የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ ድረገጽ መረጃ እንደሚለው ከሆነ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገራት መካከል የአሜሪካንን ዕርዳታ በመቀበል ቀዳሚነቱን ሥፍራ የያዘችው ኢትዮጵያ ነች፡፡ (http://www.foreignassistance.gov/) የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ወይም በጀት ከተደረገው ውጪ የሚሰጠውን ተጨማሪ ዕርዳታና ድጎማ ሳይጨምር ከ2009 - እስከ 2012 ባሉት ዓመታት ብቻ ኢትዮጵያ ከ3.3ቢሊዮን ዶላር በላይ (በወቅቱ ምንዛሪ ከ60ቢሊዮን ብር በላይ) ዕርዳታ ተቀብላለች፡፡ ገንዘቡ የሚሠጠው ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ፤ ለዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብቶችና መልካም አስተዳደር፤ ለጤና፤ ለትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች፤ ለኢኮኖሚ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ እንደሆነ ድረገጹ ያስረዳል፡፡ (በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተቀናበረ - AP Photo/Steve Parsons/pool) … [Read more...] about ግመል ሰርቆ ማጎንበስ አይቻልም
Politics
“አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል!”
2005 ዓ.ም ከ1998 ዓ.ም በኋላ በተግባር ሊታይ የሚችል የፖለቲካ እንቅስቃሴ የታየበት አመት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም ፡፡ በተለይ በግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ፣ም የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ምንአልባትም ወደኋላ ይጓዝ የነበረውን የሀገር ውስጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከማስቆም በዘለለ ወደፊት እንዲጓዝ ያደረገው ይመስለኛል፡፡ ከዚህ እለት በኋላ ባሉት ቀናቶች ውስጥ በርካታ ፓርቲዎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። በተለይ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ድርጅቱ በደሴና በጎንደር የተሳኩ ሁለት ሰልፎችን በአንድ ቀን አድርጓል፡፡ ለዛሬ ይህን እንድጽፍ ያነሳሳኝ ግን ይህን እንቅስቃሴ ተከትሎ እየተነሱ ያሉት እንዳንድ አሉታዎችን ለማየትና የራሴን ምልከታ ለመጠቆም ያህል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ … [Read more...] about “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል!”
“በስመ ተቃዋሚ ተቃቅፎ መሳሳም” – ለትልቁ ዓላማ?
ከጥቂት ጊዜያት በፌት አንድ የመጽሐፍ ዳሰሳ ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ መጽሐፉ “ፌኒክሷ ዛሬም፣ ሞታም ታንቀላፋለች” ሲሆን ጸሐፊዋ የቀድሞው የሕወሓት አባልና አመራር የአቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ወ/ሮ ውብማር ናቸው፡፡ በዳሰሳው ወቅት በትግል ጊዜ ለምን መጽሐፉ ላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እንዳልፈቱ ሲጠየቁ ወይዘሮዋ እንዲህ ብለው መልሰው ነበር፡፡ “ደርግን የሚያህል ጠላት ከፊት ለፊታችን እያለ እንዴት እርስ በርስ በመጣላት ጊዜ እናባክናለን? ነጻ ስንወጣ የሕወሓት ፖሊሲና ፕሮግራም ሁሉንም ነገር ይፈታዋል::” ብለን ተውነው ይላሉ፡፡ በኋላ ላይ ደግሞ ሕወሓትን ስለመለወጥ ሲጠየቁ ‹‹ሕወሓት ከዚህ በኋላ የሚለወጥ ድርጅት አይደለም አርጅቷል፡፡ 40 ዓመት በኋላ የድርጅት ባሕሪይ አይቀየርም›› ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ የትኛው ጠላት? የትኛው ትልቁ ዓላማ? አሁንም ሕወሓት ሥልጣን ከያዘ … [Read more...] about “በስመ ተቃዋሚ ተቃቅፎ መሳሳም” – ለትልቁ ዓላማ?
“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”
የዛሬ 10 ወር የሻለቃ ሃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ፖለቲካ የመምጣት ሁኔታን አስመልክቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሃተታ አቅርቦ ነበር፡፡ (እዚህ ላይ ይመልከቱት) ሰሞኑን አትሌቱ ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጎቱንና “በምርጫ” ለመወዳደር መፈለጉ ብዙ እየተባለበት ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን ላለው ሁኔታ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ሃተታ በድጋሚ አትመነዋል፡፡ “ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ … [Read more...] about “ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”
የኃይሌ ወደ ፖለቲካው መድረክ መምጣት እያነጋገረ ነው
“ኃይሌ ወደ ፖለቲካ መግባቱ መብቱ ቢሆንም እንደስፖርቱ በፖለቲካውም የሚያንጸባርቅ አይመስለኝም” ዶ/ር መረራ “በአገሪቱ የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል የለም። አገሪቱ የጡንቸኞች ሀገር ናት። … ገብቶ ይሞክረው” ፕሮፌሰር በየነ “እኔ ኃይሌን ብሆን ኖሮ በግል ወደ ፖለቲካ ከምገባ ወደ ፓርቲ መግባቱን ነው የምመርጠው። ከፓርቲው ደግሞ የመጀመሪያ ምርጫዬ የሚሆነው አንድነት ፓርቲ ነው” ዶ/ር ነጋሶ “ኃይሌ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ በግሉ ወይም በፓርቲ ወደ ምርጫ መግባቱን እንኳ ግልፅ አላደረገም … ፖለቲካ በግል ፍላጎት ብቻ የተወሰነ አይደለም። ፖለቲካ እራሱን የቻለ ፖሊሲ መቅረፅ ያስፈልጋል። … ፖሊሲ ማስፈፀም የሚቻለው በፓርላማው አብላጫ ወንበር ሲያዝ ነው፤ … አንድ ሰው ብቻ ከሆነ ግን “አጃቢ” የመሆን አደጋ አለው። አቶ ገብሩ “አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በክብር … [Read more...] about የኃይሌ ወደ ፖለቲካው መድረክ መምጣት እያነጋገረ ነው
ፍልስፍና አልባ የሆነ ፖለቲካ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል
ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው የአስተዳደር ብልሹነት፣ የህዝቦች ኑሮ መዘበራረቅና ዓላማ-ቢስ መሆን፣ እንዲያም ሲል በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ አሳቦ ርስ በርሱ እንዲጠላላ ማድረግና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ወደ ርስ በርስ መተላለቅ እንዲያመራ መንገዱን ማዘጋጀት፣ በተራ አነጋገር ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከአምባገነናዊ አስተዳደር መስፈንና ከዲሞክራሲ አለመኖር ጋር ሲያያዝ ይታያል። አንዳንዶች እንዲያውም እንደዚህ ዐይነቱን ዓላማ-ቢስ የህብረተሰብ ጉዞ የአፍሪካ መሪዎች ወይም የጥቁር ህዝብ ችግር አድርገው የሚመለከቱ አሉ። በእርግጥ ለአንድ አገር ስርዓት ባለው መልክ መተዳደርና፣ ህብረተሰቡም በዕቅድና በዓላማ እንዲመራ ከተፈለገ በዚያ የሰፈነው አገዛዝ ህብረተሰቡን በማደራጀት ረገድ የሚጫወተው ከፍተኛ ሚና አለ። ጥያቄው ግን አንድ ህብረተሰብ … [Read more...] about ፍልስፍና አልባ የሆነ ፖለቲካ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል
የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ?
አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው "ሬት" ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ "ክፉ ጠረን" አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ። አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ። "… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም … [Read more...] about የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ?
አቶ ኦባንግ ሜቶ እስራኤል ገቡ
የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት አቶ ኦባንግ ሜቶ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር በ21/06/2013 እስራኤል በሰላም ደርሰዋል፡፡ በወቅቱም የማህበሩ አባላት በቤንጎሪዮን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በ22/06/2013 የሚካሄደውን ጉባኤ አጠቃላይ ስነ ስርአት የያዘ ዘገባ በተከታታይ የምንልክ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ የአቀባበሉ ሥነስርዓት ምስል ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ከሰላምታ ጋር ሳሙኤል አለባቸው አድማሱ የኢትዮጵያ እናድን አንድነት ማህበር ሊ/መንበር … [Read more...] about አቶ ኦባንግ ሜቶ እስራኤል ገቡ
“Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights”
Testimony before the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and International Organizations Date: June 20, 2013 Given by: Mr. Obang O. Metho, Executive Director Solidarity Movement for a New Ethiopia “Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights” I would like to thank the Chairman of the Committee on Foreign Affairs, Congressman Edward Royce, and all ranking members of the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and … [Read more...] about “Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights”
አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም "ዘርፈው አስቀመጡት" የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር 54 ተሽከርካሪዎች ተይዘውባቸዋል። ገንዘቡን ሳይጨምር 54 ተሽከርካሪዎች በስማቸው ተመዝግበው የተያዙባቸው አቶ ነጋ ፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የንግድ ሽሪክ እንደሆኑ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የማይቀሩት አቶ ነጋ በየስብሰባው ወቅት ሻይና ቡና ሲሉ ከወ/ሮ አዜብ ጋር አብረው እንደሆነ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “አትሌት … [Read more...] about አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?










