ምን ማለት ነው እሱ ወዳጀ፤ ይሄ ሕገ ወጥ ስደተኛ ወዶ የሚሰደድ ከሌለ፤ ከሀገሩ የሚርቅ መከረኛ ነፍሱን ለማትረፍ የሻ ሰው፤ ይሸሻል እንጅ ባመራው እንግዳ አይደለ ወይ ጎብኚ፤ ፈቃድ ጠይቆ የሚገባው እስኪ ንገረኝ እባክህ፤ ለእናንተው መሐመድ ሰዎች ተቸግረው ለተሰደዱት፤ ከሀገራቸው ላለመሆን ሟች ቪዛ ተመቶላቸው ነበረ? ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ? አሳልፋቹህ ስጡን ብለው፤ በጠላት ለሰይፍ ሲታሰቡ ውሰዷቸው ተብለው ነበር? ወይስ ቤዛ ሆነ እርግቡ? ውጡልን ተብለውስ ነበር? ፊቱን ነስቷቸው ሕዝቡ? አንተ ግን ውለታ ቢሱ፤ አምላክ የማታውቅ የማትፈራ የነፍስ ብለው የተጠጉትን፤ ለማምለጥ ከአጋንንት ጭፍራ እያረድክ ፈነገልካቸው፤ ደፍረህ አርክሰህ በጠራራ ይሄ ነው ላንተ ጽድቅ ማለት፤ ደም ጠጥቶ መስከር ግፍ ሥራ ከሰይፍህ … [Read more...] about ሕገ ወጥ ስደተኛ (illegal immigrant)
Literature
ዕንባሽ ተናገረ!
ዘለላ ዘለላ ዱብ ዱብ በሚለው፤ ጉንጭሽን ሸርሽሮ ቁልቁል በሚፈሰው፤ ሳግ እንቅ እድርጎ በሚተናነቅሽ፤ በ’ንባሽ እያጠቀስኩ ስንኝ ቋጠርኩልሽ፤ ቃል ኪዳን ነውና አንብቢው አደራሽ:: (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ዕንባሽ ተናገረ!
የወገኔ ቅኔ
እንዲህ እንዲያ ብለው አሙን ፤ ተጠይቀው ሲመልሱ የወገኖቻችንን ደም ፤ በእብደት ግፍ ያፈሰሱ የኢትዮጵያ ስደተኞች ፤ ባሕላችንን ተቃረኑ ንጽሐችንን አረከሱ ፤ ነፍሳችንን አስኮነኑ መጠጥ በማዘዋወር ፤ በስርቆት ወንጀል በምኑ አንተ አረመኔ እንስሳ ፤ ምኑን ብየ ላውጣልህ ስም መጠጥ ምንህ ነውና ፤ ስካርህ የአንተ በሰው ደም አስገድዳ አልደፈረችህ ፤ ደፈርካት እንጅ በማደም መድፈርህ ሳያንስ ሳይበቃ ፤ አርደህ በላሃት ርጉም አንተ ውሉደ አጋንንት ፤ አረመኔ ዘረ ሰዶም ፡፡ ሌቦች ነበረ ያልካቸው ? እሰይ እንኳንም ሰረቁ ፈልገውት እንዳይመስልህ ፤ ምንም ነገር አይደል ድንቁ እባክህ ለከት ይኑርህ ፤ በዚህ አይታማም ወገኔ ነቢይህ ያውራህ ታሪኩን ፤ ያበሻን ማንነት ብያኔ የፍትሕ ደግነት ባለቤት ፤ ሕዝብ … [Read more...] about የወገኔ ቅኔ
እንደማያልፍ የለም
አዎ፤ የኔም እምባ ፈሷል እምነቴ ደፍርሷል ሰበዕናየ አንሷል ምክንያት ፍለጋ - መፍትሄ ፍለጋ ቀኑ እስከሚጨልም - ሌሊቱ እስቲነጋ ብቆርጥ ብቀጥል - ባነሳ ብጥለው ዘላለም ሆነብኝ - ማለቂያ የሌለው ሕመምሽ አሞኛል ድካምሽ ደክሞኛል እምባሽን ለመጥረግ - አቅም በማጣቴ ሕሊናየ ቆስሏል - ተቃጥሏል አንጀቴ እና….ጠንክሪ እህት ዓለም ይሄም ቀን ይረሳል - እንደማያልፍ የለም … [Read more...] about እንደማያልፍ የለም
ቀናችሁ አትርሳኝ!
ያልታየን አሟሟት- ባንተ አይቼ ሞትህን በቁሜ ሞቼ ሲገድሉህ የተሰበረ ቅስሜ እስካሁን አልጠገነም ህመሜ ሲገሉሽ ሞቼ ነው የከረምኩ ከስቃይሽ እኔም አልተረፍኩ ይህንን የናንተን አበሳ ልጽፈው ብዬ ብነሳ ሀዘን ዘልቆ ከገባ- አጥንት ድረስ ለካስ ቃላትም- የአንጀት አያደርስ እዬዬም ሲዳላ ነው ይባላል እንባም ስቃይ ሲከብደው- ለካስ ይደርቃል ደርቆ ይቅር- ድሮስ ምን ሊጠቅም እንባ ቃላትም በኖ ይጥፋ- ያሻው ቦታ ሄዶ ይግባ ሁለቱስ ምን አባታቸው ሊያደርጉልኝ ሞታችሁን ብረሳ ግን- ያቺ ቀናችሁ አትርሳኝ። ************** በሳውዲ ዐረቢያ አለምንም ጥፋታቸው ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ መታሰቢያ ይሁን … [Read more...] about ቀናችሁ አትርሳኝ!
የነፍስ ስደተኞች (the immigrants of survival)
ባገሩ የሚኮራ ፤ ሀገሩን አፍቃሪ ለወገን ሟች ስፍሱፍ ፤ አብሮነት ዘማሪ የነፍስ ስደተኛ ፤ እውነት አስመስካሪ የሀገሩ ነገር ፤ የወገኑ እጣ ሁሌ የሚያስጨንቀው ፤ ሲበዛ ግፍ ጣጣ ስለተገለለ ፤ አማራጭ ስላጣ እኛን ካልሆንክ ተብሎ ፤ ሕሊናው ተሸጣ ደሞ ስለተገፋ ፤ ታይቶ እንደ ባላንጣ አላፈናፍን ተብሎ ፤ ጅቡ እየተቆጣ አላቃምስ ተብሎ ፤ በራብ እየተቀጣ ወገን ሲለይበት ፤ ሆኖ ዘር መረጣ ቢብሰው ተነሣ ፤ ለስደት ጎረፈ ከሞት ጋር ተፋጦ ፤ ሞትን እያለፈ ግፍ እየተጋተ ፤ እየተቀሰፈ ገና ባልጸናለት ፤ በጨቅላ ትከሻ ስንት ስቃይ ዐየ ፤ የጣር መጨረሻ ወገኑን እያጣ ፤ የዓሣ ሲሳይ ሆኖ በአራዊት ተበልቶ ፤ በድንገት ታድኖ ስለተደፈረ ፤ እራሱን ኮንኖ በራብ በውኃ ጥም ፤ እየቀረ ደብኖ በኢሰብአዊ … [Read more...] about የነፍስ ስደተኞች (the immigrants of survival)
ሰቆቃወ ወገን!
ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ሰቆቃወ ወገን!
The Secret (ሚስጢሩ…)
ሚስጢሩ ወደኛ እየቀረበ ይሆን? የሚስጢሩን መጽሃፍ እያሳጠርኩ በመጻፍ ላይ እያለሁ ሚስጢሩን የሚአጠናክር ነገር ገጠመኝ። ከጓደኛዬ ጋር አልፈን አልፈን ውሃ የምንጎነጭባት ቤት አለች። እንደወትሮው በዛው ቤት ተገኝተናል። አንዲት ወጣት ስዊድናዊት ልታስተናግደን መጣች። ለጓደኛዬ የሞቀ ሰላምታ ሰጠችው። ስትስቅ ጉንጭና ጉንጮቿ ላይ የሚወጡት ጎድጓዳ ምልክቶች አይን ይስባሉ። ‹‹ባለፈው ጊዜ ስራ ለመቀጠር አስበሽ ያነጋገርኩሽ አይደለሽ?» አላት «አዎን! ተቀጠርኩ በጣም አመሰግናለሁ» «እኔ ምንም ያደረኩልሽ ነገር እኮ የለም» «አንተ ሄደሽ ባለቤቱን ተይቂው ባትለኝ አልጠይቀውም ነበር። ስለጠየኩት ተቀጠርኩ። በድጋሚ አመሰግናለሁ»። ፈገግታዋን ከጎድጓዳ ጉንጮቿ የሚረጭ ይመስላል። ተለየችን «ምንድነው ነገሩ? ስራ አስቀጣሪ ሆንክ እንዴ?» ጠየኩ ባለፈው ሰሞን እዚህ መጥቼ… ይቺ … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
ወገኔ በከንቱ
እዩት በየቦታው የሚታደገው አጥቶ እንዲያው ሲንከራተት ከሀገሩ ወጥቶ ወይ አላለፈለት ወይ እፎይ አላለ ሁሌ በባርነት እንዲሁ እንደቆዘመ ዘመናዊ ለማኝ አስጠጉኝ ባይ ሆነ መገፋቱ ሳያንስ መገደሉ ባሰ ። ባርነት ባአረብ አገር እስር በዐገር ቤት ስደት ካገር ውጭ ችግር በራስ አገር እርዛት አና እስር ሆኖል የብሶት መንደር ። ወገን አልባው ወገን ጠባቂ አልባው ግልገል መንጋው ተበተነ ዋይታው ለኛ ሆነ ገዳዩም ጠያቂ አጣ ስቃዩም ቀጠለ ። አቤት ፍርጃ ለዛውም ጠያቂ ያጣ ምን ይሆን ሚስጥሩ እንዲህ የመሆኑ? ማብቂያውስ መቸ ነው እንግልት ስደቱ አገር ሰላም ሆኖ ሰርቶ እሚኖርበት ሁሉም አንደቤቱ። መንግስት ምን አገባኝ ጆሮ ዳባ ልበስ ካለ ለህዝብ ለወገኑ ላገሩ ካልቆመ የወገን ደም እንደቀለም መንገድ ላይ ሲዘራ በባእዳን እጂ ወገን ሲሆን መቀለጃ ቆሞ … [Read more...] about ወገኔ በከንቱ
“ሁለቱም ባዶዎች ነበሩ!”
እ’ስራና ቅል ... አፈጣጠራቸው፣ ቢሆንም ለየቅል፤ እንደ አቅማቸው፣ ሠርተው በሀሳብ - ተግባር፣ ተግባብተው፤ ሰላም አግኝተው፣ አንድነት ይኖሩ ነበር፣ በአንድ ቤት። በፍቅራቸው፣ የሚቀናው ዱባ ግን፣ ጉረቤታቸው፤ ያሴር ነበር ሴራ፣ የሚያሥር ይሸርብ ነበር ነገር፣ የሚያደናግር፤ ያጠምድ ነበር፣ ወጥመድ ባረፉበት ቤት፣ ሳይቀር በመንገድ። እ’ሰራን ሲያገኘው፣ ብሎ ጎንበስ - ቀና የሰላምታ አይነት፣ ያዥጎደጉድና፤ በማር የተቀባ፣ የመርዝ ቃላት ይነግረው ነበረ፣ መስሎ ተቆርቅሪ፣ ለሱ ያዘነለት። ቅልንም ሲያገኘው ወይም ቤቱ ሄዶ ከአስረደው በኋላ፣ እንደሚፈልግው በፍቅሩ ተገዶ፤ ምክር ነው እያለ፣ ነገር ይነግረዋል በማያውቀው ጉዳይ፣ ደሙን ያፈለዋል። ከለ'ታት አንድ ቀን፣ ሥራ በፈቱበት በነገር ተይዘው፣ ''በተሰለቡበት''፤ እ’ስራ ተክዞ፣ … [Read more...] about “ሁለቱም ባዶዎች ነበሩ!”









