የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን … [Read more...] about ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
Opinions
መሆን ካልነበረበት ድርጊት ጋር ስንላመድ
(ለውይይት መነሻ) በዚህ ጽሁፌ ላንባቢዎቼ ለማቅረብ የፈለግሁት ሁለት ተያያዥ ጉዳዮችን ነው። የመጀመርያው፣ ወያኔ ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ሲፈጽማቸው የነበረውን “ነውሮች” እንዴት እንደ “ጽድቅ” እንደተጠቀማባቸውና የኢትዮጵያንም ህዝብ “ጽድቅ” ነው ብላችሁ ተቀበሉ ብሎ እንዳስገደንና እኛም በመላመድ ብዛት ተዋህዶን እንደተቀበልነው፣ ሁለተኛው ደግሞ ይህንን “ነውር” እንደ “ጽድቅ” በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጭኖ ሲበድል የነበረው ወያኔ (ህወሃት)፣ በምንም መልኩ የትግራይን ህዝብ እንደማይወክል ለማስረዳት ነው። ግምቱ የግሌ እንጂ የሌላ የማንንም አካል አስተሳሰብ ስላይደለ፣ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ለተካተቱት ግምቶች፣ መረጃዎችም ሆነ መደምደሚያዎች ተጠያቂው እኔ ብቻ ነኝ። ይህ እንግዲህ “ለውይይት መነሻ” የቀረበ ስለሆነ በይዘቱ ላይ ያላችሁን ሃሳብ እንደኔው በጽሁፍ ብታወጡ፣ ባገራችንን ላይ … [Read more...] about መሆን ካልነበረበት ድርጊት ጋር ስንላመድ
“እናንተ ሰው ናችሁ?” ትራምፕ ለአፍሪካ መሪዎች
ከዚህ በታች የተጻፈውን ፕሬዚደንት ትራምፕ አለ ተብሎ ፌስቡክ ላይ ያገኘሁት ነው፤ “ነፃነታችሁን ካገኛችሁ ከ50 ዓመታችሁ በኋላ ለሕዝቦቻችሁ አስፈላጊውን የመገናኛ ዘዴ ካልሠራችሁላቸው እናንተ ሰው ናችሁ? እናንተ በወርቅ ላይ፣ በዕንቁ ላይ፣ በዘይት ላይ፣ በማንጋኒዝ ላይ፣ በዩራኒየም ላይ ተቀምጣችሁ ሕዝቦቻችሁ የሚበሉት ሳይኖራቸው ሲቀር እናንተ ሰው ናችሁ? እናንተ በሥልጣን ላይ ሆናችሁ የጦር መሣሪያ ከባዕዳን ለመግዛትና ዜጎቻችሁን ለመግደል የማታመነቱ ከሆነ እናንተ ሰው ናችሁ? የናንተ ማኅበረሰባዊ ዓላማ ሕይወታችሁን በሙሉ በሥልጣን መንበር ላይ መቆየት ከሆነ እናንተ ሰው ናችሁ? እንደሚታደን አውሬ ዜጎቻችሁን የምትገድሏቸው ከሆነ ማን ያከብራቸዋል? ” (ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም!) እነዚህ ሁሉ እውነቶች የሚያጠራጥሩ አይመስለኝም። … [Read more...] about “እናንተ ሰው ናችሁ?” ትራምፕ ለአፍሪካ መሪዎች
Ailing Civic Space in an Authoritarian State: The State of Human Rights Defenders and Cost of Dissent in Ethiopia
Journalists, activists, and other civil society actors play a pivotal role in building a transparent system of governance in any society. The UN Declaration on Human Rights Defenders* affirms that everyone, individually and in association with others, has the right to submit to governmental public bodies, criticism and proposals for improving their functioning, and to draw attention to any aspect of their work that may hinder or impede the promotion, protection, and realisation of human rights … [Read more...] about Ailing Civic Space in an Authoritarian State: The State of Human Rights Defenders and Cost of Dissent in Ethiopia
የወሎ ዐማራ የሰሞኑ ጉዳይ ማጠቃለያ ሪፖርት (የእስካሁኑ ሒደት)
የትግሬ ወያኔ አፈ ቀላጤዎች ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት በወልዲያና በመርሣ ቆቦ አካባቢ እንደደረሰ ኡኡታቸውን ሲያሰሙ ሰንብተዋል። ዕውነታው ግን ሌላ ነው። የወሎ ዐማራ ጠላቱን በደንብ ለይቶ ነው ጥቃት ያደረሰው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ከትግሬዎች ንብረት በላይ የዐማራ ተወላጅ (ባንዶች) ንብረት ላይ ነው ጉዳት የደረሰው። ሁሉንም በዝርዝር ከዚህ በታች አቅርበነዋል። በባንዳ ዐማሮች ላይ የተወሰደው እርምጃ አስተማሪ ይመስለኛል። ሰውን ያክል ነገር ገድሎ እስከማቃጠል ያደረሰው በደል ምን ቢሆን ነው ብሎ የማይጠይቅ አእምሮ መቼም ቢሆን ሊማር ስለማይችል ቀጣይ ተረኛ መሆኑ አይቀርለትም። ጠቅለል አድርገን ሪፖርቱን ስናየው በመርሳ ወረዳ ለሕዝብ ተብለው የተቋቋሙ ግን ምንም ያልፈየዱ የወያኔ መሥሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። ለመዘርዘር ያክል፤ 1. የሀብሩ/መርሳ ከተማ ፍ/ቤት 2. … [Read more...] about የወሎ ዐማራ የሰሞኑ ጉዳይ ማጠቃለያ ሪፖርት (የእስካሁኑ ሒደት)
“የሃይማኖት አባቶች” የሰላም ጥሪ
“ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?” ዳንኤል ክብረት በትናንት ምሽቱ የ“ሰላም ዋጋ” ዲስኩር አፈሙዝ ሳይሆን “ዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን” ተወግዟል። የሃገሪቱ እድገት እና ትራንስፎርሜሽንም ተወድሷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ዻዻስ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴያስ ፓትሪያሪክ፣ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአክሱም ወጨጌ፣ ዘመንበረ ተክለሐይማኖት…. ወዘተ “… (ሃገሪቱ) ለሁሉም ልጆችዋ የምታበላው ከሌላት ከየት ታምጣ?” ብለውናል። “ሕዝቡ ቢያገኝም አይረካም” የሚሉን አቡነ ማቴያስ እዚያች ቦታ ላይ እንዴት እንደተቀመጡ የታወቀ ነውና ከእርሳቸው ከዚህ የተለየ ነገር ፈጽሞ አንጠብቅም። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሃጂ ከድር ሁሴንም እንደ ገለልተኛ ሰው ተሰይመዋል። የአብያተክርስቲያናት ህብረት … [Read more...] about “የሃይማኖት አባቶች” የሰላም ጥሪ
የገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ ሲተረጎም
ኦቦ ለማ መገርሳ ህወሃት ያጎራቸውን 2,345 እስረኞች ነጻ አወጡ የሚለውን ዜና በቀኝ እየሰማን፣ የገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ ደግሞ በግራ በኩል ብቅ አለ። ሰበር ጋዜጣዊ መግለጫ። በርግጥም "ወገብ የሚሰብር"። ልዩ መግለጫው ተከባብዶ ሲነገረን "ገዱ ደግሞ ስንት ሺህ አማሮችን ከእስር አስለቀቀ" እያልን በጉጉት ባንጠብቅም "የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሕዝቦች ሆይ በወልድያ እና በቆቦ ለተፈጸመው እልቂት ተጠያቂው እኔ የምመራው ብአዴን ነው" ብሎ አረፈው። ይህቺ ሃላፊነት የመውሰድ ዲስኩር ደግሞ አዲስዋ ቅኝት መሆነዋ ነው። ለትርጓሜዋ ቱርጁማን የማያሻት ቅኝት። ማራቶን ያሉት የአራቱ ድርጅቶች ስብሰባ እንዳበቃ አይቴ ደብረጽዮን ገብረ-ሚካኤልም ረገጥ ዓድርጎ ብሏታል። የናቴ ቀሚስ አድናቅፎኝ ... ምናምን የምንለው ነገር የለም። ለጠፋው ጥፋት ሁሉ ሃላፊነቱን ወስደናል። ብሎ ተነግሯል። ይህንን … [Read more...] about የገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ ሲተረጎም
ፍትሕ ለዐማራ ሕዝብ!
ኢትዮጵያ አገራችን በዘመኗ ሁሉ ብዙ ፈተናዎችን አሳልፋለች።አሁን የገጠማት በዓይነቱም ሆነ በብዛቱ በወርዱም ሆነ በቁመቱ ዘመናት ከደቀኑባት ሁሉ የተለየ ነው።ከዚህ ውስጥ አንዱ ሕዝቦቿ ጎራ ለይተው በጎጥ ተቧድነው፣ ዘረኞች እር በርሳቸው እንዲፋጁ የደገሱላት የመጠፋፋት ድግሥ ነው። ለዚህ ዕኩይ ግባቸው የመስዋዕት ጠቦት ያደረጉት ደግሞ ዐማራውን ነው። ወደ ተሻለና የሁሉም ዕኩልነት የተረጋገጠባት ዴሞክራሲያዊት አገር እንደመመሥረት እና ሁኔታዎችም ይህንኑ ፈቅደውላቸው እያለ ወደ ኋላ ቀር የዘርና መንደር ናፋቂነት የወሰዱን ዘረኞች፣ በሕዝባችን ላይ የፈጸሙትን የግፍ ዓይነት ዘርዝሮ ለመግለጽ አዳጋች ነው። ይህንን ኢሰብአዊ ወንጀል ለመፋረድና ፍትሕ ለሁሉም በዕኩል እንዲደርስ ወንጀለኞችን በፍትህ አደባባይ ለመፋረድ ሕዝቡ ሙሉ ዝግጅቱነቱን በአደባባይ እየገለጠ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ዘመንና … [Read more...] about ፍትሕ ለዐማራ ሕዝብ!
The Ethiopian Diaspora Flexing its Muscle Against a Killer Regime in Addis Ababa
(Our hard-earned foreign currency should help our beloved families, not TPLF Killers and Torturers) Ethiopian diaspora residing in industrialized nations have their country and their family at heart, so they sacrifice a lot to helping immediate and extended families in their homeland. It is very common among Ethiopians, as it is for most immigrants from other poor nations, to work two or three jobs and save some of their hard-earned money to help families, relatives and friends. Despite the … [Read more...] about The Ethiopian Diaspora Flexing its Muscle Against a Killer Regime in Addis Ababa
ሕዝብ ፍርሃትን እያሸነፈ፤ የወያኔም ጀንበር እየጠለቀች ነው!
ፍርሃትን እያሰረጸና እያነገሰ የኖረው ፖለቲካችን ነጻነታችንን፣ ክብራችንን፣ ታሪካችንን፣ ስብዕናችን እና አብሮነታችንንም ጭምር ሲያኮስስና ሲያረክስ፤ እንዲሁም የወደፊት ተስፋችንም ላይ ጥላውን ሲያጠላ እያየን ነው። የማንኛውም አንባገነናዊ ሥርዓት ሥነ-ልቦናዊ መሰረቱ ፍርሃት ነው። አንባገነኖች ያላቸውን ኃይል ሁሉ የሚያሟጥጡት ሕዝብን በማሸበር የፍርሃት ቆፈን ውስጥ እንዲቆይ በማድረግ ነው። ለዚህም አራት ነገሮችን በዋነኝነት ይጠቀማሉ። የመጀመሪያው የጡንቻቸውን ልክ ለማሳየት ዱላና ጠመንጃን በመጠቀም የጭካኔ በትራቸውን በሕዝብ ላይ ማሳረፍ ነው። ለመቀጣጫም ከማህበረሰቡ ውስጥ የነቁና ሥርዓቱን በአደባባይ የሚተቹ እና የሚያሳጡ ሰዎችን ዒላማ በማድረግ ያስራሉ፣ ይገርፋሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አልፎም ይገድላሉ። ሁለተኛው ፍርሃት የሚያሰርጹበት መንገድ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃንን በቀጥታና በተዘዋዋሪ … [Read more...] about ሕዝብ ፍርሃትን እያሸነፈ፤ የወያኔም ጀንበር እየጠለቀች ነው!










