ወቅታዊው የቴሌቭዥናችን አዝማች፤ ... ሰማንያ አንድ ዜሮ ዜሮ- ኤ ብለሽ መላዕክት ከላልሽ፣ አባይን ገድበሽ ሽልማት በሽበሽ። .... 8100 .... 8100 .... 8100-A A A የምትለው ዜማ በብዛት ትለቀቃለች። ኮሜዲያን ተሰብሰበው የሰሩዋት ዜማ ናት። ቀልደኞቹን ማኖ ለማስነካት ተብላ የተቀነባባረች ነገር ናት የሚሉም አሉ። የቴሌቭዥኑን ጣብያ ከፍቶ የሚመለከተው ሰው እጅግ ጥቂት ቢሆንም መልእክቱ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መደመጡ አልቀረም። የዚህ ማስታወቅያ አላማ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የእጣው ዝርዝር ግን ለብዙዎች እንግዳ ሳይሆን አልቀረም። አንዲት አዛውንት የልጃቸውን ተንቀሳቃሽ ስልክ እያነሱ ይቀጠቅጣሉ። በሳምንት ሶስቴ 8100 እየደወሉ 'A' ፊደልን ይጫናሉ። ከብዙ ግዜ በኋላ ታዲያ ልጃቸው አወቀባቸው። በመገረምም ለምን ይህንን ሁሉ ግዜ መደወል እንደፈለጉ ጠየቃቸው። … [Read more...] about “ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ”
Left Column
የኢትዮጵያ ጉዳይ
ግልፅ ደብዳቤ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ሀገር ማለት ባሕርዳር ዛሬም ስለልጆቿ አነባች የአምባገነኖች አከርካሪ በተባበረ የሕዝብ ክንድ ይሰበራል በሴቶች ላይ የሚፈጸም በደልና ጾታዊ ጥቃት ይቁም ኢትዮጵያዊነት በዘር ማንነት አይደበዝዝም ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገው ትግል በቀላሉ አይቀለበስም ፖሊስና ሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ መጽሔቷ በእነዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ታተማለች፡፡ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ
“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” ይላል
“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል” የሚለው ጥሬ ንባብ፤ ስለ ጅብና ስለ ቁርበት መልእክት ለማስተላለፍ አይደለም። ጅቡ የሚወክለው አካል አለ። ቁርበቱ የሚወክለው ነገር አለ። በቁርበቱና በጅቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ሳያውቁ ቁርበቱን ለጅቡ ያነጠፉለትም የሚወክሉት አለ። ይህ አገላለጽ በኢትዮጵያዊው ቅኔ ትምህርት፣ ቀመር፣ ስልት ሲመዘን፤ ጅቡ ሰም ነው። ቆርበቱም ሰም ነው። ሁሉም ሰም ነው። ወርቁ ከሰሙ ጋራ ጎን ለጎን ባለመቀመጡ፤ ወርቅ የጎደለው ‘ሰማ-ሰም’ ይባላል። ወደ ጠቅላላ ይዘቱ ስንገባ፤ በጅብና በቁርበት መካከል ያለው ግንኙነት፤ በተበይና በበይ መካከል ባለው ግንኙነት ብቻ ሳይወሰን፤ የተደራረበ ሰይጣናዊ የአጠቃቀምን ዘዴ ይጠቁማል። ጅብ ቁርበቷን እንደሚበላት በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበቷን ‘አንጥፉልኝ ’ እንደሚል፤ አንዳንድ ሰዎችም በሚታወቁበት … [Read more...] about “ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” ይላል
ዘጸአት ለኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ምድር፥ ምኒልክን (ዮሴፍን) 'ማያውቅ፥ አዲስ ንጉሥ መ'ቶ፣ "ለነፃነት" ብሎ፥ የነፃነትን ጧፍ፥ ረጋግጦ አጥፍቶ፣ "ከኔ ወዲያ ላሳር!"፥ አለን አፉን ሞልቶ፣ ያ'ባቶችን ክብር፥ አፈር መሬት ከ'ቶ። ያገሬ ፈርዖን፥ ልቡ እጅግ ደንድኖ፣ የፈጣሪን ፈቃድ፥ እንዳይሰማ ሆኖ፣ "እንደ'ኔ ያለ ንጉሥ!"፥ እያለ ይጽናናል፣ የበትሩን ምሬት፥ በጠገበ ጉልበት፥ ከተማን ያጸናል። ስንት አሮን ተላከ? ስንት ሙሴ መጣ? "የሠራዊት ጌታ፥ 'ህዝቤን ልቀቅ' ይላል!"፥ የሚል ቃል ሊያወጣ፣ ስንት ምርጫ ሆነ፥ ስንት ምርጫ ሄደ፣ ደንዳናው ፈርዖን፥ በህዝብና ፍትህ፥ እንደተጓደደ። ምልክቶች ታዩ፥ ታምራትም መጡ፣ ፈተናው ጸና እንጂ፥ የእብሪተኞችን ልብ፥ ቅንጣት አ'ለወጡ። የባሰው መጣና፥ የ'እብራውያን' በኩር፥ እየተሰደደ፣ መልአከ ሞት ጥላ ፥ 'የፈርኦንን በኩር'፥ … [Read more...] about ዘጸአት ለኢትዮጵያ
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ
ፌብርዋሪ 14, 2015 በኖርዌይ የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ 3ኛ እና 4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የሥራ ክንውን ሪፖርት የቀረበበት የተሳካ አጠቃላይ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎና በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ የድርጅቱ አባላቶች የተገኙ ሲሆን የአባላት ስብሰባው አስቀድሞ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በኖርዌጂያን የሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ 13፡30 ተጀምሮዋል። ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አቢ አማረ በ 24 ዓመት የወያኔ አረመኒያዊ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉት እና በየእስር ቤቱ በግፍ ለሚስቃዮ ንጹሀን ዜጐች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጹሎት በማድረግ ስብሰባውን ያስጀመሩ ሲሆን በመቀጠልም … [Read more...] about የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ
ሀብታችን ነጻነት እንጂ ባቡር አይደለም!
አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን ቆጥሮ በብልጭልጭ ነገር እያባበሉ ማስተኛትን ይመስላል። መጽሀፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር እንደ ብርሀን መልዐክ ለመግደልና ለማሳሳት ራሱን ይለውጣል ይላል። ታዲያ ቢያብለጨልጭ ለመግደል ብቻ መሆኑ ደግሞ ሊታሰብበት ይገባል። ስለ ሶርያ ጥቂት ነገር እናንሳ። ጥንታዊ እና ስልጣኔ የጀመረባት ሀገር እንደነበረች በከብት እርባታ እና በእርሻ ዘመናዊ ሁኔታዎች የበቀሉባት ስለመሆንዋ ተወስቶላታል። … [Read more...] about ሀብታችን ነጻነት እንጂ ባቡር አይደለም!
ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን)
ቫላንታይንስ ዴይ (ፍቅረኞች ቀን) ከወደ ምዕራቡ ከተዋስናቸው ወይም ከተጫናቸው በዓላት አንዱ ነው፡፡ ይህ በዓል በእኛ ዘንድ አሁን ያገኘውን ያህል ተቀባይነት እንዲያገኝ ከማድረግ አንጻር የብዙኃን መገናኛዎች በተለይም የኤፍ ኤም ሬዲዮዎች(ነጋሪተ ወጎች) ዐቢዩን ሚና ተጫውተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የብሔራዊው የብዙኃን መገናኛውና ሌሎች የሬዲዮ (የነጋሪተ ወግ) ጣቢያዎችም እንደዚያው ቁምነገሬ ብለው ይዘውታል፡፡ የብዙኃን መገናኛዎች በተለይም የኤሌክትሮኒክሱ (በአየር ሞገድ የሚሠራጨው) በመልካም ጎንም ይሁን በመጥፎ ጎን ለሚመጣ ውጤት ታላቅ ጉልበት አላቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ባጠቃላይ ለደረሰብን የባሕል ወረራና ጥቃት በዚህ የብዙኃን መገናኛ ከበጣም ጥቂቶቹ በስተቀር “የመዝናኛ ዝግጅት” በሚል ሥያሜ የአየር ሰዓት የወሰዱ እንደዜጋ የሀገርንና የሕዝብን እሴት ሀብት የመጠበቅ ኃላፊነትና … [Read more...] about ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን)
ኢትዮጵያ ውስጥ የስፖርት ጋዜጠኛ ወይስ ተርጓሚ ነው ያለው?
“የምን ማራዶና የምን ፔሌ ፔሌ እኛም አገር አለ ገብረመድኅን ኃይሌ” ደምሴ ዳምጤ ጎልታ የምትጠቀስለት መንቶ ግጥሙ ነበረች፡፡ ለአገሪቱ ስፖርት ዕድገት በተለይም እግር ኳሱ እንዲያብብ በሙያው ያደረገው ጥረት ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ክሂላቸው ከማንም እንደማያንስ በማንፀባረቅ ነበር፡፡ በ1970ዎቹ መጨረሻና በ80ዎቹ መጀመርያ ጎልተው ወጥተው የነበሩት እነሙሉጌታ ከበደ፣ ሙሉጌታ ወልደየስ፣ ገብረመድኅን ኃይሌን ሲያወድስ ገጣሚ ሆኖ በመገኘት ነበር፡፡ ስፖርት እንደ አንድ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ጉዳይ ራሱን የቻለ ሰፊ ርዕሰ ጉዳይ እየሆነ የመጣ ሲሆን ሊሰጠው የሚገባው ግምትም ያን ያህል እየከበደ መጥቷል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ጉዳዮች ብቻ የሚተነትኑ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዳሉ ሁሉ ስፖርታዊ ጉዳዮችን ብቻ የሚተነትኑ ጋዜጦች፣ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ውስጥ የስፖርት ጋዜጠኛ ወይስ ተርጓሚ ነው ያለው?
Ethiopia-visions of the final battle
We all should thank the Central Committee of Tigrai Peoples Liberation Front for making things a little clearer in our country. When election season is close the TPLF removes all pretenses and makes itself visible to the citizen of Ethiopia. The picture is not pretty. Their latest bold move to delete and erase Andenet is no matter how you look at it a most daring act worthy of the late visionary dictator. It was illegal, some would say irrational but vintage TPLF. If you really want to know … [Read more...] about Ethiopia-visions of the final battle
ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት
ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣ ትውልድ ለሚላቸው የሚበጅ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ይነግረናል፤ ይነግሩናል። ውስን ባለሥልጣናትና አበሮቻችው በሃብት ተመንድገዋል። በንዋይ ሰከረው የሚያደርጉት እስኪጠፋቸው ናጥጠዋል። የት ጋር አንደሚያበቃ ባይታወቅም፣ የተደሰቱ፣ የተከፉ፣ የተናቁ፣ የተሰረቁ፣ የሚሰረቁ፣ እየሰረቁ ያሉ፣ የተትረፈረፈላቸው፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ ባሪያዎችና ባንዳዎች፣ ቀን የሚጠብቁ፣ ጥርሳቸውን የነከሱ፣ ... ወዘተ “አብረው” አሉ፡፡ ዘመን፣ ወራትና ቀናት ቅዠትን በመሰሉበት ዓለም፣ ቁራሽ ለሚሞላው ከርስ ራሳቸውንና ማንነታቸውን፣ ከዚያም አልፎ የትም የማይደበቁትን ኅሊናቸውን ያቆሸሹ፣ የአገር “እንግዴ ልጆች” ወይም “ውርጃዎች” ለህወሃት የማከሰምና የመግደል ሴራ ተላላኪ ሆነው የህዝብን ክብር ሰልበው ረክሰው ያረከሳሉ። ከዚህም በላይ … [Read more...] about ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት










