ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢውን ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ ተቀምጦ እየዞረ ለአካባቢው ሰው ወተት መሸጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የግመሏ ወተት በአንድ ጊዜ ሀብታም ሊያደርገው አልቻለምና ሌላ ነገር አሰበ፡፡ በወተቱ ውስጥ ውኃ እየጨመረ ቀላቅሎ መሸጥ፡፡ ‹‹ሰውም ምነው የሰውየው አመሉም ወተቱም ተቀየረሳ›› እያለ ዝም ብሎ ይገዛ ጀመር፡፡ (ይገዛ የሚለው ቃል ጠብቆ እንዳይነበብ አሳስባለሁ) ሰውዬውም በግመል ወተቱ ላይ ውኃን እያበዛው፤ የግመሉም ቁጥር … [Read more...] about ግፍና ጎርፍ
Literature
የፍቅር ብልሃቱ
ልዩነትን አድንቅ አንድነትን አድምቅ እንቆቅልሽ ፍታ ጥላቻ ይረታ ሁሉም ብሔረሰብ ነውና ቤተሰብ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ማለት ተውክ አማራ ምንም እንኳን በአገር መንፈስህ ቢኮራ “እኔ ኦሮሞ ነኝ” ማለት ተውክ ኦሮሞ ምንም እንኳን ጥሪህ ሁሎ ቢያድር ከርሞ “ኢትዮጵያዊ አማራ” ሆነህ ስትሄድ “ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ” አገኘህ መንገድ የልብ ትርታ ሲወጣ ገሃድ ብለው ሲጠብቁ እሳትና ጭድ ፍቅር ጣልቃ ገብቶ አደረገ ጉድ የፍቅር ብልሃቱ ግርም ማሰኘቱ አንቺዬ ድንቅ አገር ኢትዮጵያ የሚሉሽ ትግሬና ሶማሌ ደቡብን የያዝሽ ጉራጌ ጋምቤላ አፋርን ያቀፍሽ ስንቱን ልጠራ ነው በዙ ልጆችሽ ነግሩ ሲጠራ እንዲሁም ሲጣራ እኩልነት ሰፍኖ ፍቅርም ልቆ ገኖ ኦሮሞ አማራ ማለቱ ይረሳና ኢትዮጵያዊ ነኝም ማለት ይቀርና ከአሁን ማንነትህ አድገህ … [Read more...] about የፍቅር ብልሃቱ
የእናት ለቅሶ
እናት በፍቅር፣ ጽንስ ይዛ፣ ዘጠኝ ወር አርግዛ፣ ራስዋን ምግብ አድርጋ፣ በማኅጸንዋ ሸሽጋ፣ ሽሉን ወደሰውነት አሳድጋ፣ የፈጣሪን ባሕርይ ተጋርታ፣ ሰው ሆና ሰው ፈጣሪ የሕይወት አለኝታ፣ በጻዕር አምጣ ወልዳ፣ አቅፋ በፍቅር አጥብታ፣ ተጨንቃ አሳድጋ፣ እንቅልፍ አጥታ፣ ሲስቅ ሲያስቃት፣ ሲያለቅስ ሲያስለቅሳት፣ ስትቆጣው እንዲያድግላት እንዲማርላት፣ ክቡር ሰው ሆኖ እንዲያኮራት፣ ያላትን ሁሉ ከፍላ መስዋእት፣ በጉጉት ስትጠብቅ -- ጨካኞች ሬሳውን ጣሉላት፡፡ ማኅጸንዋ ተኮማተረ፤ አንጀትዋ አረረ፤ አስፋልቱ ላይ የተንጣለለው ደም፣ ከልጅዋ አካል ጠብታም አልቀረም፤ ሙት አደረጋት በቁም፤ ከማኅጸንዋ እንደፈሰሰ ተሰማት፤ ተወልዶ ያደገ ልጅ አስወረዳት፤ በወጣት ልጅዋ የፈራረሰ አካል እስዋም ፈራረሰች ወየው ልጄ! ስትል፤ አካልዋ ተፍረከረከ፤ ጉልበትዋ … [Read more...] about የእናት ለቅሶ
ምነው! ፈጣሪ አምላክ!
አላለቅስም ያልኩት … እንባ የፈሪ ነው ብዬ ዋጥ ያ’ረኩት፣ አይቻል ተችሎኝ ይዤው የከረምኩት፣ ገንፍሎ ወጣና እንባዬ ፈሰሰ ጉንጮቼን ሰንጥቆ ፌቴን አዳረሰ በዛ እንባዬ መሀል አንገቴን አቅንቼ ለፈጣሪ ጮኽኩኝ! እጆቼን ዘርግቼ ምነው? ፈጣሪ አምላክ ምነው! ረሳኸን ምነው! ይሄን በደል አላይልን አልከን ምነው? የኛን ጩኸት ሰምተህ ጨከንክብን ብዬ ወተውትኩት አልኩበት እዬዬ አሁንም ይፈሳል አልቆመም እንባዬ ምነው! ፈጣሪ አምላክ! … … [Read more...] about ምነው! ፈጣሪ አምላክ!
እኔ አማልሰጣችሁ፣ እናንተ እማትወስዱት! …
ያለ ስም፣ ስም – ስጡኝ ቅጡኝ፣ አስቀጡኝ፤ አግዙኝ፣ ወርውሩኝ፣ … በማጎሪያችሁ እሰሩት… እጀን፣ … በካቴናችሁ ‘ጠንዙት’ እግሬን፣ …. በእግር ብረታችሁ ቸንክሩት፣ ገንዙት፣ … ይደንዝዝላችሁ ሽባ ሆኘ ልቅር፣ ‘’ልሰንከልላችሁ’’:: ……… እንካችሁ …. ጀርባዬን መጫሚያ፣ መዳፌን፤ ግረፉት፣ አቃጥሉት፣ …. በኮረንቲ ገመድ የሰራ አከላቴ፣ ይክሰል፣ ይሁን ዓመድ:: ……… ዝረፉት … ሀብቴን ቤትና ንብረቴን፣ በምድር ያለኝን፤ ሰብስቡ፣ አከማቹት፣ ለዓለም ይሁናችሁ ለማይጠረቃው፣ ለከርስ ዓላማችሁ ለማፍረስ፣ ለመናድ፣ ለጥፋት ግባችሁ:: ……… እንካችሁ…… ደረቴን እንካችሁ…… ግ’ባሬን፤ ለታንክ፣ ለመትረጊስ፣ ለጥይታችሁ አፍስሱት ደሜን፣……. እስኪከረፋችሁ አድቅቁት አጥንቴን፣……. እስኪወጋችሁ::……. እንካችሁ……… እንካችሁ ሥጋ – ሰውነቴን፣ … [Read more...] about እኔ አማልሰጣችሁ፣ እናንተ እማትወስዱት! …
ይድረስ — ለኃይለማርያም ደሳለኝ!
ለ’ክቡር’ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ለኢሕአዴግ ሊቀ-መንበር፣ ጠቅላይ ‘አዛዥ’ ለ"አግዓዚ" ጦር...፤ ይድረስ ለአቶ ኃይለማርያም! በስምዎ ባዘሏት ወላዲተ-አምላክ.. በወልድ በእየሱስ ክርስቶስ ስም ልያዝዎ፣ ኢትዮጵያን በጥይት አያቃጥሏት... እግዚአብሔር አባት ይቅር ይበልዎ! በደርግም ሆነ በወያኔ ዘመን ባገር ያሴሩ፣ እስከዛሬ ሕዝብን ሲያስጨፈጭፉ የኖሩ፣ “እግዚአብሔርን አናውቅም” ብለው የካዱ ነበሩ፤ እርስዎ ግን፣ ከቤተሰብዎ ጋር ማዕድ ሲጋሩ፣ የየዕለቱን ጸሎትዎን ሲያበስሩ፣ የአምላክን ስም ነጋ-መሸ እየጠሩ፣ ይመስለኝ ነበር በእምነት የከበሩ፤ ... ግና ከልብ እውነት ካልዘመሩ፣ ትዕዛዛዊ ቃላቱን ካልተገበሩ፣ እምኑ ላይ ነው ታዲያ አምልኮዎ? የአምላክን መሻት መፈጸምዎ? ከአረመኔዎች ጋር … [Read more...] about ይድረስ — ለኃይለማርያም ደሳለኝ!
እናት ሀገር!
“አንቺ እማማ ኢትዮጵያ አንቺ እናት ዓለም” ሎሬትሽ እያቆላመጠ ይነግርሽ እንደነበር በቀለም፤ እወቂበት ከእንግዲህ አብጂለት ፍቱን መላ፣ የሚሞትልሽ እንጂ የሚገልሽ ላይበላ፤ ህዋሳትሽ ይንቀሳቀስ ሰሜን-ደቡብ ምዕራብ-ምስራቅ፣ የአለላ ተምሳሌቱ የሕዝቦችሽ ህብረት ይድመቅ፤ ብድግ በይ ተራመጂ በእንፉቅቅ መዳኽሽ ያብቃ፣ የውብ ህይወት አዲስ ምዕራፍ በግዛትሽ ይገንባ! እናት አገር ባለታሪክ ተነሽ ቤትሽን አጽጂ፣ የተዝረከረከውን በፕሮፓጋንዳ ፈንጂ፣ በተከፈተው ጉድጓድ ይግባ ጠራርገሽ አስወግጂ። ዳግም እንዳትረቺም ባባይ-ጠንቋይ ጋጋታ፣ እጆችሽን ከምር ዘርጊ ወደ ፈጠረሽ ጌታ፣ አምላክሽ ካንቺው ነውና የእስላም የክርስቲያኑ፣ ፍጠኚ ታሪክ ይከወን ሳያልፍብሽ ዘመኑ። ‘ዳዊቶችሽ’ በጠጠር ‘ጎልያድን‘ ሲፋለሙ፣ የዝናሽን ውድ ዕሴት … [Read more...] about እናት ሀገር!
“እንዳትረግጡት…. የኢትዮጵያን ዐፈር – መሬት!”
‘ባካችሁ ......... ’ባካችሁ.......... እናንት በምድረ-ኢትዮጵያ ያላችሁ፤ "አትሂዱ …..በ'ግራችሁ..." ከቻላችሁ ..... "ብረሩ ክንፍአው’ታችሁ።” ግን……..አደራ……….. .......... አንዳትረገጡት ……. መሬቱን እንዳታዩት……… አፈሩን፤ ብታርሱት...... አትዘሩበት ብዘሩበት ........ አይበቅልበት፤........ ደምነውና - የትላንና- የዛሬ - የአሁን፣ ትኩስ…. የፈሰሰበት አጥንት ነውና ያልደረቀ፣ "አጸደ-ህይወት" የወደቀበት እናንተም ከእንግዲህ፣ ''ዐጽም - 'ርስቴ'' የማትሉት፤……….. ያውም … [Read more...] about “እንዳትረግጡት…. የኢትዮጵያን ዐፈር – መሬት!”
ጉ፣ የአቶ ዠ ልጅ ወይም “ጉማሬው” ዋናተኛ
አቶ ዠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ከተጫነባቸው በኋላ በUN ኢትዮጵያን ወክሎ የመቀመጥ ስልጣናቸው ቀረና ወደ ሌላ ሥልጣን ተሻገሩ። እድገት ወይም ውርደት (promotion ወይም demotion) ሳንል፣ ወደ ሌላ ሥልጣን ተሻገሩ እንላለን። አቶ ዠ የሃገሪቱ የዋና ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ። እንግዲህ “ፕሬዚደንት” የሚለው ቃል እስካለ ድረስ፣ ሹመቱ፣ ማዕረጉ ትልቅ ነው ተብሎ እንዲታሰብ የአቶ ዠ መልካም ፈቃድ ነው እንላለን። የዋና ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ሆነው የተሾሙበት ጊዜ ደግሞ እንዳጋጣሚ ሆኑ የኦሎምፒክ ውድድር የተቃረበበት ጊዜ ነበር። ዠ አዲሱ ቢሮአቸው ሆነው አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላቸው። ሃገራቸውን በኦሎምፒክ መወከል። የሃገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ በኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ ተገኝቶ ማውለብለብ...። እንዴት ያለ ድንቅ ሃሳብ ሲሉ አሰቡ አቶ ዠ። እንግዲህ መሰደብ፣ መዋረድ፣ መሰደድ፣ … [Read more...] about ጉ፣ የአቶ ዠ ልጅ ወይም “ጉማሬው” ዋናተኛ
“መዝሙሩማ…”!
“መዝሙሩማ” መዝሙር ነው - የኅብረ-ዜማ ውጤት፣ ሕዝብን ያስተሳሰረ - የአንድነት ሰንሰለት፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ - ከደቡብ እስከ ሰሜን... ተዳርሶ በድንገት፣ በቅብብሎሽ ያስተጋባ - የነጻነት አዝማች ልደት! ደራሲውም ሕዝብ ነው - መሳሪያውም ባህላዊ፣ ዘረኞችን እሚያሸማቅቅ፣ ግፈኞችን እሚያርበደብድ... ኃያል ድምፅ ምትሃታዊ! “መዝሙሩማ” መዝሙር ነው - የብሩህ ዘመን ብስራት፣ በደም ቀለም የተጻፈ! - እሚዘመር በሕዝብ አንደበት! (ስማ! አቶ “ጌታቸው”!) . . . ከእንግዲህማ አትልፋ - ዘመንህን በከንቱ አትጨርስ፣ ክፋት ፕሮፓጋንዳህን - እሳት ባገር ከመለኮስ፣ ይልቁንስ ጠጋ በል -“ሕዝበ-መዝሙሩን” በደንብ አጥና፣ ያንተም መፃዒ ዕድል - በሕዝብ ድል እንዲቃና! እንጂማ!... መዝሙሩማ ኀብረ-መዝሙር … [Read more...] about “መዝሙሩማ…”!










