• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦባማ፡ “በንግግር (ወሬ) A፣ በተግባር D” ኦባንግ ሜቶ

July 25, 2015 02:43 pm by Editor 2 Comments

ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ውጤት ቢሰጥ በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው በንግግር (በወሬ) ደረጃ A በተግባር ግን D እንደሚሰጧቸው ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ፡፡ አፍሪካውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ምዕራባውያን ዕንቅፋት ከመሆን እንዲቆጠቡ አስረዱ፡፡

በአሜሪካ ድምጽ የStraight Talk Africa አዘጋጅ ሻካ ሳሊ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን የአፍሪካ ጉብኝት በተመለከተ ከሁለት ቀናት በፊት ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ሦስት አፍሪካውያንን ተጋብዘው ነበር፡፡ ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ የሴራሊዮኑ ፕሮፌሰር አብዱል ካሪም ባንጉራ፣ የአፍሪካ ስደተኞች ስብስብ ኃላፊ ጋናዊው ኒ አኩቴ እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር ኢትዮጵያዊው ኦባንግ ሜቶ ነበሩ፡፡

በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው ለፕሬዚዳንቱ ምን ውጤት ትሰጣላችሁ በማለት ሻካ ላቀረበው ጥያቄ ዶ/ር አብዱል D እሰጣቸዋለሁ፡፡ ይህም በተለይ ከአፍሪካ ጋር ስላለላቸው ግንኙነትና እንዴት የአፍሪካ ፖሊሲያቸው ውጤት አልባ እንደሆነ በመመልከት ነው ብለዋል፡፡ ይህንን ያሉበትም ምክንያት በርካታ ሰዎችን በመጠየቅ ባደረጉት ጥናትና ምርምር እንደሆነ ሆኖም አሜሪካ ከኩባ ጋር ያላትን የሻከረ ግንኙነት በማለዘብ ደረጃ የተጫወቱ ሚና ከዚህ የወረደ ነጥብ እንዳያገኙ እንደረዳቸው ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡

ጋናዊው ኒ አኩቴ ግን ለኦባማ A እንደማይሰጡ ከተናገሩ በኋላ በዝርዝር ሳይጠቅሱ ፕሬዚዳንቱ ላከናወኑት ተግባራት ግን ተመጣጣኝ ነጥብ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በላይ ግን የትኛውም ነጥብ ይህ ነጥብ ወይም ደረጃ ለምንድነው የሚሰጣቸው ብሎ መጠየቅ ተገቢና አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡obang voa2

ኢትዮጵያዊው ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ውጤት ስጡ ቢባሉ “በንግግር (በወሬ) A በተግባር ግን D” እንደሚሰጧቸው ተናግረዋል፡፡ ይህንንም ሲያስረዱ ከዓመታት በፊት ጋናን በጎበኙ ወቅት “አፍሪካ የሚያስፈልጋት ጠንካራ መሪዎች ሳይሆን ጠንካራ ተቋማት” ነው ማለታቸውን ከጠቀሱ በኋላ “በአሁኑ ወቅት በአገሬ ያለው አገዛዝ በምርጫ መቶ በመቶ አሸንፌአለሁ” የሚል መሆኑን አውስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የተቋማት መቀጨጭ ወይም መምከን ምን ደረጃ እንደደረሰ ሲያስረዱም “በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት፣ ለሴቶች መብት፣ ለህጻናት መብት፣ ለዕርቅ፣ … መሥራት ሕግን እንደ መጣስ ተቆጥሮ” ለእስር እንደሚዳርግ አስረድተዋል፡፡ አሜሪካ የተመሠረተችባቸው እነዚህ እሴቶች በኢትዮጵያ ዋጋ የሌላቸው መሆኑን ሲገልጹ ዋንኛው ምክንያት ጠንካራ ተቋማት በኢትዮጵያ እንዳይኖሩ አገዛዙ የመያዶች ሕግ በመባል የሚታወቀውን በማወጅ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖርና ሊቃወሙት የሚችሉትን ሁሉ በሕገወጥነት በመፈረጁ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ከዚህ ሌላ በአገራቸው ጠንካራ ተቋም እንዳይመሠረት ዕንቅፋት የሚሆን የጸረ አሸባሪነት ሕግ በሥራ ላይ መዋሉን “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት በተመለከተ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ዋናው ዓላማ የአሸባሪነት ጉዳይ ተብሎ መጠቀሱ ኦባማ ለአፍሪካ ያላቸውን አመለካከት ያሳያል ብለዋል፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም የአፍሪካ መሪ ሕዝቡን እያሸበረ የአሜሪካንን ጥቅም እስካስከበረ ድረስ የዜጎች መብት መረገጥ ነገር ለአሜሪካም ሆነ ለምዕራባውያን ከጉዳይ እንደማይቆጥሩት የጋራ ንቅናቄው መሪ ኦባንግ አስረድተዋል፡፡ “ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ ጠንካራ ተቋማት መመሥረት የሚችሉ ብሩህ ኅሊና ያላቸው ጦማሪያንና ጋዜጠኞችና የነጻነት ድምጾች በአሸባሪነት ተፈርጀው በእስር የሚማቅቁት” በማለት ኦባማ በንግግር ደረጃ ለጠንካራ “ተቋማት መመሥረት ቢያወሩም በተግባር ግን የከሰሩ ናቸው፤ (የአፍሪካ ኅብረትን ሰብስበው ሲያናግሩም) የሚናገሩት ከጠንካራ መሪዎች ጋር ነው” ብለዋል፡፡

ኦባንግ ቀጠሉ “ዛሬ ኢትዮጵያ የምትተዳደረው በአፓርታይድ ዓይነት ዘረኛ አገዛዝ ነው፤ (ወደ አዘጋጁ ሻካ ሳሊ በመጠቆም) ለምሳሌ እኔና አንተ እዚህ አሜሪካ አገር በመጀመሪያ ሰዎች ነን፤ ወንድማማች ነን እንጂ ኢትዮጵያዊ ወይም ዑጋንዳዊ ተባብለን በዘርና በአካባቢ የተለያየን አይደለም፤ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ግን ይህ አይደለም፤ አንዲያውም በቅርቡ ከአሜሪካ የኔብራስካ ጠቅላይ ግዛት ወደ ኢትዮጵያ የሄደች አንዲት እህት መታወቂያ ካርድ ለማውጣት ስታመለክት ዘርሽ (ብሔርሽ) ምንድነው ተብላ ስትጠየቅ የሁለት ቅልቅል በመሆኗ ይህ ነው ብላ መናገር እንደማትችል፤ ኢትዮጵያዊ መሆኗን ብታስረዳም የግድ እንደሆነ ከኃላፊዎች ሲነገራት በማመልከቻው ቅጽ ላይ አማራ + ኦሮሞ = ______ በማለት እናንተው ሙሉት በሚል ክፍት አድርጋ ትታዋለች፤ (በኢትዮጵያ ሰው ከመሆንህ በፊት ዘርህ ይቀድማል) የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር – ህወሃት የሚባለው ከደርግ ለመታገል በረሃ ወረደ፤ ደርግ ከተወገደ በኋላ ኢህአዴግ በማለት ራሱን የቀየረ በመምሰል አሁንም (ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም) እየገዛ ይገኛል፤ ዛሬ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት በህወሃት ቁጥጥር ሥር ውሎ ዜጎች ይበረበራሉ፤ ሚሊታሪው፣ ኢኮኖሚው፣ ደኅንነቱ፣ በሙሉ በህወሃት ቁጥጥር ሥር ነው፤ በመሆኑም ኦማባ እስካሁን በኢትዮጵያ ላይ የተከተሉት ፖሊሲ ይህንኑ የሚደግፍና ከሕዝቡ ያልወገነ ነው” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አስረድተዋል፡፡

ጠያቂው ሻካ ሳሊ “እርስዎ ከበርካታ የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎችና ከፍተኛ የፖለቲካ ኃላፊዎች ጋር በየጊዜው ይገናኛሉ፤ ከእነዚህ ሰዎች ጋር በሚያደርጉት ንግግር ወቅት እነዚህ ባለሥልጣናት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ስላላት አቋም በተመለከተ ምንድነው የሚሉት” በማለት ለኦባንግ ላቀረቡላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “በየጊዜው የሚሉት በኢትዮጵያ ጠንካራ ተቃዋሚ የለም ነው፤ እኔ የማስረዳቸው ደግሞ አገዛዙ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር በስልት እንዴት እንዳደረገ ነው፤ ኢንተርኔቱን ተቆጣጥረውታል፤ ከሃያ ዓመታት በላይ መንግሥት የሌላት ሶማሊያ በኢትንተርኔት አጠቃቀም ኢትዮጵያን ትበልጣለች፤ በየጊዜው የሚነሱ የነጻነት ድምጾች ታፍነዋል፤ ታስረዋል፤ ኢትዮጵያውያን በውጪ መደራጀት ይችላሉ ሆኖም በአገር ውስጥ (ህወሃት) ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር አድርጓል” በማለት በየጊዜው ለሚያገኟቸው የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንደሚያስረዱ ጠቁመዋል፡፡

ፕ/ር አብዱል በተራቸው በሙያቸው ባደረጉት ጥናት ኦባማ ለአፍሪካ እጅግም የበጀ ወይም በዋንኘነት የሚጠቀስ ተግባር አለመፈጸማቸው ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር አብዱል ማመጣጠን እንዳለባቸው አዘጋጁ ሻካ ሳሊ በመጥቀስ ለአብነት ያህል በራሳቸው በፕ/ሩ የትውልድ አገር ሴራሊዮን የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ በመከላከል ኦባማ ያደረጉት አስተዋጽዖ ታላቅ እንደሆነ የሴራሊዮኑ ፕሬዚዳንት መናገራቸውን፣ እንዲሁም በላይቤሪያ ኦባማ የፈጸሙት ተግባር ተጠቃሽ እንደሆነ ፕሬዚዳንት ሰርሊፍ የመሰከሩ መሆኑን ከዚህም ባሻገር ወጣት አፍሪካውያንን ወደ አሜሪካ እየመጡ እንዲማሩ በማድረግ ለአህጉሪቱ የወደፊት ራዕይ የሚበጅ Young Africans Leadership Initiative (YALI) ፕሮግራም መመሥረታቸው ሊጠቀስ እንደሚገባው በቃለምልልሱ ወቅት አውስቷል፡፡

ፕ/ር አብዱል ከበፊቱ ጠንከር ባለ ሁኔታ እንዲያውም ፕሬዚዳንት ኦባማ በኬኒያም ሆነ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉብኝት የደመቀ አከባበርም ሆነ ዳንስና ጭፈራ እንደማያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱም ፕሬዚዳንቱ ለሥራ የመጡ ከሆነ ያላቸውን ጊዜ ሁሉ ምን መደረግ እንዳለበት በዝርዝርና ነጥብ በነጥብ ከአፍሪካውያን ጋር ጊዜያቸውን በሙሉ ማዋል ይገባቸዋል፡፡ ጊዜው የጭፈራና የዳንስ ሳይሆን የሥራና ተግባራዊ ለውጥ የሚታቀድበት ሊሆን እንደሚገባ ፕ/ር አብዱል አስረድተዋል፡፡

obang voa5“ፕሬዚዳንት ኦባማ ይህንን ፕሮግራም ቢመለከቱ ለእርሳቸው የሚነግሩት መልዕክት ምንድነው? ካሜራውን እየተመለከቱ መልዕክት አስተላልፉ” በማለት ሻካ ለኦባንግ ሜቶ ላቀረበላቸው ጥያቄ ጥቁሩ ሰው “ከሥልጣን ከለቀቁ በኋላ ስለሚቀጥለው ሌጋሲዎ የሚያስቡ ከሆነ እና መታወስ፣ መታሰብ የሚፈልጉ ከሆነ ሲታወሱ ሊኖሩበት የሚችልበት አንዱ መንገድ ለአምባገነኖች በሠሩት ተግባር ሳይሆን ለሕዝብ በሚያከናውኑት ሥራ ነው፤ የአፍሪካ ኀብረት 50ዓመታት እለፎታል በአኅጉሪቷ (ፖለቲካ) ላይ ያመጣው ይህ ነው የሚባል ለውጥ የለም፤ ስለዚህ በሕዝብ ላይ ኢንቨስት ያድርጉ፤ (ከሕዝብ ጋር ይቁሙ)፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማነቆ የሆኑት የጸረ አሸባሪነት ሕግ እና የመያዶች ሕግ እንዲሻሻሉ ወይም እንዲሻሩ ማድረግ ይችላሉና በዚህ ላይ ይሥሩ፤ በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት አሜሪካ እንዳደረገችው በኢትዮጵያም የሲቪክ ማኅበረሰቦች (መያዶች) በነጻነት እንዲንቀሳቀሱና ሕዝብን በማንቃት ረገድ ተግባራቸውን እንዲወጡ እርስዎም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ይቁሙ” በማለት በቀጥታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሲቀጥሉም “የኢኮኖሚ ዕድገት አለ ይባላል፤ የሚታይ እንቅስቃሴ አለ፤ መንገድ ይሠራል፤ ፎቅም ይገነባል፤ ሆኖም የኢኮኖሚን ዕድገት በፎቅና መንገድ ሥራ መለካት አይቻልም፤ ኢኮኖሚው በእርግጥ እያደገ እየተመደገ የሄደ ከሆነ ለምንድነው ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን መስዋዕት በማድረግ ቀይባህርን አቋርጠው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ የሚሰደዱት፤ ከአጠቃላዩ ሕዝብ 6 በመቶ በማይበልጥ አናሳ ብሔረተኞች ቁጥጥር ስር ስለሆነ አድጓል የሚባለው ኦኮኖሚ ይህ ነው የሚባል ለውጥ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ሊያመጣ አልቻለም” በማለት ኦባንግ ሜቶ በመላው ዓለም ፕሮግራሙን ለሚከታተሉ የአገራቸውን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም የጋራ ንቅናቄው ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ “አፍሪካውያንም ሆነ ኢትዮጵያውያን ኦባማን ወይም አሜሪካንን ወይም ምዕራባውያንን ነጻ እንዲያወጡን እየለመንን አይደለም፤ ራሳችንን እንዴት ነጻ እንደምናወጣ እናውቃለን፤ ነገር ግን (ከአምባገነኖች ጋር በማበር) በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን” በማለት ግልጽ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://staging.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. TeferiMekonnen says

    July 25, 2015 05:05 pm at 5:05 pm

    Obama is not like Fascist Meles Zenawi to build an industry in his place of birth or he is not a TPLF general to loot the national bank and build 20 storey building either in Kenya or the USA. Obama talks well and that helped him to be elected and reelected but what he does is dictated by US interest and the interest of the capitalists. If he deviates he knows the consequence as an admirer of JFK. Dictators like fascist Meles can do good for their people if they want but democratic governments cannot do anything because they wanted they have to follow rules, regulations and guidelines. Do not expect too much from Obama, or Clinton instead unite and dismantle the home grown fascists and make fascism/tyrany in Ethiopia history.

    Reply
  2. Ayu says

    July 31, 2015 06:06 am at 6:06 am

    President Obama is like a LION without TEATH.
    He just SPEAK with out ACTION PLAN.
    African Leaders have not EARS to HEAR HIM.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule