* “ባለውለታችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ አዝኖባችኋል፣ አርቃችሁ እዩ” “በትግሉ ወቅት ለነጻነት ስትዋደቁ ኢትዮጵያ በጋምቤላ አኙዋክ ምድር ላይ ሙሉ ከለላና ዋስትና በመስጠት ያበረከተችው አስተዋጽኦ የሚረሳ ነው? ከነጻነት ታጋዮችችሁ ጎን በመሰለፍ ብረት ያነሱ የአኙዋክ ኢትዮጵያውያን ልጆች መስዋዕትነት ይዘነጋችኋል? አሁን ድረስ የትግሉ የመስዋዕትነት ቁስላቸው ያልዳነ የአኙዋክ ልጆች እንዳሉ ትዘነጋላችሁ?" በማለት የተናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ ናቸው። በታላላቅ መድረኮችና በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተሰሚነታቸውና ስብዕናቸው እየጎላ የሄደው ጥቁሩ ሰው ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ ከላይ የተገለጸውን ህሊና የሚፈታተን ጥያቄ ያቀረቡት ለደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባርናባ ማሪያል ቤንጃሚን ነው። ለረዥም … [Read more...] about ኦባንግ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር ተነጋገሩ
በደቡብ ሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ
በደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን መንግሥት ለመገልበጥ እሁድ ማታ ለሰኞ አጥቢያ ሙከራ ተደርጎ መክሸፉ ተሰማ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሙከራው መክሸፉንና መንግሥት ሁሉንም ነገር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን በመግለጽ ለደቡብ ሱዳን ሕዝብ መግለጫ ሰጡ፡፡ በዋንኛው ጎሣ ዲንቃ እና ኑዌር ጎሣ መካከል የተከሰተው ፍጥጫ እስካሁን የለየለት መስመር አልያዘም፡፡ ከወራቶች በፊት የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ንቅናቄ (ኤስ.ፒ.ኤል.ኤም.) ዋና ጸሐፊ የሆኑት ፓጋን አሙን የአመራር ብክነትና ሌሎች ችግሮች አሉባቸው በሚል እንዲገመገሙ ፕሬዚዳንቱ የመርማሪ ኮሚሽን አቋቁመው ነበር፡፡ ኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊው የአመራር ጉድለት የታየባቸው በመሆኑ ከሥልጣን እንዲነሱ የውሳኔ ሐሳብ ሰጥቷል በሚል ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ዋና ጸሐፊውን ጨምሮ የአገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሬይክ ማቻር ከሥልጣናቸው ባለፈው ሐምሌ ወር … [Read more...] about በደቡብ ሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ
አይ አበሻ! አበሻና ልመና፦ አንድ
በዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር አበሻ አንደኛ ከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለአበሻ፣ ልመና የኑሮ ዘዴ ነው፤ እንዲያውም ከልመና ውጭ የሆነ ኢትዮጵያዊ ኑሮ የለም ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ ስለዚህም ልመና ባህላዊ ጥበብ ሆኖአል፤ አንዳንድ አላዋቂዎች፣ አንዳንድ አዋቂዎችም አንዳንዴ እየተሳሳቱ ልመናን እንደነውር ይገልጹታል፤ ልመና ነውር አይደለም፤ ለጨዋ ልጆችማ አንዳንድ አጥንትን የሚያበላሽ ሥራ ከመሥራት ለምኖ መብላት ክብር ነው፤ ይህ ባህላዊ ጥበብ ያልገባቸው የድሬ ዳዋ ለማኞች ብቻ ናቸው፤ እጃቸውን እየዘረጉ ‹‹እስቲ አሥር ብር ስጠኝ!›› ይላሉ! በጫት ሞቅ ሲላቸው መቶ ብር ይጠይቃሉ፤ የድሬ ዳዋ ልመና መሆኑ ነው! የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቄሶቹ ምንም ይስበኩ በተግባር እንደሚታየው ጽድቅ የሚገኘው በልመና ነው እንጂ … [Read more...] about አይ አበሻ! አበሻና ልመና፦ አንድ
ጉቦ በመቀበል እስረኞችን የለቀቁ ታሰሩ!
ከ300 እስከ 500 ሺህ ብር እየተቀበሉ በሀሰተኛ ሰነድ ታራሚዎችን ከማረሚያ እንዲወጡ አስደርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የስራ ሀላፊዎችና አምስት ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ ኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ፣ ረዳት ኦፊሰር ኢሳያስ ከበደና ዋርደር ኢብራሂም መሀመድ ሲሆኑ፥ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የእስረኞች አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ናቸው። ከእነዚህ የስራ ሃላፊዎች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የተቀሩት ግለሰቦች ደግሞ ፥ በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረው አቶ ሰለሞን ገለታ፣ አቶ ብሩክ ሀይሌ፣ ወይዘሪት ሳባ ገብረሚካኤል፣ አቶ ናታን ዘላለምና አቶ ቴዎድሮስ ግደይ ናቸው። የፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት … [Read more...] about ጉቦ በመቀበል እስረኞችን የለቀቁ ታሰሩ!
ኢህአዴግ ከብሔር “ተኮር” ተቃዋሚዎች ጋር ሊሸማገል ነው
ኢህአዴግ በብሔርና በክልል ደረጃ ከተደራጁ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚንቀሳቀሱት ቅድሚያ በመስጠት ለመደራደር የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ በማመቻቸት ላይ መሆኑን የጎልጉል ምንጮች ገለጹ። ምንጮቹ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ለዚህ ተግባሩ ወዳጅ ጎረቤት አገሮችን፣ አንጋፋ የጎሳ መሪዎችንና ያፈገፈጉ የቀድሞ ተቃዋሚ መሪዎችን እየተጠቀመ ነው። ህወሃት አሁን በአገሪቱ ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ የሄደው አለመረጋጋት እንዳሳሰበው የጠቆሙት የኢህአዴግ ሰው ድርጅቱ እርቅ ላይ ከመቼውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ስትራቴጂ መንደፉን አመልክተዋል። "ከውጥረት ለመውጣት ወይም ውጥረትን ለመቀነስ" በሚል ኢህአዴግ ትኩረት ሰጥቶ የጀመረው አዲሱ የ"ሰላም" መንገድ ህብረ ብሔር ድርጅቶችን ያላከተተበትን ምክንያት አልተብራራም። ይሁን እንጂ ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር … [Read more...] about ኢህአዴግ ከብሔር “ተኮር” ተቃዋሚዎች ጋር ሊሸማገል ነው
ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ አጎታቸውን ገደሉ!
ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኧን አጎታቸውንና በሰሜን ኮሪያ የሥልጣን እርከን ሁለተኛ የነበሩትን ጃንግ ሶንግ-ታዬክ አስገደሉ፡፡ ግድያውን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም የመንግሥት ሚዲያ እንዳለው ከሆነ አጎትየው ጃንግ “መንግሥት ለመገልበጥ ሙከራ በማድረግ አስጸያፊ ወንጀል ሰርተዋል” ብሏል፡፡ ሰሜን ኮሪያን ለረጅም ዓመታት ሲመሩ የነበሩትንና ሥልጣናቸውን ከመጀመሪያው የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ኤል ሱንግ የተረከቡት ኪም ጆንግ ኢል ባልተጠበቀ ፍጥነት ሲሞቱ ወጣቱ ኪም ጆንግ ኧን ሥልጣን መንበር ላይ ተቆናጠጡ፡፡ በወቅቱ በሃያዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙት ኧን ከልምድ ማነስ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ በማሰብ አባታቸው ኪም ጆንግ ኢል አስቀድመው ከጎናቸው የሚሆኑ ሞግዚትና አለማማጅ አዘጋጅተው ነበር፡፡ ኪም ጆንግ ኢል የጤናቸው ሁኔታ … [Read more...] about ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ አጎታቸውን ገደሉ!
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለምኒሊክና ስለኢትዮጵያ
የአጼ ምኒሊክን መቶኛ የሙት አመት መከበር ምክንያት በማድረግ በ DW ሬድዮ በተደረገው ጥያቄና መልስ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ ዶ/ር ሓይሌ ላሬቦና ዶ/ር ሹመት ሲሳይ (የታሪክ ተመራማሪዎች) ቃለ መጠይቅ ተደርጎ በሚሰጠው መልስ ላይ ስለ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተናገሩት ላይ አስተያየቴን አቀርባለሁ። አንባቢያንን ቃለመጠይቁን ቢያዳምጡ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፤ ሁለቱ የታሪክ ምሁራን ትምህርታዊ ትንተና ይሰጣሉና፡፡ ውሸት ሲደጋገም እውነት ሊመስል ይችላል፤ በተለይም የአገራችንን የኢትዮጵያን ታሪክ ለማያውቁ እውነታው ምን እንደሚመስል መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ። አቶ ቡልቻ ኦሮሞ ከባሌ እየተስፋፋ ሲመጣ ልብነ ድንግል እንዳይስፋፋ አቆሙት ይላሉ፡፡ ለምን ይህን ምሳሌ እንዳቀረቡም ግልጽ አይደለም ለሳቸው ትንታኔ የማይመች በመሆኑ፤ ለዛውም በአጼ ልብነ ድንግልና በኦሮሞች መሀከል ስለነበረው ግኑኝነት … [Read more...] about አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለምኒሊክና ስለኢትዮጵያ
አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች !
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ጥቅምት መጨረሽና ህዳር ወር 2006 እጅግ አሳዛኝና በህይወት እስከአለን ድረስ የማንረሳው ክፉ አጋጣሚ በእህቶቻችንና በወንድሞቻችን ላይ ግድያን፣ መድፈርን፣ እስርን፣ መታረድንም፣ በመኪና እየተገጩም ጭምር መሞትንም መጀመሩን ያየንበትና የሰማንበት:: ክፉ ወር:: ብዙዎቻችን በውስጣችን ከራሳችን ጋር የተሟገትንበት፣ ምን እናድርግ? ብለን ከቅርብ ጓደኞቻችን ጋር የተነጋገርንበት:: ሌሎቻችንም ተሰባስበን በውስጣችን ያለውን ሃዘን በግልጽና በአደባባይ ዓለም ሁሉ እየሰማ የተነፈስንበት:: ሳውዲ አረቢያዎች ለዘመናት አብሮአቸው የነበረውን ጭካኔ በአይናችን የተመለከትንበት ምን አልባትም እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከዚህ በላይ ሲጨቆኑና ሲረገጡ መኖራቸውንም ለማየት የቻልንበት ጊዜ ይህ ይፋ ወጣ እንጂ:: በእርግጥም ሳውዲዎች ጨካኞች ናቸው ስራቸውም እጅግ አሳፋሪ ነው:: … [Read more...] about አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች !
እምዬ ምኒልክ፡ የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
ዛሬ ታህሳስ 3ቀን የሚከበረው የዳግማዊ አጼ ምኒልክ 100ኛ የዕረፍት ዓመት “እምዬ ምኒልክ ምን ዓይነት ውርስ ትተውልን ሄዱ?” ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ጦርነት ለመግባት ሳይፈልጉ “በግድ” ወደሄዱበት የጣሊያን ጦርነት መለስ ብለን የሆነውን እንድናስብ ወደድን፡፡ ክተት፡- “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት ለሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፤ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬ ከብት ማለቁንና የሰዉን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር … [Read more...] about እምዬ ምኒልክ፡ የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
‘‘ፍርድ ሲዘገይ ሀገር እንደታሰረ መቆጠር አለበት’’ ተማም አባቡልጉ (የሕግ ጠበቃ)
አቶ ተማም አባ ቡልጉ ከአዲስ ጉዳይ መጽሄት ቁጥር 128 ህዳር/2006 ዕትም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ አዲስ ጉዳይ፡ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደ ታህሳስ 3 ሲዛዋወር እንደ ጉዳዩ ዓቃቤነትዎ እንዲያውቁት ተደርገው ነበር? ተማም፡ በፍጹም ለእኔ የተነገረኝ ነገር አልነበረም፡፡ ከእኔ ጋር አብሮ የሚሰራ ጠበቃ ፍርድ ቤት ድረስ ሄዶ ‘ጉዳዩ እንዴት ነው?’ ሲለኝ አይ እዚያው ነው ብዬ ሳረጋግጥለት ‘አረ ፍርድ ቤቱ ባዶ ነው’ የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡ አንዳንድ ጠበቆች ጋር ስደውልም እከሌ የተባለ ጠበቃ እኮ ፍርድ ቤት በነበረበት ወቅት ከጽ/ቤት ተነግሮት ነበር አሉኝ፡፡ በዚህ ዓይነት መልኩ ነው ቀጠሮው መራዘሙን የሰማሁት፡፡ አዲስ ጉዳይ፡ በይፋ የተነገራችሁ ነገር የለም ማለት ነው? ተማም፡ ለእኛ በይፋ ምንም የተገለፀልን ነገር የለም፡፡ በፍርድ ቤት በይፋ … [Read more...] about ‘‘ፍርድ ሲዘገይ ሀገር እንደታሰረ መቆጠር አለበት’’ ተማም አባቡልጉ (የሕግ ጠበቃ)










