ርሃብ፣ ድካም እና ሰቆቃው ለላፉት 12 ወራት ተፈራርቀውበታል። አንዴ በሰሃራ በረሃ ሌላ ግዜ ደግሞ በሜዲትራንያን ባህር የሰው አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ስቃይ አልፎ እግሩ አውሮፓን ምድር ከረገጠ እነሆ አንድ ሌሊት አለፈ። ሰነድ ገብረጻድቅ ይባላል። ፊቱ እጅግ ተጎሳቅሏል። ከሰውነቱ ላይ አጥንቶቹ ይቆጠራሉ። ወጣቱ ተስፋ ወዳደረገባት የአውሮፓ ምድር ለመግባት የተነሳው ከአመት በፊት ነው። እንብርቱ የተቀበረችበትን ሃገር ተሰናብቶ ከወጣ ጀምሮ የደረሰበት መከራ ይህ ነው አይባልም። ሰነድን እመንገድ ወድቆ ነበር ያገኘሁት። ለጥቂት ደቂቃ አነጋገርኩት። ንግግሩ የሚረብሽ ነው። አጭር የቪዲዮ ቆይታችንን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ። ከ 300 በላይ የኢትዮጵያውያ እና የኤርትራ ተወላጆች የፈጀው የላምፔዱሳ እልቂት በአለም አቀፍ ዜና እየታወጀ ባለበት ሰዓት፤ ሌላ መርከብ ከሊቢያ ተነስታ … [Read more...] about መንገድ ወድቆ አየሁት
Opinions
የምርትና የሕዝብ እድገት እሽቅድድም
እአአ በ1798 (ከሁለት መቶ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት) መምሬ ቶማስ ሮበርት ማልቱስ የሚባል የ32 ዓመት የብሪታንያ ቄስ የዘመኑን የነገረ ንዋይ አስተሳሰብ የለወጠ አዲስ ሀሳብን የያዘ መጽሐፍ አሳተመ፤ ሀሳቡ በጣም ግልጽ ነበረ፤ የሰው ልጆች ቁጥር እድገት መጠኑ እያጠፈ የሚሄድ ነው፤ የሕዝብ ቁጥር 1፣ 2፣ 4፣ 8፣ 16፣ 32፣ 64፣ 128፣ እያለ የሚጨምር ነው፤ ከእርሻ የሚገኘው ምርት ደግሞ የእድገቱ መጠን አያጥፍም፤ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10፣ እያለ የሚሄድ ነው፤ የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ በሌላ መንገድ ካየነው የበላተኞች ቁጥር እያጠፈ ሲያድግ የምግቡ አቅርቦት የሚያድገው ግን በጣም በዝግተኛ ፍጥነት ነው፤ የሚል ነው፤ እንግዲህ የሕዝብ ቁጥርና የምርት አቅርቦት እኩል መጓዝ ሲገባቸው የሕዝቡ ቁጥር እየቀደመ ስለሚገኝ፣ መምሬ ማልቱስ የደረሰበት … [Read more...] about የምርትና የሕዝብ እድገት እሽቅድድም
መሬት የማን ነው?
አገር ማለት በአባቶች፣ በአያቶችና በቅድማያቶች አጥንትና ደም ተገንብቶ የታጠረ መሬት ነው፤ የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ዋይታ እየኮረኮረ የሚያወጣውና የሚያስተጋባው የፍቅር ስሜት ምንጭ ነው። የተከሰከሰውና ተፈረካክሶ አፈር የሆነው አጥንትና የወረደው የአያቶችና የቅድማያቶች ደም እየፈሰሰ መሬቱ ላይ በሚገኙ ወንዞች ውስጥ ሁሉ ገብቶአል፤ እንዲያውም እነዚህ ወንዞች ወስደው በቀይ ባሕር፣ በሜዲቴራንያን ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ጨምረውታል፤ ይህ በአጥንትና በደም የታጠረ መሬት የማን ነው? በመሬቱ ላይ የባለቤትነት መብትን ለማስከበር ከውጭ ኃይሎች ጋር የተጋደሉት ጥንታውያን ነፍጠኞች ቅድሚያን የሚያገኙ ይመስለኛል፤ እነዚህ ጥንታውያን ነፍጠኞች ብቻቸውን አልነበሩም፤ ለምግብ የሚሆናቸውን ሁሉ የሚያመርቱ ገበሬዎች ነበሩ፤ ለልብስ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚፈትሉና የሚሸምኑ ባለሙያዎች ነበሩ፤ … [Read more...] about መሬት የማን ነው?
“ያላወቂ ሳሚ … ይለቀልቃል”
የጎልጉል ጥብቅ ማሳሰቢያ! ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ዋናው ዓላማ የሕዝብ እንደመሆኑ በጨዋነት የሚላኩልንን ጽሁፎች የምናትም መሆናችንን ስንገልጽ ቆይተናል፡፡ ሆኖ ግን አልፎ አልፎ የሚላኩልን ጽሁፎች በግለሰብ ዙሪያ ያጠነጠኑ ከመሆናቸው ባሻገር ምንም እንኳን ጸያፍ ቃላትን በግልጽ የሚታይባቸው ባይሆንም የሚሰነዘሩት ሃሳቦች ግን የግለሰቦችን ሰብዕና የሚነካ ከመሆኑ ባሻገር በስራችን ላይ ከፍተኛ ውስብስብ ነገር የሚፈጥርና ወደ አልተፈለገ እንካሰላንቲያ የሚመራ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በመሆኑም በእንደዚህና መሰል ጽሁፎች ላይ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለየት ያለ የኤዲቶሪያ ፖሊሲ በመጠቀም ጽሁፎችን እንደሁኔታው እያየን የምናትም መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ በተለይ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አስተያየት ዙሪያ የሚላክልንን ማንኛውንም ጽሁፍ የማንቀበል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ በጉዳዩ ለመነጋገር … [Read more...] about “ያላወቂ ሳሚ … ይለቀልቃል”
የልማት መጀመሪያው ሰብዓዊ መብትን ማክበር ነው!
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about የልማት መጀመሪያው ሰብዓዊ መብትን ማክበር ነው!
A Journalist kidnapped, Threatened, and Beaten by Intelligence and Security Agents in Ethiopia
The Ethiopian journalist Bisrat Woldemichael was kidnapped, threatened, humiliated, and beaten by the Ethiopian intelligence and security agents on 28 August, 2013. He has reported this incident today to journalists. Bisrat reported that the dreadful incident took place at Gotera, a place in the capital Addis Ababa as he was walking home from work. He said he was victimized for exercising his right to free expression in conjunction with the related right to press freedom. Bisrat Woldemichael … [Read more...] about A Journalist kidnapped, Threatened, and Beaten by Intelligence and Security Agents in Ethiopia
ዲያስፖራ ላሜ ቦራ
ይኸ መጣጥፍ መጀመሪያ የተጻፈውና በኢትዮመዲያ፣ በኢካዲኤፍ፣ በአዲስ ቮይስ፣ በኢኤምኤፍ እና በጎልጕል ድረ-ገጾች የተበተነው በእንግሊዝኛ ተደርሶ ነበር። በጣም ብዙ አስተያየት ሰጪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዬም ኢ-ሜይል ሳይቀር የተሰማቸውን አካፍለውኛል። ሁሉም ወደ አማርኛ እንደመልሰውና ብዙ ኢትዮጵያውያን ለማንበብ ዕድል እንዲያገኙ አጥብቀው ስለአሳሰቡኝ ጥይቄአቸውን ተቀብዬ ወደ አማርኛ መለስኩት። ከኢትዮጵያ የሚደርሱን ቀልዶች ለዛቸው ጨምሯል። ሰሞኑን፣ አንድ ከአገር ቤት የመጣ እንግዳ፣ የወያኔ ባለሥልጣናት፣ ዲያስፖራን “ላሜ ቦራ” እያሉ እንደሚሾፉብን አጫውቶን አዝናንቶናል። እውን እኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ የተሰደድን ኢትዮጵያውያን ያለማቋረጥ የምንታለብ የካሽ ጥገቶች ነን? መቼም በኔ ዕድሜ ትምህርት ቤት የሄዳችሁ ሁሉ፣ስለላሜ ቦራ የተተረከ የልጆች ጣፋጭም አሳዛኝም ታሪክ ሳታነቡ … [Read more...] about ዲያስፖራ ላሜ ቦራ
የፖለቲካ ኃይል ምንጮች
ክፍል አንድ የዝንጀሮዎቹ ጌታ አጭር ታሪክ የተወሰደው ቻይናዊው ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የሞራል ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው። ይኽ አጭር ታሪክ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ከየት እንደሚፈስላቸው (ምንጩ ምን እንደሆነ) እና እንዴት ምንጩን በመቆጣጠር የአምባገነኖችን አቅም መቆጣጠር አልፎም ምንጩን በማድረቅ አምባገነኖችን ማስራብ እንደሚቻል በምሳሌ አድርጎ ግልጽ ያደርጋል። ሰለዚኽ የሰላማዊ ትግል ተመራማሪው እና ዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስ ጠበብቱ ሲድኒ ታይ (Sidney Tai) ከቻይንኛ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ተረጎመው። የእንግሊዘኛ ትርጉሙን “በማጭበርበር መግዛት” (“Rule by Tricks”) የሚል ርዕስ ሰጠው እና ሰላማዊ ቅጣቶች (Nonviolent Sanctions) በሚል ርዕስ የአልበርት አነስታይን ሰላማዊ ትግል ምርምር ተቋም በሚያትማት ጋዜጣ ላይ … [Read more...] about የፖለቲካ ኃይል ምንጮች
አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት!
ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ። ቀን መስከረም 8: 2006 ለ5ኛ ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ኮኔትነር ውስጥ፡ የአንዲት ኢትዮጵያዊት አስዛኝ፡ ህልፈተ ህይወት የአካባቢውን ማህበረሰብ እምባ ሲያራጭ፡ ደረት ሲያዳቃ መዋሉን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ኮንትራት የመጣች የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗን የሚናገሩት እነዚህ የአይን እማኞች የወጣቷ ሬሳ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱን አረጋግጠዋል። የእህቶቻችን ሞት ከሚፈበረክበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የስደተኞች ጊዜ ያዊ መጠለያ ኮንቴነር፡ ያለምንም ህክምና እና በቂ መሰረታዊ ፍጆታ በለሌለበት ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ የኮንቴነር የብረት በር ተከርችሞባቸው ከሚገኙ እህቶቻችን መሃከል አንድ … [Read more...] about አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት!
የኤርትራ ጉዳይ በሶስት ትውልዶች ውስጥ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ እንደቀልድ እና እንደ እልህ የጀመሩት ''ኤርትራ ኢትዮጵያዊ አይደለችም'' ብሎም ''የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው'' አጀንዳን የሻብያ አጀንዳ እንዲሆን ካስደረጉ በኃላ ከእሳቸው በፊት የነበረው ትውልድ ባይቀበላቸውም የእሳቸውን ትውልድ ''የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው'' የሚለውን ገለፃ ለመንገር አላንገራገሩም። አቶ ኢሳያስ በአንድ ጎናቸው ተንቤን ትግራይ ቢወለዱም ያነሷት ጉዳይ ግን ኢትዮጵያን ለማዳከም ለዘመናት ከሚያልሙ አንዳንድ የአረብ ሀገራትም ሆነ ጎረቤት ሱዳንን የሚያማልል ብሎም ዳጎስ ያለ ድጎማ የሚያስገኝ የወቅቱ አዋጪ ''የገበያ ማስታወቅያ'' መሆኑን የተረዱት ይመስላሉ። ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ በነፃ ትምህርት ዕድል ይማሩ የነበሩት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ''የኤርትራ ነፃነት ግንባር'' (ELF) … [Read more...] about የኤርትራ ጉዳይ በሶስት ትውልዶች ውስጥ









