የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፈንታ አጨልመን እንድናይ ከሚያስገድዱን ሁነቶች ውስጥ ለእስልምና ሃይማኖት የትኞችም አይነት ጥያቄዎች በአገዛዙ በኩል እየተሰጡ ያሉ አሉታዊ ምላሾች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሐምሌ 27/2007 ዓ/ም የተላለፈው “የፍርድ ውሳኔ” ኢሕአዴግ የሚል ገዥ መደብ እስልምናን በምን ያህል መጠን አፍኖ እየገዛ እንዳለ የአደባባይ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል፡፡ በኮሚቴው አባላት ላይ የተላለፈውን “የፍርድ ውሳኔ” ከሃይማኖታዊ መነጸር ባሻገር ጉዳዩን ከፍትህና ከሞራል ልዕልና አኳያ ማየት ተገቢ ነው፡፡ የዚህ አጀንዳ ቀዳሚ ጉዳይ የኮሚቴውን አመሰራረት በማስታወስ የፍርድ ሂደቱን በመጠኑም ቢሆን በመቃኘት የኮሚቴ አባላቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ በተመለከተ ሦስት የሚሆን እድል (Scenarios) በማስቀመጥ ማሳየት ይሆናል፡፡ የንቅናቄው … [Read more...] about ታሪክ የማይረሳው የኮሚቴዎቹ ስቅየት
Full Width Top
ኢህአዴግ በኤርትራ አራት አቅጣጫዎች ጥቃት ሊሰነዝር አስቧል
ኢህአዴግ በአራት አቅጣጫዎች የጦር ጥቃት ለመሰንዘር ማሰቡ ተሰማ፡፡ ይኸው ሃሳብ ለአሜሪካ ቀርቦላታል፡፡ በቅርቡ የተጠናከረ እንቅስቃሴ የጀመረው የአርበኞች ግንቦት ፯ ኃይል በተደጋጋሚ በሚያወጣው መረጃ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ማድረሱን በይፋ ቢገልጽም ኢህአዴግ ጥቃቱን በቀጥታ ለማስተባበል እስካሁን አልወደደም። ይሁን እንጂ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ “ህዝብ አስፈቅደን” ሲሉ ኤርትራን እንደሚወጉ ይፋ አድርገዋል። አብዛኞች እንደሚስማሙበት ዛቻው ግጭት ስለመኖሩ የሚያረጋግጥ ነው። በሌላው አንጻር ደግሞ ይህንን የሃይለማርያም ንግግር የኤርትራው ሹም በዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የተለመደ የህወሃት/ኢህአዴግ ማስፈራሪያና ዛቻ በማለት አጣጥለውታል፡፡ የግጭቱን ደረጃና በኢህአዴግ ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ኢሳት ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ኤርትራን መውቀሰና ማስፈራራት የጀመረው ኢህአዴግ፣ … [Read more...] about ኢህአዴግ በኤርትራ አራት አቅጣጫዎች ጥቃት ሊሰነዝር አስቧል
የአብዮቱ አይቀሬነትና ጥቁምታዎቹ!
በፖለቲካ ሳይንስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “አብዮት” የሚለው ቃል “አዲስ ሥርዓትን በመሻት የነባሩን መንግስታዊ ወይም ማህበራዊ ሥርአት በግዳጅ ማስወገድ” በሚል የትርጉም ማዕቀፍ ላይ ሊያርፍ ይችላል፡፡ ‹የሰው ልጅ አብልጦ የሚሻው የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት በየአገራቱ አስካልተመሰረተ ድረስ አብዮት በየትኛውም የዓለም ክፍል አይቀሬ ክስተት› እንደሆነ የፖለቲካ ሳይንስ መምህራኑ አብዝተው ያስተምራሉ፡፡ ሰሚ የለም እንጂ፡፡ ኢህአዴግ የሚባል ገዥ መደብ ፣ ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል አገሪቱን እንደ “መንግስት” በመራበት ተራዛሚ የአገዛዝ ዘመኑ ከፍ ሲል ከአምሮ በላይ የሆኑ፣ ስልጣን ላይ በወጣ ስብስብ ይፈፀማሉ ተብለው የማይታሰቡ ውስብስብ የፖለቲካ ሴራዎችን በመስራት ያደረሰው ሰብአዊ ውድመት፤ ዝቅ ሲል ደግሞ ከሰውነት በታች በወረደ የዝቅተኝነት ስሜት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው የማህበረ ኢኮኖሚ … [Read more...] about የአብዮቱ አይቀሬነትና ጥቁምታዎቹ!
ቴድሮስ አድሃኖም “ኢህአዴግ ቂመኛ አይደለም” አሉ
የኢህአዴግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም “ኢህአዴግ ቂመኛ አይደለም” ሲሉ ከቪኦኤ አማርኛው ክፍል ባልደረባ ትዝታ በላቸው ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስታወቁ። ሚኒስትሩ ድርጅታቸውን ከደርግ ጋር በማነጻጸር ከቂም የጸዳ እንደሆነ ሲያስረዱ ጋዜጠኛዋ አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ በቂም በቀል ስለተፈጸመውና እየተፈጸመ ስላለው ግፍ ጥያቄ አላቀረበችም። ሚኒስትሩ ኢህአዴግ በህግ የበላይነት ስለማመኑ በመረጃ አልተሞገቱም። በዘር፣ በብሄርና በጎሳ ላይ ተንጠልጥሎ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ የቆየው ኢህአዴግ፣ በ፩፱፰፫ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በገሃድ አማርኛ ተናጋሪዎችን ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር በማናከስ፣ ቂም በማቋጠር፣ የስርአተ ማህበሮችን ችግሮች ከነፍጥ ጋር በማያያዝ እያላከከባቸው፣ “ነፍጠኛ” የሚል ስም በመስጠት የህዝብ ንብረት በሆነው መገናኛ የጥላቻ ዘመቻ በማራገብ … [Read more...] about ቴድሮስ አድሃኖም “ኢህአዴግ ቂመኛ አይደለም” አሉ
ኦባማ፡ “በንግግር (ወሬ) A፣ በተግባር D” ኦባንግ ሜቶ
ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ውጤት ቢሰጥ በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው በንግግር (በወሬ) ደረጃ A በተግባር ግን D እንደሚሰጧቸው ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ፡፡ አፍሪካውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ምዕራባውያን ዕንቅፋት ከመሆን እንዲቆጠቡ አስረዱ፡፡ በአሜሪካ ድምጽ የStraight Talk Africa አዘጋጅ ሻካ ሳሊ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን የአፍሪካ ጉብኝት በተመለከተ ከሁለት ቀናት በፊት ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ሦስት አፍሪካውያንን ተጋብዘው ነበር፡፡ ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ የሴራሊዮኑ ፕሮፌሰር አብዱል ካሪም ባንጉራ፣ የአፍሪካ ስደተኞች ስብስብ ኃላፊ ጋናዊው ኒ አኩቴ እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር ኢትዮጵያዊው ኦባንግ ሜቶ ነበሩ፡፡ በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው ለፕሬዚዳንቱ ምን ውጤት ትሰጣላችሁ በማለት ሻካ ላቀረበው ጥያቄ ዶ/ር አብዱል D … [Read more...] about ኦባማ፡ “በንግግር (ወሬ) A፣ በተግባር D” ኦባንግ ሜቶ
ኢትዮጵያ ከ184 አገራት 171ኛዋ ደሃ አገር!
ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የአምስት ዓመታት አኻዝ ያካተተ የዓለማችንን ሃብታምና ደሃ አገራት ዝርዝር ሰሞኑን አውጥቷል፡፡ የዓለም የፋይናንስ መጽሔት ላይ የታተመው ይኸው ዘገባ እንደሚያሳየው በሃብታምና ደሃ አገራት መካከል ያለው ልዩነት በእጅጉ እየጨመረ እንደመጣ ነው፡፡ በዚህ የአምስት ዓመት አኻዛዊ ዘገባ መሠረት ከ184 አገራት መካከል ኢትዮጵያ 171ኛ ተራ ላይ የምትገኝ ስትሆን ይህም በድህነት ከሚጠቀሱት ቀዳሚ አገራት ቁጥር ውስጥ አስገብቷታል፡፡ ዘገባውን የተመለከቱ የኢኮኖሚ ባለሙያ የአንድ አገር ኢኮኖሚ በከተሞች ውስጥ በሚሰራ ፎቅ ብዛት እና የመንገድ ሥራ አይለካም ይላሉ፡፡ ሌላ የኢኮኖሚ ባለሙያ ደግሞ “ኢኮኖሚ ከቁጥር ሌላ ሥነ ልቦናዊ ጉዳይም ነው፡፡ የኑሮ ጉዳይም ነው፡፡ የጉሮሮ ጉዳይም ነው፡፡ በቁጥር ብቻ አይለካም፡፡ … የሕንፃ መሐንዲስ ቢሳሳት ሕንፃ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ከ184 አገራት 171ኛዋ ደሃ አገር!
የሸገር ወላጆች ምሬት Vs የግል ት/ቤቶች ቅሬታ
እንደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አህዛዊ መረጃ በመዲናዋ ውስጥ 1671 የሚሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ መረጃው ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ኮሌጅ መሰናዶ ድረስ ያሉትን የግል ትምህርት ቤቶች የሚያጠቃልል ሲሆን ፤ ትምህርት ቢሮው በ2006 የትምህርት ዘመን መጨረሻ ወራት ላይ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፣ በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የሚሆኑ ተማሪዎች ይማራሉ፡፡ ትምህርት ቢሮው የ2007 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ አህዛዊ መረጃ አጠናቅሮ በድረ ገፁ ይፋ ባያደርግም ቁጥሩ ካለፈው የትምህርት ዘመን ሊልቅ እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም ከሚጠናቀቀው የሚሊንየሙ የልማት ግቦች አንዱ የሆነውን ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ዕድሜቸው ለትምህርት ለደረሱ ህፃናት የማዳረስ ዕቅድ ያላት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሚሊንየሙን የልማት ግቦች … [Read more...] about የሸገር ወላጆች ምሬት Vs የግል ት/ቤቶች ቅሬታ
የግፍ ሠንደቅ ወረደ!
በአሜሪካ የደቡብ ካሮላይና ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ የሸንጎ ሕንጻ ላይ ከ50 በላይ ሲውለበለብ የነበረው ሠንደቅ አርብ ወረደ፡፡ “ውሸት ለዘላለም መቆየት አይችልም፤ የዘረኝነት ምልክት እና ዘረኝነት መፍረስ ይገባቸዋል” በማለት የሠንደቁን መውረድ የደገፉ ተናገሩ፡፡ በእንግሊዝኛው አጠራር “የኮንፌዴሬት” ሠንደቅ የሚባለው በአሜሪካ የእርስበርስ ጦርነት ወቅት ከኅብረቱ ለመለየት የፈለጉ ግዛቶች የራሳቸውን ፕሬዚዳንት መርጠው ከኅብረቱ ደጋፊዎችና አብርሃም ሊንከን ጋር ጦር በገጠሙበት የተጠቀሙበት ሠንደቅ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት አብርሃም በአሜሪካ ውስጥ የተንሰራፋውን በዘር ላይ የተመሠረተውን ባርነት ለመደምሰስ ህግጋትን እያወጡ በነበሩበት ወቅት በባሪያ ፈንጋይነት የሚታወቁት የደቡብ ጠቅላይ ግዛቶች የባርነትን መወገድ በመቃወም ከኅብረቱ ለመገንጠል በመፈለጋቸው በአሜሪካ የእርስበርስ ጦርነት … [Read more...] about የግፍ ሠንደቅ ወረደ!
ይድረስ ለገራፊዎቻችን – እኛ የፀናነው እናንተንም ነፃ ለማውጣት ነው!
"በምርመራው ወቅት የነበረው ድብደባ እና ክብረ ነክ ስድብ ወደ ምድር የመጣሁበትን ቀን እንድረግም አደረጉኝ፡፡ በተለይ ከአሁን በኋላ ልጅ መውለድ እንደማልችል እየዛቱ የውስጥ እግሬን ክፉኛ ገረፉኝ፡፡ . . . እኔም ልብሴን እንደማላወልቅ ነገርኳቸው፡፡ በዚህም ከአሁን ቀደሙ ለየት ያለ ከባድ ድብደባ አስተናገድኩ፡፡ ድብደባው ከአቅሜ በላይ ሲሆን ግን ከውስጥ ሱሪዬ ውጭ ያለውን ልብሴን ለማውለቅ ተገደድኩ፡፡ የውስጥ ሱሪዬንም እንዳወልቅ አዘዙኝ፡፡. . . " ሐምሌ 5/2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ የክረምት መግቢያ መባቻ፣ ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ደግሞ የፆም ሐዋሪያት መፍቻ ነው፡፡ በዚች እለት እኔም እንደወትሮዬ በአካባቢዬ በምትገኝ አንዲት ካፌ ውስጥ ቁጭ ብዬ ከስርዓቱ አፈና የተረፉትን ጥቂት መጽሔቶች እና ጋዜጦች ላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ዜናዎችን ማንበብ ተያያዝኩት፡፡ በዕለቱ … [Read more...] about ይድረስ ለገራፊዎቻችን – እኛ የፀናነው እናንተንም ነፃ ለማውጣት ነው!
“ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ይጋቡ” ጠቅላይ ፍርድቤት
* “ፍቅር ፍቅር ነው” ኦባማ ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ጋር ጋብቻ መፈጸም ይችላሉ፤ ለእነርሱ የጋብቻ ሠርቲፊኬት መከልከል ሕገመንግሥቱን ይጥሳል በማለት የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መጋባት እንደሚችሉ ወሰነ፡፡ ለጋብቻ ቅድስናና ክቡርነት የሚከራከሩ “የእግዚአብሔርን ሕግ ምድራዊ ፍርድ ቤት ይህን መለወጥ አይችልም” በማለት ውሳኔውን አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡ በምንም መልኩ ይገለጽ ፍቅር ፍቅር ነው በማለት ፕሬዚዳንት ኦባማ ውሳኔውን ደግፈዋል፡፡ ዋናውን (ዓቃቤ ፍትህ) ጨምሮ ዘጠኝ የፍትህ ዳኞች የያዘው የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ የሰዶማውያን ጋብቻ ላይ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጉዳዩ ከቀረበለት ጊዜያት ተቆጥረዋል፡፡ በአሜሪካ የፍትሕ ሥርዓት ምዕራፍ ከፋች የተባለለት ውሳኔ አርብ ዕለት ሲተላለፍ የፍትሕ ዳኞቹ በአምስት ለአራት በመወሰን ነው ያጸደቁት፡፡ … [Read more...] about “ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ይጋቡ” ጠቅላይ ፍርድቤት










