የለቅሶ ሳግ በያዘው አንደበት የመረረ ሃዘን ይሰማል። ተናጋሪዋ የሚሰሩት ድራማ ወይንም ዘጋቢ ፊልም ሳይሆን በትክክል የደረሰባቸውን ነው። የልጃቸው አስከሬን እንደ ምናምንቴ በማዳበሪያ ተደርጎ ነው የተሰጣቸው። ልብ ይነካል። ያማል። ጉዳዩ ከሃዘንም በላይ ይሆናል። አንድ ልጃቸው "መመኪያዬ" የሚሉት ተገደለባቸው፤ ሌላኛው ክፉኛ ተደብድቦ ታሟል፤ ሁለቱ ታስረዋል። እኚህ የ65 ዓመት አዛውንት ሲያልቅ አያምር ሆነና ባዶ ሆኑ። "ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ" አሉ። አስከትለው አስከሬኑ መበላሸቱንና ደም ይፈሰው እንደነበር ገለጹ። ወግ አይቀር ተቀበረ። አሁን አሁን "ወዴት እየሄድን ነው" ከማለትም ያለፈ ይመስላል። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የወረዳው አስተዳዳሪ "በአሁኑ ሰዓት እንዲህ ያለ ችግር የለም" ማለታቸው፣ ዋና አስተዳዳሪውና የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ምላሽ ለመስጠት አለመፈለጋቸው ሌላው … [Read more...] about “ልጄን ገድለው በማዳበሪያ አመጡልኝ” እናት
Full Width Top
የቴድሮስ ቅሌት!!
ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት እየተወዳደረ ያለው የህወሃቱ ዕጩ ቴድሮስ አድሃኖም ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት አቅቶት በተደጋጋሚ ግልጹን ጥያቄ እንዲብራራለት ሲጠይቅ መዋሉ ብዙዎችን ያነጋገረና ያሳፈረ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ውርደቱ የከነከናቸው ትንታጉን አንደበተ ርቱዕ ኮ/ሎ ጎሹ ናፍቀዋል፡፡ በ2017 የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር በመሆን የሚያገለግል ለመምረጥ ለ194 ዓባል አገራት በቀረበው ጥሪ መሠረት ህወሃት/ኢህአዴግ ከሚገዛት ኢትዮጵያ፣ ከጣሊያን፣ ከፈረንሣይ፣ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከፓኪስታንና ከሃንጋሪ ስድስት ዕጩዎች አገራቱ አቅርበዋል፡፡ በተያዘው ዕቅድ መሠረት ዕጩዎቹ ባለፈው ማክሰኞና ረቡዕ የቃል መግለጫ ካቀረቡ በኋላ ከአባል አገራት ጥያቄዎች ቀርበውላቸውል፡፡ ቴድሮስ አድሃኖም ከአልጄሪያ፣ ከጀርመን፣ ከአውስትራሊያ፣ ከህንድ የቀረቡለትን ጥያቄዎች ጥቂቶቹን በቀጥታ … [Read more...] about የቴድሮስ ቅሌት!!
“ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል”
ሰሞኑን በከፍተኛ ደረጃ የዓለም መገናኛዎች ርዕስ የኢትዮጵያ ሰራዊት ከሶማሊያ ለቆ የመውጣቱ ጉዳይ ነው። የሶማሊያ ባለሥልጣናት ስለጉዳዩ የተነገራቸው አንዳችም ነገር እንደሌለ መግለጻቸው፣ አልሸባብም የሠራዊቱን እግር እግር እየተከተለ የተነጠቃቸውን ወረዳዎች መቆጣጠሩና ኢህአዴግ ጉዳዩን ያስተባበለበት አግባብ ጎልጉል የመረጃ አቀባዮቹን እንዲያነጋግር መነሻ ሆኗል። እንደ መረጃ ሰዎቹ ከሆነ በስም ተለይቶ ባይገለጽም ህወሃት በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ በጥርጣሬ መዝገብ ውስጥ ከገባ ሰነባብቷል። ሟቹ የኢህአዴግ ሊቀመንበር መለስ ዜናዊ ሠራዊቱ ወደ ሶማሊያ ሲንቀሳቀስ ፓርላማው ሳይወስን በመሆኑ ይህንን ለማብራራት በተጠራ ስብሰባ ላይ በዋናነት ያሰመረበት ጉዳይ የደህንነት ስጋትን ነበር። “የደህንነታችን ስጋት የሆኑትን አሸባሪዎች ከምንጫቸው ማድረቅ” በሚል … [Read more...] about “ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል”
ሕዝብ ላይ የሚፈጸም የፖለቲካ ውርጃ!!
አሁን የሚፈለገው የሚያሻገሩ መሪዎችን ማግኘት ብቻ ነው። ሕዝብ በፖለቲካ መሪዎች ሃፍረትን እየተግሞጠሞጠና ደሙ ደመ ከልብ እየሆነ የሚኖርበት ዘመን እንዲያከትምለት ይፈልጋል። የአንተ ደም የእኔ ደም ነው በማለት የችግሩ ጉያ ውስጥ ሆኖ አጋርነቱን፣ አንድነቱን ሲያሰማ ሩቅ ተቀምጦ እንደ ቅጥረኛ የወገንን ሞራል ማላመጥ አግባብ አይሆንም። ውሎ አድሮ ከገዳዮቹ በላይ ያስጠይቃል። በቅጥረኛነትም ያስመድባል። ከአገራችንም ሆነ ከዓለም ዘመን የማይረሳቸው የውብ ስብእና ባለቤቶች ሕዝባቸውን አሻግረዋል። ክፉዎች የቀበሩትን የቂምና የጥላቻ ገመድ በጣጥሰው አገራቸው በልዕልና፣ ሕዝባቸው በሰላም እንዲኖር አስችለዋል። በቀናነት ጀምረው፣ በቀናነት ጨርሰዋል። በታማኝነት ሃላፊነትን ተረከበው በታማኝነት አለፈዋል። ዝርዝር ውስጥ ባንገባም በህይወት ያሉም አሉ። እንዲህ ያሉትን የሚያስቡ “እኛንስ ማን … [Read more...] about ሕዝብ ላይ የሚፈጸም የፖለቲካ ውርጃ!!
Ato Emmanuel Abraham (1913-2016)
Ato Emmanuel Abraham who had served his country in a number of important diplomatic and ministerial posts for nearly four decades and half (1931-1974) has died at a great age of 103 on Wednesday. Emmanuel was ambassador to Britain and Italy and cabinet minister and director general at the Ministry of Foreign Affairs and director general of the Ministry of Education and Fine Arts, Minister of Posts, Telegraphs and Telephones; Minister of communications and Transport; and finally, minister of … [Read more...] about Ato Emmanuel Abraham (1913-2016)
ኢሰመጉ ከየት ወዴት?
አምስት ዓረፍተ ነገሮች፤ ኢሰመጉ መንፈሳዊ ተልእኮ ያለው መንፈሳዊ ድርጅት ነው፤ ዓላማው በሰው ልጆች መሀከል የሚከተሉትን ተልእኮዎች መዝራት ነው፡-- 1.1. እኩልነትንና ነጻነትን 1.2. ፍቅርንና ስምምነትን 1.3. ፍትሕንና ሕጋዊነትን 1.4. ሰላምንና ማኅበረሰባዊ እድገትን 1.5. የእውነትንና የእውቀትን ብርሃን ማስፋፋትን ኢሰመጉ የተቋቋመው በሁለት ምክንያቶች ነው፤-- 2.1. የደርግ አገዛዝ ወድቆ አዲስ መንግሥት በአዲስ ሥርዓት ይመሠረታል በሚል ተስፋ አዲሱ ሥርዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ እንዲመራ ለመርዳት ነበር፤ 2.2. የኢትዮጵያን ሕዝብ በመብት ጉዳይ ለማንቃትና ራሱን ከተገዢነት ወደገዢነት ደረጃ እንዲለውጥ ለማስቻል ነበር፡፡ ለትውልድ የሚተላለፍና ስምን ሲያስጠራ የሚኖር ሥራ ለመሥራት ሀብት ጥሩ መሣሪያ ነው፤ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው … [Read more...] about ኢሰመጉ ከየት ወዴት?
“የጣዕር ጊዜ አዋጁ” እና ኢትዮጵያ
የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ህወሃት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስላወጀው "አትኑሩ" አዋጅና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ስለሰጡት አስተያየቶች ያቀናበረውን ከዚህ በታች እንዳል አስፍረነዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና ኢትዮጵያ * "በብሔራዊ ደረጃ የመጣ ጥፋት ነዉ" የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ የደነገገዉን የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ የሚያጠናክሩ ማብራሪያዎችን ይፋ ከተደረጉ ወዲህ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ስጋታቸዉን መግለጽ ጀምረዋል። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ፤ ይደረጋሉ የተባሉት መሻሻሎች፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ትንታኔ ይፋ ሲደረግ በተቃራኒዉ መንገድ የሚጓዝ ነገር መኖር እንደሚያመላክት ነዉ የተጠቀሰዉ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከዉጭ የሚሰራጩ የሽብርተኛ ድርጅቶች ልሳን ያላቸዉን መገናኛ ብዙሃን ማዳመጥ ያግዳል፤ … [Read more...] about “የጣዕር ጊዜ አዋጁ” እና ኢትዮጵያ
መንፈሳዊ ወኔና ሥልጣን
ባለሥልጣኖቻችን ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን በጣም የናቋቸው ይመስላል፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀውን ሁሉ ያውቃሉ፤ የኢትዮጵያን ቴሌቪዥን ያያሉ፤ የኢትዮጵያን ራድዮ ይሰማሉ፤ ባሎቻቸውና አባቶቻቸው የዛሬ ሳምንት የተናገሩትን ረስተው፣ ወይም ክደው፣ ወይም ዋሽተው ተቃራኒውን ሲናገሩ መሸማቀቃቸው አይቀርም፤ እንዲህ ያለው የንግግር መገለባበጥ የእምነት መገለባበጥን፣ የማሰብ ችግርን፣ የመንፈስ ልልነትን ያሳያል፤ ታዲያ ሚስቶችና ልጆች እየተሸማቀቁ አካላቸውም ነፍሳቸውም ሲያልቅ ለባለሥልጣኖቹ አይታወቃቸውም? ወይስ የቤተሰብ አባሎች ጠባይ እየሆነ ሽታዬ ሽታዬ እየተባባሉ ነው? አንዳንዶች ባለሥልጣኖች ወንበሩ ላይ የወጡት እግዚአብሔርን ሳይይዙ ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ እግዚአብሔርን ይዘው ወንበሩ ላይ ይወጡና እግዚአብሔርን ከተቆናጠጡ በኋላ እግዚአብሔርን ከውስጣቸው የሚያስወጡት … [Read more...] about መንፈሳዊ ወኔና ሥልጣን
የኦሮሚያ ሰነድ – አዲሱ ቃል ኪዳን?
ጊዜ ገድቦ መናገር ይከብድ ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ አይቀሬ ስለመሆኑ ክርክር የለም (አንዳንድ የወያኔ አንጋሽ ምዕራባውያን ባለሙያዎች በጥቂት ወራት ይተምኑታል)። ይህ እውነት ቢሆንም አንዳንድ “የፖለቲካ መክለፍለፎች” ሊወድቅ የተቃረበውን አገዛዝ እንዲውተረተር ዕድል ሊሰጠው ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው ወገኖች ከያቅጣጫው ብቅ እያሉ ነው። የስጋታቸው መንስኤ ደግሞ በዋናነት የግልጽነት፣ ያለመተማመን፣ የውድድርና “ጊዜን” የመጠቀም ተራ እሽቅድምድም እንደሆነ እነዚሁ ስጋት የገባቸው ክፍሎች ይናገራሉ። ከየአቅጣጫው የሚሰሙት የ“ሽግግር” ዜናዎች፣ ዳር ዳሩን በለሆሳስ ይሰማ የነበረው “የሃሜት በሽታ” ገልጠውታል። በዚሁ መነሻ ይመስላል ለኦሮሚያ የሽግግር ሰነድ እንደሚዘጋጅ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ሰፊና ግልጽ ያለ መልስ ከሚመለከታቸው የእነ በቀለ ገረባ ወኪሎች ህዝብ እየጠበቀ … [Read more...] about የኦሮሚያ ሰነድ – አዲሱ ቃል ኪዳን?
ህወሃት “አስከሬን ልግዛችሁ” አለ!
በሙት መንፈስ አገር እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በይስሙላነት ባስቀመጠው ፕሬዚዳንት አማካኝነት ፓርላማ ብሎ በሰየመው የራሱ ስብስብ በኢትዮጵያ ያለ አንዳች ልዩነት ለገደላቸው ወገኖች አስከሬን መግዣ ብር ሰይሜአለሁ ብሏል፡፡ ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ላፈሰሰው መድቤአለሁ ያለው 2.4 ቢሊዮን ብር እስካሁን የት እንደገባ አይታወቅም፡፡ የሙት (መለስ ዜናዊን) ፎቶ ከፊት አስቀምጦ አሁንም በአስከሬን አገሪቱን እንደሚመራ በገሃድ ያሳየው ህወሃት ለመለወጥም ሆነ ስለ ለውጥ ለማሰብ ፍላጎት እንደሌለው ነው በጥቅሉ ያመላከተው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን በእስር እያማቀቀ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት፣ ፓርቲዎች እንዳንቀሳቀሱና ኅልውና እንዳኖራቸው በርካታ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ ምርጫ ኮሚሽን ማዋቀር፣ … የሚሉ የጥገናዊ ለውጦች ስሜት እንኳን የሌላቸውን ጉዳዮች … [Read more...] about ህወሃት “አስከሬን ልግዛችሁ” አለ!










