በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጭቆና፣ ስቃይ እና መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካደረጉት ምክንያቶች መካክል አንዱ፣ የወያኔ መንግስት ከምዕራባዊያን የሚያገኘው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ሙገሳ ትልቅ ቦታ ይይዛል። ከነዚህ መንግስታት የሚያገኘው ድጋፍ እና ሙገሳ ምክንያት የማን አለብኝነት ስሜት ስርዓቱ እንዲሰማውና የኢዴሞክራሲያዊ ስርዓት በህዝቡ ላይ እንዲንያሰራፉ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ስርዓቱም ከነችግሩ ለረዥም ጊዜ በስልጣን እንዲቆይ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የምዕራባዊያን ድጋፍ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። እነዚህ ሀገራት የራሳቸውን ብሄራዊ ጥቅም ብቻ ትኩረት በመስጠታቸው ላለፉት 25 ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ በጭቆና ውስጥ እንዲያሳልፍ አድረገውታል። የሀገሪቱ መልካምድር\ጅኦግራፍያዊ አቀማመጥ፣ የመንግስት ለምዕራባዊያን ፍላጎት አጎብዳጅነት እና … [Read more...] about አምባገነናዊውን ስርዓት አቅፈውና ደግፈው የያዙት ምዕራባዊ አገራት
Opinions
የሰላማዊ ሰልፍ መንፈስ መመለስ
በበርካታ ኢትዮጲያዊያን ትውስታ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ሲባል ወደ አእምሮአቸው የሚመጣው በምርጫ 97 ሰሞን የነበሩት ህዝባዊ የመብት ጥያቄዎች ናቸው። በወቅቱም ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው ከአሁን በውሃላ ማንም ሰው አደለም ተሰልፎ ሰብሰብ ብሎም መቆም አይችልም ብለው ማስጠንቀቂያ በመስጠት ህዝቡን በየእስር ቤቶ ካጎሩት በውሃላ መብትን በሰልፍ የመጠየቅ ነገር በዛ በይስሙላ ህገ መንግስት ላይ ብቻ ተወስኖ በሰልፍ መብትን የማስከበር መንፈስም በእጅጉ ተቀዛቅዞ ነበር። እንደውም በአንድ ወቅት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳን ከእስር መፈታት አስመልክቶ ለተጠራው ሰልፍ መንግስት ከሁለት መቶ ሃምሳ ሰው በላይ መሰለፍ አይፈቀድም የሚል ብዙዎችን በግርምት ያስደመመ ተሰምቶ የማያውቅ የሰላማዊ ሰልፍ ፍቃድ አሰጣጥ ሂደትንም አስተውለን ነበር። ምንም እንኳን በራሱ በወያኔ … [Read more...] about የሰላማዊ ሰልፍ መንፈስ መመለስ
ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት ይቻላልን?
ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት በቅድሚያ ሀገር ማለት ራሱ ምን ማለት ነው? እንዴትስ ትፈጠራለች? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይኖርብናል፡፡ ሀገር ማለት በአንድ ጥላ ስር የሚኖርባት ትልቅ ቤት ማለት ናት፣ ሀገር ማለት ጋርዮሽ ማለት ናት፣ ሀገር ማለት ከመንደር ከቀየ የገዘፈች የጋራ ጥቅም የፈጠሩ ሕዝቦች የራሳችን የግላችን የሚሉት የተከለለ ምድርና በውስጡ ያሉ ሁሉ ነገሮች ማለት ናት፡፡ ሀገር እንዴት ትፈጠራለች? ሀገር በሦስት መንገድ ትፈጠራለች የተለያየ ቋንቋ ባሕል ሃይማኖት ወዘተ ያላቸው ሕዝቦች በመልክአ ምድር አቀማመጥ በአየር ንብረት መመሳሰልና ተጽዕኖ ሊጋሩት በሚፈልጉት ወይም በሚገደዱት የተፈጥሮ ሀብት አጣማሪነት በስምምነት ትፈጠራለች፡፡ የጋራ ጥቅም ባላቸው ወይም በፈጠሩ አንድ ዓይነት ቋንቋ ባሕል ሃይማኖት ወዘተ ባለው ሕዝብ ያንን የጋራ ጥቅም ለራሳቸው ብቻ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት ይቻላልን?
Open Letter to Italian Minister of Foreign Affairs
Ufficio Relazioni con il Pubblico The Honorable Minister of Foreign Affairs, Federica Mogherini Ministero Affari Esteri Piazzale della Farnesina, 00135 Roma ITALY Your Excellency: The Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause presents its compliments to the Honorable Foreign Minister of Italy, Federica Mogherini. Our Alliance recalls, with deep appreciation, the long and historic relations between our two nations, Ethiopia and Italy, and wishes to draw Your Excellency’s kind … [Read more...] about Open Letter to Italian Minister of Foreign Affairs
ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ
ከ1500 በላይ በሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚተዳደር የሚታወቀው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት በዲፕሎማቱ ቁጥጠር ስር መዋሉን የሚገልጹ ምንጮች ማርች 28 2014 በኤምባሲው ደብዳቤ የስብሰባ ጥሪ ተላልፎላቸው የነበሩ ወላጆች ባለመገኝታቸው የስብሰባው አዳራሽ ባዶ ሁኖ መዋሉን አክለው ገልጸዋል። ንብረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደነበር የሚነገርለትን ት/ቤት ኤምባሲው ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥረት ከግል ጥቀም የመነጨ መሆኑንን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ት/ቤቱን ከኮሚኒቲው በመነጠል ከወላጆች በሚመረጥ የቦርድ አስተዳደር ይመራል በሚል ሽፋን ላለፉት 5 አመታት በት/ቤቱ ጥሬ ገዝንዘብ ላይ ግልጽ የሆነ ምዝበራ መፈጸሙን ይናገራሉ። ይህን አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ዲፕሎማቱ ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልበጠሱት ቀጠል … [Read more...] about ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ
አባ ፋኑኤል አዲስ ተክል ናቸው
“ወኢይኩን ተክለ ሐዲሰ ከመ ኢይትዐበይ ወኢይደቅ ውስተ ፍትሀ ዲያብሎስ። (፩ኛ ጢ ፫፡፮) የክርስቶስን ትህትና ጠልቆ ያልተረዳ ክርስቲያን በዲያብሎስ ትእቢት ይሸነፋልና በመንፈሳዊ አመራር ላይ አታስቀምጥ።” አዲስ ተክል ማለት አዲስ ገና ያልበሰለ አማኝ ማለት ነው። መግቢያ አባ ፋኑኤል ባዲስ ተክልነታቸው ነቢዩ ኢሳይያስ ስለ ጾም ከተናገረበት ምዕራፍ አንዲትን ሀረግ በጥሰው፤ በምእመናን እና በሶስት ቀሳውስት በቀድሞው ቄስ ታደሰ ሲሳይ ላይ የተላለፈውን ቃለ ውግዘት በቀላጤ ለማንሳት ባደረጉት ሙከራ “የከሳሾች ካህናት ጥላቻ ችግርና አለማመን ከዚህ ላይ ይጀምራል” በማለት የጻፉት ወረቀት ህዝቡን እንዳያደናብር ይህችን ጽሁፍ በማዘጃገት ላይ ሳለሁ፤ ይሄይስ አእምሮ የተባሉ ወገን “የሃይማኖት እርጅና አያድርስ” በሚል ርእስ March 9/ 20014 የጻፏትን መልእክት ሁለት ወዳጆቼ ላኩልኝ። … [Read more...] about አባ ፋኑኤል አዲስ ተክል ናቸው
ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር
መዝሙረ ኢህአዴግ! (በላይ ማናዬ) የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በተደረገላቸው ግብዣ ወደ አሜሪካ ያመራሉ፡፡ በጉዞው ዓላማና በተለያዩ የአገራችን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያና የዩክሬኑ ግጥምጥሞሽ * ባለ ቀለሙን አብዮት ማን ይመራዋል? (በጌታቸው ሺፈራው) አዲስ ጠብመንጃ በምንሽር፤ አገዳደሉ ሆድ የሚያሽር፡፡ (በዝክረ ታሪክ አምድ፡- አቶ ታዲዎስ ታንቱ) “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ” (ግርማ ሞገስ) ኑሮ ሆነብን እሮሮ (ጋሻው መርሻ) የኢትዮጵያ ፖለቲካና የሴቶች ተሳትፎ (ኤልሳቤት ወሰኔ) ሰላማዊ ትግሉ መሪዎቹን ይሻል (ታምራት ታረቀኝ) ኢትዮጵያዊነት ለእኔ! (አፈወርቅ … [Read more...] about ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር
Some policy considerations regarding the Ethiopian outmigration
In our December 19, 2013 article entitled “Explaining the Ethiopian outmigration: incentives or constrains” we alerted readers and policy makers in Ethiopia about the push, pull and mediating factors of outmigration in general and outlined the factors as they relate to Ethiopia. In this short article we aim to discuss further the incompatibility between macroeconomic growth and outmigration and close the piece by outlining potential mitigation strategies. By the end of 2013 and early 2014 the … [Read more...] about Some policy considerations regarding the Ethiopian outmigration
የእነ ሠዓሊ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን የቅስቀሳ ዘመቻ የታሪክ ነጠቃ ኣካል ነው፣
አንድ ነገር ለማለት ያነሳሰኝ ጉዳይ ይህ ግላሰብ ያለ ዕውቀቱና ምንም በማያገባው ነገር ውስጥ ገብቶ ሲያምስ ስላገኘሁት ነው። ይህም “የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን?” በሚለው ርዕስ ሥር የወሬ ወሬ ጽሁፍ ደራርቶ ራሱንና መሰሎቹን ለማስደሰት ስለ ፈጸመው ጉዳይ ትንሽ ለማለት ፈለግሁ። … [Read more...] about የእነ ሠዓሊ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን የቅስቀሳ ዘመቻ የታሪክ ነጠቃ ኣካል ነው፣
የጎሣ ግጭቶችና የአለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ሚና
የተባበሩት መንግሥታት በ1948 ዓ.ም. ባወጣው የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ መግለጫ አንቀጽ 2 ላይ እያንዳንዱ ሰው በዘር፣ በቀለም፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አስተያየት፣ በኅብረተሰብ ምንጭ፣ በሃብት፣ በትውልድ፣ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ምንም ዓይንነት ልዩነት ሳይደረግበት በመግለጫው ላይ በተጠቀሱት መብቶችና ነፃነቶች በእኩል የመጠቀም መብት እንዳለው የደነግጋል። ይህንን ድንጋጌም መነሻ በማድረግ ዘረኝነትንና ሌሎች ከሰብአዊ መብቶችና ነፃነቶች ጋር የሚቃረኑ የአድልዎ ተግባራትን ለማስቀረት በሚል በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ስምምነቶችና መግለዋዎች በተባበሩት መንግስታት አባል አገራት ጸድቀው ወጥተዋል። ከእነዚህም መካከል በተባበሩት መንግስታት ጸድቆ የወጣውና ከጃንዋሪ 04 ቀን 1969 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለው “ማንኛውንም ዓይነት የዘር አድልዎ ለማስወገድ … [Read more...] about የጎሣ ግጭቶችና የአለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ሚና








