ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም የሚገዛው ህወሃት ላለፉት 25ዓመታት መብት በገፍ ሲሰጥ የቆየ ይመስል ህገመንግሥታዊ መብቶችን የሚገፍ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። አዋጁ ለስድስት ወር ይቆያል ማለቱ የህወሃት ዕድሜ ከስድስት ወር እንደማይቆይ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ከህወሃት በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ኃይለማርያም ደሳለኝ ትላንት እሁድ በሃገሪቱ “ያንዣበበውን አደጋ ለመቀልበስ” በሚል ሚኒስትሮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጁን አስታውቋል። እንደ ኃይለማርያም ንግግር ህገመንግሥታዊ መብቶች የማይጣሱ መሆናቸው ቢነገርም እዚያው የኃይለማርያም ካቢኔ አባል የሆነው የጠቅላይ አቃቤ ሹመኛው ጌታቸው አምባዬ ህወሃት በቀጣይ እንደፈለገ የሚያደርጋቸውንና የሚገድባቸውን መብቶች በዝርዝር ተናግሯል። እነዚህም:- 1) ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማንኛውንም ሰው ይታሰራል፤ … [Read more...] about ህወሃት/ኢህአዴግ ዕድሜዬ ከ6 ወር አይበልጥም አለ
Full Width Top
የኢሬቻ የጅምላ ጭፍጨፋ ሃውልት እንዲሰራ ሃሳብ ቀረበ
የትግራይ ህዝብ ከማን አገዛዝ ነጻ እንዲወጣ እንደሚፈለግ በውል ባይታወቅም ራሱን “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር” የሚለው ህወሃት በቢሾፍቱ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ የሚዘክር ሃውልት እንዲቆም ሃሳብ መቀረቡ ተሰማ። የኢሬቻን ክብረ በዓል ለማክበር የተሰባሰቡ የኦሮሞና የሌሎች ቦታዎች ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ ትውልድ ሁሉ በማንና እንዴት እንደተፈጸመ እንዲያውቅ፣ እንዲማርና የተከፈለው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ እንዲረዳ፣ እንዲሁም ምስክር ሊሆን በሚያስችለው መልኩ ሃውልቱ እንደሚታነጽ ለማወቅ ተችሏል። ለመብታቸው የተነሱና በሰላማዊ መንገድ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን “በቃህ፣ ልቀቀን” በማለታቸው የኦሮሞ ተወላጆች ላለፉት አስራ አንድ ወራት ሲገደሉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲገረፉና ሲሰቃዩ መቆይታቸው ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ቢሾፍቱ የኢሬቻን ክብረ በዓል … [Read more...] about የኢሬቻ የጅምላ ጭፍጨፋ ሃውልት እንዲሰራ ሃሳብ ቀረበ
“አሁን ደም ተቃብተናል፤ ዕርቅ የለም፤ ሌላ ሳይከተል ልቀቁልን”፤ “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም” የሕዝብ ምላሽ
ኦሮሚያ ብቻ ሳትሆን ድፍን አገርን ማቅ ያለበሰው የጅምላ ጭፍጨፋ እያደር አጥንት የሚያደቅ መረጃ እየወጣበት ነው። ህወሃት የእርቅ መንገዶችን በሙሉ አሟጦ የቀበረበት ይህ “ይቅርታ የሌለው ወንጀል” እስካሁን የ678 ንጹሃንን ህይወት አጥፍቷል። የትዳር ጓደኛውን አስከሬን በግል ተሽከርካሪ ጭኖ እያነባ ወደ ቤተሰቡ የወሰደ አለ። ገንዘብ ተዋጥቶለት የሚስቱን አስከሬን ጭኖ ወደ ሱሉልታ የተጓዘ መኖሩ ተሰምቷል። እናትና ልጅ ባንድነት ቀብራቸው ተከናውኗል። በአንድ ቀን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ወገኖች ከቤተሰባቸው ጎድለዋል። አስከሬን አሁን ድረስ እየተቆፈረ እየወጣ ነው። ሃይቅ ላይ የተንሳፈፉ አስከሬኖች እየተለቀሙ ነው። ህዝብ ቁጣው ገንፍሎ በተለያዩ ስፍራዎች እምቢተኛነቱን እየገለጸ ነው። ህወሃት ግን አሁንም ይዋሻል። በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ በታጣቂዎች … [Read more...] about “አሁን ደም ተቃብተናል፤ ዕርቅ የለም፤ ሌላ ሳይከተል ልቀቁልን”፤ “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም” የሕዝብ ምላሽ
በሕዝብ አቆጣጠር አሁን ሁሉም ነገር አበቃ
ዛሬ ጨለሞ ዋለ። ዛሬ አገር ማቅ ለበሰች። ዛሬ የሆነውን ማመን ይከብዳል። ቄጤማና ቅጠል ይዘው የወጡ ሰላማዊ ዜጎች በጅምላ ተረሸኑ። "Down! Down! Woyane … Down! Down TPLF! …" በማለት ቁጣውን የገለጸ ሕዝብ እገዛሃለሁ በሚለው የትግራይ ህዝብ ተገንጣይ ቡድን (በህወሃት) ተጨፈጨፈ። ከአየርና ከምድር ጭስና ጥይት የተረጨበት ህዝብ፣ የሚገባበት ጠፍቶት የውሃ ራት ሆነ። ሞተ። ቆሰለ። በውሃ ተበላ። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሚባለው የወንበዴው ቡድን መሪ መለስ ሞት በድንገት እንደ ቡሽ ክዳን አፈናጥሮ ሲወስደው ጥቁር ለበሶ ሳግ እየተናነቀው ዜና ያወጀው ተመስገን በየነ፣ ዛሬ ነጭ በነጭ ለብሶ አኻዝ ባይጠቅስም የሰው ህይወት ማለፉን የተናገረው “ሰፊውና የተከበረው የኦሮሞ ህዝብ” በማለት ነበር። ተመስገን ከጌታቸው የተላከለትን ሰዎች “በመረጋገጥ” … [Read more...] about በሕዝብ አቆጣጠር አሁን ሁሉም ነገር አበቃ
ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፍሉኝ አለ
ኢትዮሚዲያ በ26/09/2016 ከግደይ ዘርአፅዮን ጋር ያካሄደውን ቃለ ምልልስ አንብቤዋለሁ። ግደይ ዘርአፅዮንን የማውቀው ገና ትግሉ ሳይጀመር በፊት ነው። ግደይ በጥሩ ቤተሰብ ያደገ ግለሰብ ነው። ትግሉ ሳይጀመር በመስከረም 1967 አዲስ አባባ ውስጥ (ማኅበረ ገስግስቲ ብሔረ ትግራይ) ማገበትን መሰረቱ። የመሰረቱትም አረጋዊ በርሄ፣ ገደይ ዘርአፅዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ዘርኡ ገሰሰ፣ ሃይሉ መንገሻና አስፍሃ ሃጎስ ናቸው። ከዚያ በኋላ እነ መለስና ስብሃት ወዘተ ተቀላቀሉ። ግደይ ስለእኔ፤ ገብረመድህን፤ መስራች አልነበረም ብሎ ነው የተናገረው። ያለው ትክክል ነው፤ እኔ የማገበት - ተሓህት መስራች አልነበርኩም። ማገበት እንደተመሰረተ በተራ አባልነት ተመልምዬ ከማገበት ጀመሮ ትግሉን ለማጠናከር ስንቀሳቀስ የነበርኩ ተራ አባል ነበርኩኝ እንጂ መስራች አይደለሁም። ስለ (ተጋዳሊ … [Read more...] about ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፍሉኝ አለ
“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”
ሰዎችን እንደ እህል በዘር ጆንያ እየሠፈረ በፈለገበት ሣጥን ውስጥ ማስገባት ዓላማው የሆነው የትግራይ ሕዝብ ነጻአውጪ ግምባር (ህወሃት)፤ በኦሮሞ ተቃውሞ #oromoprotest እና በአማራ ተጋድሎ #amhararesistance የተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ዕንቅልፍ ስለነሳው በተለይም ደግሞ የሁለቱ በኅብረት መቆም ኅልውናው ላይ አደጋ ስለጣለበት ሶማሊና አፋር ክልል መንጎዳጎድ ጀምሯል፡፡ ለኢትዮጵያ ቅንጣት ታህል ደንታ የሌለው ህወሃት የኦጋዴንን ሕዝብ እንዴት እንደፈጀ፣ ሴቶችን (ህጻናትንና ወንዶች ልጆችን ጨምሮ) እንደደፈረ፣ ለመከራና ለስቃይ እንደዳረገ የተረሳ መስሎት ሰሞኑን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ቅኝቱንም ሆነ ዜማውን የሶማሊ አድርጎታል፡፡ የህወሃትን ግፍ እንኳንስ የክልሉ ነዋሪዎች ሊረሱት ስዊድናውያኑ ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን እስከ ሞት የሚረሱት አይደለም፡፡ “ዝም … [Read more...] about “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”
በኢህአዴግ ጎጆ ያልበሰበሰው ማን ነው?
ተሰብሳቢዎቹ አገሪቱን “በስብሰናል፣ ሸተናል፣ ማስተዳደር አቅቶናል …” እያሉ ራሳቸውን የሚሰድቡት የኢህአዴግ ምክርቤት አላባት ናቸው። በእነርሱ አነጋገር አንድም “ልውጥ” ሰው መካከላቸው የለም። ሰብሳቢዎቹ “ቅምጥ” የሚባሉት ታማኝ የህወሃት ታዛዦች “ጓድ ሃይለማርያም ደሳለኝና ምክትላቸው ደመቀ መኮንን” ነበሩ። የኃይል አሰላለፉ በራሱ የቤቱንና የአስተዳደሩን መብከት የሚያሳብቀው ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢዎች ፊት የቆሙት ራሳቸው ኢህአዴጎች ነበሩ። በፊት አውራሪዎቻቸው ፊት ቆመው ሪፖርት የሚያቀርቡት ሰዎች ኢህአዴግ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በፊት አውራሪዎቻቸው የተሾሙ ነበሩ። የተሾሙት በድርጅቱ መዋቅር ስር ባሉ አደረጃጀቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ዘልቀው በመግባት እንዲያጠኑ ነበር። ከሙስና ጀምሮ ኢህአዴግ “ገለማሁና፣ በሰበስኩ” የሚልበትን መስመር መርምረው እንዲያቀርቡ የተሰየሙት … [Read more...] about በኢህአዴግ ጎጆ ያልበሰበሰው ማን ነው?
የወያኔ አገዛዝና የኢትዮጵያ ወደፊት
የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ የወያኔን አገዛዝ ማውረድ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኗል፤ ይህ የሚያከራክር አይመሰለኝም፤ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ በጠመንጃ ጉልበትና በሲአይኤ ድጋፍ ሰንጎ የገዛ ቡድን በቃህ ቢባል አይደንቅም፤ ሌላው ጥያቄ ‹‹የወያኔን አገዛዝ ማውረድ የሚቻለው እንዴት ነው?›› የሚል ሲሆን በዚህ ላይ ስምምነት ያለ አይመስለኝም፤ መልሱ ሰላማዊ ወይም የትጥቅ ትግል የሚል ምርጫ ብቻ ሳይሆን፣ የወያኔን አገዛዝ ለማውረድ የተሰለፉትስ እነማን ናቸው? ዓላማቸውስ ከቃል ባሻገር ምንድን ነው? የሚልም ይሆናል፤ ባልተቀነባበረ መንገድ በተለያዩ ቦታዎች አሁን የሚታዩትና በያለበት ኩፍ ኩፍ የሚሉት የመንተክተክ ምልክቶች ለወደፊቱ ሥርዓት ያለውን ሰልፍ አያሳዩም፤ አዲስ ነገርና የምሬቱ መግለጫ መገዳደል መጀመሩ ነው፤ ገዳይ መለዮ ለባሹ ብቻ መሆኑ እየቀረ ነው፤ እነዚህ ምልክቶች ለውጥ … [Read more...] about የወያኔ አገዛዝና የኢትዮጵያ ወደፊት
አሜሪካ ስለ ህወሃት – “እጃችንን ብናነሳ በህይወት አይኖሩም”
“አሁን አሜሪካኖቹ እያመረሩ ነው” የሚለው ዜና አየሩን ወጥሮታል። በተለይም የኦባማ አስተዳደር ለኢህአዴግ/ህወሃት የጻፈው የከረረ ደብዳቤና ትዕዛዝ ለአገዛዙ የመቀመጫ ላይ ቁስል ሆኖበታል። ለዚህም ይመስላል ሃይለማርያም ሳይፈልጉ መለስን እንዲሆኑ ታዝዘው አሜሪካንን ወርፈዋል። ይኸው የሃይለማርያም ዘለፋ ያበሳጫቸው የስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች “ሰዎቹ ከማን ጋር እንደሚያወሩም አያውቁም። ደቡብ ሱዳን መሰልናቸው” ማለታቸውን የመሰክሩ ለጎልጉል ገልጸዋል። ይህንኑ ተከትሎ ሃይለማርያም ደሳለኝ ባስቸኳይ አሜሪካ እንዲመጡ ታዝዘዋል። በወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀውስ ዙሪያ የአሜሪካ መንግስት ከህወሃት/ኢህአዴግ ጋር እያደረገ ያለውን ግንኙነት በቅርብ የሚከታተሉና በቂ መረጃ ያላቸውን በመጠቀስ የጎልጉል የአሜሪካ ዜና አቀባይ እንደዘገበው፣ የኦባማ አስተዳደር የጻፈው ደብዳቤ ሃይለማርያምን … [Read more...] about አሜሪካ ስለ ህወሃት – “እጃችንን ብናነሳ በህይወት አይኖሩም”
ጥልቅ ተሃድሶ “በመበስበስ” ጀመረ!
የኢህአዴግ አካል የሆነው ኦህዴድ “ጥልቅ ተሃድሶውን” “በመበስበስ” መጀመሩን የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ያሰራጨው ዜና አመልክቷል፡፡ ዜናውን ተከትሎ “በጥልቀት የመታደሱ” ጉዳይ “በመበስበስ” መጀመሩ አመላካች ነው ተብሏል፡፡ በሌሎች ክልሎችም የመበስበስ መጠናቸው የጠለቀና ለህወሃት ከመታመን ውጪ ተስፋ በሌላቸው ታማኞች በመተካት ሹምሽር እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡ የኦህዴድ ምክትል ሆነው የተሾሙት ጄኔራል፣ ዶክተር፣ አቶ፣ አሁን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ብቅ ያሉት የኦሮሞን ብሔር የማይወክሉ የትግራይ ተወላጅ እንዶኑ በስፋት የሚነገርላቸው ሻሸመኔ ያደጉት ወርቅነህ ገበየሁ ናቸው፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት?” በሚል ርዕስ (July 6, 2013) ስለ ወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” መጠነኛ ዘገባ … [Read more...] about ጥልቅ ተሃድሶ “በመበስበስ” ጀመረ!






![“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2016/06/Slide15-e1466825122855-300x188.jpg)



