የጣና በለስ ፕሮጀክት አጭር ታሪክ የጣና በለስ ፕሮጀክት ልማታዊ ግቦች/ህልሞች ምን ነበሩ? የጣና በለስ ፕሮጀክት በአፄው ስርዓት ተጠንስሶ፥ በደርግ አብቦ፥ በህወሀት/ኢህአዴግ እንዴትና ለምን ፈራረሰ? ዛሬ በጣና በለስ ላይ የተጋረጠው አዲስ እና አስደንጋጭ አደጋስ ምንድን ነው? መፍትሄውስ? መግቢያ የአባይ ተፋሰስ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ተፋሰሶች የላቀ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለው ልዩ ቦታ በመሆኑ በርካታ ጥናቶች ተደርገውበታል። የመጀመርያው የአባይና ጣና ዳሰሳ ጥናት የተካሄደው በእንግሊዞች ነበር። ቀጣዩ ዝርዝርና ጥልቅ ጥናት የተካሄደው በአጼ ኃይለሥላሴ ልዩ ጥያቄ ሲሆን ምክንያቱም አወዛጋቢው የእንግሊዝና ጣልያን በ1925 ዓ.ም የተፈራረሙት ውል ነበር። ይህ የወራሪ ሃይሎች ውል ጣልያን ኤርትራ የሚገኘውን ቅኝ ግዛቷንና ሶማሌ ያለውን ቅኝ … [Read more...] about የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ
Opinions
በወልቃይት ጉዳይ የተሰጥ ምላሽ
አቻምየለህ ታምሩ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ አዳነች ፍሰሃዬ ወልቃይትን አስመልክቶ ላነሳችው አመክንዮዎች የሰጠው ምላሽ:- ይድረስ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኛ አዳነች ፍስሀዬ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬ ካለሽበት ቦታ ይድረስሽ። በዛሬው እለት (ህዳር 28, 2016) «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት» በሚል ርዕስ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ዶክተር ብርሀኑ መንግስቱን፣ ፕሮፌሰር አለማንተ ገብረሥላሴና ዶክተር ገላውዲዮስ አርአያን ጋብዘሽ ስለወልቃይት ያቀረብሽውን ዝግጅት በጥሞና ተከታትየዋለሁ። ይህንን ግልጽ አስተያየት እንድጽፍልሽ የገፋፋኝ ምክንያት አንቺ አዘጋጅና አቅራቢ ሆነሽ ባሰናዳሽው በዚህ «የምሁራኖች» የውይይት መድረክ ላይ ይዘሽ የቀረብሽው የግል አቋምና የተሳሳተ ግንዛቤ አመክንዮ የሌለው መሆኑን በመታዘቤ በጉዳዩ ላይ ጥናት እንዳደረገ ሰው ምናልባት … [Read more...] about በወልቃይት ጉዳይ የተሰጥ ምላሽ
የመረራ ምክር ለበረከትና ኢህአዴግ
ወያኔ ሊታደስም ሊታከምም የሚችል ኃይል አይደለም! መወገድ ያለበት እንጂ!
"በገሀነም ውስጥ እጅግ የሚያቃጥለው ቦታ የተያዘላቸው የሞራል ቀውስ በሚታይበት ወቅት ለህዝብ ወገናዊነትን ለማያሳዩ ሰዎች ነው።" Dante መግቢያ ሰሞኑን ወያኔ የሚያወናብደው ራሱን ለማደስ እንደተዘጋጀና ጊዜም እንደሚያስፈልገው ነው። በአገዛዙ ውስጥ የአስተደዳደር ብልሹነት አለ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ባህል ተስፋፍቷል፣ ሙስና ለቢሮክራሲው ማነቆ በመሆን ስራ አላሰራም በማለት የአገርን ዕድገት እየጎተተ እንደሆነ እየመላለሰ ይነግረናል። እነዚህንና ሌሎች የአስተዳደር ብልሹዎችን በየስብሰባውና በቴሌቪዢን „የውይይት መድረከ“ ላይ የሚያወሩልን የአገዛዙ የመሪ ቁንጮዎች በሽታዎቹ ከሰማይ እንደወረዱ እንጂ እነሱ ለአጋዛዛቸው እንዲያመቻቸው ሆን ብለው የፈጠሩትና ከተበላሸ ኢ-ሳይንሳዊና አገር አፍራሽ የአሰራር ዘዴ ጋር እንደተያያዘ አድርገው አይደለም የሚያቀርቡት። በሌላ አነጋገር፣ ለከፋፍለህ ግዛ … [Read more...] about ወያኔ ሊታደስም ሊታከምም የሚችል ኃይል አይደለም! መወገድ ያለበት እንጂ!
Ethiopia: End State of Emergency restrictions on political dissent and targeting of human rights defenders
The Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) is deeply concerned with the wide-ranging restrictions the state of emergency decree has enabled, which severely affect freedom of expression, freedom of assembly, association and peaceful protest in Ethiopia. Ethiopia’s close allies and partners in the international community unequivocally condemn the grave violations of human rights in Ethiopia and the misuse of the directive to silence political dissents, to threaten and systematically … [Read more...] about Ethiopia: End State of Emergency restrictions on political dissent and targeting of human rights defenders
The current alarming state of Ethiopia
Center for Rights of Ethiopia Women (CREW) is deeply concerned with the current state of affairs in Ethiopia. Since the government declared a state of emergency in October, thousands of men, women and particularly young people including journalists, opposition leaders and member were arrested by Ethiopian security forces. According to human rights organizations reports, the body that is authorized with the execution of the state of emergency has been conducting unlawful search of homes and … [Read more...] about The current alarming state of Ethiopia
ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?
ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ይህንን ጽፈዋል፣ ፊደል ካስትሮ፦ የኢትዮጵያና አፍሪካ የቁርጥ ቀን ወዳጅ፤ የክፍለዘመኑ ዳዊት የ፳ኛው ክ/ዘ ካፈራቸው ታላላቅ መሪወች ውስጥ ሁልጊዜም ፍትህና ነጻነት ከሚሹት ጋር በመቆም፤ ሁሌም በትክክለኛው የታሪክ ገጽ በመገኘት ፊደል ካስትሮን የሚስተካከል ማን አለ? ከኒካራጓና ቺሌ እስከ ቬትናም ከፍልስጤም እስከ አልጀሪያ ብሎም ደቡባዊ አፍሪካ ነጻነት ለናፈቃቸው ሁሉ የካስትሮን ያህል ታላቅ ድጋፍ ያደረገ ሌላ መሪ ማንም የለም። በተለይ የአፍሪካ አገራት ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ባደረጉት ትንቅንቅ የካስትሮና የኪውባ ቁርጠኝነት ከጉዳዩ ባለቤቶች ያልተለየ ነበር። ኪውባ ለአንጎላ ያደረገችው እጂግ መጠነሰፊና ከአስር አመት በላይ የዘለቀ ድጋፍ ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። ካስትሮ አንጎላ ከፖርቹጋል ቅኝ ነጻ ለመውጣት ካደረገችው ተጋድሎ ጀመሮ በአሜሪካ ድጋፍ … [Read more...] about ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?
ዲያስጶራዎቻችን
ዲያስፖራ (ዲያስጶራ) የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹ብትን /የተበተነ›› ወይም በአጪር አነጋገር ከትውልድ አገሩ ውጭ ተበታትኖ ያለ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ በዚህ ትርጓሜ ከኢትዮጵያ መቶ ሜትርም ይሁን አንድ ሺሕ ማይል ይራቅ ከድንበር ማዶ ያለ ሁሉ ዲያስፖራ ነው፡፡ የምንገኝበት አገር፣ የትምህርት ደረጃችን፣ የወጣንበት መንገድ፣ ሃይማኖታችን ወይም ብሔራችን ዲያስፖራ ከመሆን (ከመበትን) አያድነንም፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በአውሮፕላንም ይሁን በመርከብ፣ ጥገኝነት ጠይቆም ይሁን አግብቶ፣ ፊደል የቆጠረም ይሁን ፕሮፌሰር የሆነ፣ እስላምም ይሁን ክርስቲያን፣ ዐማራም ይሁን ኦሮሞ ወይም ጉራጌ ወይም ሌላ ከድንበር ወጥተን ወደ ሌላ ሉዓላዊ አገር ከገባን ተበትነናል ማለት ነው፡፡ የምንገኝበት አገርም መመዘኛ አይደለም፡፡ አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤዥያ ወይም ኦሽኒያ መሆናችን ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ … [Read more...] about ዲያስጶራዎቻችን
“የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ነው…” “BBN (አቶ አብዲረሂም አህመድ)
በኦሮሞ ስም እየተደረጉ ያሉትን አብዛኛዎቹን ስብሰባዎች ላስተዋለ ሰው፣ የኦሮሞ ጎሳ ብቻ ሳይሆን በአመዛኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ስብስብ እየመሰለም (“ሆኗል” አለማለታችን ይያዝልን) ሄዷል። አቶ ጃዋር ሙስሊም ከመሆኑ እና ራሱን የኦሮሞ የፖለቲካ ተወካይ/ተጠሪ አድርጎ በየመድረኩ ብቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የኦሮሞ ተውላጅ ልሂቃን፣ አቶ ጃዋርን “በሜጫ አንገት የመቁረጥ” ፉከራው ጋር አዝለው፣ አንድም ጊዜ በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ ማድረግ ሳይችሉ እና እነሱም ሳያወግዙ፣ እስካሁን ድረስ ተሸክመው የመዝለቃቸውም ነገር እኛ በ“ኢትዮጵያ ሴኩላር ሰብዓዊያን” ስር የተሰባሰብነውን ግለሰቦች እጅግ አሳዝኖናል፣ አሳስቦናልም። እሱ ሲገርመን አሁን ደግሞ በቅርቡ BBN በሚባል ስም የሚታወቀው፣ በጸረ-ህወሃት የፖለቲካ አቋሙ እና በእስልምና ሃይማኖት አራማጅነቱ … [Read more...] about “የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ነው…” “BBN (አቶ አብዲረሂም አህመድ)
የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር
መግቢያ ያለፉትን 40 ዓመታት ፖለቲካችንን ለመረመረ አገርን በሚመለከት የሚሰነዘሩት አስተያየቶች ወይም የሚሰጡት ትንተናዎች ሁሉ ሳንይሳዊ ይዘት ይኑራቸው አይኑራቸው የሚጠይቅ የለም። በተለይም ፖለቲካ ፍልስፍናዊ መሰረት ያለው ታላቅ ፅንሰ-ሃሳብ መሆኑ ግንዛቤ በሌለበት አገርና፣ ማንኛውም ህብረተሰብንና የአገርን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከት ረገድ የግዴታ ሳይንሳዊ ትንተና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቶ ስሜት ዋናው መመሪያ በሆነበት አገር የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ትክክል መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ቁጭ ብሎ በሰከነ መንፈስ ለመመርመር የሚቃጣ ሰው በፍጹም የለም። እንደሚታወቀው በተለይም በአብዮቱ ወቅት ሳይንስና ፍልስፍና መመሪያ መሆናቸው ቀርቶ ስሜት የፖለቲካውን መድረክ በመያዙ እንደተከታተልነው ለብዙ መቶ ሺህ ህዝብ መሞትና ለአገር ውድመት የራሱን አስተዋፅዖ አበርክቶ አልፏል። ዛሬ … [Read more...] about የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር









