ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አዲስ አበባ አመልካች፡- ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው ጉዳዩ፡- በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ (በአየር ሞገድ በሚሰራጩ የብዙኃን መገናኛዎች) በፖለቲካዊና በሕገወጥ መመሪያዎች የመደመጥ ወይም የመስተናገድ ዕድል ስለመነፈግ በአየር ሞገድ የሚደመጡ የብዙኃን መገናኛ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሚለቀቁ ዘፈኖች በአንድ ነጠላ ርእሰ ጉዳይ ላይ ማለትም በጾታዊ ፍቅር ላይ ብቻ ማተኮር እና ከያኔያኑም ቀድሞ ከነበረን የኪነት አትኩሮት በተቃራኒው ሀገርን ወደፊት ሊያራምዱ የሚችሉ፣ ትውልድን የሚቀርጹ ማለትም ሥነ-ምግባሩን ሥነ-ልቦናውንና ሰብእናውን የሚያንጹ ስንት ቁምነገሮች እያሉ ይህንን ርእሰ ጉዳይ ብቻ ያውም አንጋዶ ማለትም ከግብረ-ገባዊ አመለካከት አንጻር ትክክል ባልሆነ አቅጣጫ ሙጥኝ ብሎ መቅረት አገራችን ድሀ እና ልማት የጠማት ሀገር ከመሆኗ አንጻር … [Read more...] about የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ተከሰሱ!!
Opinions
ሰላማዊ ትግል በካዮች እና መከላከያ ምክሮች!
ህውሃት (መንግስት) ህዝብን የሚገዛበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ አቅሙ ከሰማይ የሚወርድለት ወይንም በተፈጥሮው ከውስጡ የሚንጠፈጠፍለት ሳይሆን ከህዝብ የሚነጭለት ነው። ፖሊሱም፣ ደህንነቱም፣ የኢቲቪ ሰራተኛውም፣ የቃሊቲ አስተዳዳሪውም፣ የኢምባሲ ሰራተኛውም፣ ወ.ዘ.ተ. ከህዝብ የሚመለመሉ ናቸው። ለህውሃት በደሞዝ ክፍያ ያገልግሉ እንጂ የሰዎቹም ሆኑ የደሞዛቸው ምንጭ ህዝብ ነው። በግብር እና በሌሎች ምክንያቶች ከህዝብ የሚሰበሰብ ነው ደሞዛቸው። አሊያም በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከውጭ በዕርዳታ፣ በብድር ወይንም በሌሎች ስምምነቶች የሚያገኘው ነው ደሞዛቸው። የፋብሪካ፣ የኢንዱስትሪ፣ የመገናኛ፣ የትራንስፖርት፣ የአየር መንገድ፣ የመድህን ሰራተኞች፣ የንግድ እና አገልግሎት ድርጅቶች ወ.ዘ.ተ. በሙሉ ስራ ቢያቆሙ ከህዝብ መንጭቶ ወደ ህውሃት የሚፈሰው ሃብት ብር ይቋረጣል። ህውሃት … [Read more...] about ሰላማዊ ትግል በካዮች እና መከላከያ ምክሮች!
ፖለቲካ ሳይንስ ነው ወይ? ፖለቲካ ምሁራዊነት ያስፈልገዋል ወይ?
መግቢያ በዚህ አርዕስት ላይ ለመጻፍ ከአሰብኩ ረዥም ጊዜ ሆነኝ። እንደሚታወቀው አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ቀላል አይደለም። የመንፈስ ርጋታን የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ ለአንባቢ የሚቀርበው ጽሁፍ ከርስ በርስ ቅራኔዎች የተላቀቀና አሳማኝ እንዲሆን አድርጎ ለመጻፍና ለማስነበብ ረዥም ጊዜን ይፈጃል። ብዙ ዕውቀትንና ምርምርን ይጠይቃል። ተመራምሮና የተለያዩ አስተሳሰቦችን አወዳድሮና አመዛዝኖ ለአንባቢ አንድ የሚያረካና እንደመመሪያ ጥናት ለማቅረብ ረዥም ጊዜ ብቻ ሳይሆን ቢያንስ የሶስትና የአራት ሰዎችን የስራ ክፍፍል ይጠይቃል። አንድ ሰው ብቻ የሚጽፍ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ የሶስት ወር ዝግጅት ማድረግ አለበት። በተጨማሪም በኢንስቲቱሽንና በገንዘብ የሚደገፍ መሆን አለበት። በተለይም ለአገር ዕድገትና ነፃነት ተብሎ የሚጻፍ ጽሁፍና የፖለቲካ ሀተታ በአቦ ሰጡኝ የሚቀርብ ሳይሆን ብዙ ጥንቃቄን … [Read more...] about ፖለቲካ ሳይንስ ነው ወይ? ፖለቲካ ምሁራዊነት ያስፈልገዋል ወይ?
መልካም ጅምር፡ ተደጋጋሚ ስህተቶች
የአንድነት ፓርቲ አመራር አካላት በፈረንጅ አቆጣጠር ኦገስት 30 ቀን ከሚድያ አካላት ጋር ያደረጉትን የቴሌ ኮንፈረንስ ውይይት በጥሞና ተከታትያለሁ:: መልካም ጅምር ቢሆንም ተደጋጋሚ ስህተቶች ከመፈጸም ግን የተቆጠብን አይመስልም:: በውይይቱ ላይ ብዙ መልካም ነገሮች ቢሰሙም የሚፈጸሙት ስህተቶች ግን ያው የጥንት የጠዋቱ በመሆኑ ውይይቱ ምን ያህል ወደፊት የሚያራምድ መሆኑ መገመት ይከብዳል:: የተንሸራሸሩት ሀሳቦች አዲስ ፈጽሞ የማናውቃቸው አይደሉም:: የተቃዋሚ ኅይሉ ደጋፊዎች ስጋት የታወቁ ናቸው:: ትልቁ ጥያቄ መልስ በአጥጋቢ ደረጃ ያልተገኘለት ተቃዋሚዎች አንድ ላይ መስራት ለምን ይቸግራቸዋል የሚለው ነው? የተቃዋሚ አመራር አካሎችን አብረው እንዲስሩ ደጋፊ አደራ የሚጥልባቸው ወይም ተጽዕኖ የሚያሳድርባቸው መንገዶች ተድበስብሰው በመታለፋቸው ካለፈው አሁን ምን አሻሸላችሁ … [Read more...] about መልካም ጅምር፡ ተደጋጋሚ ስህተቶች
ህዝበ-ሙስሊሙን ያለአግባብ በስጋት መፈረጅ፤ ማዋከብና መግደል በአፋጣኝ ይቁም!!
የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀጽ 11 ቁጥር 3 ”መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሀይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ” ይላል፡፡በሀገራችን ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ በወታደራዊው ደርግ እንዲሁም አሁን ስልጣን ላይ ባለው ወያኔን ጨምሮ ሁሉም ሀይማኖቶች ከመንግስት ጣልቃገብነት ነፃ ሆነው አያውቁም። ፍትህ፣ ነጻነት፣ እኩልነት እና አንድነት ለብዙ ሀይማኖቶች መሰረታዊ እሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ እሴቶች ላለፉት 22 ዓመታት በዘረኛው የወያኔ መንግስት እየተሸረሸሩ እና እየተመናመኑ ዛሬ ከነአካቴውም ለመጥፋት ተቃርበዋል፡፡ ስለመሰረታዊ የሰው ልጅ መብት እና ነጻነት እንዳይወራ የወያኔ የጥይት አፈሙዞች በእያንዳንዱ ሰው እና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ተደቅኗል፡፡የእምነት ቦታዎችንም ሳይቀር በመድፈር ህዝበ-ምዕመኑ የኔ የራሴ የሚለው የአምልኮ ቦታ እና የአምልኮ ስርዓት … [Read more...] about ህዝበ-ሙስሊሙን ያለአግባብ በስጋት መፈረጅ፤ ማዋከብና መግደል በአፋጣኝ ይቁም!!
ተመስገን እላለሁም ፣ አልልምም !
በሰላም አውሎ ላሳደረኝ ፈጣሪ ስተኛም ሆነ ስነሳ " ተመስገን ፈጣሪየ! " የምትለዋን ምስጋና ከማቅረብ ተቆጥቤ አላውቅም ። ቸርነቱ የማያልቅበት ፈጣሪ አምላኬ አጉድሎብኝ አያውቅም! ጤና ስጠኝ ስለው ጤናውን ፣ ጥበብ መላ ላጣሁለት መላ ስጠኝ ስለው መላ ብልሃቱን ፣ ጉልበቴን አበርታው ስለው ብርታቱን ፣ ቅን ልቦና ስጠኝ ስለው ርህራሔውን እና የፈለግኩትን ሁሉ አያጓድልብኝም! እናም ዘወትር ተመስገን እለዋለሁ ! ገና ከአልጋየ ሳልነሳ ከአፊ ውስጥ አንድ ቃል ይመላለሳል ፣ ቃሉ ወደ አረፍተ ነገር ሺር በሎ ተቀየረ ! በጨለማ የማያይ አይኔን ወደ ድቅድቁ ጨለማ የመኝታ ክፍል ጣራ አፍጥጦ በምናብ አነበንበዋለሁ ... በጀርባየ ተኝቸ ወደ ጣራ ካፈጠጥኩበት ወደ ጎን ግልበጥ እልና እጆቸን ጭንቅላቴ ስር ወሸቅ አድርጌ ከአፊ የማወጣውን አረፍተ ነገር ደጋገምኩ " ተመስገን ተመስገን ተመስገን … [Read more...] about ተመስገን እላለሁም ፣ አልልምም !
Tigray Republic flaunting her wealth at glittering TDA functions across the globe.
Created by the dead enclave hero Meles Zenawi and officially known as the regional state of Tigray, state within a state and the birthplace of the current ruling party in Ethiopia, Tigre People Liberation Front/TPLF; Tigray republic is holding its glittering annual Tigray Development Association/TDA functions around the world with tyrannized and indigent Ethiopian taxpayers footing the huge bill. After a week long music and dance spectacle in various US cities, where scrumptious meals and … [Read more...] about Tigray Republic flaunting her wealth at glittering TDA functions across the globe.
የአንድነቶች ሰላማዊነት ጽናት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮሚያ!
“አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ሰላማዊ ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡” የሚለውን መርሃቸውን አንድነቶች ካስተዋወቁን ከርመዋል። ባለፈው ሳምንት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮምያ የተተከሉት መረን የለቀቁ አምባገነን አስተዳደሮች እና ደህንነቶች የፈጸሙባቸውን ወደር የለሽ የአንደበት፣ የሳይኮሎጂ እና የአካል ጥቃት በፈገግታ በመቀበል እየሞቱ ሳይገድሉ በሰላማዊ ትግል ህገ-መንግስቱን ለማስከበር ያላቸውን ጽናት ደግመው አሳይተውናል አንድነቶች። አንድነቶች የሚሰብኩትን የሚፈጽሙ መሆናቸውን ኢትዮጵያ እንደገና ባለፈው ሳምንት ተመልክታለች። የባሌ ሮቤ እና የፍቼ አምባገነን አስተዳዳሪዎች እና ደህንነቶች አረመኔነት አሳፋሪ ነበር። በፍጹም የስልጣኔ አየር የነፈሰባቸው አይመስሉም። ዘመናዊ አስተሳሰብ ለአንድ ቀንም የጎበኛቸው አይመስሉም። ይባስ ብሎ የባሌ ሮቢ … [Read more...] about የአንድነቶች ሰላማዊነት ጽናት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮሚያ!
The Totolamo-Kofele blood bath victims named, death toll still climbing.
“Wolahi, Wolahi…” swears 85 year old Totolamo village barley farmer and cattle herder Hajji Abdinur Shifa when a reporter asked him if he know any terrorist hiding in his village. His face looks like a paint of sorrow and grief. His wife affectionately called by the villagers, Adiyo, was too fragile to talk about the August 3 2013 blood bath that turned their agriculture and livestock rich village into an inferno. “My son took three bullets and died a day later at Sashemene general hospital. … [Read more...] about The Totolamo-Kofele blood bath victims named, death toll still climbing.
ዘረኝነት ምንድን ነው?
አንዳንዴ፣ ጊዜና ሁኔታውን ከጠበቁ አንድ ሁለት ቃላት፣ ከሺ ዓ/ነገሮች የበለጠ በአእምሮ ውስጥ ይገቡና እውነቱን ቁጭ ያደርጉታል። አውሮፓውያን መቼም በዘረኝነት የተጠመቁበት ጊዜ አለፎና ተመክሮዋቸውን ሰብስበው ለራሳቸው፣ በተለይ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ፣ በሰላም ለመኖር ይሞክራሉ፤ የኋላኋላ ተባብረው፣ ቀደም ሲል ደግሞ ቢያንስ በየራሳቸው መንግሥታት ሥር። በተለይም ጀርመን ስለዘረኝነት ተመክሮ ያውራ ቢባል፣ ይህ እንደማይሳነውና እንደሚችል ማንንም አያጣላም። ይህም ሆኖ ግን አሁንም ህዝቡ ከዳር እስከ ዳር፣ ከዚህ በሽታ ነጻ ነው ማለት አይደለም። ስለሆነም በስፖርት ሜዳ ላይ ሁሉ በተለይም እግርኳስ ጨዋታ ላይ ይህ የዘረኝነት በሽታ ደጋግሞ ይንጸባረቃል። አልፎ አልፎም ከአፍሪቃ በመጡ ወይንም እዚህ በተወለዱ ጥቁር ተጫዋቾች ላይ የዘረኝነት ስድቡ ሲበዛ፣ አእምሮ ያለው ዳኛ ጨዋታውን … [Read more...] about ዘረኝነት ምንድን ነው?










