የህወሃትና የአሜሪካ ፍቅር ቀደም ሲል ይወራ እንደነበረው “በመካከላቸው ንፋስ ገባ” ከሚባልበት ደረጃ ባለፈ እየሰለለ መምጣቱን የሚጠቁሙ እውነታዎች እየታዩ ነው። ራሱ ህወሃት ይህንኑ ፍትጊያ የሚያጎሉ ጉዳዮች እያከናወነ ይገኛል። ለልዩነቱ መክረር ፍንጭ እየታየ ነው። ከኦባማ ዘመን ማብቃት ጋር ተያይዞ የቀድሞ ወዳጆቹ የነበሩት “ነጭ ወያኔዎች” ሥልጣን መልቀቅ እውን ሊሆን ሲቃረብ የተቀሩት "በዳግም ውልደት" እየከዱት ነው የሚል መረጃ ሲነገር ይደመጣል፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያወጣው መግለጫና ማሳሰቢያ ክብደቱ መጨመሩ፣ የአገሪቱ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለስልጣናትና ቁልፍ አማካሪዎች፣ እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሚዲያዎች ህወሃትን እያብጠለጠሉትና ክፉኛ እየነቀፉት ነው። ከውስጥ የሚወጡ መረጃዎች ደግሞ በውይይት ህወሃት “አደረጋለሁ” እያለ ማጨበርበሩ አሜሪካኖቹን … [Read more...] about “የነጭ ወያኔዎች” ሥልጣን መልቀቅና የተቀሩት “የዳግም ውልደት” ክህደት
በወልቃይት ጉዳይ የተሰጥ ምላሽ
አቻምየለህ ታምሩ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ አዳነች ፍሰሃዬ ወልቃይትን አስመልክቶ ላነሳችው አመክንዮዎች የሰጠው ምላሽ:- ይድረስ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኛ አዳነች ፍስሀዬ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬ ካለሽበት ቦታ ይድረስሽ። በዛሬው እለት (ህዳር 28, 2016) «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት» በሚል ርዕስ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ዶክተር ብርሀኑ መንግስቱን፣ ፕሮፌሰር አለማንተ ገብረሥላሴና ዶክተር ገላውዲዮስ አርአያን ጋብዘሽ ስለወልቃይት ያቀረብሽውን ዝግጅት በጥሞና ተከታትየዋለሁ። ይህንን ግልጽ አስተያየት እንድጽፍልሽ የገፋፋኝ ምክንያት አንቺ አዘጋጅና አቅራቢ ሆነሽ ባሰናዳሽው በዚህ «የምሁራኖች» የውይይት መድረክ ላይ ይዘሽ የቀረብሽው የግል አቋምና የተሳሳተ ግንዛቤ አመክንዮ የሌለው መሆኑን በመታዘቤ በጉዳዩ ላይ ጥናት እንዳደረገ ሰው ምናልባት … [Read more...] about በወልቃይት ጉዳይ የተሰጥ ምላሽ
የዶ/ር መረራ እስር፤ ህወሃትና ምዕራባውያን ፖለቲከኞች
ከአውሮጳ ስብሰባ ወደአገራቸው ሲመለሱ የታፈኑትና በኋላ መታሰራቸው የተሰማው ዶ/ር መረራ ጉዲና የአሜሪካና የአውሮጳ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ጉዳይ የከረረ አቋም እንዲወስዱ እያደረጋቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡ [ህወሃት] "ይበልጥ አምባገነናዊ ወደሆነ አስተዳደር እያመራ" ሲሉ አንድ የአሜሪካ ሴናተር ተችተዋል፡፡ መታሰራቸውን እንደሰሙ “I am very upset with this” ያሉት የአውሮጳ ፓርላማ አባል አና ጎሜዝ የዶ/ር መረራ እስር በጣም እንደሚያሳስባቸው በመግለጽ ለስቃይና እንግልት እንደሚዳረጉ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡ በመቀጠልም “በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ በጣም ጥብቅ የሆኑ አካሄዶች ከአውሮጳ ኅብረት በኩል ሊደረግ ይገባል” የሚል ማሳሰቢም ሰጥተዋል፡፡ (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)፡፡ በመቀጠል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ይህንን መግለጫ አወጣ፤ “የኦሮሞ … [Read more...] about የዶ/ር መረራ እስር፤ ህወሃትና ምዕራባውያን ፖለቲከኞች
የመረራ ምክር ለበረከትና ኢህአዴግ
ወያኔ ሊታደስም ሊታከምም የሚችል ኃይል አይደለም! መወገድ ያለበት እንጂ!
"በገሀነም ውስጥ እጅግ የሚያቃጥለው ቦታ የተያዘላቸው የሞራል ቀውስ በሚታይበት ወቅት ለህዝብ ወገናዊነትን ለማያሳዩ ሰዎች ነው።" Dante መግቢያ ሰሞኑን ወያኔ የሚያወናብደው ራሱን ለማደስ እንደተዘጋጀና ጊዜም እንደሚያስፈልገው ነው። በአገዛዙ ውስጥ የአስተደዳደር ብልሹነት አለ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ባህል ተስፋፍቷል፣ ሙስና ለቢሮክራሲው ማነቆ በመሆን ስራ አላሰራም በማለት የአገርን ዕድገት እየጎተተ እንደሆነ እየመላለሰ ይነግረናል። እነዚህንና ሌሎች የአስተዳደር ብልሹዎችን በየስብሰባውና በቴሌቪዢን „የውይይት መድረከ“ ላይ የሚያወሩልን የአገዛዙ የመሪ ቁንጮዎች በሽታዎቹ ከሰማይ እንደወረዱ እንጂ እነሱ ለአጋዛዛቸው እንዲያመቻቸው ሆን ብለው የፈጠሩትና ከተበላሸ ኢ-ሳይንሳዊና አገር አፍራሽ የአሰራር ዘዴ ጋር እንደተያያዘ አድርገው አይደለም የሚያቀርቡት። በሌላ አነጋገር፣ ለከፋፍለህ ግዛ … [Read more...] about ወያኔ ሊታደስም ሊታከምም የሚችል ኃይል አይደለም! መወገድ ያለበት እንጂ!
Ethiopia: End State of Emergency restrictions on political dissent and targeting of human rights defenders
The Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) is deeply concerned with the wide-ranging restrictions the state of emergency decree has enabled, which severely affect freedom of expression, freedom of assembly, association and peaceful protest in Ethiopia. Ethiopia’s close allies and partners in the international community unequivocally condemn the grave violations of human rights in Ethiopia and the misuse of the directive to silence political dissents, to threaten and systematically … [Read more...] about Ethiopia: End State of Emergency restrictions on political dissent and targeting of human rights defenders
The current alarming state of Ethiopia
Center for Rights of Ethiopia Women (CREW) is deeply concerned with the current state of affairs in Ethiopia. Since the government declared a state of emergency in October, thousands of men, women and particularly young people including journalists, opposition leaders and member were arrested by Ethiopian security forces. According to human rights organizations reports, the body that is authorized with the execution of the state of emergency has been conducting unlawful search of homes and … [Read more...] about The current alarming state of Ethiopia
ኮንሶ – የግፍ ምድር!
አንደኛዋ ባለቤታቸው ሶስት ጊዜ ቀዶ ጥገና አድርጋለች። ሌላኛዋ ባለቤታቸው ከአንድ ልጇ ጋር ሁሉም እስር ላይ ናቸው። እመጫትም ከእርጥብ ልጇ ጋር ታስራለች። እነዚህ ማሳያ እንጂ በኮንሶ ከእስር የተረፉ ተሰደዋል። በወረዳው ያሉት 43 ትምህርት ቤቶች እስር ቤቶችና የወታደሮች ካምፕ ሆነዋል። ወደ አጎራባች ቀበሌ ወይም ጫካ የመሸጉ ሰዎች ህይወታቸውን የሚገፉት በመከራ ነው። ይህ ሁሉ ምሬት ሲሰማ ክልሉ ምንም ነገር እንደሌለ ነው የሚናገረው - ኮንሶ ግን ፍጹም ግፍ የሚፈጸምባት ሆናለች! ህዳር 27 ቀን 2016 ቪኦኤ ያናገራቸው ሁለት የኮንሶ ነዋሪዎች “ኮንሶዎች የሚኖሩት በሌላዋ ኢትዮጵያ ነው” ይላሉ። በኮንሶ መተንፈስ አይቻልም። መቃወም አይፈቀድም። ጥያቄ ማቅረብ ክልክል ነው። የሚማርበትን ዩኒቨርሲቲና የራሱን ስም ለጥንቃቄ ሲል በመደበቅ አጭር ቃለ ምልልስ ያደረገው የኮንሶ ተወላጅ … [Read more...] about ኮንሶ – የግፍ ምድር!
ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?
ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ይህንን ጽፈዋል፣ ፊደል ካስትሮ፦ የኢትዮጵያና አፍሪካ የቁርጥ ቀን ወዳጅ፤ የክፍለዘመኑ ዳዊት የ፳ኛው ክ/ዘ ካፈራቸው ታላላቅ መሪወች ውስጥ ሁልጊዜም ፍትህና ነጻነት ከሚሹት ጋር በመቆም፤ ሁሌም በትክክለኛው የታሪክ ገጽ በመገኘት ፊደል ካስትሮን የሚስተካከል ማን አለ? ከኒካራጓና ቺሌ እስከ ቬትናም ከፍልስጤም እስከ አልጀሪያ ብሎም ደቡባዊ አፍሪካ ነጻነት ለናፈቃቸው ሁሉ የካስትሮን ያህል ታላቅ ድጋፍ ያደረገ ሌላ መሪ ማንም የለም። በተለይ የአፍሪካ አገራት ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ባደረጉት ትንቅንቅ የካስትሮና የኪውባ ቁርጠኝነት ከጉዳዩ ባለቤቶች ያልተለየ ነበር። ኪውባ ለአንጎላ ያደረገችው እጂግ መጠነሰፊና ከአስር አመት በላይ የዘለቀ ድጋፍ ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። ካስትሮ አንጎላ ከፖርቹጋል ቅኝ ነጻ ለመውጣት ካደረገችው ተጋድሎ ጀመሮ በአሜሪካ ድጋፍ … [Read more...] about ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?
ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል
የመድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ ረቡእ ማምሻውን በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ለማረጋገጥ ችለናል። በዛሬው እለት ፕ/ር መረራ ጉዲና መኖርያ ቤት በደህንነቶች እና ከባድ መሳርያ በታጠቁ የአጋዚ አባላት ተከብቦ መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ብእር ብቻ ለያዘ አንድ ሰላማዊ ሰው ይህን ሁሉ ሃይል ማሰማራት ስርዓቱ ምን ያህል እንደተብረከረከ የሚያሳይ መሆኑን እማኞቹ ጨምረው ገልጸዋል። በአውሮፓ ህብረት ጥሪ ተደርጎላቸው ሃገሪቱ ስላለችበት መስቀለኛ መንገድ ገለጻ አድርገዋል። ከዚያም በሆላንድ፣ በጀርመን እና በስዊዘርላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ስለ ሃገሪቱ ሁኔታ መወያየታቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ ችግር በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ያገኛል ብለው በምርጫ እና በሰላማዊ አግባብ ሲታገሉ የነበሩት ፕ/ር መረራ ጉዲና ለምን እንደታፈኑ … [Read more...] about ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል








