዳልሆነ በተደጋጋሚ እያሳዩን ነው። በአገሪቱ ውስጥ ያለው የሕግ ማእቀፍ (አንዳንዶቹ ሕጎች በራሳቸው የማፈኛ መሳሪያ ተደርገው የተቀረጹ መሆኑ ሳይረሳ) ለወያኔ ተጋዳላዮችና ተራ ካድሬዎች ሳይቀር ምናቸውም አይደለም። ሲሻቸው ይገድላሉ፣ ያፍናሉ፣ ይሰውራሉ፣ ባደባባይ ይደበድባሉ፣ ሺዎችን በየማጎሪያው ያሰቃያሉ፣ ያዋርዳሉ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ ይሞስናሉ፣ ይሰርቃሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ያስፈራራሉ፣ ሴቶችን ይደፍራሉ፣ ህዝብን … [Read more...] about የሕግ አምላክ የሞተባት አገር፤ በሕገ መንግሥት ሳይሆን በወያኔ የጫካ ሕግ ለሃያ ዓመታት
What did they do to deserve mass killings? All they did was protest peacefully
CREW strongly condemns the killing of students and their supporters from within the community in the various parts of Oromia region in Ethiopia. Sixteen students were killed at Ambo University alone and more than ten students at other universities in the region. They were killed by government security forces for protesting against a new Integrated Development Master Plan of the city of Addis Ababa which the students believe is a plan to annex several towns in the area and displace Oromo … [Read more...] about What did they do to deserve mass killings? All they did was protest peacefully
ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት?
አንድ በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤ ለዚህ ነው ይህንን መልስ የምጽፈው፤ ወይዘሮ መስከረም በአጋጠሟትና በምታያቸው እንቅፋቶች ላይ ማተኮርዋ እንደርስዋ መንፈሳዊ ወኔው የሌላቸውን ያስፈራራቸዋል እንጂ አያበረታታቸውም፤ የማንንም አፍአዊ ጫና ተቋቁመው በራሳቸው የውስጥ ኃይል እንዲመሩ እናድርግ። አንድ መጽሐፍን በመጥቀስ ወይዘሮ መስከረም የሚከተለውን … [Read more...] about ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት?
ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ለመሆኗ አለም ይመሰክርላታል፡፡ አንቱ የተባሉ ምሁራንን በማፍራት ለዓለም አበርክታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአለም ካሉ ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት እስከ አመራነት ድረስ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህ ምሁራን በተሰማሩበት ስራ መስክ የሚያስመዘግቡት ውጤት እና በስራቸው ተሸላሚ መሆን ላነሳነው ሀሳብ ማጠናከሪያነት ያገለግለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ግን ሀገራችን ከእነዚህ ውድ ልጆቿ ተገቢውን ዋጋ አለማግኘቷ ነው፡፡ ሀገራችን የወላድ መካን እየሆነች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚቀነባበር ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ብትሆንም ቅሉ በተከታታይ ስልጣኑን የጨበጡት ጭፍን አንባገነኖች በሚያራምዱት አግላይ ምሁር ፖሊሲ ምክንያት እውቀታችሁን እና … [Read more...] about ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!
አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ
የሰው ልጅ ግላዊና ማህበራዊ ህይወቱን ለማሻሻል እንዲሁም የለት ተለት ህይወቱን የተሻለ ለማድረግ በአካባቢው ወይም በሚኖርበት ሃገር ያለውን አካባቢያዊና መንግስታዊ ስርዓት ጤናማ መሆኑ ግድ ነው። የማህበረሰቡም የለት ተለት ህይወት ከግዜ ወደ ግዜ አስቸጋሪ እየሆነ ሲሄድ የዛ ማህበረሰብ መንግስት ወይም አገዛዝ መቀየሩ አንደኛው መፍትሄ ነው። እንደሁለተኛ አማራጭ መፍትሄ የሚወሰደው ደግሞ የነበረውን አገዛዝ ለአነስተኛና ከፍተኛ ለውጦች ካለው ምቹነት አንፃር ተመዝኖ አስፈላጊ የሚባሉ የፖሊሲና የመንግስታዊ አወቃቀር ለውጦችን መተግበር ሲሆን ይህም በሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ጥሩ ሊባል የሚችል ለውጥ ሲያስገኝ ተስተውሏል። ነገር ግን ወደ ሃገራችን መንግስት ስንመጣ ከበድ ያሉ የማስተካከያ መፍትሄዎችን ቀርቶ እጅግ አነስተኛ የሚባሉ የማህበረሰብ የመብት ጥያቄዎችን እንኳን በሃይል በመጨፍለቅ … [Read more...] about አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ
ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም
"የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።..." የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልእክት ያላጋጠመው ቢኖር ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ። አስር ለሚያህሉ አርሶአደሮች እና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ደውለው አልተሳካለቸውም። ለሁሉም ጥሪ ያገኙት ምላሽ "የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።" የሚል ሲሆንባቸው ራሳቸውን ነቀነቁ። ሰው ሁሉ የጨከነባቸው መሰላቸው። እንዲህም አሉ። "የሃገሬ ሰው እንኳን የስልክ ጥሪ፤ የእናት ሃገር ጥሪስ መች ተቀበለ።" ለአመታት በተከታታይ በሁለት ድጅት እያደገች ያለች ሃገር የስልክ መስመር ችግር ይገጥማታል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ችግሩን በደንብ ላልተረዳው፣ ሰው የሞባይል ስልክ የሚገዛው እንዲሁ ይዞ ለመታየት ነው ያስብል … [Read more...] about ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም










