የጎጆዎቻንን ገመናስ እንሸፍንበት ገዶን አያውቅም፤ ድሮ በደህናው ጊዜ፣ ኑሮ ርካሽ በነበረበት ዘመን፣ ኑሮ ከሀገራችን እድገት ጋር እንዲህ አብሮ ሳያድግ፣ የጋገርነውን የዘንጋዳ ቅይጥ፣ ባሰጣነው ማኛ፣ እርቃናችንን በሰልባጅ እንሸፍነው ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን እንደየአቅማችን ገመናችንን እንሸፍንበት አልገደደንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መሶባችን ባዶ ሆኖ የሚበላ ቢጠፋ፣ ጦም መዋላችንን እንሸፍንበት የከራረመ ስቴኪኒ ከጥርሳችን አይጠፋም፡፡ እንደርበው ጃኬት ባይኖረን፣ ቆዳ በሚያሻክር ብርድ ሙቀቱን እናማርራለን፡፡ አቦ የራስን ገመና ይሸፍኑበት መች ይገዳል! ሀገሬ የገደደው ያንቺ ገመና ይሸፈንበት መንገድ ነው፡፡ ሁሉም የጎጆውን ገመና ለመሸፈን ደፋ ቀና ሲል፣ የአንቺ ገመና እንደአዳል በግ ላት ተገልብጦ አረፈው፡፡ ለነገሩማ፤ አዎ ያስተማርሻቸው ልጆች አሉሽ፤ ህገ-መንግስትም አቁመሻል፤ ህግ … [Read more...] about ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል አንድ)
ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሁለት)
በቀደም ሳት ብሎኝ፣ ለ መጀመሪያ ልጄ ብቻ የፈረንጅ ሸራ ጫማ ገዝቼ ገባሁ። ያለወትሮዬ ማለቴ ለወትሮው ገበያ የምወጣው ሁለቱንም ልጆቼን ይዤ ስለነበረ ነው። ታዲያ ያን እለታ ማታ ትልቅዋ ልጄ ጫማውን ስትለካ፣ የታናሽ እህትዋ አይን ከሚለካው ጫማ ጋር ሲንከራተት ተመለከትኩ፤ ወይም የተመለከትኩ መሰለኝ። ከወደድሽው ላንቺም ይገዛልሻል አልኳት፤ የትንሽዋን ልጄን አይን እየሸሸሁ። በውስጤ አድሏዊነት ተላወሰ። በልጅትዋ ህሊና ውስጥ ይህ ስሜት እንደማያድር ባውቅም፣ የእኔን ሃሳብ ግን ቶሎ ላስወግደው አልቻልኩም። አየሽ ሀገሬ? እንኳን ህዝበ አዳምና ሔዋንን በእኩልነት ቤት ሆኜ አኖራለሁ የሚል ሀገር፣ አንድ ተራ ምስኪን ወላጅ እንኳን በጎጆው አድሏዊነት እንዳይሰፍን ይጥራል። አንቺ ግን ሀገሬ! … አንቺ ግን ዝሆንና ጥንቸል እያፋለምሽ ለአሸናፊው ታጨበጭቢያለሽ፤ ትሸልሚያለሽ። መቼም ማንም … [Read more...] about ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሁለት)
ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሶስት)
ሀገሬ አንዳንዴ ከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ከምስራቅ ወደ ምእራብ የዘረጋሻቸውን ጎዳናዎች፣ ልታነጥፊያቸው ደፋ ቀና የምትይላቸውን ሀዲዶች ስመለከት ደስ ይለኛል። የአዲስ አበባን አስፋልትና በየአስፋልቱ ዳር ያቆምሻቸውን ህንፃዎች አዲስነት ስመለከት ደግሞ፣ ‹‹ቆይ ሀገሬ፣ መንገድም፣ ህንፃም አልነበራትም እንዴ?›› ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። እውነቴን ነው የምልሽ ሀገሬ ግንባታሽን ለተመለከተ ፈርሶ የሚሰራ ሀገር ነው እኮ የምትመስይው! ግን እኔ ልማትሽን፣ እድገትሽን፣ ትራንስፎርሜሽንሽን . . . አልነግርሽም! እንደነገርኩሽ ጉዳዬ ከገመናሽ ነው። ለልማት ለትራንስፎርሜሽንማ ራዲዮና ቲቪሽ መች አነሰሽ! ዋናው ራዲዮና ቲቪ አልበቃ ብሎ ኤፍ.ኤም፣ ኢቲቪ1፣ ኢቲቪ 2 . . . ልማትና እድገትሽ ራስምታትሽ እስኪሆን ይነግርሽ የለ! ነጋሪ ያጣው እኮ ገመናሽ ነው! እና እኔ ልጅሽ ልንገርሽ! በትልልቅ … [Read more...] about ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሶስት)
ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?
የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት … [Read more...] about ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?
“አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት የባንዳ ልጆች ናቸው”
“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች የነበሩ” አቶ ታዲዎስ ታንቱ በአፋር ክልል ሰዎች በርሃብ እየሞቱ ነው የተመስገን ደሳለኝ ብዕር እየዶለዶመ ይሆን? መንግስት ህገወጥ የእስር ዘመቻውን ቀጠለ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በፌደራል ፖሊስ ከግቢ እናስባርራችኋለን ተብለናል አሉ ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው? (ሙሉው ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about “አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት የባንዳ ልጆች ናቸው”
“እግዚአብሔር የቀባው”
አቡነ ማትያስ ባሜሪካ ራዲዮ አማካይነት የኢትዮጵያ ህዝበ ክርስቲያን በ፭፻ ድምጽ መርጦ ፓትርያርኩ አደረገኝ ማለት ጀምረዋል። እውነት እንደሚሉት ባገር ውስጥና በውጭ ካሉት ሁሉ ሰዎች በሙያቸው፥ በቅድስናቸው፥ በምንኩስናቸውና ባገልግሎታቸው ከሳቸው የተሻለ ሰው ጠፍቶ እሳቸው ልቀው ተገኝተው የኢትዮጵያ ህዝበ ክርስቲያን ትምህርታቸውን፥ በረከታቸውንና ቅድስናቸውን ፈልጎ በ፭፻ ድምጹ መረጣቸው? (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) (Photo: OCP News Service) … [Read more...] about “እግዚአብሔር የቀባው”
አባባሱባት!
ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌ ጥቃት እንደተሰነዘረባት ነው። ክፉ ክፉው መዘዝ የሚመዘዝባት፣ ሁዳዴ ጾም አካባቢ ነው። በዙ አሳልፋለች። ይንከባከቧታል ተብለው ታምነው የነበሩ ትላልቅ አባቶች እየመዘበሯት ስላስቸገሩ፣ መነኲሴ አንዴ ሙቶ ተገንዟልና አደራ አይበላም ለገንዘብና ለሥልጣን አይጓጓም ተብለን ለመነኲሴ ነኝ ባዩ ግለሰብ ቢያስረክቧት፣ እንኳን ሊሻላት እንዲያውም አባባሱና፣ አረፉ። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about አባባሱባት!
ሃይማኖት፣ ፖለቲካና ህብረተሰብ!
የዐለማችን ሁኔታ በጣም እየተወሳሰበ መጥቷል። በየአገሮች ውስጥ የማህበራዊና የፖለቲካ ጥያቄዎች ሳይፈቱ የሃይማኖት ጥያቄ ራሱን የቻለ አጀንዳ ሆኖ በመምጣት ብዙ አገሮችን እያተራመሰ ነው። በተለይም የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮች ውስጥ ያለው የፖለቲካ አወቃቀር ምሁራዊ ብስለት ስለሚጎድለው፣ አፍጠው አግጠው የሚመጡ እንደ ሃይማኖት የመሳሰሉ ጥያቄዎችን በውውይትና በክርክር ከመፍታት ይልቅ ግብግቡ ወደ አመጽ በማምራት አክራሪዎች በሚባሉትና በመንግስታት መሀከል የሚደረግ ዐይነት ፍጥጫ እየሆነ በመምጣት ላይ ነው። መንግስታት ወደ ዕምነት ያመራውን የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል በጭፍኑ በአክራሪነት በመወንጀል በተለኮሰው እሳት ላይ ቤንዚን እየነሰነሱበት ነው። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about ሃይማኖት፣ ፖለቲካና ህብረተሰብ!
የትናንቷን እሁድ በወፍ በረር ስንቃኛት
ዛሬ እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2005ዓ.ም ነው፡፡ የዚህችን ዕለት ውሎየን ነው እንግዲህ የማካፍላችሁ፡፡ እኔም እንዳቅሜ የቤተሰቤን ፍላጎት አፍኜ አልጀዚራን ብቻ በመክፈት በማየው ነገር ሁላ በንዴት ስፎገላ ነው የትም ሳልሄድ ቤቴ ተከርችሜ የዋልኩ፡፡ እርግጥ ነው ከሰዓት በኋላ የኢትዮጵያንና የቦትስዋናን የዓለም እግር ኳስ አፍሪካዊ የማጣሪያ ጨዋታ ተከታትያለሁ - ሀገሬ አንድ ለዜሮ በማቸነ‹ፏ›ም ተደስቻለሁ፡፡ የተቀረውን ግን አታንሱት - እኔ ግን ላነሳው ነኝ፡፡ (አይ የኛ ሀገር ነገር! በ‹ቸ›ና በ‹ሸ› አጠቃቀም ሳይቀር እንናቆር ነበር እኮ! ምን ቢዞርብን ይሆን!) በነገራችን ላይ ዘመነ ምፅዓት አሁን ካልሆነ መቼም አይሆንም፡፡ ይህ ድምዳሜየ በዛሬው ውሎዬ ብቻ የተደረሰበት እንዳይመስላችሁ - ዛሬ አጠናከረልኝ እንጂ የቆዬ ነው፡፡ በዚያ ላይ በለሲቱ … [Read more...] about የትናንቷን እሁድ በወፍ በረር ስንቃኛት
ነጋሶ ሞገቱ ወይስ ተሞገቱ?
“ ... አንተም ሆንክ ማንም ኢትዮጵያዊ ውጪ ያሉትን ጨምሮ ቢደግፉን ደስ ይለናል። በዚህ መንገድ ሂዱ ብለው እንዲጠመዝዙን ግን አንፈልግም። … ሰላማዊ ትግል የምትሉት ለውጥ አያመጣም ይሉናል። እንደዚህ የምትሉ ከሆነ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አትርዱን እንላቸዋለን … ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና አንሰጠውም" ከዶ/ር ነጋሶ የተመረጡ መልሶች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዶ/ር ነጋሶ ሊሞገቱ ሄደው ሞገቱ የሚል ርዕስ ለጽሁፌ መረጥኩ። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አንድነትን በመወከል ሬዲዮ ፋና በሚያዘጋጀው የ"ሞጋች" ቃለ ምልልስ ክፍለ ጊዜ ላይ ተገኝተው ነበር። ቃለ ምልልሱ ከመጀመሩ በፊት "ጋዜጠኛው" ፕሮግራሙ ፈረንጆቹ እንደሚሉት "ሃርድ ቶክ አይነት ነው" አለ። ይህን ጊዜ ቀልቤን ሳበኝ። የቢቢሲው የሃርድ ቶክ ክፍለጊዜና የጠያቂው ጠልቆ የመግባት ችሎታ ታየኝና ዶ/ር … [Read more...] about ነጋሶ ሞገቱ ወይስ ተሞገቱ?







