ሰኞ ሐምሌ 27፣ 20017 (ኦገስት 3፣ 2015) በሞስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ላይ የህወሓት/ኢህአዴግን ፍላጎት በማስፈጸም የሚታወቀው ፍርድ ቤት ከሰባት ዓመት እስከ 22 ዓመት የሚደርስ እስራት እንደበየነባቸው ይፋ ሆኗል። የሞስሊሙ ኅብረተሰብን የተቃውሞ ድምጽ መሠረት በማድረግ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ በማፈላለግ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩት እነአቡበከር አህመድ የታሰሩት ከሁለት ዓመት በፊት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት በሙስሊሙ ማኅበረሰብ እምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባት አመራሩን ለመቆጣጠርና እሱ የሚፈልገውን የእምነት ፈርጅ ኢትዮጵያውያን ሞሰሊሞች በግዴታ እንዲቀበሉ ያውጠነጠነውን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር እምቢ ማለታቸውን ተከትሎ እንደነበር ይታወሳል። (ሙሉውን የሸንጎ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ … [Read more...] about በሞስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ላይ የተወሰነውን እስራት ሸንጎ ያወግዛል
Opinions
የሰላም ትግሉ ያቸንፋል
የሰላማዊ ትግል ተግባራዊነትና ስኬት መለኪያው ምንድን ነው? በዚህ ልጀምር ጽሑፌን። በርግጥ መጀመር ያለበት፤ ሰላማዊ ትግል ምንድን ነው? የት ተተገበረ? እንዴት ተተገበረ? ከትጥቅ አመጹ በምን ተሽሎ ይገኛል? እዚህ ሰላማዊ ትግል፤ እዚያ ግን የትጥቅ ትግል የሚባለው እንዴት ነው? በሚሉት ነበር። ነገር ግን፤ አንባቢዬ በትክክል እንደሚረዱት፤ አሁን የያዝነው፤ በተጨባጩ በሀገራችን ባለው የፖለቲካ ሀቅ፤ ምን ላይ ነው ያለነው? ምን ማድረጉ ለትክክለኛው ሕዝባዊ ድል አመርቂ ውጤት ያስገኝልናል? ከሚለው በመነሳት ነው። እንግዲህ መሠረታዊው መነሻ፤ አሁን ያለንበት የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ ነው፤ ማለት ነው። እዚህ ላይ ነው እኔ፤ ሽንጤን ገትሬ፤ “ሰላማዊ ትግሉ ያቸንፋል!” በማለት የቆምኩት። እናም ላስረዳ! ገዥው ወገንተኛ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፣ ከሕዝቡ ተነጥሎ … [Read more...] about የሰላም ትግሉ ያቸንፋል
ሁለቱ ትግሎች
ብርሃኑ ነጋ ዱር ገባ! አንዳርጋቸው ጽጌ መፅሃፍ ጨረሰ! ኦባማ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መመረጣችንን እውቅና ሰጠ! እነዚህ እንግዲህ የሰሞኑ ፖለቲካዎች ናቸው። ያለወትሯቸው በአሜሪካ ድምፅ ላይ ለቃለመጠይቀ የቀረቡት ዶ/ር ቴድሮስ አድኅኖም ያልበላቸውን ሲያኩ ተደምጠዋል። አድማጭ ልብ ሊለው የሚገባ ጉዳይ አለ። ዶፍተሩ ስለ ብርሃኑ ነጋም ሆነ ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ የተናገሩት ሳይጠየቁ ነበር ይኼ እንግዲህ “የማርያምን ... ምን የበላ …” እንደሚባለው ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በዚህ ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይዘገባሉ፡፡ ይህ በጎልጉል … [Read more...] about ሁለቱ ትግሎች
ከሳሽ ሲከሰስ
(ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ቢኖር እኛ ኢትዮጵያን ሙስሊሞች እንዲህ ብለን እንከስ ነበር!) የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 የተመለከተውን በመተላለፍ የተከፈተ ክስ የቀ/ቁ/001/2006 የወ/መ/ቁ. 01/0001/06 ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ በመላው ዓለም ከሳሽ ….. ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች (የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ) ተከሳሾች… 1/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የሽብር ቡድኑ አጠቃላይ አስፈጻሚ 2/ የህውኃት/ኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሽብር ቡድኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 3/ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (በሌሉበት) የሽብር ቡድኑ የቀድሞ አመራር 4/ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ የሽብር ቡድኑ አመራር 5/ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ 6/ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል 7/ … [Read more...] about ከሳሽ ሲከሰስ
አዱሊስ/Adulis
ባለ 21 ገጽ የአዱሊስን ልዩ ዕትም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about አዱሊስ/Adulis
በሳውዲ “ድምጻችን ይሰማ” ላይ የተቃጣው ሴራ ከሸፈ
ሳውዲ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም የትግል አንድነት ላይ የተቃጣው የህወሃት/ኢህአዴግ ሴራ መክሸፉ ተሰማ! ከዕርዳታ አሰባሰብ ጋርም በተያያዘ የተፈጸመው ተግባር ለሕዝብ ይፋ ሆኗል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግ ካድሬዎች መቀመጫቸውን ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ ካደረጉ ወዲህ የህዝበ ሙስሊም እንቅስቃሴ ለማፈን የተለያዩ ስልቶችን ነድፈው ከአካባቢው የመንግስት ሹማምንቶች ጋር ሲንቀሳቀሱ እንደ ነበር ይታወቃል። እነዚህ ምስለኔዎች ለአገዛዙ ባላቸው ታማኝነት ከጅዳ እስከ ሪያድ በዘለቀ የስለላ መረባቸው በሳውዲ “ድምጻችን ይሰማ የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ” በሚያደርገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚሳተፉ ሙስሊም ወገኖቻቸውን ስም ዝርዝር ለኢህአዴግ በማቅረብ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ግፊት ሲያደርጉ የነበረ ከነፍሳቸው ይልቅ ለጥቅም ያደሩ መሆናቸውን አያሌ የእምነቱ ተከታዮች ይገልጻሉ፡፡ በተለይ እነዚህ … [Read more...] about በሳውዲ “ድምጻችን ይሰማ” ላይ የተቃጣው ሴራ ከሸፈ
የፌዝ ችሎት
በኢትዮጵያ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የታሰሩበትን ፖለቲካዊ ጉዳይ ህጋዊ ለማስመሰል የተሰየመው የፊዝ ችሎት ለአመታት የከረመበትን ተውኔት ከ 7 አመት እስከ 22 አመት እስር በመፍረድ አጠናቋል፡፡ የፍርዱን ዜና ተከትሎ የሚሰማው የሚነበበው ስሜት ከዚህ በተቃራኒ ፍትሀዊ የሆነ ፍርድ የጠበቁ ሰዎች እንደነበሩ የሚያመለክት ነው፡፡ ከወያኔ የፌዝ ችሎት ይህን ማሰብ ወያኔን አለማወቅ ወይንም ትናንትን መርሳት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ ትግሉ በሚጠይቀው ጽናትና ቁርጠኝት እንዳይካሄድ የሚያደርግ ነው፡፡ ወያኔ በፍትህ ሲያላግጥ በህግ ሽፋን ወንጀል ሲፈጽም እውነትን በጠመንጃው ሲረግጥ ወዘተ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በሀሰት ወንጅሎ፣ በትእዛዝ የሚፈርዱ ዳኞች ሰይሞ፣ የፌዝ ችሎት አቋቁሞ፣ ኣቃቤ ህግ ሳይሆን አቃቤ ወያኔ አቁሞ ፣ በፍትህ ላይ ትያትር ሲሰራ እኛ … [Read more...] about የፌዝ ችሎት
The Conflict between Human Rights and Western Interests In Ethiopia
Ethiopia is an ancient country with modern challenges. In the past forty years, endemic corruption, poor governance, recurrent drought, intense civil war and misuse of foreign aid brought sever famine and disaster to the country. On top of this, Ethiopia has lost its national port and became a landlocked country since 1993. Furthermore, the country is divided into nine regional states which are defined on the basis of ethnicity. Consequently, a number of ethnic conflicts erupted in different … [Read more...] about The Conflict between Human Rights and Western Interests In Ethiopia
ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው!
ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ያደረገው ንግግር ብዙ ጥያቄዎችን መልሷል፤ የኦባማ ጉብኝት ያስከተለው ጫጫታ ሁሉ መልስ አገኘ፤ የሰው ልጆች በመሀከላቸው ምንም ዓይነት የአድልዎ ልዩነት ሳይደረግባቸው በሰውነታቸው ብቻ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብራቸውንና ሞገሣቸውን አስከብረው መኖር እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናገረ፤ ዛሬ የአሜሪካኑ ፕሬዚደንት ያደረገው ንግግር ከፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ እስከ ፖሊሶች፣ መርማሪዎችና አዛዦቻቸው፣ እስከጦር ኃይሉና አዛዦቻቸው፣ አስከዓቃብያነ ሕግና ዳኞች፣ እስከወህኒ ቤት ጠባቂዎችና አዛዦች በየሥልጣን ተዋረዱ ላይ ሆነው የኢትዮጵያውያንን የሰውነትና የዜግነት እኩልነት አፈራርሰው በጎሣ መሠረት ላይ ሊበታትኑት የሚሞክሩትን በኃይለኛ ቃላት ከመሬት በታች ከቶአቸዋል፤ ማሰብና ማስተዋል የጎደለው፣ ከአፍንጫ የራቀ አመለካከት የሌለበት፣ አገርን የሚያጠፋ፣ ከሰውነት ጎዳና … [Read more...] about ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው!
Democracy at Work: Making it Happen in Diaspora
There needs to be a paradigm shift as to how to go about forming a more united front. The usual practice is for one or couple of organizations making the call for unity in one form or shape. We have seen several meetings like this that couldn’t bring all to the table. How can the diaspora model a life of democracy by coming together to create an environment for a dialogue that brings consensus towards One Voice for Ethiopia? We do that by choosing a path we didn’t choose before. The Road Less … [Read more...] about Democracy at Work: Making it Happen in Diaspora









