ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአፍሪካውያንን ህልውና እየተፈታተኑ ካሉ ጉልህ ችግሮች መካከል ኣሸባሪነት ዋና ጉዳይ ሆኗል። ISIL በሊቢያ፣ ኣልሸባብ በምስራቅ ኣፍሪካ፣ ቦኮሃራም በምእራብ ኣፍሪካ በከባድ ፍጥነት እያደጉ ነው። አፍሪካውያን ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሽብር ስራዎች ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያነሱ የሚገባበት፣ ህዝቦች ግንዛቤያቸውን በማስፋትና የዚህን ኣሸባሪ መንፈስ ሊዋጉ የሚገባበት ሰዓት ላይ ነንና እኛ ኢትዮጵያውያን በዚህ ጉዳይ ላይ በጽኑ መወያየት ያሻናል። በተለይ ወጣቱ በኣህጉራችን ስላለው የሽብር እንቅስቃሴ በሚገባ ሊረዳ ይገባዋል:: መምህራን አፍሪካ ውስጥ ስላጠላው የሽብር ጥላ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ኖሯቸው ተማሪዎቻቸውን ሊያስተምሩ ይገባል። ወደ ዋናው ውይይታችን እናምራ። ስለ ሽብርተኞች ሲነሳ የሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ይኖራሉ። ለመሆኑ እነዚህ ኣሸባሪ ቡድኖች ምንድነው … [Read more...] about ሃራም ቦኮ ሃራም – ሃራም አልሸባብ
Left Column
“ሙዚቃ መምራትን ለዓለም ያስተዋወቀችው ኢትዮጵያ ናት”
ሙዚቃን በተለየ መንገድ በማዋሐድ ሙላቱ አስታጥቄ የሙዚቃ ሳይንቲስት መሆኑን በአምስት አሠርታት የሙዚቃ ጉዞው ውስጥ አስመስክሯል፡፡ የተለያዩ ቅላፄዎችንና ምቶችን ከተለያዩ አፍሪካ አገሮች፣ አሜሪካና አውሮፓ ሙዚቃ በመውሰድና በማጣመር አዲስ የሆነ ሙዚቃንም ለዓለም አበርክቷል፡፡ የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪው ሙላቱ አስታጥቄ የሙዚቃ ትምህርቱን ያጠናው በለንደን፣ ኒውዮርክና ቦስተን ከተሞች ሲሆን፣ የራሱን የሆነ የሙዚቃ ስልት ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅኝቶች ጋር አጣምሮ ኢትዮ ጃዝን ፈጥሯል፡፡ በቀላሉ በዓለም አቀፍ ሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ጆሮ ማግኘት የቻለው ሙላቱ ከመቶ ሺሕ በላይ የሚሆኑ ታዳሚዎችም ኮንሠርቱን ለማየት መሽቀዳደም የተለመደ ሆኗል፡፡ ከሙዚቃ ክህሎቱም በተጨማሪ በጥንታዊ ሙዚቃዎች ላይ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ምርምሮችንም በማካሄድ ነው፡፡ የአምስት አሠርታት የሙዚቃ ጉዞውንም በተመለከተ ከሪፖርተሩ … [Read more...] about “ሙዚቃ መምራትን ለዓለም ያስተዋወቀችው ኢትዮጵያ ናት”
እግርና ጫማ
እግርና ጫማ ተጣብቀው አንድ ላይ በክር ተሳስረው አብረው ውለው ስታይ እውነት አይምሰልህ ያ ሁሉ ፍቅራቸው ሲመሽ ወደማታ ሄደህ ብታያቸው በአንሶላ መካከል እግር ተዘርግቶ ጫማ በራፉ ላይ ወድቋል አፉን ከፍቶ! … [Read more...] about እግርና ጫማ
«የእሣት ልጅ አመድ» የሆነው የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ማንነቱን ያስከብር!
ከዛሬ ሰማኒያ ዓመታት በፊት የነበሩት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን እና እናቶቻችን፣ ከትግራይ እና ከኤርትራ ምድር በበቀሉ ባንዶች አጋዥነት በፋሽስት ጣሊያኖች ጦር ማይጨው ላይ ድል ሲመቱ «እሺ፣ አሜን፣ እንገዛለን» ብለው እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም። ራሣቸው ፋሽስቶችም እንዳመኑት፥ በተለይ በሰሜን ሸዋ፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በጉራጌ፣ በጅባት እና ሜጫ እንዲሁም በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የነበሩት አርበኞች በመረጧቸው የጎበዝ አለቆቻቸው እየተመሩ፣ ለአምሥት ዓመታት የፋሽስት ጣሊያንን ጦር ከእነ ባንዳ ግሣንግሱ መውጫ መግቢያ አሣጥተውታል። ከዚያም ከየካቲት 1933 ዓም ጀምረው ጀግኖች አርበኞቻችን ባደረጉት የተቀነባበረ የጥቃት ዘመቻ ልክ የዛሬ 75 ዓመት ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓም በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ መሪነት በድል አድራጊነት ዋና ከተማችንን አዲስ አበባን ለመቆጣጠር … [Read more...] about «የእሣት ልጅ አመድ» የሆነው የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ማንነቱን ያስከብር!
የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው?
ጥያቄ አለኝ፥ የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው? ዛሬ ያላቅሜ አንድ ጥያቄ ማንሳት ከጅያለሁ። ለነገሩ ዶክተር ያልተጠየቀ ማን ይጠይቃል? እናም ዶክተርን ልጠይቅ ነው። ዶክተር መሳይ በኢትዮጵያ የዘውግን ፖለቲካ የጀመረው ማነው? ዶ/ር መሳይ ከበደ፥ የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ፥ በሚል ርእስ በአንድ መድረክ አቅርቤው ነበር ያሉትን ፅሁፍ በዚህ ድረ-ገፅ ላይ አውጥተው አስነብበውናል። እንደውነቱ ከሆነ በመድረኩ ተገኝተን ፅሁፋቸውን ለመከታተል እድል ላላገኘን ሰዎች በረከቱን ስላሳተፉን አመሰግናለሁ። ግን ጥያቄ አለኝ። ለጥቂቶች ስውር የስልጣን ጥም ማርኪያ፣ ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ደግሞ የህልውና ፈተና የሆነውን የዘውግ ፖለቲካ በዚያች አገር የተከለው ማነው? ህወሃት ወይስ አማራ? ለችግሩ መፍትሄው ክልሎችን ማጥፋት ሳይሆን ራስ ገዝ ማድረግና ስልጣን መስጠት ነው … [Read more...] about የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው?
የሲቪሉ ሰራተኛ ኑሮ በሁለቱ ዘመናት
ከ25 ዓመታት በፊት አንድ የኮሌጅ ዲፕሎማ የነበረው አስተማሪ ሲቀጠር የመነሻ ደመወዙ 347 ብር ነበር። ይህን ገቢ በወቅቱ ከነበረው የዶላር ምንዛሬ አንጻር ስናየው 173.5 ዶላር ይመዝን ነበር። ይህ አስተማሪ ገና ሲቀጠር የቀን ገቢው 5.8 ዶላር ነበር ማለት ነው። ከፍ ያለ ነበር። ከ25 አመት “እድገት” በሁዋላ በህወሃት ኢህዓዴግ ዘመን አንድ የኮሌጅ አስተማሪ ዲፕሎማውን ይዞ ሲቀጠር 1663 ብር ቢከፈለው አሁን ባለው ምንዛሬ ሲታይ 77.3 ዶላር ያገኛል። ይህ ማለት የቀን ገቢው በዶላር 2.57 ሳንቲም ነው ማለት ነው። ይህ ማለት የደርግ ጊዜው አስተማሪ ደመወዝ ከህወሃት ኢህዓዴግ ጊዜ አስተማሪው ደመወዝ ከሁለት እጥፍ በላይ ይበልጣል ማለት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የድህነት ወለል የሚባለው ሁለት ዶላር አካባቢ ሲሆን ይህ በህወሃት ኢሃዴግ ዘመን የኮሌጅ ዲፕሎማ የያዘው አስተማሪ … [Read more...] about የሲቪሉ ሰራተኛ ኑሮ በሁለቱ ዘመናት
ብክነትና ምክነት
በኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ የሚያባክን ማን እንደሆነ እናውቃለን። ጊዜም የሚያባክነው ማን እንደሆነ ሳናውቅ አንቀርም። እንዲሁም ወንድና ሴት እንደየተፈጥሯቸው እንዳይወልዱ የሚያመክናቸው ምን እንደሆነ አሳምረን እናውቃለን። አንናገርም እንጂ። ምሁራንንስ የሚያባክንንና የሚያመክን ማነው? ጎበዝ ማለት ይህን የሚያውቅ ነው። እኔም ማወቅ የምፈልገው ያገሬን ምሁራን የሚያባክንብኝና የሚያመክንብኝ ማን እንደሆነ ነው። ሰሞኑን ያዲስ አበባው መንግስት ቀለም ቀለም ሲሸተው ጊዜ እኔንም እንዲሁ ቀለም ቀለም ስለሸተተኝ ስለምሁራን ብንጫወት ምናለ ብዬ ለዛሬ ቁም ነገሬ እንዲሆን መረጥኩት፤ የኢትዮጵያ ምሁራን ጉዳይ፤ በተለይ ያቋማቸውና የጥቅማቸው ጉዳይ። በይበልጥ ደግሞ እንዲያው እንደዋዛ የመባከናቸው ነገር። ባክነዋል እንዴ? ካላችሁ መልሴ እንክት ነዋ! የሚል ነው። ላስረዳ። የምናገረው ባሁኑ ወቅት … [Read more...] about ብክነትና ምክነት
የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ
ይህ ጽሁፍ በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ ያቀረብኩት ነው። የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በሠላም ወይም በኃይል ከሥልጣን ለማውረድ ቢችሉም እንኳን፤ ባለፉት 24 ዓመታት የተዘረጋውን ዘውጋዊ ክፍፍል ለማብረድና ብሔራዊ አንድነትን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ራዕይና ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚስተዋሉት ችግሮች ሁሉ ተቀዳሚና እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ዘውጋዊ ፖለቲካ በመሆኑ ያለውን መንግሥት ለመጣልና አዲስ ሥርዓት ለመመስርት ስለ ዘውግና ዘውጋዊ ፖለቲካ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘትን ይጠይቃል። ወያኔ ከተሸነፈ የዘውግ ፖለቲካ በራሱ ይጠፋል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት ነው። ይህ ጽሁፍም “የዘውግ ፖለቲካ ዋና ዓላማ ምንድን ነው? ከብሔራዊ አንድነት ጋር በምን ሁኔታ ሊጣጣም … [Read more...] about የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ
The Width And Depth of The Leadership Gaps Ethiopia Faces
Following my presentation entitled “Bridging The Leadership Gap: For smooth transition and successful post conflict Ethiopia” on March 26, 2016 at Georgetown Marriott Hotel in Washington DC, some audience members chatted with me afterwards, and gave me some feedbacks. While many of them recognized the gap and glad that it was discussed at this conference, some of them challenged whether the elephant in the room is a leadership gap after all.Since the time allotted to each speech was 20 minutes … [Read more...] about The Width And Depth of The Leadership Gaps Ethiopia Faces
የታፈነ ሁሉ ይፈነዳል! የተከለከለም ይጣፍጣል!!
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የታፈነ ሁሉ ይፈነዳል! የተከለከለም ይጣፍጣል!!










