መንግስት በምእራብ አርሲ ዞን የተገደሉትን ሙስሊሞች ቁጥር መቀነሱን የአካባቢው ሰዎች ገለጹ በምእራብ አርሲ ዞን በኮፈሌና አካባቢዋ የፌደራል ፖሊሶች በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በወሰዱት እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸውና 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የኦሮምያን ፖሊስ በመጥቀስ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ቢዘግቡም የኢሳት ምንጮች በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር ከ18 እስከ 25 ይደርሳል ይላሉ። በአካባቢው የሚገኝ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የሟቾችን ቁጥር 18 መሆኑን ሲገልጽ፣ ወደ ኮፈሌ እና ዋቢ ከተሞች ለመግባት ሙከራ አድርጎ በፖሊሶች ፍተሻ ተንገላቶ ሳይሳካለት የቀረው ዘጋቢያችን ከከተሞች ሲወጡ ያገኛቸውን ሰዎች አነጋግሮ እንዘገበው የሟቾች ቁጥር ከ15 እስከ 20 ሊደርስ እንደሚችል ገልጿል። መንግስት ሙስሊሞቹ የጦር መሳሪያዎችን እንደያዙ አድርጎ ያቀረበው ዘገባ ትክክል አለመሆኑና … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እና የመቀሌያችን መታፈን ከነመፍትሄው!
የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ወደፊት በመገስገስ ላይ ይገኛል። አንድነቶች የኢትዮጵያን ጸረ-ሽብር ህግ ለማሰረዝ የዜጎች ፊርማ በማሰባሰብ ዘመቻ ላይ ናቸው። የቀድሞውን የግብጽ ፕሬዘዳንት ሞርሲን ከስልጣን የማውረድ እንቅስቃሴ ያስጀመረው ከአስራ አምስት ሚሊዮን በላይ የሚገመተው የግብጾች ፊርማ ከተለያዩ ከተሞች የተሰበሰበው በሶስት ወሮች ነበር። በግብጾች አይን ሲታይ አንድነቶች በሶስት ወሮች አንድ ሚሊዮን ፊርማ ማሰባሰብ አይችሉም ብለን መገመት ያዳግተናል። እርግጥ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ ትግል ባህል እና ክህሎት እንደ ግብጾች ብዙ አልዘለቅንም። ይሁን እንጂ ካሰብነው ቁጥር እንደምንደርስ ጥርጥር የለኝም። የአንድነት መሪዎች መታሰር ቢደርስባቸውም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት የመጀመሪያው ዘመቻ በጎንደር እና በደሴ ከተሞች ሐምሌ 7 ቀን በስኬት ተፈጽሟል። በጎንደር እና በደሴ ከተሞች … [Read more...] about የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እና የመቀሌያችን መታፈን ከነመፍትሄው!
በግብረሰዶም ተጠርጣሪዎች ላይ የሳይኮሎጂና የሳይካትሪ ባለሙያ የምስክርነት ቃል ሰጡ
ሁለት የ10 እና የ11 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የአራተኛና የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የግብረሰዶም ጥቃት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት የካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ ስድስት መምህራን ክስ ላይ፣ ከዓቃቤ ሕግ ምስክሮች በተጨማሪ አንዲት የሳይኮሎጂና የሳይካትሪ ባለሙያ ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የሙያ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የመሠረተውን የወንጀል ክስ በማየት ላይ ያለው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሰባተኛ የወንጀል ችሎት፣ ስማቸው በሚዲያ እንዳይገለጽ የከለከለላቸው የሳይኮሎጂስትና የሳይካትሪ ባለሙያዋ፣ በተጠርጣሪ መምህራን የግብረሰዶም ጥቃት ደርሶባቸዋል የተባሉትን ሁለት ወንድ ሕፃናት፣ ለሦስት ጊዜያት አግኝተው እንዳነጋገሯቸው ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹንም ሆኑ የጥቃቱ ሰለባ ናቸው የተባሉት … [Read more...] about በግብረሰዶም ተጠርጣሪዎች ላይ የሳይኮሎጂና የሳይካትሪ ባለሙያ የምስክርነት ቃል ሰጡ
የሚፈራው መጣ!!
ኢትዮጵያችን ታማለች። ኢትዮጵያችን ተወጣጥራለች። ኢትዮጵያችን በአደገኛ መርዝ ተበክላለች። ኢትዮጵያችን ውስጧ ነፍሯል። ኢትዮጵያችን እየቃተተች ነው። ቆዳዋ ሳስቷል። የሚሰማትና የሚደርስላት ስላጣች የያዘችውን ይዛ ልትነጉድ ከጫፍ ላይ ነች። እናም ቅድሚያ ለመቀመጫ፤ ቅድሚያ ለእምዬ ኢትዮጵያ!! ማጣፊያው ሳያጥር ሁሉም መንገዱን ይመርምር!! ኢትዮጵያ በጭንቀት ጣር ውስጥ ስለመገኘቷ ማብራሪያ የሚጠይቁ ዜጎች ያሉ አይመስለንም። ምናልባት ሳያውቁ እየተፈረደባቸው ያሉ ህጻናት ካልሆኑ በስተቀር፤ ችግር ፈጣሪውም፣ የችግሩ ሁሉ ሰላባ የሆነው ህዝብ፤ ሁሉም ከበቂ በላይ መረጃ አላቸው። ኢትዮጵያ ህመሟ ወደ "ሚድን ካንሰርነት" መቀየር የሚችል ስለመሆኑ ዜጎች ያለ "ሰበር ዜና" ይረዱታል። የሚድን ስንል በቀላል አገላለጽ ችግር ፈጣሪው ኢህአዴግ፣ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት፣ የህወሃት አገልጋዮች፣ … [Read more...] about የሚፈራው መጣ!!
Open letter to OPDO, ANDM, SEPDF, SOMALI, GAMBELA, B.GUMUZ and AFAR
Most decisive points why OPDO, ANDM and SEPDF political party, Other EPRDF affiliate Somali Gambela, Harari , Afar and Bensishangiul Gumuz political party members stand against TPLF and support Ethiopian people struggle for freedom and democracy . 1. You have a conscience to judge your status quo in EPRDF versus TPLF overall dominance 2. You have a conscience to measure your political power in the region you are ”lading” versus any junior TPLF member 3. You have a conscience to … [Read more...] about Open letter to OPDO, ANDM, SEPDF, SOMALI, GAMBELA, B.GUMUZ and AFAR
በኮፈሌ የሟቾችና ቁስለኞች ቁጥር ግልጽ አልሆነም
ባለፈው ዓርብ በመላው አገሪቱ አንድ ወጥ የ"ድምጻችን ይሰማ" የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት የወጣውን መርሃ ግብር ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ እስከ ግድያ ሊደርስ የሚችል ርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የሚያመላክት መግለጫ አውጥቶ ነበር። የድምጻችን ይሰማ አመራር መሆናቸውን የሚገልጹት ክፍሎች ፌደራል ፖሊስ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ተቃውሞው እንዲቀር መመሪያ ማስተላለፋቸውን ይናገራሉ። በዋቤ መስጊድ ቦንብ ያፈነዳው ማን ነው? ለምን እንዲፈነዳ ተደረገ? ፖሊስ በከረሩ ቃላቶችና በማስጠንቀቂያ አጅቦ ባወጣው መግለጫ " … አክራሪ ወሃቢ ሰለፊዎች ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረጉ ፖሊስ ለሚወስደው ርምጃ ተገቢውንና የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን" በማለት አስፈራርቶ ነበር። "ምንደኛ፣ ከውጪ በሚላክላቸው ንዋይ ዓይናቸው ታውሮ አርብ በመጣ ቁጥር በተመረጡ መስጊዶች … [Read more...] about በኮፈሌ የሟቾችና ቁስለኞች ቁጥር ግልጽ አልሆነም
የግሎባላይዜሽን ውጤቱ
መግቢያ በዘጠናዎቹ ዐመታት ግሎባላይዜሽን የሚባለው ጽንሰ-ሀሳብ በዜና ማሰራጫዎች ሲወራ፣ ለዓለም ማህበረ-ሰብ ጠቃሚነቱን ለማስረዳት የምዕራብ አገር ኤክስፐርቶች ወዲህና ወዲያ ውርውር ሲሉና የሶስተኛው ዓለም አገሮችም ሊካተቱ የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ጥድፊያ ሲደረግ፣ በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ አዲስ የቀን ብርሀንን የሚያይ መስሎት በጉጉት ይጠባበቅ ገባ። ከእንግዲህ ወዲያ ዓለም ወደ „መንደርነት“ እየተለወጠች ነው፤ እዚያ ውስጥ ገብቶ መወዳደርና ብቁነትንም ማሳየት ነው፤ በየቦታው የሚመረተውን ምርት ብቻ ሳይሆን ይህንንም ያሚያሽከረክረውን የፊናንስ ካፒታል ተካፋይ መሆንና በደስታ ዓለም ውስጥ እየተዝናኑ መኖር ነው የሚለው ብዙዎችን ወደ ማሳመን እንደገባ የማይታበል ሀቅ ነው። በመሆኑም ግሎባላይዜሽን አማራጭ የሌለው ነው፤ ይህንን ሀቅ አለመቀበልና በርን መዝጋት ለብዙ መቶ … [Read more...] about የግሎባላይዜሽን ውጤቱ
ግመል ሰርቆ ማጎንበስ አይቻልም
የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ ድረገጽ መረጃ እንደሚለው ከሆነ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገራት መካከል የአሜሪካንን ዕርዳታ በመቀበል ቀዳሚነቱን ሥፍራ የያዘችው ኢትዮጵያ ነች፡፡ (http://www.foreignassistance.gov/) የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ወይም በጀት ከተደረገው ውጪ የሚሰጠውን ተጨማሪ ዕርዳታና ድጎማ ሳይጨምር ከ2009 - እስከ 2012 ባሉት ዓመታት ብቻ ኢትዮጵያ ከ3.3ቢሊዮን ዶላር በላይ (በወቅቱ ምንዛሪ ከ60ቢሊዮን ብር በላይ) ዕርዳታ ተቀብላለች፡፡ ገንዘቡ የሚሠጠው ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ፤ ለዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብቶችና መልካም አስተዳደር፤ ለጤና፤ ለትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች፤ ለኢኮኖሚ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ እንደሆነ ድረገጹ ያስረዳል፡፡ (በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተቀናበረ - AP Photo/Steve Parsons/pool) … [Read more...] about ግመል ሰርቆ ማጎንበስ አይቻልም
እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው
አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ። በሰኔ (ጁን) ወር "… የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ክሪስ ስሚዝ አዲስ አበባ መምጣት ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሏል። "ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ" በሚል አጀንዳ ተዘጋጅቶ የነበረውን የምክክር ስብሰባ የመሩት የአሜሪካን ምክር ቤት እንደራሴ /ኮንግረንስማን/ ክሪስ ስሚዝና ሌላዋ ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ ኢህአዴግ እስር ቤቶችን እንዲያሳይ፣ … [Read more...] about እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው
ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ!
የየሱስ ክርስቶስ ክስ፣ ፍርድና ሞት ተገቢው የሕግ አሠራር የተከተለ አይደለም፤ ጉዳዩም እንደገና መታየት አለበት በማለት ኬኒያዊው ጠበቃ ዶላ ኢንዲዲስ ሔግ ለሚገኘው ዓለምአቀፉ ፍርድቤት ክስ ማሰማቱን ጀሩሳሌም ፖስት ኬኒያ የሚታተመውን ናይሮቢያን ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የቀድሞ የኬኒያ ፍርድቤት አፈቀላጤ የነበረው ይኸው ጠበቃ በወቅቱ የሮም ቄሣር የነበረውን ጢባሪዮስ ቄሣር፣ ጲላጦስን፣ የአይሁድ መሪዎችን፣ ንጉሥ ሔሮድስን፣ የአሁኑን የጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል፡፡ “ማስረጃው በመጽሐፍቅዱስ ላይ ይገኛል፤ ይህንን ደግሞ ማንም ሊክድ አይችልም” የሚለው ጠበቃ የሱስ በወቅቱ ተገቢውን ፍርድ እንዳላገኘ ጉዳዩም በትክክል በፍርድ ሒደት ውስጥ እንዳላላፈ ጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ ሁለት ሺህ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁን ያሉት የጣሊያንና የእስራኤል መንግሥታት በዚያን ጊዜ (በስቅለት) … [Read more...] about ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ!










